ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - christ...

80
ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ ...በእየለቱ የሚነበብ መንፈሳዊ መጸሐፍ Chris Oyakhilome

Upload: others

Post on 11-Aug-2020

74 views

Category:

Documents


3 download

TRANSCRIPT

Page 1: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - Christ Embassycedmvas.org/wp-content/uploads/2017/11/Rhapsody-Of... · እንደሆነ ያስባሉ፤ ምን ማለት እንደሆነ ከተረዳችሁ፣

ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ

...በእየለቱ የሚነበብ መንፈሳዊ መጸሐፍ

Chris Oyakhilome

Page 2: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - Christ Embassycedmvas.org/wp-content/uploads/2017/11/Rhapsody-Of... · እንደሆነ ያስባሉ፤ ምን ማለት እንደሆነ ከተረዳችሁ፣

www.rhapsodyofrealities.orgemail: [email protected]

All rights reserved under International Copyright Law. Contents and/or cover may not be reproduced in whole or in part in any form without the express written permission of LoveWorld Publishing.

USA:Believers’ LoveWorld4237 Raleigh StreetCharlotte, NC 28213Tel: +1 980-219-5150

CANADA:Christ Embassy Int’l Office, 50 Weybright Court, Unit 43BToronto, ON MIS 5A8Tel.:+1 647-341-9091

CANADA:600 Clayson Road North York Toronto M9M 2H2 Canada.Tel/Fax:+1-416-746 5080

UNITED KINGDOM: Believers’ LoveWorldUnit C2, Thames View Business Centre, Barlow Way Rainham-Essex, RM13 8BT. Tel.: +44 (0)1708 556 604Fax.: +44(0)2081 816 290

NIGERIA:Christ Embassy Plot 97, Durumi District, Abuja, Nigeria.

LoveWorld Conference CenterKudirat Abiola Way, OregunP.O. Box 13563 Ikeja, LagosTel.: +234-812-340-6547 +234-812-340-6791

USA:Christ Embassy Houston,8623 Hemlock Hill DriveHouston, Texas. 77083 Tel.: +1-281-759-5111; +1-281-759-6218

SOUTH AFRICA:303 Pretoria AvenueCnr. Harley and Braam Fischer, Randburg, Gauteng South Africa.Tel.:+27 11 326 0971Fax.:+27 113260972

KuKÖ S[Í“ }ÚT] KT²´:

ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ ...በእየለቱ የሚነበብ መንፈሳዊ መጸሐፍISSN 1596-6984ግንቦት 2010 editionCopyright © 2010 by LoveWorld Publishing

u}K¾ G<’@� “M}Ökc ue}k` G<KU Øpf‹ ŸSÅu—¨< ¾SêNõ pÆe ¾}¨cÆ “†¨<::

Page 3: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - Christ Embassycedmvas.org/wp-content/uploads/2017/11/Rhapsody-Of... · እንደሆነ ያስባሉ፤ ምን ማለት እንደሆነ ከተረዳችሁ፣

የ 2010 ዓ.ም. ተወዳጁ “ የራኘሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ “ እትም፣ የመንፈሳዊ ህይወትህ እርምጃና እድገት ለማሳደግ በተለየና ባማረ ሁኔታ ለተሻለ ነገር በሚያነሳሳ

መልኩ የተዘጋጀ ነው፡፡ በመረጃና በመገለጥ ከተሞሉ ፁሁፎች በተጨማሪ የዚህ ወር ዕትም በየዕለቱ የእግዚአብሔርን መለኮታዊ መገኘት ለማወቅ በምታደርገው ጉዞ እምነትህን በእግዚአብሔር ቃል ላይ እንድታሳድግ በተመቻቸ ሁኔታ ተዘጋጅቶ ቀርቦልኃል፡፡ በየቀኑ ባጠናኽው፣ ባሰላሰልከውና በአፍህ በተናገርከው ወይም ደግሞ ባወጅከው መጠን እየታደስክ ትሄዳለህ፡፡

የእግዚአብሔርን ቃል በየቀኑ በወሰድን ጊዜ የእግዚአብሔርን የክብር መገኘትና ድል ዓመቱን በሙሉ እንዲደሰቱበት ጥሪ እናደርጋለን፡፡ በጣም እንወዳችኋለን፡፡ እግዚአብሔር ይባርካችሁ!

- ይህንን መነቃቅያ እንዴት በበለጠ መጠቀም ይቻላል -

መግቢያ

-ፓስተር ክሪስ ኦያኪሎሜ

ይህን ጽሁፍ አንብብና በጥንቃቄ አሰላስል፡፡ ፀሎቶቹንና የአፍ ምስክርነት ቃሉን

በየቀኑ ለራስህ ድምጽህን ጎላ አድርገህ መናገርህ የእግዚአብሔር ቃል በሕይወትህ

እንዲያልፍ ያደርጋል፡፡

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ወይም በአዲሱ የሁለት ዓመት የመጽሐፍ

ቅዱስ ጥናት በሚገባ አንብቡ

የዕለታዊው የመጽሐፍ ቅዱስ ንባቡን በጠዋትና በማታ ከፍለህ ማንበብ ትችላለህ

መነቃቅያውን በጸሎት ተጠቀሙበትና በእያንዳንዱ ወራት ያላችሁን ግብ ጻፉና

ከአንዱ ግብ ወደ ሌላው ግብ ያላችሁን ስኬት በሚገባ ለኩ

Page 4: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - Christ Embassycedmvas.org/wp-content/uploads/2017/11/Rhapsody-Of... · እንደሆነ ያስባሉ፤ ምን ማለት እንደሆነ ከተረዳችሁ፣

eU

݃^h

eM¡

¾ÓM S[Í

Page 5: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - Christ Embassycedmvas.org/wp-content/uploads/2017/11/Rhapsody-Of... · እንደሆነ ያስባሉ፤ ምን ማለት እንደሆነ ከተረዳችሁ፣

ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ

www.rhapsodyofrealities.org

...በእየለቱ የሚነበብ መንፈሳዊ መጸሐፍ

Page 6: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - Christ Embassycedmvas.org/wp-content/uploads/2017/11/Rhapsody-Of... · እንደሆነ ያስባሉ፤ ምን ማለት እንደሆነ ከተረዳችሁ፣

amharic

በብሉይ ኪዳን ላይ፤ የሞዓብ ንጉስ የሆነው ባላቅ በእስራኤል ላይ ተቆጣና እስራኤልን እንዲረግም በለዓም የተባለውን ነብይ

ቀጠረው፤ በለዓም እስራኤልን ሊረግም በሞከረበት ጊዜ ሁሉ፤ ከአፉ የሚወጣው በረከት ስለነበረ ቅሬታ ተሰምቶት ነበር፡፡ ከዚያም ለባላቅ እንዲህ አለው፡- “…እነሆ ለመባረክ ትእዛዝ ተቀብያለሁ እርሱ (እግዚሃብሄር)፤ እመልሰውም ዘንድ አልችልም” (ዘኁልቅ 23፡20)::

ከሶስት ያልተሳካ ሙከራዎች በኋላ፤ በለዓም በመጨረሻ እስራኤልን መርገም አቆመ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ በለዓምም እግዚአብሔር እስራኤልን ይባርክ ዘንድ እንዲወድድ ባየ ጊዜ፥ አስቀድሞ ያደርግ የነበረውን አስማት ከማድረግ እንደተቆጠበ ይነግረናል። (ዘኁልቅ 24፡1)፡፡ በሌላ አነጋገር እግዚሃብሄር የባረካቸውን መርገም ወይም እነርሱን የሚቃወሙ ሴራዎችን ማዘጋጀት ውጤት እንደሌለው አስተዋለ፡፡ በመክፈቻ ጥቅሳችን ያነበብነውም ይህን ጉዳይ በተመለከተ እርሱ የደረሰበትን ድምዳሜ ነው፡፡ ‘ጉድ ኒውስ’ የተሰኘው የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም እንዴት እንዳስቀመጠው ተመልከቱ፡- “በእስራኤል ላይ ሊሰራ የሚችል ምንም አይነት ምትሃታዊ ድግምት፣ ምንም አይነት ጥንቆላ፤ አይሰራም…”፤ ዛሬም ቢሆን እንደዚህ አይነት ነገሮች ይከሰታሉ፡፡ እንደ ጠላት የሚያይዋቸውን ወይንም የስራ ባልደረቦቻቸውን ለመርገም ወደ ጠንቋይ ወይንም አስማተኛ ይሄዳሉ፡፡

አንዳንድ ጊዜ ሰዎች፣ በተደረገባቸው እርግማን የተነሳ፣ ከዚያ በፊት ምንም አይነት የህመም ምልክት ወይንም ታሪክ ሳይኖራቸው፣ በድንገት በሚገድል በሽታ ሊጠቁ ወይንም ሊያብዱም ይችላሉ፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ደግሞ በእርግማን የተጠቁት ሰዎች፤ በእነሱ ላይ እየሰራ ያለው እርግማን እንደሆነ እንኳን አያውቁም፡፡ ያጋጠማቸው ችግር በምንም አይነት

በእናንተ ላይ ምንም አስማት አይሰራም

በያዕቆብ ላይ አስማት የለም፤ በእስራኤል ላይም ሟርት አይሰራም።

(ዘኁልቅ 23፡23)

ማክሰኞ 1

Page 7: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - Christ Embassycedmvas.org/wp-content/uploads/2017/11/Rhapsody-Of... · እንደሆነ ያስባሉ፤ ምን ማለት እንደሆነ ከተረዳችሁ፣

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሉቃስ ወንጌል 24:13-35 & መጽሀፈ ሳሙኤል ካልእ 9-11

1ኛ ቆሮንጦስ 2:1-11 & መዝሙረ ዳዊት 143-144

ኦሪት ዘህልቁ 23:7-9; ኤፌሶን 1:3-4; ኤፌሶን 2:10

የተባረክህ አባት ሆይ! በክርስቶስ በሰማያዊ ስፍራ በሁሉም መንፈሳዊ በረከቶች ባርከኸኛል፤ ይህንን እውነት እና በዚህ ዓለም ባሉ ሁሉም የጨለማ ኃይላት፣ ሥልጣናት እና ገዥዎች ላይ ያለኝን ሥልጣን አውቃለሁ! እኔ በበረከት ብቻ እመላለሳለሁ፤ የጠላት አሰራሮችንና የክፋት ስልቶችን በመቃወም ጸንቼ፣ በክርስቶስ ተጠብቄአለሁ፤ በኢየሱስ ስም፡፡ አሜን፡፡

ጸሎት

የህክምናም ሆነ የሰዎች ጥረት የማይፈታ ይሆናል፡፡ነገር ግን ለእግዚሃብሄር ምስጋና ይድረሰው! አንዴ ዳግም

ከተወለዳችሁ፤ ማንም ሊረግማችሁ አይችልም፤ ምክንያቱም እናንተ በእግዚሃብሄር የተባረካችሁ ናችሁ፡፡ አዲሱ ፍጥረት በእግዚሃብሄር የተባረከ ነው፡፡ እኛ በእርሱ የተመረጥን ነን፡- “ነገር ግን እናንተ የተመረጣችሁ ትውልዶች፤ የንጉስ ካህናት፤ ቅዱስ ህዝብ፤ ለርስቱ የተለየ ወገን” (1ኛ ጴጥሮስ 2፡9)፡፡

ጠንቋዮችን፤ አስማተኞችን፤ ምትሃተኞችን፤ ደብተራዎችን አትፍሩ፤ ምንም ያህል ጥረት ቢያደርጉ፣ እናንተ ላይ የሚያደርጉት ሁሉ ዋጋ የለውም:: መተት ሊደረግባችሁ አይቻልም፡፡ ድግምት ሊደረግባችሁ አይቻልም:: ልትረገሙ አትችሉም፡፡ እናንተ በበረከት ብቻ ትመላለሳላችሁ፤ እናም በህይወታችሁ ውስጥ የሚሆነው የጌታ የበረከት ቃል ብቻ ነው፡፡ ሃሌሉያ!

Page 8: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - Christ Embassycedmvas.org/wp-content/uploads/2017/11/Rhapsody-Of... · እንደሆነ ያስባሉ፤ ምን ማለት እንደሆነ ከተረዳችሁ፣

amharic

በማርቆስ 11፡23 ጌታችን ኢየሱስ በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ብንሆን ለውጥ የምናመጣበትን መንገድ አሳይቶናል፡፡ እንዲህ

ብሏል፡- “እውነት እላችኋለሁ፤ ማንም ያለው ነገር እንዲደረግለት ቢያምን በልቡ ሳይጠራጠር ይህን ተራራ ተነቅለህ ወደ ባህር ተወርወር ቢል ይሆንለታል”፡፡ በሌላ አነጋገር፣ ተስፋ የሌላቸውን ሁኔታዎች ለመቀየር፣ ማድረግ ያለባችሁ ተራራውን ማናገር ነው፡፡ የሚያሳዝነው ግን ሰዎች ተራራው በማናገር ፋንታ፣ ስለ ተራራው ሲያወሩ እናገኛቸዋለን፤ ያ ደግሞ ነገሮችን አይቀይርም፡፡

ስለተግዳሮቶቹ ማውራት እስከቀጠላችሁ ድረስ፤ ከችግሮቹ ጋር ህብረት እያደረጋችሁ ነው፡፡ ይልቁኑ ከቃሉ ጋር ህብረት አድርጉ፡፡ እያለፋችሁባቸው ያሉትን ችግሮች ሳይሆን፣ ቃሉን አሰላስሉ፤ ምክንያቱም ተግዳሮቶቹ እውን አይደሉም፤ እውን የሆነው ቃሉ ብቻ ነው፡፡ ማድረግ ያለባችሁ ቃሉ ስለ ሁኔታችሁ የተናገረውን ማሰላሰል ነው፡፡

ምናልባትም በሰውነታችሁ ውስጥ አንድ እባጭ ኖሮ፣ እናንተም በዙርያችሁ ላሉ ሰዎች ስለሁኔታው እያጉረመረማችሁ ከሆነ፤ ነገሮችን የምትቀይሩበት ጊዜው አሁን ነው! ቃሉን አውጁ፡፡ “ሰውነቴ የመንፈስ ቅዱስ ቤተ-መቅደስ ስለሆነ፣ አንተ ዕባጭ፤ በኢየሱስ ስም ከሰውነቴ ላይ ጥፋ፡፡” በሉ፡፡

ምናልባትም ለውጥ የሚያስፈልገው የገንዘብ ሁኔታችሁ ከሆነ፤ የቃል ህክምና ጀምሩ፡፡ ስለገንዘብ ብልጽግና የሚናገሩትን እንደ 3ኛ ዮሐንስ 1፡2፣

ችግሮቻችሁን ሳይሆን፣ቃሉን አሰላስሉ

የማይታየውን እንጂ የሚታየውን ባንመለከት፤ ቀላል የሆነ የጊዜው መከራችን የክብርን የዘላለም ብዛት ከሁሉ መጠን ይልቅ ያደርግልናልና፤ የሚታየው የጊዜው ነውና፤ የማይታየው ግን የዘላለም ነው። (2ኛ ቆሮንቶስ 4፡18)

ረቡዕ 2

Page 9: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - Christ Embassycedmvas.org/wp-content/uploads/2017/11/Rhapsody-Of... · እንደሆነ ያስባሉ፤ ምን ማለት እንደሆነ ከተረዳችሁ፣

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሉቃስ ወንጌል 24:36-53 & መጽሀፈ ሳሙኤል ካልእ 12-14

1ኛ ቆሮንጦስ 2:12-16 & መዝሙረ ዳዊት 145-146

መዝሙረ ዳዊት 1:1-3; የሐዋርያት ስራ 20:32; 2ኛ ቆሮንጦስ 4:17-18

ውድ አባት ሆይ፤ በህይወቴ ስለተትረፈረፈው ጸጋና፤ ስለተሸከምኩት ክብርህ አመሰግንሃለሁ፡፡ በሁሉም ነገር ባለጸጋ ስላደረገኝ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ አመሰግንሃለሁ፡፡ ለህይወትና እግዚአብሄርን ለመምሰል የሚሆነውን ሁሉ ሰጥተኸኛል፤ እናም ቅዱስ ስምህን አከብራለሁ፡፡

ጸሎት

ምሳሌ 23፡1፣ 2ኛ ቆሮንቶስ 9፡8፣ 2ኛ ቆሮንቶስ 8፡9፣ 1ኛ ቆሮንቶስ 3፡21፣ የሐዋሪያት ስራ 20፡32፣ ወ.ዘ.ተ. ያሉትን የመጽሀፍ ቅዱስ ጥቅሶች መናገር ጀምሩ፡፡ የምታስቡት፤ የምታዩት እና የምታወሩት ሁሉ ብልጽግና እስኪሆን ድረስ እነኚህን ቃላቶች አሰላስሉ፡፡ እግዚሃብሄር አፍ የሰጣችሁ ለመብላት ብቻ ሳይሆን፤ በዋነኝነት የምትመኙትን ውጤት ለማምጣት በመናገር እንድታሰላስሉ ነው፡፡

ኢያሱ 1፡8 እንዲህ ይላል፡- “የዚህ ህግ መጽሐፍ ከአፍህ አይለይ፤ ነገር ግን የተጻፈበትን ሁሉ ትጠብቅና ታደርግ ዘንድ በቀንም በሌሊትም አስበው፤ የዚያን ጊዜም መንገድህ ይቀናልሃል ይከናውንልሃልም”፡፡ እግዚሃብሄር ለኢያሱ ቀላል የሆነ የስኬትን መንገድ አሳየው፤ ይኸውም ቃሉን ማሰላሰል ነው፡፡ ችግሮችን በማማረር ውድ ጊዜን ከማጥፋት ይልቅ፣ ከችግሮቹ በላይ በሚያደርጋችሁ እና ሁኔታውን በሚቀይረው የእግዚአብሄር ኃይልና የቃሉ ውጤታማነት ላይ አተኩሩ፡፡

Page 10: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - Christ Embassycedmvas.org/wp-content/uploads/2017/11/Rhapsody-Of... · እንደሆነ ያስባሉ፤ ምን ማለት እንደሆነ ከተረዳችሁ፣

amharic

አብዛኛውን ጊዜ ክርስቲያኖች፣ የአንዳንድ ቃላቶችን ትክክለኛ ትርጉም ሳያውቁ ይጠቀማሉ፡፡ ለምሳሌ ለአንዳንድ ሰዎች

“እግዚሃብሄር ይባርክህ” ማለት የሚያስደስት የቤተ-ክርስቲያን ሰላምታ ብቻ እንደሆነ ያስባሉ፤ ምን ማለት እንደሆነ ከተረዳችሁ፣ ይህ አባባል በእርግጥ ኃይል ያለው ነገር ነው፡፡ መባረክ ማለት ለመበልጸግ ኃይል ማግኘት ማለት ነው፤ ተባርካችኋል ማለት በሁሉም የህይወታችሁ ክፍል ለብልጽግና፤ ለልቀት፤ ለድል፤ ለፍሬያማነት እና ለምርታማነት ኃይል አግኝታችኋል ማለት ነው፡፡

አሁን ስለተባረካችሁ ልትሸነፉና ልትጎዱ አትችሉም፤ በጌታ ተጠብቃችኋል፤ ተከልላችኋልም፡፡ ይህ ማለት ግን ተግዳሮቶች አያጋጥማችሁም ማለት አይደለም፤ ነገር ግን ምንም አይነት ተግዳሮት ወይንም ተቃዋሚ ቢያጋጥማችሁ፤ ሁሌም ታሸንፋላችሁ፤ ሌሎች ሲወድቁ እናንተ ታሸንፋላችሁ፡፡ እንደ ክርስቲያን ህይወታችሁ ይህ ነው ፡፡ በሁሉም ነገር እንድትበለጽጉና የህይወት ጉዳዮችን በጥበብ እንድትመሩ ኃይል ተሰጥቷችኋል፡፡ ይህ መንፈስ ቅዱስን ስትቀበሉ ሆኗል፡፡

በበረሃ ወይንም በምድረ በዳ ብትቀመጡ እንኳን፤ መበልጸጋችሁ አይቀርም፤ እናንተ በጌታ የተባረካችሁ ስለሆናችሁ፣ በረሃው ወደ ፍሬያማ እርሻ ይቀየራል፡፡ እያንዳንዱን ቀን በዚህ አስተሳሰብ ኑሩ፡፡

ለመበልጸግ ኃይል ያለው

በእግዚሃብሄር የታመነ እምነቱም እግዚሃብሄር የሆነ ሰው ብሩክ ነው፡፡ በውሃ አጠገብ እንደተተከለ፤ በወንዝም

ዳር ስሩን እንደሚዘረጋ ሙቀትም ሲመጣ እንደማይፈራ ቅጠሉም እንደሚለመልም፤ በድርቅ አመትም እንደማይሰጋ

ፍሬውንም እንደማያቋርጥ ዛፍ ይሆናል። (ኤርሚያስ 17፡7-8)

ሐሙስ 3

Page 11: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - Christ Embassycedmvas.org/wp-content/uploads/2017/11/Rhapsody-Of... · እንደሆነ ያስባሉ፤ ምን ማለት እንደሆነ ከተረዳችሁ፣

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የዮሐንስ ወንጌል 1:1-18 & መጽሀፈ ሳሙኤል ካልእ 15-17

1ኛ ቆሮንጦስ 3:1-9 & መዝሙረ ዳዊት 147-148

ኦሪት ዘፍጥረት 12:2-3; ገላትያ 3:8-9

ውድ አባት ሆይ፤ በሁሉም ነገር እንድበለጽግና ጎዳዮቼን በሙሉ በጥበብ እንድመራ ባርከኸኛል፤ ኃይልንም ሰጥተኸኛል፡፡ በማያቋርጥ መለኮታዊ ሞገስ እየተመላለስኩ፣ እኔ ልእለ ተፈጥሮአዊ በሆነ ሁኔታ ተከልዬአለሁ፤ ተጠብቄአለሁም ፤ ከእኔ ጋር የተገናኘ ነገር በሙሉ ይበለጽጋል፤ በጌታ በኢየሱስ ስም፡፡ አሜን፡፡

ጸሎት

Page 12: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - Christ Embassycedmvas.org/wp-content/uploads/2017/11/Rhapsody-Of... · እንደሆነ ያስባሉ፤ ምን ማለት እንደሆነ ከተረዳችሁ፣

amharic

“ትንሹ” እና “ትልቁ” የሚሉት የግሪክ ቃላት ፍሬ ነገሩ ደረጃ እና የበላይነትን የሚመለከት እንደሆነ እንድንረዳ ያግዙናል::

በእርግጥም የሚመለከተው ያነሰ ጥንካሬ ያለው በበረታው እንደሚባረክ ነው፤ ይህም ማለት በከፍተኛ ደረጃ ላይ ያለ ሰው፣ በዝቅተኛ ደረጃ ላይ ያለውን ሲባርክ ነው፡፡ ለምሳሌ፣ ወላጆች ልጆቻቸውን መባረክ ይችላሉ፡፡ አንድ አገልጋይ የእርሱን ጉባዔ አባላት መባረክ ይችላል፡፡ በብሉይ ኪዳን ካህናት የእስራእልን ህዝብ እንዲባርኩ ተጠይቀው ነበር፡፡ በአዲሱ ኪዳንም ተመሳሳይ ነገር እናገኛለን፡፡

ለምሳሌ ሐዋሪያው ጳውሎስ ቤተ-ክርስቲያናትን ባርኳል፡፡ በመደምደሚያ ደብዳቤው፣ ለሮሜ ክርስቲያኖች እንዲህ ብሏል፡- “የሰላምም አምላክ ሰይጣንን ከእግራችሁ በታች ፈጥኖ የቀጠቅጠዋል:: የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን” (ሮሜ 16፡20)፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ ለቆሮንቶስ ሰዎች በጻፈው ሁለተኛ ደብዳቤ፤ እንዲህ በማለት ባረካቸው፡- ”የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የእግዚሐብሄርም ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም ህብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን፡፡ አሜን፡፡ ” (2ኛ ቆሮንጦስ 13፡14)፡፡

በረከት በዋነኛነት የሚተላለፈው በቃላት ነው፤ አስቀድሞ “ያልተባረከን” ሰው ደግሞ መባረክ አትችሉም፤ ይህ ምስጢር ነው፤ ነገር ግን መንፈሳዊ እውነታም ነው፡፡ መባረክ የምትችሉት አስቀድሞ የተባረከን ሰው ብቻ ነው፡፡ በብሉይ ኪዳን እግዚሃብሄር ካህናት የእስራኤልን ልጆች እንዲባርኩ እንዴት እንዳዘዛቸው አንብበናል፡፡ እንዲህ አለ፡- “ለአሮንና ለልጆቹ ንገራቸው የእስራኤልን ልጆች ስትባርኩአቸው እንዲህ በሉአቸው፤ እግዚሃብሄር ይባርክህ፤ ይጠብቅህም፤ እግዚሃብሄር ፊቱን ያብራልህ፤ ይራራልህም፤ እግዚሃብሄር ፊቱን ወደ አንተ ያንሳ፤ ሰላምንም ይስጥህ” (ዘኁልቁ 6፡23-26)፡፡

አስቀድሞም የተባረኩ ሰዎች ናቸው፤ ነገር ግን ህብረት ባደረጉ ጊዜ

በረከቶችን ተናገሩ

ትንሹም በታላቁ እንዲባረክ ክርክር የሌለበት ነገር ነው። (ዕብራውያን 7፤7)

አርብ 4

Page 13: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - Christ Embassycedmvas.org/wp-content/uploads/2017/11/Rhapsody-Of... · እንደሆነ ያስባሉ፤ ምን ማለት እንደሆነ ከተረዳችሁ፣

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የዮሐንስ ወንጌል 1:19-51 & መጽሀፈ ሳሙኤል ካልእ 18-19

1ኛ ቆሮንጦስ 3:10-23 & መዝሙረ ዳዊት 149-150

1ኛ ተሰሎንቄ 3:12-13; ዕብራውያን 13:20-21

ሁሉ፤ በእነርሱ ውስጥ አስቀደሞ ያለውን በረከት ለማነቀቃት፣ እንኚህን ባርኮቶች በእነርሱ ላይ ይናገርባቸዋል፡፡ ስለዚህ እንደ እግዚሃብሄር ልጅ፣ በረከቶችን መናገር ተማሩ፡፡ እናንተ ለመባረክ ተባርካችኋል፡፡ ስለሆነም ጠዋት ስትነሱ በረከትን ተናገሩ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፡- “ክፉን በክፉ ፈንታ ወይም ስድብን በስድብ ፈንታ አትመልሱ በዚህ ፈንታ ባርኩ እንጂ፤ በረከትን ልትወርሱ ለዚህ ተጠርታችኋልና” (1ኛ ጴጥሮስ 3፡9)፡፡ በየዕለቱ በቤተሰባችሁ፣ በስራችሁ፣ በልጆቻችሁ፣ በንግዳችሁ፣ በአገልግሎታችሁ፣ በትምህርታችሁ፣ ወ.ዘ.ተ. ላይ በረከትን ተናገሩ፡፡

እኔ በክርስቶስ ወንጌል በረከቶች በሙላት ተባርኬአለሁ፡፡ እኔ በከተማም በመስክም ተባርኬአለሁ፤ በመውጣቴም በመግባቴም ተባርኬአለሁ፡፡ አሁንና ለዘላለም፣ መንገዴ ህይወትና ሰላም፣ ክብር፣ መትረፍረፍ፣ እና ዘላለማዊ ሐሴት ነው፤ በኢየሱስ ስም፡፡ አሜን፡፡

ጸሎት

Page 14: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - Christ Embassycedmvas.org/wp-content/uploads/2017/11/Rhapsody-Of... · እንደሆነ ያስባሉ፤ ምን ማለት እንደሆነ ከተረዳችሁ፣

amharic

በቀደመው ጥናታችን፣ ባርኮቶችን የመናገር አስፈላጊነትን አይተናል፤ አለማቋረጥ ባርኮቶችን መናገር አለብን፡፡ ነገር ግን

ባርኮቶች የሚታወጁት ወይንም የሚነገሩት በእምነት ነው፤ አለበለዚያ ባዶ ቃላቶች ይሆናሉ፡፡ የምንናገራቸው የባርኮት ቃላት፣ የእምነት ቃላት ሊሆኑ ይገባል፤ ይህም እምነት ከእግዚሃብሄር ጋር የተገናኘ ፣ በእግዚሃብሄር ቃል መገለጥ ላይ የተመሰረተ መሆን አለበት፡፡ ቃላቱ እንዲያሸንፉ የሚያደርጋቸው ይህ እምነት ነው፡፡

በመግቢያ ጥቅሳችን “ይስሐቅ ሊመጣ ስላለው ነገር ያዕቆብንና ኤሳውን በእምነት ባረካቸው” (ዕብራዊያን 11፡20) እንዳለ አንብበናል:: በተመሳሳይ ሁኔታ ዕብራዊያን 11፡21 እንዲህ ይላል፡- “ያዕቆብ ሲሞት በእምነት የዮሴፍን ልጆች እያንዳንዳቸውን ባረካቸው፤ በዘንጉም ጫፍ ተጠግቶ ሰገደ”፡፡ ይህ በጣም አስደናቂ ነው! ያዕቆብ በጊዜው ማየት ተስኖት ነበር፤ አይኖቹ ደብዝዘው ነበር፤ ነገር ግን የልጅ ልጆቹን በመንፈስ መገለጥ ባረካቸው፡፡

የልጆቹ አባት ዮሴፍ፣ አባቱ ያዕቆብ ግራ እጁን በትልቁ ወንድ ልጅ ላይ ቀኝ እጁን ደግሞ በትንሹ ወንድ ልጅ ላይ ሲጭን የተሳሳተ መስሎት፣ አባቱን ሊያርመው ሞከረ (ዘፍጥረት 48፡18-19)፡፡ ነገር ግን አይደለም፤ ስህተት አልነበረም፡፡ ያዕቆብ ልጆቹን የባረከው በእምነት ነበር፡፡ እርሱ የወደፊቱን እያየ፤ እግዚሃብሄር ወደ ፊት ያቀደላቸውን፤ በቃል ባርኮት በእነርሱ ላይ አዘዘ፡፡

ሰዎች ካልተባረኩ፣ ምንም እንኳን እግዚሃብሄር ለእነርሱ መልካም ዕቅድ ያቀደላቸው ቢሆንም፤ የማይፈጸመው ለዚህ ነው፤ ምክንያቱም በህይወታቸው ላይ ባርኮቶችን የተናገረባቸው ማንም ሰው አልነበረም፡፡ አዎን፣ እነኛ ባርኮቶች አስቀድሞ በመንፈሳዊው ዓለም ውስጥ አሉ፤ ነገር ግን የሚነቃቁት በተነገረ ቃል ማለትም በእምነት አዋጅ ብቻ ነው፡፡

በረከቶችን መናገር በእምነት ነው

ይስሐቅ ሊመጣ ስላለው ነገር ያእቆብንና ኤሳውን በእምነት ባረካቸው፡፡ (ዕብራውያን 11፡20)

ቅዳሜ 5

Page 15: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - Christ Embassycedmvas.org/wp-content/uploads/2017/11/Rhapsody-Of... · እንደሆነ ያስባሉ፤ ምን ማለት እንደሆነ ከተረዳችሁ፣

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የዮሐንስ ወንጌል 2:1-25 & መጽሀፈ ሳሙኤል ካልእ 20-21

1ኛ ቆሮንጦስ 4:1-10 & መጽሀፈ ምሳሌ 1

ኦሪት ዘፍጥረት 48:14-16; ሮሜ 10:8; 2ኛ ቆሮንጦስ 4:13

በትክክለኛው ቤተ-ክርስቲያን በመገኘት፣ የእግዚሃብሄርን በረከት በህይወታችሁ የሚያውጅ የእግዚሃብሄር ሰው ሊኖራችሁ ከሚገባው ምክንያቶች አንዱ ይህ ነው፡፡ እነዚያ ቃላት ወደ መለኮታዊው ፍጻሜያችሁ በመምራት፤ በዚያ ውስጥ እንድትመላለሱ፤ እና ለህይወታችሁ ያለውን የእርሱን ፍጹም ፈቃድ እንድትፈጽሙ ያደርጓችኋል፡፡

የባርኮት ቃላትን በእምነት ስናገር፤ ልእለ-ተፈጥሮአዊ የሆነውን የብልጽግና፤ የጤንነት፤ የአሸናፊነት፤ የጥንካሬ እና የእድገት ህይወትን፤ በራሴና በምወዳቸው ሰዎች ላይ አነሳሳለሁ፡፡ በእነዚህ ቃላት፣ ለዘላለም ከተፈጥሮ በላይ ወደሆነው የክብር ህይወት እመነጠቃለሁ፡፡ በእምነትና በእግዚሃብሄር ክብር፣ ዛሬ በድል አድራጊነት እኖራለሁ፤ በኢየሱስ ስም፡፡ አሜን፡፡

ጸሎት

Page 16: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - Christ Embassycedmvas.org/wp-content/uploads/2017/11/Rhapsody-Of... · እንደሆነ ያስባሉ፤ ምን ማለት እንደሆነ ከተረዳችሁ፣

amharic

አንዳንዶች፣ ስለወደፊታቸው መረጃ ለማግኘት ሲሉ ሙታንን ለመገናኘት መሞከር ጥሩ ነው ብለው የሚያስቡ ሰዎች አሉ::

ይህ ስህተት ነው:: በብሉይ ኪዳን ውስጥ እግዚአብሔር የእስራኤል ልጆች ይህንን እንዳያደርጉ በግልፅ አስጠንቅቋል:: የእስራኤል ንጉሥ ሳኦል ይህን አደረገ፤ እናም ችግር ውስጥ ገባ::

ሙታን የወደፊቱን አያውቁም፤ ስለዚህ እነርሱን ስለወደፊቱ ለማማከር መሞከር ሞኝነት ነው:: የወደፊቱን የሚያውቀው መንፈስ ቅዱስ ብቻ ነው፤ እናም እርሱ በሚሰጠን ዕይታ አማካኝነት፣ እርሱ በገለጠልን መጠን ስለወደፊቱ ነገሮችን ልናውቅ እንችላለን::

ኢየሱስ እንዲህ አለ፡- “ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤ የሚሰማውን ሁሉ ይናገራል እንጂ ከራሱ አይነግርምና፤ የሚመጣውንም ይነግራችኋል”(ዮሐንስ 16:13)። በሆነ መንገድ፣ አንድን ሚስጥር ለእናንተ ይገልጥልናል ወይም ስለወደፊታችን አንድ ልዩ የሆነ መረጃ ይሰጠናል ብላችሁ፤ አንድ የሞተ ሰው መንፈስን ተስፋ ከምታደርጉ ይልቅ፤ መንፈስ ቅዱስን ተማመኑበት፡፡

በእርግጥ መንፈስ ቅዱስ በተለያዩ መንገዶች እኛን የሚያገለግልባቸው መገለጫዎች አሉ፡፡ እርሱ፣ መልእክትን ወይም ቃልን ለእናንተ ለማድረስ፤ የመጋቢያችሁን፥ የወንድማችሁን ወይም የእህታችሁን ፊት ሊጠቀም ይችላል፤ እንዲህ ያሉ ነገሮችን ያደርጋል:: ወደ ጌታ በተወሰደ አንድ ሰው ድምጽ እና ፊት አማካኝነት ሊያናገራችሁ ይችላል:: እርሱ ዘለዓለማዊ ነውና ይህን ሊያደርግ ይችላል፤ እርሱ አይገደብም::

ይሁን እንጂ የምትሰሙት ሁሉ ከተገለጠው እውነት ማለትም

ወሳኙ ቃሉ ብቻ ነው

ነገር ግን እኛ ብንሆን ወይም ከሰማይ መልአክ፥ ከሰበክንላችሁ ወንጌል የሚለይ ወንጌልን ቢሰብክላችሁ፥

የተረገመ ይሁን ። (ወደ ገላትያ ሰዎች 1:8)

እሁድ 6

Page 17: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - Christ Embassycedmvas.org/wp-content/uploads/2017/11/Rhapsody-Of... · እንደሆነ ያስባሉ፤ ምን ማለት እንደሆነ ከተረዳችሁ፣

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የዮሐንስ ወንጌል 3:1-21 & መጽሀፈ ሳሙኤል ካልእ 22

1ኛ ቆሮንጦስ 4:11-21 & መጽሀፈ ምሳሌ 2

2ኛ ጴጥሮስ 1:18-19; 1ኛ ዮሐንስ 4:1-3; የሉቃስ ወንጌል 21:33

ከእግዚአብሔር ቃል ጋር የሚጣጣም መሆን አለበት:: የሰማችሁት ምንም ይሁን ከማንም፤ ከቃሉ ጋር የማይጣጣም ከሆነ አስወግዱት:: ወሳኙ ነገር መልእክቱ ከቃሉ ጋር ያለው መስማማት ነው::

በአንድ መልአክ መምጣቱ መልእክቱን የበለጠ እውነት አያደርገውም:: መልእክቱን እውነት የሚያደርገው እና ኃይል የሚሰጠው ከተገለጠው ከእግዚአብሔር ቃል ጋር ያለው መጣጣም ነው:: ሁሉንም ትንቢቶች መፈተን ያለብንና (1ኛ ቆሮንቶስ 14:29) ሁሉም መናፍስት ከእግዚአብሔር መሆናቸውን ለማወቅ መመርመር ያለብንም (1ኛ ዮሐንስ 4:1) በዚሁ ተመሳሳይ ምክንያት ነው::

የተባረክህ አባት ሆይ፣ ከዘለአለማዊው ቃልህ ስለተቀበልኩት አስተማማኝ ምሪት እና በመንፈሴ ውስጥ ስለሚገልጠው ብርሃን አመሰግንሃለሁ:: ቃልህ ህይወቴ ነው፤ እናም በቃልህ ላይ ባለኝ እምነት፣ ከሁኔታዎች በላይ እሆናለሁ፤ ለንግስናህም ክብርን አመጣለሁ፤ በኢየሱስ ስም:: አሜን፡፡

ጸሎት

Page 18: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - Christ Embassycedmvas.org/wp-content/uploads/2017/11/Rhapsody-Of... · እንደሆነ ያስባሉ፤ ምን ማለት እንደሆነ ከተረዳችሁ፣

amharic

በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ ቃላት እጅግ ጠቃሚ ስለሆኑ በግዴለሽነት ፈጽሞ ልንጠቀምባቸው አይገባም:: እውነተኛ

ማንነታችሁ በቃላቶቻችሁ ይገለጣል:: እየቀለድኩ ነው ብላችሁ ባሰባችሁ ጊዜ እንኳን፤ የምትናገሩት ነገር ፍጻሜያችሁን ሊያደርግ ወይም ሊያበላሽ ይችላል:: ከቃሉ ጋር የሚጻረር ቀልድ መናገርን በጭራሽ አትድፈሩ::

ለምሳሌ ዔሳውን ውሰዱ፤ አንዳንዶች “ተራ ቃላቶች” ብለው በሚወስዱት፤ የብኩርና መብቱን ለወንድሙ ለያዕቆብ አሳልፎ ሰጥቶአል:: ታሪኩን አንብቡ፤ ረሃብ ተሰማውና ምግብ ፈለገ፡፡ ታናሽ ወንድሙ ያዕቆብ ወጥ እየሰራ ነበርና እንዲሰጠው ጠየቀው:: ቀጣይ ንግግራቸውን አንብቡ፤ ዔሳው “ከዚህ ከቀዩ ወጥ አብላኝ፥ እኔ እጅግ ደክሜአለሁና አለው”::

ያዕቆብም “በመጀመሪያ ብኵርናህን ሽጥልኝ…” ብሎ መለሰለት። ዔሳውም “... እነሆ፥ እኔ ልሞት ነኝ ይህች ብኵርና ለምኔ ናት? አለ። ያዕቆብም፦ “ እስኪ በመጀመሪያ ማልልኝ አለው። ማለለትም ብኵርናውንም ለያዕቆብ ሸጠ።ያዕቆብም ለዔሳው እንጀራና የምስር ወጥ ሰጠው በላ፥ ጠጣ፥ ተነሥቶም ሄደ እንዲሁም ዔሳው ብኵርናውን አቃለላት” (ዘፍጥረት 25:30-33)። በእርግጥ በጣም አሳዛኝ ነው!

በ”ስህተት” ቢሆንም እንኳን፣ የዚህ ውጤት ይስሐቅ በረከቱን ሲያስተላልፍ ለትልቁ ልጁ ለዔሳው ሳይሆን ለያዕቆብ አሳልፎ ሰጠው:: ነገር ግን ይህ ሊሆን ግድ ነበር፤ ምክንያቱም ዔሳው በራሱ ቃል የብኩርና መብቱን ለወንድሙ ለያዕቆብ አሳልፎ ሰጥቶአልና::

ምንም እንኳን ዔሳው የተናገረው ያን ውጤት ያመጣል ብሎ “በማሰብ” እንዳልሆነ ግልጽ ቢሆንም፤ ሁኔታውን ለመቀየር ጊዜው እጅግ አልፎ ነበር:: ቆይቶም ያንን በረከት በእንባ ቢፈልገው እንኳን ሊያገኘው እንደማይችል ተረዳ: - “ከዚያ በኋላ እንኳ (ዔሳው) በረከቱን ሊወርስ በወደደ ጊዜ እንደ ተጣለ ታውቃላችሁና፤ በእንባ ተግቶ ምንም ቢፈልገው ለንስሐ ስፍራ አላገኘምና”” (ዕብራውያን 12:17)።

ለቃላት ከፍተኛ ዋጋ ስጡ

ከቃልህ የተነሣ ትጸድቃለህና ከቃልህም የተነሣ ትኰነናለህ። (የማቴዎስ ወንጌል 12:37)

ሰኞ 7

Page 19: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - Christ Embassycedmvas.org/wp-content/uploads/2017/11/Rhapsody-Of... · እንደሆነ ያስባሉ፤ ምን ማለት እንደሆነ ከተረዳችሁ፣

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የዮሐንስ ወንጌል 3:22-36 & መጽሀፈ ሳሙኤል ካልእ 23-24

1ኛ ቆሮንጦስ 5:1-13 & መጽሀፈ ምሳሌ 3

መጽሀፈ ምሳሌ 15:4; የማቴዎስ ወንጌል 12:36-37; የማርቆስ ወንጌል 11:23

ቃላቶቻቸሁ እናንተን ይወክላሉ፤ እነሱ ሁሉም ነገር ናቸው:: በግድየለሽነት ተናግራችሁ “ከልቤ አይደለም!” አትበሉ፤ እውነትን ተናገሩ:: መጽሐፍ ቅዱስ ጻድቅ ለመመለስ ያስባል፤ ለመናገር ያሰላስላል ይላል (ምሳሌ 15:28):: ለመንፈሳዊ ነገር ምንም ደንታ እንደሌለው እና ብኩርናውን በንግግሩ እንደሸጠው እንደ ዔሳው አትሁኑ::

ለቃላት ከፍተኛ ዋጋ ስጡ:: ከቃላችሁ የተነሣ ትጸድቃላችሁ፤ ከቃላችሁም የተነሣ ትኰነናላችሁና፤ ልክ ኢየሱስ የቃል ጌታ እንደነበረው ሁሉ፣ እናንተም የቃል ጌታ ሁኑ፤::

ውድ አባት ሆይ፣ ከተፈጥሮ በላይ የሆነ ማስተዋል፥ ጥበብ እና እውቀት ስለሰጠኸኝ አመሰግንሃለሁ:: ሁልጊዜ በጥበብ ነገሮችን እፈጽማለሁ፤ እናገራለሁም፡፡ እኔ እውነትን እናገራለሁ፤ የአንተም ቃል እውነት ነው:: ዛሬ ቃልህ፣ በእኔ ውስጥና በእኔ በኩል ጽድቅን እያፈራ፤ በልቤ እና በአፌ ነው፤ በኢየሱስ ስም:: አሜን::

ጸሎት

Page 20: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - Christ Embassycedmvas.org/wp-content/uploads/2017/11/Rhapsody-Of... · እንደሆነ ያስባሉ፤ ምን ማለት እንደሆነ ከተረዳችሁ፣

የውሀ ጥምቀት መውሰድ ይገባኛል?

በእርግጥ አዎ! እንደ ክርስቲያን፣ የውሀ ጥምቀት እናንተ ማድረግ ከሚገባችሁ ዋና ዋና የቤተክርስቲያን ስነ-ስርዓቶች አንዱ ነው፡፡ የቤተክርስቲያን ስነ-ስርዓት ማለት የውስጥ ጸጋን ስለሚያካፍል፣ መንፈሳዊ ትርጉም ያለው አንድ አካላዊ ተግባር ወይም ትዕዛዝ ነው፡፡ ለምን ያስፈልጋል? የውሃ ጥምቀት አስፈላጊ የሆነበት ዋና ምክንያት፣ የአንድ መንፈሳዊ ክስተት አካላዊ ምልክት በመሆኑ ነው፡፡ ልክ መገረዝ እግዚአብሄር ከአብርሃም ጋር ላደረገው ቃል ኪዳን አካላዊ ምልክት እንደነበረው ሁሉ፣ የውሃ ጥምቀትም እናንተ ከክርስቶስ ጋር አንድ የመሆናችሁ አካላዊ ምልክት ነው፡፡ “ባፕቲዝም” የሚለው የእንግሊዘኛ ቃል (የውሃ ጥምቀት በአማርኛ) የመጣው “ባፕቲዞ” ከሚለው የግሪክ ቃል ነው፤ ትርጉሙም ሙሉ በሙሉ መጥለቅ ወይም በአንድ ነገር ውስጥ ሙሉ በሙሉ መስመጥ ማለት ነው፡፡ ስለዚህ የውሃ ጥምቀት አወሳሰድ ሙሉ በሙሉ ውሃ ውስጥ መጥለቅ እንጂ አንዳንድ ሰዎች እንደሚያስቡት በውሃ መረጨት አይደለም፡፡ በውሃ ውስጥ ስትጠልቁ በእምነት ከክርስቶስ ጋር በሞቱ፣ በቀብሩ እና በትንሣኤው አንድ መሆናችሁን እያወጃችሁ ነው፡፡ ስለዚህ አሁን ከክርስቶስ ጋር አብሮ ወራሾች እና ኢየሱስ አስታራቂ የሆነበት የአዲስ ኪዳን በረከቶችና ጥቅሞች ተካፋዮች ናችሁ፡፡

የውሃ ጥምቀት ባልወስድ ወደ መንግሥተ-ሰማያት እገባለሁ? ጌታ ኢየሱስ እንዲህ ብሏል:- “ያመነ የተጠመቀም ይድናል፥ ያላመነ ግን ይፈረድበታል።” (ማርቆስ 16፡16)፡፡ እርሱ በውሃ ካልተጠመቅን እንደማንድን አልነገረንም፡፡ ልክ የጌታ ራት እንዳለመውሰድ ነው፤ ወደ መንግስተ-ሰማያት አለመግባት ማለት ግን አይደለም፡፡ ነገር ግን፣ እነኚህ ነገሮች ጌታ አድርጉት ስላለን ማድረግ ያለብን ለቤተክርስቲያን የተሰጡ አስፈላጊ የሆኑ ስርዓቶች ናቸው፡፡

የውሃ ጥምቀት ለመውሰድ ምን ያስፈልገኛል? የውሃ ጥምቀት ለመውሰድ ብቸኛው መመዘኛ ዳግም መወለድ ነው፡፡ በኢየሱስ ክርስቶስ የሚያምን ማንኛውም ሰው ውሃ ጥምቀት ለመውሰድ ብቁ ነው፡፡ ዳግም ተወልዳችሁ ከሆነ፣ በአጥቢያ ቤተክርስቲያናችሁ የውሃ ጥምቀት መውሰዳችሁን አረጋግጡ፡፡ እግዚአብሄር ለሁሉም ልጆቹ ቤተሰባዊ የሆነ ሁኔታን የሚሰጠው በአጥቢያ ቤተክርስቲያኖች አማካኝነት ስለሆነ፣ በአጥቢያ ቤተክርስቲያን ውስጥ ተሳተፉ፡፡

Page 21: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - Christ Embassycedmvas.org/wp-content/uploads/2017/11/Rhapsody-Of... · እንደሆነ ያስባሉ፤ ምን ማለት እንደሆነ ከተረዳችሁ፣

Te ¨h

Te ¨

h

Page 22: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - Christ Embassycedmvas.org/wp-content/uploads/2017/11/Rhapsody-Of... · እንደሆነ ያስባሉ፤ ምን ማለት እንደሆነ ከተረዳችሁ፣

amharic

ጌታ ኢየሱስ በመስቀል ላይ የተሰቃየው፣ ህመምን የተቀበለው እና የተዋረደው፤ በራሱ ሀጢአት ምክንያት ወይም ለራሱ ሲል

ሳይሆን፤ ለእኛ ሲል ነው:: የእኛን ቦታ ወስዶ በእኛ ቦታ የኃጢአትን ቅጣትን ተቀበለ:: በመስቀል ላይ የኃጢያታችንን ሸክም ተሸክሞ፤ በስቃይ እየጮኸ “ኤሎሄ፥ ኤሎሄ፥ ላማ ሰበቅታኒ? ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ፤ ትርጓሜውም አምላኬ፥ አምላኬ፥ ለምን ተውኸኝ? ማለት ነው” (ማርቆስ 15:34)።

የእኛ ኃጢአቶች በእርሱ ላይ ስለነበሩ፤ እግዚአብሔር በኢየሱስ ላይ ጀርባውን አዞረበት:: ዕንባቆም 1:13 እግዚአብሔር ጻዲቅ እና ጠማምነትንም መመልከት እንደማይችል ይነግረናል:: ኢየሱስ፤ በእኛ ኃጢአት ምክንያት ከአባቱ መለየት ፈጽሞ የማይፈልገው ስለነበረ፤ በጌተሰማኒ የአትክልት ስፍራ እንዲህ በማለት ጸልይዋል፡- “ብትፈቅድ ይህችን ጽዋ ከእኔ ውሰድ፤ ነገር ግን የእኔ ፈቃድ አይሁን የአንተ እንጂ”።

የአብ ፍቃድ አሸነፈ፤ ኢየሱስም በመስቀል ላይ ሞተ፤ ወደ ሲዖልም ወረደ :: ለሥቃይም ተዳረገ:: አስፈላጊ የሆነውን ቅጣት ሁሉ ከተቀበለ በኋላ መጽሐፍ ቅዱስ በመንፈስ ጸደቀ ይላል (1ኛ ጢሞቴዎስ 3:16) እናም እንደገና ህያው ሆነ:: ለእኛ ጽድቅ እርሱ ህያው ሆነ፥ “ስለ በደላችን አልፎ የተሰጠውን እኛን ስለ ማጽደቅም የተነሣውን...” (ሮሜ 4:24-25)::

መጽደቅ ማለት ከበደል ነጻ መሆን፥ ጻዲቅ መባል ማለት ነው:: እርሱ በሞቱም በትንሳሄውም የእኛ ምትክ ሆነ:: እርሱ ሲሞት እናንተ አብራችሁ ሞታችኋል፥ እርሱ ሲቀበር እናንተም አብራችሁ ተቀበራችኋል:: እግዚአብሔር ከሙታን ሲያስነሳው እናንተም አብራችሁ በአዲስ ህይወት ተነስታችኋል!

ኃጢያት እና የኃጢያት ተፅእኖዎች እና ውጤቶች በእናንተ ላይ

ስለእኛ ሀጢያት እርሱ ተቀጣ

እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ ...

(ኢሳይያስ 53:5)

ማክሰኞ 8

Page 23: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - Christ Embassycedmvas.org/wp-content/uploads/2017/11/Rhapsody-Of... · እንደሆነ ያስባሉ፤ ምን ማለት እንደሆነ ከተረዳችሁ፣

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የዮሐንስ ወንጌል 4:1-26 & መጽሀፈ ነገስት ቀዳማዊ 1

1ኛ ቆሮንጦስ 6:1-11 & መጽሀፈ ምሳሌ 4

ሮሜ 5:7-11; 2ኛ ቆሮንጦስ 5:21

የበላይነት የላቸውም:: በጽድቅ እና በእውነተኛ ቅድስና እግዚአብሔርን ለማገልገል እና ለእርሱ ለመኖር ነጻ ናችሁ:: እናንተ ጻዲቅ ብቻ ሳይሆን በክርስቶስ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ጽድቅ ተደርጋችኋል::

ውድ አባት ሆይ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ለኃጥያት የመጨረሻውን መስዋዕት እንደከፈለ በማወቅ ሐሴት አደርጋለሁ፤ አሁን፤ በአንተ መገኘት ጻዲቅ ሆኜ ቆሜያለሁ:: እኔ አሁን ከክርስቶስ ጋር ለዘላለም ወደምነግስበት እና ወደምገዛበት አዲስ የጽድቅ ህይወት ስላስገባኸኝ አመሰግንሃለሁ፤ በኢየሱስ ስም:: አሜን::

ጸሎት

Page 24: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - Christ Embassycedmvas.org/wp-content/uploads/2017/11/Rhapsody-Of... · እንደሆነ ያስባሉ፤ ምን ማለት እንደሆነ ከተረዳችሁ፣

amharic

የእግዚአብሔር ቃል ታማኝ ነው:: እርሱ የሚናገረው ሁሉ ፍጹም እውነት ነው፤ እናም በህይወታችሁ ልትወራረዱበት ትችላላችሁ::

ጌታ ኢየሱስ ለመስበክ የጴጥሮስን ጀልባ ተጠቅሞ ሲጨርስ መረቡን ወደ ባህር እንዲጥልና ዓሣ እንዲያጠምድ አዘዘው::

ጴጥሮስና ጓደኞቹ ዓሣ ለማጥመድ ሌሊቱን ሙሉ ያለምንም ውጤት ደክመዋል፤ ስለዚህ ኢየሱስን እንዲህ አለው፡- “…አቤቱ፥ ሌሊቱን ሁሉ አድረን ስንደክም ምንም አልያዝንም …” (ሉቃስ 5:5)፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር ይመስገን ጴጥሮስ ያንን ብሎ ብቻ አልቆመም፤ እንዲህ ሲል ቀጠለ፡- “… ነገር ግን በቃልህ መረቦቹን እጥላለሁ አለው”። ጌታ ስለተናገረ ጴጥሮስ አደረገ፤ እናም ውጤቱ እጅግ ታላቅ ስለነበር፤ ብዙ ዓሣዎችን ወደ ባሕሩ ዳርቻ ማውጣት እንዲያግዙት ከጓደኞቹ እርዳታ አስፈለገው (ሉቃስ 5:6-7):: አዎን፤ ቃሉን ማድረግ የእግዚአብሔርን ኃይል ያነሳሳል!

አብዛኛውን ጊዜ፥ ሰዎች የእግዚአብሔር ኃይል በህይወታቸው የበላይ እንደሚያደርጋቸው ምንም ጥርጥር የላቸውም፤ ነገር ግን እንዴት ኃይሉን ማነሳሳት እና በግል ህይወታቸው እንዴት ሊጠቀሙበት እንደሚችሉ አያውቁም:: አንዳንዶች እንዲህ ይላሉ፡- “የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ እንደሚናገር አውቃለሁ፥ ነገር ግን…!”፡፡ ችግራቸው ያ ነው፤ ቃሉን በተመለከተ “ይህ ካልሆነ” እና “ነገር ግን” የሚባል ነገር የለም፤ ቃሉን ብቻ አድርጉት! ስታደርጉት እርሱ በሃይሉ ያረጋግጠዋል፤ እናም መለኮታዊ ውጤት ይመጣል::

ጌታ ኢየሱስ በቃና ዘገሊላ የሠርግ ድግስ ላይ ውሃን ወደ ወይን የለወጠበትን ጊዜ አስታውሱ! ከተአምሩ በፊት፥ ማርያም ለአገልጋዮቹ

ቃሉን ማድረግ

ስምዖንም መልሶ፦ አቤቱ፥ ሌሊቱን ሁሉ አድረን ስንደክም ምንም አልያዝንም፤ ነገር ግን በቃልህ መረቦቹን እጥላለሁ

አለው። (ሉቃስ 5:5)

ረቡዕ 9

Page 25: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - Christ Embassycedmvas.org/wp-content/uploads/2017/11/Rhapsody-Of... · እንደሆነ ያስባሉ፤ ምን ማለት እንደሆነ ከተረዳችሁ፣

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የዮሐንስ ወንጌል 4:27-54 & መጽሀፈ ነገስት ቀዳማዊ 2-3

1ኛ ቆሮንጦስ 6:12-20 & መጽሀፈ ምሳሌ 5

የማቴዎስ ወንጌል 7:24-27; Á°qw 2:20-22

“የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ አለቻቸው”(ዮሐንስ 2:5) ብላቸው ነበር። ሚስጥሩ ይህ ነው:: ጌታም አገልጋዮቹ ጋኖቹን ውኃ እንዲሞሉአቸው አዘዘ፤ ይህ ስሜት የሚሰጥ ባይሆንም እንኳን፤ እንደተነገራቸው አደረጉ:: እንግዶችም ሲጠጡት፤ ከቀመሱት ወይን ሁሉ የተሻለ ጣዕም ያለው ወይን ነበር (ዮሐንስ 2:1-10)::

ቃሉን ለሚያደርግ ሰው ሁልጊዜ ተዓምር እና ምስክርነት አለ:: ሁልጊዜም ከቃሉ ጋር የሚጣጣም ነገር ተናገሩ እና አድርጉ፤ እናም የእግዚአብሔር ኃይል ይቆጣጠራችኋል፤ የምትፈልጉትንም ውጤት እንድታገኙ ያስችላችኋል:: ሃሌሉያ!

የእግዚአብሔር ቃል የህይወቴ ብርሀን ነው፤ እናም በቃሉ በየትኛውም ሥፍራ በጥበብ እየተመላለስኩና የእግዚአብሄርን ክብር እየገለጥኩ፣ በክርስቶስ ያለኝን ርስት አያለሁ፤ እወርሳለሁም፡፡ ዛሬ ሁኔታዎችን በማስገዛት በልዕለ ተፈጥሯዊ ማንነት እመላለሳለሁ፤ አሳያለሁም፤ በኢየሱስ ስም:: አሜን::

የእምነት አዎጅ

Page 26: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - Christ Embassycedmvas.org/wp-content/uploads/2017/11/Rhapsody-Of... · እንደሆነ ያስባሉ፤ ምን ማለት እንደሆነ ከተረዳችሁ፣

amharic

ኢየሱስ በእርግጥ ማን እንደሆነ የማያውቁ አንዳንድ ክርስቲያኖች አሉ፤ እናም እስከምታውቁት ድረስ በእርሱ እውነተኛ እምነት

ሊኖራችሁ አይችልም:: ብዙዎች የሚያውቁት እርሱ የእግዚአብሄር ልጅ እንደሚባል ብቻ ነው፡፡ “የእግዚአብሔር ልጅ” ማለት ምን ማለት ነው ብላችሁ ስትጠይቁ ግን ብዙዎች አያውቁም::

“የእግዚአብሔር ልጅ” ማለት በሥጋ የተገለጠው እግዚአብሔር ማለት ነው:: በዮሐንስ 4:24 ላይ ኢየሱስ ለሳምራዊቷ ሴት “እግዚአብሔር መንፈስ ነው” አላት፤ ይህም ማለት ሥጋዊ አካል የለውም ማለት ነው:: ስለዚህ ኢየሱስ ማን ነው? ኢየሱስ “የእግዚአብሔር አካል” ነው::

የመክፈቻ ጥቅሳችን “በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና” ይላል:: ይህ ማለት ደግሞ የመለኮት ሙላት ሁሉ በኢየሱስ አካል ውስጥ ይኖራል ማለት ነው:: ኢየሱስ በምድር ላይ በተመላለሰበት ጊዜ፣ የመለኮት ሙላት ሁሉ በእርሱ ውስጥ መኖርያውን አድርጎ ነበር:: እርሱ በሰው አካል ውስጥ ሆኖ የሚራመድ እና የሚያወራ ህያው እግዚአብሔር ነበር:: ስለዚህ እግዚአብሔር በመልክ ምን እንደሚመስል ማወቅ ከፈላጋችሁ ኢየሱስን ተመልከቱ::

ብሎ መናገሩ አያስገርምም:: በመቀጠልም በዮሐንስ 14:9 ላይ “…እኔን ያየ አብን አይቶአል…” ብሏል:: ሕግን ለሙሴ የሰጠው እና ሙሴን ከቁጥቋጦው እሳት እና የእስራኤልን ልጆች በክብሩ ያናገረው እግዚአብሔር፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ውስጥ ሆኖ በገሊላ መንገዶች የተመላለሰው ያው እግዚአብሔር ነው:: ሆኖም ግን አላወቁትም ነበር::

ዮሐንስ 1:10-11 እንዲህ ይላል፡- “በዓለም ነበረ፥ ዓለሙም በእርሱ ሆነ፥ ዓለሙም አላወቀውም። የእርሱ ወደ ሆነው መጣ፥ የገዛ ወገኖቹም አልተቀበሉትም።” እግዚአብሔር በክርስቶስ አካል ውስጥ ሆኖ ወደ ዓለም መጣ፤ ነገር ግን አላወቁትም ነበር:: መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፡

የመለኮት ሙላት መገለጫ

በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና። (ቆላስይስ 2:9)

ሐሙስ 10

Page 27: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - Christ Embassycedmvas.org/wp-content/uploads/2017/11/Rhapsody-Of... · እንደሆነ ያስባሉ፤ ምን ማለት እንደሆነ ከተረዳችሁ፣

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የዮሐንስ ወንጌል 5:1-30 & መጽሀፈ ነገስት ቀዳማዊ 4-6

1ኛ ቆሮንጦስ 7:1-9 & መጽሀፈ ምሳሌ 6

ቆላስያስ 1:26-27; 1ኛ ዮሐንስ 4:4; ቆላስያስ 3:3

- “እግዚአብሔር ሙላቱ ሁሉ በእርሱ (በኢየሱስ) እንዲኖር…ፈቅዶአልና” (ቆላስይስ 1:19-20)።

እንግዲህ አስደናቂው ነገር ይህ ነው፤ ቆላስይስ 2:10 እንዲህ ይላል፡- “…በእርሱ (በኢየሱስ ክርስቶስ) ሆናችሁ ተሞልታችኋል”። “ተሞልታችኋል” የሚለው ቃል ሙሉነትን ፥ ሙሉ መሆንን ያመለክታል! በዛ ኢየሱስ ሙሉ በሆነበት፣ እናንተም ሙሉ ተደርጋችኋል:: ስለዚህ የመለኮት ሙላት በእናንተ ውስጥ መኖሪያውን አድርጓል ማለት ነው::

ስለዚህ ልክ እንደ ኢየሱስ፥ እናንተም የመለኮት አምሳያ ናችሁ:: ይህም የሆነው መንፈስ ቅዱስ ወደ ህይወታችሁ ሲመጣ ነው፥ እርሱ የመለኮትን ሙላት ወደ እናንተ አምጥቶአል፥ ልክ በኢየሱስ ውስጥ እንደነበረው ዛሬ በእናንተ ውስጥም የመለኮት ሙላት ይኖራል:: ስለዚህ እንደ እርሱ እናንተም የሕያው እግዚአብሔር ህያው ማደሪያዎች ናችሁ::

እኔ በእግዚአብሔር ተሞልቻለሁ፥ እግዚአብሔር በእኔ ውስጥ አለ፥ እርሱ በእኔ ውስጥ ይራመዳል፥ እርሱ በእኔ ውስጥ ይናገራል፥ ስለዚህ እኔ ተራ ሰው አይደለሁም:: በእኔ ውስጥ ያለው በዓለም ካለው ይበልጣል:: ዓለም ከእግሬ በታች ነው፤ እናም በድል እና በብልጽግና መንገድ እጓዛለሁ፡፡ ሃሌሉያ!

የእምነት አዋጅ

Page 28: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - Christ Embassycedmvas.org/wp-content/uploads/2017/11/Rhapsody-Of... · እንደሆነ ያስባሉ፤ ምን ማለት እንደሆነ ከተረዳችሁ፣

amharic

በኤፌሶን ምእራፍ አንድ ፣ የእግዚአብሄር መንፈስ በሃዋርያው ጳውሎስ በኩል ለኤፌሶን ቤተክርስቲያን እንዲህ ብሎ ጸለየ፡-

“የክብር አባት የጌታችን የእየሱስ ክርስቶስ አምላክ እርሱን በማወቅ የጥበብና መገለጥ መንፈስ እንዲሰጣችሁ እለምናለሁ” (ኤፌ 1፡17)፡፡

የጸሎቱን ትኩረት አስተውሉ፤ እግዚአብሄር የጥበብና የመገለጥ መንፈስ እንዲሰጣቸው ነው፤ ለክርስቲያን ህይወት በመለኮታዊ ጥበብ መራመድ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ወደ እግዚአብሄርን ቃል መድረሻ ካገኛችሁ፣ ለመለኮታዊ ጥበብም መድረሻ አግኝታችኋል፤ ምክንያቱም የእግዚአብሄር ቃል የእግዚአብሄር ጥበብ ነው፡፡

በህይወታችሁ ያላችሁ ልምምድ ምንም ቢሆን ለውጥ አያመጣም፤ መካሪዎቻችሁ ማንም ቢሆኑ ግድ አይልም፤ ያነበባችኋቸው መጽሃፍት ብዛት ወይም በህይወት ያያችኋቸው ነገሮች ግድ አይሉም፤ ቃሉ በውስጣችሁ ከሌለ፣ የእግዚአብሄር ጥበብ አጥሯችኋል፡፡ ለእናንተ ደግሞ በህይወት ስኬታማ ለመሆን ጥበብ ያስፈልጋችኋል፡፡ ጥበብ አይነተኛ ነገር ናት (ምሳ4፡7)፣ በሌላ አነጋገር፣ የሚያስፈልጋችሁ ዋናው ነገር ጥበብ ነው፡፡

የሰው ጥበብ እስከ አንድ የተወሰነ ቦታ ድረስ ያደርሳችኋል፤ እስከመጨረሻው የሚያደርሳችሁ የእግዚአብሄር ጥበብ ብቻ ነው፤ እናም ሁለንተናዊ የሆነ ስኬት እንዲኖራችሁ ያደርጋችኋል፡፡ መጽሃፍ ቅዱስ ሲናገር ክርስቶስ ለእናንተ ጥበብ ተደርጓል (1ኛ ቆሮ 1፡30) ይላል፤ ስለዚህ ጥበብ አይጎድላችሁም፡፡ ሁሉም ጥበብና እወቀት በውስጡ ያሉት ክርስቶስ በእናንተ ውስጥ ነው፤ ሚስጥርን ወደ ማወቅና ያልተገለጠውን ወደ መግለጥ የሚያበቃ ዕይታ አላችሁ፡፡

እናንተ ከተፈጥሮ በላይ የሆነ የአእምሮ ብቃት፣ ጥበበኛና እንዲሁም

ወደ መለኮታዊ ጥበብ መድረሻ

ነገር ግን የሚመካ በእግዚአብሄር ይመካ ተብሎ እንደተጻፈው ይሆን ዘንድ ፣ከእግዚአብሄር ዘንድ ጥበብና ጽድቅ ቅድስና ቤዛነትም በተደረገልን በክርስቶስ እየሱስ

የሆናችሁ ከእርሱ ነው። (1ኛ ቆሮ 1፡30)

አርብ 11

Page 29: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - Christ Embassycedmvas.org/wp-content/uploads/2017/11/Rhapsody-Of... · እንደሆነ ያስባሉ፤ ምን ማለት እንደሆነ ከተረዳችሁ፣

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የዮሐንስ ወንጌል 5:31-47 & መጽሀፈ ነገስት ቀዳማዊ 7-8

1ኛ ቆሮንጦስ 7:10-24 & መጽሀፈ ምሳሌ 7

1ኛ ቆሮንጦስ 1:30-31; ኤፌሶን 1:17-19; ኤፌሶን 3:10-12

ነገሮችን ፈጥኖ የመረዳት ችሎታ ያላችሁ ናችሁ፡፡ ይህንን እውነት ለራሳችሁ እወቁና በዚህ ብርሃን ተመላለሱ፡፡ መጽሃፍ ቅዱስ ሲናገር “የእምነትህ ህብረት፣ በእኛ ዘንድ ያለውን በጎ ነገር ሁሉ በማወቅ፣ ለክርስቶስ እየሱስ ፍሬ እንዲያፈራ እጠይቃለሁ”(ፊል 1፡6)፡፡ ክርስቶስ ጥበባችሁ ነው፤ አረጋግጡት፡፡ የጥበብ መንፈስ በእናንተ ውስጥ ስላለ፣ መጥፎ ውሳኔ እንደማትወስኑ አውጁ!

ዛሬ ያሰባችኋቸውን ነገሮች ልትሰሩ ስትወጡ፣ አስተሳሰባችሁ ክርስቶስ ጥበባችሁ እንደሆነ ይሁን፤ ስለዚህ ምርጫዎቻችሁ፣ ተግባራችሁ እና ቃሎቻችሁ እግዚአብሄር ለህይወታችሁ ካለው እቅድና አላማ ጋር የተጣጣመ ይሆናል፡፡

ውድ አባት ሆይ በክርስቶስ የጥበብ መቀለጫ ስላደረግኸኝ አመሰግንሃለሁ። ክርስቶስ ጥበቤ ስለሆነ፣ እኔ ጥበበኛ ነኝ፤ ዛሬ በድርጊቶቼ ጥበብ ይታያል፤ በቃሌም ጥበብ ይሰማል፤ ለሚስጥራት ዕይታ አለኝ፤ ጥርጣሬዎችን አስወገግጄ አስቸጋሪ አረፍተ ነገሮችን እገልጣለሁ፡፡ ሃሌሉያ!

ጸሎት

Page 30: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - Christ Embassycedmvas.org/wp-content/uploads/2017/11/Rhapsody-Of... · እንደሆነ ያስባሉ፤ ምን ማለት እንደሆነ ከተረዳችሁ፣

amharic

በመግቢያ ጥቅሳችን ማን እንደሆንን እና እግዚአብሄር ምን እንድናደርግ እንደሚፈልግ በግልጽ ተቀምጧል፤ እኛ የክብሩ

መገለጫ እና የእርሱ ማንነት ግልጽ ምስል ነን፡፡ አለም እንዲያየው የተቀመጠ የእርሱ ዋንጫዎች ነን፡፡ የእርሱን በጎነትና ፍጹምነት እናሳያለን፡፡

ሌሎች እንደሚያይዋችሁ ወይም እናንተ እራሳችሁን እንደምታዩት ሳይሆን፤ እግዚአብሄር እናንተን በሚያይበት ማለትም ቃሉ እናንተን በሚገልጽበት መንገድ ራሳችሁን ማየት እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ እምነታችሁ ውጤታማ እንዲሆን ያደርገዋል፡፡ አንዳንዴ ህይወታችሁን ታዩና በእርግጥ እግዚአብሄር ናችሁ እንዳላችሁ እንዳልሆናችሁ ታስባላችሁ፤ ያ የሚሆነው ግን እናንተ የተሳሳተው ነገር ላይ ስላተኮራችሁ ነው፡፡ ትኩረታችሁን ከራሳችሁ ላይ አንሱና፣ በቃሉ ላይ አተኩሩ፡፡ ቃሉ ስለእናንተ በተናገረው ማንነታቸሁ፣ በእውነተኛ ማንነታችሁ፣ ገደብ በሌለው ማንነታችሁ፣ እና በክርስቶስ ኢየሱስ ባላችሁ ክብር ላይ አሰላስሉ፡፡

2ኛ ቆሮ 3፡18 ሲናገር “እኛ ሁላችን በመጋረጃ በማይከደን ፊት የጌታን ክብር እንደ መስተዋት እያብለጨለጭን መንፈስ ከሚሆን ጌታ እንደሚደረግ ያን መልክ እንመስል ዘንድ ከክብር ወደ ክብር እንለወጣለን”፡፡ የእግዚአብሄርን ክብር በቃሉ ውስጥ (በእግዚአብሄር መስታወት) ስታዩት፣ በቃሉ ውሰጥ ወደምታዩት ተመሳሳይ ምስል ትለወጣላችሁ፡፡

ቃሉን የበለጠ ባያችሁ ቁጥር፣ የበለጠ ማን እንደሆናችሁ ታውቃላችሁ። መንፈሳችሁ ምን እንደሚመስል የምታውቁበት ብቸኛው መንገድ፣ ቃሉን መመልከት ነው፡፡ ቃሉ እውነተኛ ምስላችሁን ያሳያችኋል! ሃሌሉያ!

የእናንተ እውነተኛ ምስል

እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ ፣የንጉስ

ካህን ፣ቅዱስ ህዝብ ፣ለርስቱ ተለየ ወገን ናችሁ። (1ኛ ጴጥ 2፡9)

ቅዳሜ 12

Page 31: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - Christ Embassycedmvas.org/wp-content/uploads/2017/11/Rhapsody-Of... · እንደሆነ ያስባሉ፤ ምን ማለት እንደሆነ ከተረዳችሁ፣

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የዮሐንስ ወንጌል 6:1-24 & መጽሀፈ ነገስት ቀዳማዊ 9

1ኛ ቆሮንጦስ 7:25-40 & መጽሀፈ ምሳሌ 8

1ኛ ዮሐንስ 4:17; 2ኛ ቆሮንጦስ 3:18

የተባረክህ አባት ሆይ፣ እውነተኛ ምስሌን ስለሚያሳየው አስደናቂ ቃልህ አመሰግንሃለሁ፤ ቃልህን ሳሰላስል ህይወቴ ይቀየራል፤ በዙርያዬ ባሉ ነገሮች እና ሰዎች በሙሉ ላይ ተጽዕኖ እያመጣ፣ ክብርህ በእኔ ውስጥና በእኔ በኩል ያለማቋረጥ እየጨመረ ነው፤ በኢየሱስ ስም፡፡ አሜን፡፡

ጸሎት

Page 32: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - Christ Embassycedmvas.org/wp-content/uploads/2017/11/Rhapsody-Of... · እንደሆነ ያስባሉ፤ ምን ማለት እንደሆነ ከተረዳችሁ፣

amharic

ጌታ ኢየሱስ ከላይ ባለው ጥቅስ ላይ፣ ለአባቱ ለእኛ በጸለየው ጸሎት ትኩረት የሚስብ ንግግር አድርጓል፤ እና አባቱ እንደሰማውም

እናውቃለን፡፡ ስለዚህ እኛ የኢየሱስ ክብር አለን፡፡ ይሄ እጅግ ጥልቅ ነገር ነው!

መጽሃፍ ቅዱስ ሲናር ኢየሱስ ክርስቶስ የክብሩ መንጸባረቅና የባሕርዩ ምሳሌ ነው ይላል (ዕብ1፡3)፡፡ ዛሬ በትክክል የእኛ ማንነት ይህ ነው፤ ምክንያቱም መጽሃፍ ቅዱስ በእርሱ ምሳሌና አምሳል ተፈጥረናል ይላል፡፡ የተወለዳችሁት የእግዚአብሄር ክብር ለመሆን ነው፡፡

ቆላ 1፡27 “የክብር ተስፋ ያለው ክርስቶስ በእናንተ ውስጥ ነው” ይላል፤ ያ ማለት ክርስቶስ በእናንተ ወስጥ ስለሆነ ክብሩ እየመጣ ነው ማለት አይደለም፡፡ ይልቁኑ ክርስቶስ በውስጣችሁ ስላለ፣ ክብር መጥቷል ማለት ነው፡፡ እግዚአብሄር ይባረክ! 2ቆሮ 3፡18 የእግዚአብሄርን ክብር በመስታወት ስናይ ወደምናየው ምስል እንደምንቀየር ያስረዳል፤ የምናየውም ምስል የእግዚአብሄር ክብር ነው፡፡ ስለዚህ እኛ የእግዚአብሄር ክብር በውስጣችን መኖሩ ብቻ ሳይሆን፣ እኛ የእግዚአብሄር ክብር ነን፡፡

የሰማይ አባታችን “የክብር አባት” ተብሎ ቢጠራ አያስገርምም፤ ቤተክርስቲያን የእግዚአብሄር ክብር ናት፡፡ መስተዋት ስታዩ የምታዩት ያ ምስል ማለትም ቃሉ፣ የእናንተ ትክክለኛው ማንነታችሁ ነው!

በአዲስ ኪዳን የተነገሩን መገለጦች በክርስቶስ ያላችሁን ማንነትና ክብር ያንጸባርቃሉ፡፡ ስለዚህ ወደ እግዚአብሄር መስተዋት መመልከትን ቀጥሉ፣ ቃሉን ማሰላሰል እና ማጥናት ቀጥሉ፣ እንደዛ ስታደርጉ በቋሚነት ከክብር

ክብሩ በእናንተ ውስጥ

እኛም አንድ እንደ ሆንን አንድ ይሆኑ ዘንድ፤ እኔም በእነርሱ አንተም በእኔ ስትሆን፥ በአንድ ፍጹማን እንዲሆኑ፥ የሰጠኸኝን ክብር እኔ ሰጥቻቸዋለሁ፤

(ዩሃ 17፡22)

እሁድ 13

Page 33: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - Christ Embassycedmvas.org/wp-content/uploads/2017/11/Rhapsody-Of... · እንደሆነ ያስባሉ፤ ምን ማለት እንደሆነ ከተረዳችሁ፣

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የዮሐንስ ወንጌል 6:25-59 & መጽሀፈ ነገስት ቀዳማዊ 10-11

1ኛ ቆሮንጦስ 8:1-13 & መጽሀፈ ምሳሌ 9

2ኛ ቆሮንጦስ 3:7-10; ሮሜ 8:30

ወደ ክብር ትቀየራላችሁ፡፡አሁን ሐሴት እያደረጋችሁ እንዲህ ብላችሁ አውጁ፡- “እኔ የእግዚአብሄር

ክብር ነኝ፤ ዛሬና ሁሌም፣ ጽድቅን፣ ልቀትን እና ፍጽምናን እገልጻለሁ፤ የእኔ ህይወት ሁልጊዜም የሚጨምር የክብር ህይወት ነው ፡፡” ሃሌሉያ!

ክርስቶስ ህይወቴ፣ጽድቄ እና ሁለንተናዬ ነው! እርሱ የሆነውን ሁሉ አድርጎኛል፤ እርሱ ያለውንም ነገር ሁሉ ሰጥቶኛል! አሁን የእርሱ ህይወትና የጽድቅ ተፈጥሮ ተካፋይ ስለሆንኩኝ፣ የክብሩ ማንጸባረቂያ መሆኔን በማወቅ፣ ደስ ይለኛል፤ እኔ የእርሱ ውበት ፍጻሜ ነኝ፡፡ እግዚአብሄር ለዘላለም ይባረክ!

የእምነት አዋጅ

Page 34: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - Christ Embassycedmvas.org/wp-content/uploads/2017/11/Rhapsody-Of... · እንደሆነ ያስባሉ፤ ምን ማለት እንደሆነ ከተረዳችሁ፣

amharic

በምድር ላይ ያላችሁ ዋነኛ አላማ የእግዚአብሄርን መንግስት መመስረት ነው፡፡ ወንጌሉ ለሚያምን ሁሉ የእግዚአብሄር

ሃይል ለማዳን እንደሆነ አንብበናል፡፡ በሌላ አባባል፤ ለማዳን፣ ለመርዳት፣ ነጻ ለማውጣት እና ለመባረክ የእግዚአብሄር ሃይል በወንጌሉ ውስጥ ነው፡፡ ሰው የሚያስፈልገው ነገር ቢኖር የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል መስማትና ማመን ብቻ ነው፤ ከዚያም ለዘላለም ይለወጣል፡፡

በቀድሞው ቤተክርስቲያን የነበሩ ክርስትያኖች፣ ወንጌሉን ካለፍርሃት ለመስበክ ቁርጠኝነትን የሰጣቸው ይህ መረዳት ነበር፤ እነርሱ በወንጌሉ ድፍረት እና መተማመን ነበራቸው፡፡ ለወንጌል ሲሉ የታሰሩት፣ የተደበደቡት እንዲሁም የተገደሉት፣ የእግዚአብሄር የማዳን ሃይል ወንጌሉ እንደሆነ በመረዳታቸው ነው፡፡ ጠንካራ ተቃውም እና ስደት ቢገጥማቸውም፣ የኢየሱስን ስም ካለፍርሃት ከመስበክ አልተገደቡም (ሐዋ 5፡41)፡፡

ወንጌሉን መስበክ ብቻ በቂ አይደለም፣ የምትሰብኩትን ወንጌል መረዳት እና ሰው ሁሉ ያለው ብቸኛ ተስፋ መሆኑንም ማመን አለባችሁ። እናንተ በግል ያላችሁ የወንጌል መረዳት በጣም አስፈላጊ ነው፤ ምክንያቱም ህይወታችሁ “የወንጌላችሁ” ነጸብራቅ ስለሆነ ነው፡፡ የእናንተ ወንጌል ክርስቶስ ምን ሊያደርግ እንደመጣ እና በእናንተ የግል ህይወት ውስጥ ስላመጣው ጥቅም፣ ተጽእኖ እና ግንኙነት ያላችሁ መረዳት ነው፤ መልክታችሁን የሚቀርጸው ያ ነው፡፡ ስለዚህ የክርስቶስን ወንጌል በሙላት ካልተረዳችሁ፣ ስህተት የሆነ መልእክትን ትሰብካላችሁ፡፡

ሃዋርያትም የሰበኩት፣ ኢየሱስ ለማድረግ እና ለማስተማር የጀመረውን መልእክት (ሃዋ 1፡1)፣ ዛሬ እኛ ለአለማችን ለመውሰድ እድል የተሰጠን ያው መልእክት ነው፡፡ የምትሰብኩት እውነተኛውን መልእክት እንደሆነ እርግጠኛ ሁኑ፡፡ ይህንን መልእክት አጥኑት ፣ተረዱት እና ለሰው ልጅ መዳን ብቸኛው

ስለወንጌሉ ያላችሁ መረዳት

በወንጌል አላፍርምና ፣አስቀድሞ ለአይሁዳዊ ደግሞም ለግሪክ ሰው ለሚያምኑ ሁሉ የእግዚአብሄር ሃይል ለማዳን

ነውና። (ሮሜ 1፡16)

ሰኞ 14

Page 35: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - Christ Embassycedmvas.org/wp-content/uploads/2017/11/Rhapsody-Of... · እንደሆነ ያስባሉ፤ ምን ማለት እንደሆነ ከተረዳችሁ፣

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የዮሐንስ ወንጌል 6:60-71 & መጽሀፈ ነገስት ቀዳማዊ 12-14

1ኛ ቆሮንጦስ 9:1-10 & መጽሀፈ ምሳሌ 10

ዕብራውያን 5:13-14; ሮሜ 1:15-17

ተስፋና ሃይል እንደሆነም እርግጠኛ ሁኑ፡፡ከወንጌሉ ውጪ አማራጭ የለም፡፡ ከኢየሱስ ክርስቶስ ውጪ ሌላ

ወደ አብ ምንም መንገድ የለም፡፡ እርሱ እንዲህ አለ፡- “…እኔ መንገድና እውነት ህይወትም ነኝ ፣ በኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም”(ዩሃ 14፡6)፡፡ ይሄ ፍጹም እውነታ ነው፤ የእናንተ ቁርጠኝነት መመስረት ያለበትም በዚህ ላይ ሊሆን ይገባዋል፤ ንግግራችሁ፣ አስተሳሰባችሁ እና ስለ ህይወት ያላችሁ አመለካከት፣ ስለክርስቶስና ስለወንጌሉ ባላችሁ መረዳት እና መተማመን ላይ የተመሰረተ ሊሆን ይገባዋል፡፡

በምልክት የሚከተለውን የወንጌሉን የላቁ እውነታዎች እንዳውቅና እንድኖር በመንፈስ ቅዱስ የተሰጠኝን ይህንን መገለጥ፣ በማወጅ፣ የክርስቶስ ኢየሱስ ወንጌል ፍጹም መረዳት አለኝ፤ በኢየሱስ ስም፡፡ አሜን፡፡

ጸሎት

Page 36: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - Christ Embassycedmvas.org/wp-content/uploads/2017/11/Rhapsody-Of... · እንደሆነ ያስባሉ፤ ምን ማለት እንደሆነ ከተረዳችሁ፣

Te ¨h

Te ¨

h

amharic

Page 37: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - Christ Embassycedmvas.org/wp-content/uploads/2017/11/Rhapsody-Of... · እንደሆነ ያስባሉ፤ ምን ማለት እንደሆነ ከተረዳችሁ፣

Te ¨h

Te ¨

h

Page 38: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - Christ Embassycedmvas.org/wp-content/uploads/2017/11/Rhapsody-Of... · እንደሆነ ያስባሉ፤ ምን ማለት እንደሆነ ከተረዳችሁ፣

amharic

ጌታ ኢየሱስ በስጋ የተገለጠው የእግዚአብሄር ቃል ነው፤ ነገር ግን ያ እኛም እንደዚያ እንደሆንን ታውቃላችሁ? በ1ጴጥ 1፡23

መጽሃፍ ቅዱስ “ዳግመኛ የተወለዳችሁት ከሚጠፋ ዘር አይደለም ፣በህያውና ለዘላለም በሚኖር በእግዚአንሄር ቃል ከማይጠፋ ዘር ነው እንጂ”፡፡ ከቃሉ ተወልደናል፤ ያ ማለት ደግሞ እኛ የቃሉ ልጆች ነን፡፡

ክርስቲያን ማለት ከአንዱ ሃይማኖት ወደ ሌላው የሚቀያይር ወይም ነገሮችን የሚያደርግበትን መንገድ የቀየረ ሰው ማለት አይደለም፡፡ ክርስቲያን ማለት ቃል በቃል ሲገለጽ፣ ከእግዚአብሄር ማለትም ከቃሉ የተወለደ ማለት ነው፡፡ ያ ማለት ደግሞ በእናንተ ውስጥ ያለው ህይወት የቃሉ ህይወት

ነውጸሎት ከአሁን ወዲያ ከሚጠፋው የሰው ዘር አይደላችሁም፡፡ ጌታ ኢየሱስ “ከስጋ የተወለደ ስጋ ነው ከመንፈስ የተወለደ መንፈስ ነው” (ዮሐ 3፡6)፡፡ እናንተ ከስጋ ሳትሆኑ ከመንፈስ ናችሁ፡፡

1ኛ ዮሃ 4፡4 “ልጆች ሆይ እናንተ ከእግዚአብሄር ናችሁ…” ይላል፡፡ የእናንተ ምንጭ እግዚአብሄር ነው፤ የተገኛችሁት ከእርሱ ነው፡፡ ሃሌሉያ! ይህ እውቀት ሙሉ በሙሉ ህይወታችሁን እና የምትኖሩበትን መንገድ ይቀይራል፡፡ በክርስቶስ ያላችሁን እውነተኛ ማንነት ስታውቁ፣ በየቀኑ በድል አድራጊነት ትኖራላችሁ፡፡

መጽሃፍ ቅዱስ “ከእግዚአብሄር የተወለደ ሁሉ አለምን አሸንፎአል” (1ኛ ዮሃ 5፡4)፡፡ በ1ኛጴጥ 1፡23 ላይ ያነበብነውን ስታሰላስሉ፣ ያንን በአእምሮአችሁ ያዙ፡- “ዳግመኛ የተወለዳችሁት ከሚጠፋ ዘር አይደለም፣ በህያውና፤ ለዘላለም በሚኖር በእግዚአብሄር ቃል ከማይጠፋ ዘር ነው እንጂ”፡፡

እናንተን የወለደው ቃል ለዘላለም ህያውና የሚኖር ነው፡፡ ያ

የቃሉ ልጆች

ለፍጥረቱ በኩራት አይነት እንድንሆን በእውነት ቃል አስቦ ወለደን። (ያዕቆ 1፡18)

ማክሰኞ 15

Page 39: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - Christ Embassycedmvas.org/wp-content/uploads/2017/11/Rhapsody-Of... · እንደሆነ ያስባሉ፤ ምን ማለት እንደሆነ ከተረዳችሁ፣

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የዮሐንስ ወንጌል 7:1-24 & መጽሀፈ ነገስት ቀዳማዊ 15-17

1ኛ ቆሮንጦስ 9:11-19 & መጽሀፈ ምሳሌ 11

2ኛ ቆሮንጦስ 3:2-3; 1ኛ ጴጥሮስ 1:23; Á°qw 1:18

ስለእናንተ ተፈጥሮ፣ ማንነት ይናገራል፤ ፈጽሞ የማትበገሩ ናችሁ፤ የማትጠፉ

ናችሁጸሎት አለምን አሸንፋችኋል! ዳግም በተወለዳችሁበት ቅጽበት፣

የሚጠፋው የሰው ዘር በእግዚአንሄር ህይወትና ተፈጥሮ ተተክቷልጸሎት እናንተ ተራ ሰዎች አይደላችሁም፡፡ ክርስቶስ መኖርያውን በእናንተ ውስጥ አድርጓል፤ ከእርሱ ጋር አንድ ሆናችኋል፡፡ እርሱ እንዳለ እናንተም

ናችሁጸሎት እግዚአብሄር ይባረክ!

የተባረክህ አባት፣ ቃልህ ህይወቴ ነው! ከማይጠፋው ቃልህ ስለተወለድኩኝ፣ እኔ መለኮታዊ ህይወት አለኝ፡፡ በዚህ አለም ላለ ጨለማ፣ ችግር እና ጥፋት የማልበገርና ነጻ ነኝ፡፡ በአለም ካለው ይልቅ በእኔ ያለው ይበልጣል፡፡ ለዘላለም በክብርና በድል እኖራለሁ፤ በኢየሱስ ስም፡፡ አሜን፡፡

ጸሎት

Page 40: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - Christ Embassycedmvas.org/wp-content/uploads/2017/11/Rhapsody-Of... · እንደሆነ ያስባሉ፤ ምን ማለት እንደሆነ ከተረዳችሁ፣

amharic

እግዚአብሄር ቃሉን እንድታውቁ ይፈልጋል፤ በክርስቶስ ውስጥ እንዴት መመላለስ እንዳለባችሁ እንድታውቁ፣ መንፈሳችሁ

በመንፈሳዊ እውነታዎች እንዲሰለጥን እና እንዲማር ይፈልጋል፡፡ ዳግም በመወለዳችሁ፣ ወደ ክርስቶስ ተወልዳችኋል፤ እናንተ አሁን የምትኖሩት በዚያ ነው፡፡ ክርስቶስ ስብእና ብቻ ሳይሆን ስፍራም ነው፤ እናም ወደዚያ ስፍራ ስትመጡ፣ የምትኖሩትና የምትረዱት ከዚያ ስፍራ ነው፡፡

በክርስቶስ ውስጥ፣ የጥበብ እና የእውቀት ሃብት ሁሉ ለእናንተ ተገልጠዋል፣ ለሚሥጢራትና ላልተገለጠ ነገር ሁሉ ዕይታ አላችሁ፡፡ ህይወት ምስጢር ሳይሆን፣ የተረጋጋ የሚያስደስት እና በክብር የተሞላ ነው። በክርስቶስ ውስጥ በጥበብና በጽድቅ እንመላለሳለን፤ በድልና በበላይነት እንመላለሳለን፣ መቼም አንሸነፍም፡፡ እንዲህ ያለ ቦታ መኖር እንዴት አስደናቂ ነው! እናንተ ከዚህ ዓለም አይደላችሁም፡፡

ኢየሱስ እንዲህ ብሏል፡- “እኔ ከዓለም መረጥኋችሁ” (ዮሐንስ 15፡19)፡፡ ታዲያ ምን ይሁን? በክርስቶስ ውስጥና ከክርስቶስ ጋር ኑሩ! ክርስቶስ ከተማችሁና ሃገራችሁ ነው፤ ያም በመክፈቻ ጥቅሳችን ያነበብነው ተራራ ነው፤ ስሙም የጽዮን ተራራ ነው፤ የህያው እግዚአብሄር ከተማ ነው! በዚያ የጌታ መኖርያ ቤት በሆነው ተራራ ላይ ተተክለናል፤ የእግዚአብሄር ውበት እና ክብር ሁሉ የሚገኘው በዚያ ነው፡፡ አሁን ህይወታችሁ ለምን የውበት እና የክብር ብቻ እንደሆነ ልትረዱ ትችላላችሁ፡፡ መዝሙር 50፡2 እንዲህ ይላል፡- “ከክብሩ ውበት ከጽዮን እግዚአብሔር ግልጥ ሆኖ ይመጣል።”

መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፡- “ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥ ሁሉም አዲስ ሆኖአል።”

እናንተ ከዚህ ዓለም አይደላችሁም

ነገር ግን ወደ ጽዮን ተራራና ወደ ሕያው እግዚአብሔር ከተማ ደርሳችኋል፥ ወደ ሰማያዊቱም ኢየሩሳሌም፥ በደስታም ወደ ተሰበሰቡት ወደ አእላፋት መላእክት፥ (ዕብራውያን 11፡22)

ረቡዕ 16

Page 41: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - Christ Embassycedmvas.org/wp-content/uploads/2017/11/Rhapsody-Of... · እንደሆነ ያስባሉ፤ ምን ማለት እንደሆነ ከተረዳችሁ፣

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የዮሐንስ ወንጌል 7:25-8:1-11 & መጽሀፈ ነገስት ቀዳማዊ 18-19

1ኛ ቆሮንጦስ 9:20-27 & መጽሀፈ ምሳሌ 12

የዮሐንስ ወንጌል 15:19; ቆላስያስ 1:12-13

(2ኛ ቆሮ 5፡17)፡፡ በክርስቶስ እናንተ አዲስ ፍጥረት ናችሁ፤ አሮጌው ነገር ማለትም ባለፈው ጊዜ የነበሩ ውደቀቶች፣ በሽታዎች፣ ድካሞች፣ ጭንቀቶች እና ተስፋ መቁረጦች አልፈዋል፡፡ በሠይጣን እና በጨለማው ኃይላት ላይ የበላይነት ወዳለው የህይወት አዲስነት ገብታችኋል፡፡

ክርስቶስ ቦታዬ ነው፤ ምክንያቱም በእርሱ ውስጥ እኖራለሁ፤ እንቀሳቀሳለሁ፤ ማንነቴም በእርሱ ነው፡፡ እርሱ የእኔ ጥበብና ጽድቅ ነው፡፡ እኔ እግዚአብሄርን ስለምወደውና ለእርሱም ዓላማ ስለተጠራሁ፣ ለእኔ ሁሉም ነገር ለመልካም ይሰራል፡፡

የእምነት አዋጅ

Page 42: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - Christ Embassycedmvas.org/wp-content/uploads/2017/11/Rhapsody-Of... · እንደሆነ ያስባሉ፤ ምን ማለት እንደሆነ ከተረዳችሁ፣

amharic

የመክፈቻ ጥቅሳችን ከተፈጥሮ በላይ የሆነ ህይወት የመኖርን ምስጢር ይሰጠናል፤ ይህም በመንፈስ ቅዱስ መሞላት ነው፡፡

እንደ ክርስቲያን፣ በክርስትና ጉዟችሁ ውጤታማ መሆን ካለባችሁ፣ ይህ አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው፡፡ እናንተ ሁልጊዜ በመንፈስ ቅዱስ መሞላት አለባችሁ፡፡ “ይህ በእርግጥ የሚቻል ነገር ነው? ሁልጊዜ እኛ በመንፈስ ቅዱስ በቋሚነት ልንሞላ እንችላለን ወይ?” ብላችሁ ልትጠይቁ ትችላላችሁ፡፡

አዎ በእርግጥ ትችላላችሁ! ቃሉ እንደምንችል ይነግረናል፤ እናም የሚቀጥሉት የመክፈቻ ጥቅሳችን ቁጥሮች ከ19-21 እንዴት ሊሆን እንደሚችል ያሳየናል፡፡ እንዲህ ይላል፡- “በመዝሙርና በዝማሬ በመንፈሳዊም ቅኔ እርስ በርሳችሁ ተነጋገሩ፤ ለጌታ በልባችሁ ተቀኙና ዘምሩ፤ ሁልጊዜ ስለ ሁሉ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አምላካችንንና አባታችንን ስለ ሁሉ አመስግኑ። ለእያንዳንዳችሁ በክርስቶስ ፍርሃት የተገዛችሁ ሁኑ።”::

በየዕለቱ በመንፈስ ቅዱስ መሞላትን ተለማመዱ፡፡ ከቤታችሁ ወጥታችሁ ከመሄዳችሁ በፊት በመንፈስ ቅዱስ ተሞሉ! አምልኮ ከመምራታችሁ፣ ለወንጌል ስርጭት ከመውጣታችሁ፣ እና ወደ ስራችሁ ከመሄዳችሁ በፊት፣ በመንፈስ ቅዱስ ተሞሉ፡፡ በመንፈስ ቅዱስ ስትሞሉ፣ ከእናንተ የሚወጡ ቃላት የእናንተ ሳይሆኑ የእግዚአብሄር ናቸው፡፡ ስለሆነም እናንተ የምትናገሩት ሁሉ በኃይል ይወጣል፤ እናም በእርግጠኛነት ይፈጸማል፡፡

እናንተ በመንፈስ ቅዱስ ስትሞሉ፣ በእናንተ ላይ ወይንም በዙርያችሁ ምንም ቢከሰት አትናወጡም፡፡ ልክ እንደ ጳውሎስ “ምንም ነገር አያናውጠኝም” ትላላችሁ፡፡ ይህ ከተለመደው የመረዳት ደረጃ ያለፈ ህይወት ነው፤ ከሰው አእምሮ መረዳት እና ችሎታ በላይ የሆነ ህይወት ነው፤ ከዚህ ዓለም ባሻገር ያለ ህይወት ነው፡፡

ይህ፣ ኢየሱስ ለእኛ ያመጣልን ከተራ በላይ የሆነ ህይወት ነው፡፡

ሁልጊዜ በመንፈስ ቅዱስ መሞላትን ተለማመዱ

መንፈስ ይሙላባችሁ እንጂ በወይን ጠጅ አትስከሩ ይህ ማባከን ነውና፤ (ኤፌ 5፡18)

ሐሙስ 17

Page 43: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - Christ Embassycedmvas.org/wp-content/uploads/2017/11/Rhapsody-Of... · እንደሆነ ያስባሉ፤ ምን ማለት እንደሆነ ከተረዳችሁ፣

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የዮሐንስ ወንጌል 8:12-30 & መጽሀፈ ነገስት ቀዳማዊ 20-21

1ኛ ቆሮንጦስ 10:1-13 & መጽሀፈ ምሳሌ 13

2ኛ ጢሞቴዎስ 1:6; የያዕቆብ መልእክት 1:20; የሉቃስ ወንጌል 4:1

እርሱ እንዲህ ብሏል፡- “ሌባው ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፋም እንጂ ስለ ሌላ አይመጣም፤ እኔ ሕይወት እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸውም መጣሁ።” እናንተ ተራ ሰዎች አይደላችሁም፡፡ ብዙ ክርስቲያኖች፣ አብዛኛውን ጊዜ በመንፈስ ቅዱስ ስለማይሞሉ፣ ተራ ህይወትን ይኖራሉ፡፡ ያለማቋረጥ በመንፈስ ቅዱስ ከተሞላችሁ፣ ህይወታችሁ የማያልቅ የልዕለ ተፈጥሯዊ ምንጭ ይሆናል፡፡

ወደማያልቅ የስኬት ህይወት ተጠርተናል፡፡ ሚስጥሩ በመንፈስ ቅዱስ መሞላት ነው፤ እናንተ ልእለ ተፈጥሯዊ በሆነ መንገድ ነገሮችን ከከፍተኛ ቦታ ላይ የማየት ኃይልን አግኝታችኋል፤ እናም በክርስቶስ ውስጥ ያለውን የከፍታ ህይወት ትኖራላችሁ፡፡

በክርስቶስ ውስጥ የከፍታን ህይወት እኖራለሁ፤ በዚህ ዓለም ላይ ፍጹም በሆነ ድልና የበላይነት እኖራለሁ! ለዘላለሙ የክብር ንጉሥ ለጌታ ለኢየሱስ ክርስቶስ ክብር፣ የህይወት ሁኔታዎችንና ክስተቶችን በማስገዛት፣ በበላይነትና በንግስና እኖራለሁ፡፡ ሃሌሉያ!

የእምነት አዋጅ

Page 44: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - Christ Embassycedmvas.org/wp-content/uploads/2017/11/Rhapsody-Of... · እንደሆነ ያስባሉ፤ ምን ማለት እንደሆነ ከተረዳችሁ፣

amharic

የተጎዱ መስሎ የሚሰማቸው አንዳንድ ሰዎች አሉ፤ ምናልባትም እንደዚህ የሚሰማቸው ተምረው ዲግሪ ስሌላቸው፣ ወደ

ትምህርት ቤት ስላልሄዱ ወይም የሆነ ጊዜ ትምህርታቸውን ስላቋረጡ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ ሁኔታ እናንተን ወይም የምታውቁትን አንድ ሰው የሚገልጽ ከሆነ፣ ይህ የዓለም መጨረሻ ማለት አይደለም፡፡ ወደ ትምህርት ቤት የመሄድ ዕድል አምልጧችሁ እንኳን ቢሆን፣ ለመማር ግን ዕድል አላመለጣችሁም። ብቻ ስብእናችሁን ወይም ማንነታችሁን ለማሳደግ ስሩ፡፡

ትክክለኛ ነገሮችን አድምጡ፤ ትክክለኛ መጽሐፍትን አንብቡ፤ ለትክክለኛ እውቀትና መረጃ አእምሮአችሁንና አስተሳሰባችሁን ክፍት አድርጉ፡፡ የእናንተን ህይወት የሚወስነው፣ ከእናንተ የትምህርት ደረጃ ይልቅ፣ የእናንተ የስብእና ወይም የማንነት ዓይነት ማለትም በአእምሮአችሁና በልባችሁ ላይ የሰራችሁት ወይም ያስቀመጣችሁት ነገር ነው፡፡

በአንድ ወቅት ዴይዚ ኦዝቦርን እንዲህ ብላለች፡- “በማንነታችሁ ላይ እንጂ ነገሮችን ለማግኘት አትስሩ፤ ምክንያቱም ከማንነታችሁ የተነሳ ነገሮች ይኖርዋችኋል”:: እንዴት ያለ እውነት ነው! በሌላ ቀላል አገላለጽ “አንድን ነገር ለማግኘት አትስሩ፤ ይልቁኑ አንድ ነገር ለመሆን ስሩ፡፡” ማለት ነው፡፡ በማንነታችሁ ላይ በመስራት በዚህ ዓለም ታዋቂ ሆናችሁ ከመመላለሳችሁም ባለፈ በማንነታችሁ ላይ በሰራችሁት ስራ የተነሣ፣ በተጨባጭ በዓለም ላይ ለውጥን ታመጣላችሁ፡፡ ስኬት ማለት ይህ ነው፡፡ ራሳችሁን አስተካክሉ። ዋጋችሁን አሻሽሉ፡፡

ዓለም በፍጥነት እየተለወጠች ነው፤ ስለሆነም የበላይ በሚያደርጋችሁና የተሻለ ጥቅምን በሚያስገኝላችሁ ስፍራ ላይ በሚያስቀምጣችሁ ትክክለኛ መረጃ አእምሮአችሁን ልታጥለቀልቁት ይገባል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን በጥንቃቄ ስታጠኑ፣ እውቀት ኃይል እንደሆነ ትረዳላችሁ፡፡ የመክፈቻ ጥቅሳችን እንዲህ ይላል፡- “…አዋቂም ሰው ኃይሉን ያበዛል።” “ኃይሉን” የሚለው ይኸው ቃል በሌላ ቦታዎች “ችሎታ” በሚል ተተርጉሟል፡፡ ስለዚህ በእውቀት

ስብእናችሁን ለማሳደግ ስሩ

ጠቢብ ሰው ብርቱ ነው፥ አዋቂም ሰው ኃይሉን ያበዛል። (ምሳሌ 24፡5)

አርብ 18

Page 45: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - Christ Embassycedmvas.org/wp-content/uploads/2017/11/Rhapsody-Of... · እንደሆነ ያስባሉ፤ ምን ማለት እንደሆነ ከተረዳችሁ፣

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሐዋርያት ስራ 8:31-47 & መጽሀፈ ነገስት ቀዳማዊ 22

1ኛ ቆሮንጦስ 10:14-21 & መጽሀፈ ምሳሌ 14

መጽሀፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 2:8; መጽሀፈ ምሳሌ 18:15; 2ኛ ጴጥሮስ 1:2; የሐዋርያት ስራ 20:32

ችሎታዎቻችሁን ታበዛላችሁ፤ ማለቂያ የሌላቸውን እምቅ ችሎታዎቻችሁን ታያላችሁ፡፡

ዳግም ከመወለዳችሁ አስቀድሞ የነበራችሁበት ቦታ ወይም የኖራችሁት ህይወት ምንም ይምሰል ምን ለውጥ አያመጣም፡፡ ምናልባትም ከምድራዊ ቤተሰባችሁ መካከል ማንም መቼም ስኬታማ የሆነ አንድም ሰው የለም ይሆናል፤ እናንተን በተመለከተ ግን ያ መጥፎ ዕድል ተሰብሯል። አሁን ዳግም ተወልዳችኋልና፣ ለእናንተ ለምታምኑት ሁሉም ነገር ይቻላል። (ማርቆስ 9፡23)፡፡ እግዚአብሄር ይባረክ!

ልዩነት የሚያመጣው እውቀት ነው፡፡ በቃሉ ላይ ባላችሁ እውቀት እና በማንነታችሁ ላይ በሰራችሁት ትክክለኛ ስራ የተነሣ፣ ጌታ በእናንተ ህይወት ማንኛውንም ነገር ማድረግ ይችላል፡፡

እኔ ከተራ ያለፈ ከፍተኛ የመረዳት ችሎታ አለኝ፤ እግዚአብሄር ጥበብ፣ እውቀት እና ደስታ ስለሰጠኝ፣ የከበረ ህይወት ለመኖር የሚያስችሉኝን መረጃዎች ሁሉ አገኛለሁ፡፡ እኔ ስኬታማና ለዓለሜ ድንቅ ነኝ! የእኔ ችሎታዎች ገደብ የላቸውም፤ ለስኬት፣ ለታላቅነትና ለክብር፣ በመንፈስ ቅዱስ ስፍራዬን ይዣለሁ፡፡ ሃሌሉያ!

የእምነት አዋጅ

Page 46: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - Christ Embassycedmvas.org/wp-content/uploads/2017/11/Rhapsody-Of... · እንደሆነ ያስባሉ፤ ምን ማለት እንደሆነ ከተረዳችሁ፣

amharic

ሠይጣን በርካታ የእግዚአብሄርን ልጆች ለጸሎቶቻቸው መልስን ለመቀበል ብቁ እንዳልሆኑ እንዲሰማቸው በማድረግ ጨቁኖ

ይዟል፡፡ ጌታ እናንተ ከእርሱ ለመቀበል ፈቃደኛ ከሆናችሁት በላይ እናንተ የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ ለማድረግ ፈቃደኛ መሆኑን አስተውሉ፡፡ ሮሜ 8፡32 እንዲህ ይላል፡- “ለገዛ ልጁ ያልራራለት ነገር ግን ስለ ሁላችን አሳልፎ የሰጠው ያው ከእርሱ ጋር ደግሞ ሁሉን ነገር እንዲያው እንዴት አይሰጠንም?”፡፡

በሚያሳዝን ሁኔታ፣ ለቃሉ ዕውቀት ከማጣታቸው የተነሳ፣ እግዚአብሄር ከኃጥያታቸው የተነሳ በእነርሱ ላይ እንደተቆጣ ይገምታሉ፡፡ “እኔ ኃጥያትን ሰርቻለሁ፤ ሰለሆነም ሁኔታዎችን እስካስተካክል ድረስ ከአብ ጋር ህብረት ለማድረግ ወይንም ማንኛውንም ነገር ከእርሱ ለመጠየቅ አልችልም፡፡” ይላሉ። ሌሎች ደግሞ ከአብ ጋር በቀጥታ ለመነጋገር በበቂ ሁኔታ “ቅዱስ” እንዳልሆኑ ያምናሉ፤ ስለሆነም አንዳንድ “ቅዱሳን” በእነርሱ ምትክ ሆነው ለእግዚአብሄር እንዲጸልዩላቸው ይፈልጋሉ፡፡

የእርሱን ቃል በተረዱ ኖሮ! በኢሳያስ 1፡18 እግዚአብሄር እንዲህ ብሏል፡- “ኑና እንዋቀስ ይላል እግዚአብሔር ኃጢአታችሁ እንደ አለላ ብትሆን እንደ አመዳይ ትነጻለች እንደ ደምም ብትቀላ እንደ ባዘቶ ትጠራለች።” ጌታ ኢየሱስ መጥቶ ይህን እውን አድርጎታል፡፡ እርሱ በውድ ደሙ እንደ በረዶ አንጽቶ አጥቧችኋል፤ “…ነገር ግን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በአምላካችንም መንፈስ ታጥባችኋል፥ ተቀድሳችኋል፥ ጸድቃችኋል።” (1ኛ ቆሮ 6፡11)፡፡

2ኛ ቆሮ 5፡19 እንዲህ ይላል፡- “እግዚአብሔር በክርስቶስ ሆኖ ዓለሙን ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበርና፥ በደላቸውን አይቆጥርባቸውም ነበር፤…።” እግዚአብሄር በእናንተ መቼም ቢሆን አይቆጣም፡፡ ሮሜ 5፡10 እንዲህ ይላል፡- “ጠላቶች ሳለን ከእግዚአብሔር ጋር በልጁ ሞት ከታረቅን፥ ይልቁንም ከታረቅን በኋላ በሕይወቱ እንድናለን፤”፡፡ ሃሌሉያ!

ጌታ ቸርና ደግ ነው

እንግዲህ ምሕረትን እንድንቀበል በሚያስፈልገንም ጊዜ የሚረዳንን ጸጋ እንድናገኝ ወደ ጸጋው ዙፋን በእምነት

እንቅረብ። (ዕብራዊያን 4፡16)

ቅዳሜ 19

Page 47: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - Christ Embassycedmvas.org/wp-content/uploads/2017/11/Rhapsody-Of... · እንደሆነ ያስባሉ፤ ምን ማለት እንደሆነ ከተረዳችሁ፣

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የዮሐንስ ወንጌል 8:48-59 & መጽሀፈ ነገስት ካልዕ 1-3

1ኛ ቆሮንጦስ 10:22-33 & መጽሀፈ ምሳሌ 15

ትንቢተ ኤርምያስ 31:3; የዮሐንስ ወንጌል 16:23-24; ሰቆቃወ ኤርሚያስ 3:22-23

እናንተ የሚያስፈልጋችሁ በጸጋው መጠቀምና በፍቅሩ መተማመን ብቻ ነው፡፡ እንደዚያ ሲሆን በእርሱ የመደመጥ መብት እንዳላችሁ በማወቅ፣ ሁልጊዜም ወደ እርሱ ለመቅረብ ድፍረት ይኖራችኋል፡፡ በኢየሱስ ስም ጥያቄዎችን ስታቀርቡ ወይም ትእዛዛትን ስታስተላልፉ፣ መልሶችን ለመቀበል ተሾማችኋል፤ “እኔ መረጥኋችሁ እንጂ እናንተ አልመረጣችሁኝም፤ አብም በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ እንዲሰጣችሁ፥ … ሾምኋችሁ።” (ዮሐንስ 15፡16)

ይህ እውነት በእናንተ ውስጥ እምነትን በማነሳሳት የምትፈልጉትን ማንኛውንም ነገር እንድትጠይቁ የሚያስችላችሁን መተማመን ያበርታው፤ እናንተ ለመጠየቅና ለመቀበል ካላችሁ ፈቃደኛነት የበለጠ፣ አብ ለእናንተ ሊሰጣችሁ ፈቃደኛ ነው፡፡ እርሱ ቸር እና ደግ ነው፡፡

ውድ አባት ሆይ፣ ለእኔ ሁሌም ስለቀረበልኝ የአንተ የተትረፈረፈ ጸጋ አመሰግንሃለሁ፡፡ በክርስቶስ ለእኔ ስለሰጠኸኝ በረከቶች፣ እና በአንተ መገኘት ስላለኝ የመደመጥ መብት አመሰግንሃለሁ፡፡ በክርስቶስ ገዢነት ስለምመላለስ ከህይወት ሁኔታዎች በላይ ሆኜ በድል አድራጊነት እኖራለሁ፤ በኢየሱስ ስም፡፡ አሜን፡፡

ጸሎት

Page 48: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - Christ Embassycedmvas.org/wp-content/uploads/2017/11/Rhapsody-Of... · እንደሆነ ያስባሉ፤ ምን ማለት እንደሆነ ከተረዳችሁ፣

amharic

በመክፈቻ ጥቅሳችን የተጠቀሰው ቃል እጅግ የመጠቀ ነው፡፡ የአሁኑ ሰዓት የሆነ ከተራነት ያለፈ እውነታ ሲሆን፣ ያም የእኛ ብቃት

ከእግዚአብሄር ነው! እኛ የተጠራነው፣ የተቀባነውና የተላክነው በመንፈስ ቅዱስ ስለሆነ፣ የእርሱን ሥራ በእርሱ መለኮታዊ ኃይል እንጂ በስጋ እንድንሰራ አይጠብቅም፡፡

ከላይ በተጠቀሰው ጥቅስ ላይ ብቃት የሚለው ቃል የተተረጎመው ሂካኖቴስ ከሚለው የግሪክ ቃል ሲሆን፣ ትርጉሙም ብቁ ችሎታ ያለው ማለት ነው፡፡ ጳውሎስ ስለራሱ እነ ከእርሱ ጋር ይሰሩ ስለነበሩ ሌሎች አገልጋዮች እንደተናገረው፣ እናንተም ብቃታችሁ ከእግዚአብሄር እንደሆነ መናገር ትችላላችሁ፡፡ ሁሉንም ነገር ማለትም ሁሉንም እግዚአብሄር እንድትሰሩት የጠራችሁን ነገሮች ለመስራት ብቃት አላችሁ፡፡ ጳውሎስ፣ ሲላስ እና ጢሞቴዎስ ሁሉም ወደ ሰማይ ሄደዋል፤ ዛሬ ጽድቁን እያሰራጫችሁ እና በሰዎች ልብ ውስጥ እርሱን መንግስት በምድር ላይ እያጸናችሁ ያላችሁት እናንተ ናችሁ፡፡

ምናልባትም አንድ የተወሰነ ፕሮጀክት ወይም ስራ እንድተሰሩ ተመድባችሁ “ከየት ልጀምረው፡፡ ይህ ስራ እጅግ ግዙፍና ተስፋ አስቆራጭ ነው፡፡” እያላችሁ እያሰባችሁ ይሆናል፡፡ አትጨነቁ፡፡ ለዚያ ስራ ብቁ ናችሁ። እናንተ በክርስቶስ ብቃት ብቁ ስለሆናችሁ፣ ያንን ፕሮጀክት በላቀ ሁኔታ ስኬታማ ለማድረግ የሚያስፈልገው ሁሉ አላችሁ፡፡

ከመንፈስ ቅዱስ እንዲህ የመሰለ ማስተማመኛ እያላችሁ አንድን ዓላማ ለማሳካት ትችሉ አትችሉ እንደሆነ እንዴት ያሳስባችኋል፤ እርሱ ችሎታችሁ ነው፡፡ በራሳችሁ ሰብዓዊ ጥበብና ጥንካሬ አትችሉ ይሆናል፤ ነገር ግን

በህይወት አሸናፊዎች

ብቃታችን ከእግዚአብሔር ነው እንጂ፥ በገዛ እጃችን እንደሚሆን አንዳችን እንኳ ልናስብ ራሳችን የበቃን

አይደለንም፤ (2ኛ ቆሮ 3፡5)

እሁድ 20

Page 49: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - Christ Embassycedmvas.org/wp-content/uploads/2017/11/Rhapsody-Of... · እንደሆነ ያስባሉ፤ ምን ማለት እንደሆነ ከተረዳችሁ፣

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የዮሐንስ ወንጌል 9:1-41 & መጽሀፈ ነገስት ካልዕ 4-5

1ኛ ቆሮንጦስ 11:1-11 & መጽሀፈ ምሳሌ 16

2ኛ ቆሮንጦስ 4:7; ፈልጵሱዮስ 4:13; ኤፌሶን 2:10

በመንፈስ ቅዱስ ሁሉን ማድረግ ትችላላችሁ፤ እናንተ ሁልጊዜ ታሸንፋላችሁ፤ በነገሮች ሁሉ እናንተ ፍሬያማና ውጤታማ ናችሁ (ቆላ 1፡10)፤ ለየትኛውም የስራ መስክ ብቁ ናችሁ፡፡ በደስታና በመተማመን “የትም ቦታ አስቀምጡኝ፤ እኔ የላቀ ሆኜ እገኛለሁ፤ በእርሱ ብቃት ብቁ ስለሆንኩ፣ እኔ ሁልጊዜም ስኬታማ እሆናለሁ፡፡” ብላችሁ መናገር ትችላላችሁ፡፡

ዘካርያስ 4፡6 እንዲህ ይላል፡- “…በመንፈሴ እንጂ በኃይልና በብርታት አይደለም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፦”፡፡ በመንፈስ ቅዱስ እናንተ በህይወት አሸናፊዎች ናችሁ! ሃሌሉያ!

ውድ አባት ሆይ፣ ለአንተ ክብር ሁሉንም ስራዎችና ፕሮጀክቶች እስከ ፍጻሜያቸው ድረስ በልቀት ለመስራት የሚያስፈልገው ብቁ ችሎታ ወይም ብቃት ያለኝ መሆኔ እንዴት ያለ ልዩ ጥቅም ነው! በእኔ ውስጥ በሙላት በሚንቀሳቀሰው እና በሚሰራው የአንተ ቅባት፣ እኔ ሁሉንም ነገር መስራት እችላለሁ፡፡ እግዚአብሄር ይባረክ!

የእምነት አዋጅ

Page 50: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - Christ Embassycedmvas.org/wp-content/uploads/2017/11/Rhapsody-Of... · እንደሆነ ያስባሉ፤ ምን ማለት እንደሆነ ከተረዳችሁ፣

amharic

አንድ ክርስቲያን ያልነበረና መንፈስ ቅዱስንም እንዳልትቀበለ ግልጽ የሆነ ሰው፣ በጉባዔ መካከል በልሳን ተናገረ፡፡ “ይህ እንዴት

ሊሆን ይችላል?” መልካም፣ እንግዲህ ሆኗል፡፡ ለዚያ ሰው የሆነለት ነገር ልክ ከጳውሎስ ከአካሉ ጨርቅ ወይም ልብስ ድውዮችን ለመፈወስ በወሰዱ ጊዜ እንደሆነው መካፈል ነው፡፡

ለምሣሌ፣ እኔ ከእናንተ ጋር ብተሻሽ ከልብሴ ላይ ያሉ ብናኞች በእናንተ ላይ ይሆናሉ፤ ላቅፋችሁና የእኔም መዓዛ በእናንተ ላይ ሊተላለፍ ይችላል፤ ይህ ግን እኔ እናንተ ውስጥ ነኝ ማለት አይደለም፡፡ በተመሳሳይ መንገድም፤ ያ ሰው በልሳን ተናገረ የሚለው እውነታ መንፈስ ቅዱስ በእርሱ ውስጥ ነበር ማለት አይደለም፡፡ በዘኁልቁ 22፡28 ላይ አንድ አህያ በሰው ቃል ተናግሮ የነብዩን እብደት እንዴት እንዳገደ እናነባለን፡፡ እግዚአብሄር በአህያው ውስጥ ይኖር ነበር? አይደለም!

የእግዚአብሄር ኃይል በአህያው ላይ መጣና አህያው እንደ ሰው ተናገረ፤ ያ ማለት ግን አህያው በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ ነበር ማለት አይደለም፡፡ የእግዚአብሄር መንፈስ እንዲከሰቱ የሚያደርጋቸው ነገሮች አሉ፡፡ ለምሳሌ፣ እንደ አማኞች እኛ በቤተክርስቲያን ውስጥ በተሰበሰብን ጊዜ በቤቱ ውስጥ መንፈሳዊ መገኘት አለ፤ ያ ግን መንፈስ ቅዱስ በአካል በቤቱ ውስጥ ተገኝቶ በመቀመጡ ሳይሆን በእኛ ውስጥ ካለው በእርሱ መገኘት የተነሣ ነው፡፡ ያ መገኘቱ በእኛ በኩል ወደ ከባቢው ይተላለፋል፡፡ በዚያ መልኩና በዚያ መንገድ እኛ በውስጣችን በምንሸከመው በእግዚአብሄር መገኘት የተነሣ ያን ሥፍራ እንቀድሰዋለን፡፡

ስለዚህ ዋናው ቁም ነገር፣ ቀደም ሲል እንዳየናቸው ምሳሌዎች መተሻሸት፣ መነካካት ወይም የእርሱን መገኘት መካፈል አይደለም፤ እነኚህ

የእርሱ መገኘት በእናንተ ውስጥ

እግዚአብሔርም በጳውሎስ እጅ የሚያስገርም ተአምራት ያደርግ ነበር፤ ስለዚህም ከአካሉ ጨርቅ ወይም ልብስ ወደ

ድውዮች ይወስዱ ነበር፥ደዌያቸውም ይለቃቸው ነበር ክፉዎች መናፍስትም ይወጡ ነበር። (የሐዋ 19፡11-12)

ሰኞ 21

Page 51: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - Christ Embassycedmvas.org/wp-content/uploads/2017/11/Rhapsody-Of... · እንደሆነ ያስባሉ፤ ምን ማለት እንደሆነ ከተረዳችሁ፣

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የዮሐንስ ወንጌል 10:1-21 & መጽሀፈ ነገስት ቀዳማዊ 6-7

1ኛ ቆሮንጦስ 11:12-19 & መጽሀፈ ምሳሌ 17

የሐዋርያት ስራ 1:8; የዮሐንስ ወንጌል 14:16-17; ቆላስያስ 1:27

ዘለቄታዊነት የላቸውምና፤ ነገር ግን ዋናው ነገር የእርሱ በእናንተ ውስጥ በቋሚነት መገኘት ነው! መንፈስ ቅዱስን በተቀበላችሁ ጊዜ፣ ዋናው የኃይል ምንጭ በእናንተ ውስጥ ሊኖር መጥቷል፡፡ ኢየሱስ መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ፣ ኃይልን ትቀበላላችሁ ብሏል፡፡ (ሐዋ 1፡8)፡፡

ዋናው የኃይል ምንጭ ራሱ በእናንተ ውስጥ ይኖራልና፤ ኃይልን ከሌላ ከአንዳችም ስፍራ ልትሹ አይገባችሁም፡፡ በእናንተ ውስጥ ያለውን የእርሱን የከበረ መገኘት ውሰዱና ዛሬ ተጠቀሙበት፡፡ በዚህ ንቃተ-ህሊና በሆናችሁ ጊዜ፣ ልክ እንደተባለው ያህል በልዕለ ተፈጥሮአዊው ትመላለሱና በክርስቶስ ውስጥ ያለውን ከፍ ያለውን ህይወት ትኖራላችሁ፡፡

ውድ አባት ሆይ፣ በእኔ ውስጥ ስለሚኖረው የአንተ መንፈስ አመሰግንሃለሁ፤ ህይወቴን ስለሚያስውበው እና ዓለሜን ስለሚለውጠው በእኔ ውስጥ ስላለው የአንተ መለኮታዊ መገኘት ንቁ ነኝ፡፡ ክርስቶስ ክርስቶስ በእኔ ውስጥ፣ እኔን ከአሸናፊ በላይ ድል አድራጊና፣ በዚህ ህይወት ድል ነሺ አድርጎኛል፡፡ ሃሌሉያ!

የእምነት አዋጅ

Page 52: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - Christ Embassycedmvas.org/wp-content/uploads/2017/11/Rhapsody-Of... · እንደሆነ ያስባሉ፤ ምን ማለት እንደሆነ ከተረዳችሁ፣

Te ¨h

Te ¨

h

amharic

Page 53: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - Christ Embassycedmvas.org/wp-content/uploads/2017/11/Rhapsody-Of... · እንደሆነ ያስባሉ፤ ምን ማለት እንደሆነ ከተረዳችሁ፣

Te ¨h

Te ¨

h

Page 54: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - Christ Embassycedmvas.org/wp-content/uploads/2017/11/Rhapsody-Of... · እንደሆነ ያስባሉ፤ ምን ማለት እንደሆነ ከተረዳችሁ፣

amharic

አንድ ሰው የትንቢት ቃል ሊኖረውና ከዚያም ወጥቶ ሊካፍለው ይችላል፤ ነገር ግን ምንም እንኳን ትንቢታዊ መልእክቱ እውነት

ቢሆንም፣ የተነገሩት ቃላት ባዶ፣ ስራና ውጤት አልባ ይሆናሉ፤ ለዚህም ምክንያቱ የተነገሩት ቃላት የመንፈሱ ኃይል የሌለባቸው ስለሆነ ነው፡፡

በመንፈሱ ለመሞላት ልዩ ጊዜ ወስደን በመንፈስ እንድንጸልይ ከምንጠየቅበት ምክንያቶች አንዱም ይኸው ነው፡፡ ኤፌ 5፡18 “መንፈስ ይሙላባችሁ እንጂ በወይን ጠጅ አትስከሩ ይህ ማባከን ነውና፤” ይላል፡፡

እነዚህ ቃላት በመጀመሪያ የተጻፉት ቀድሞውኑ በመንፈስ ተሞልተው ለነበሩት በኤፌሶን ለነበሩት ክርስቲያኖች ነበር፡፡ ስለሆነም፣ የእግዚአብሄር መንፈስ በሐዋርያው ጰውሎስ በኩል እኛ ሁልጊዜ በቀጣይ በመንፈሱ ተጽዕኖ፣ አገዛዝና ምርኮ ስር መሆን እንዳለብን እንደሚያመለክት ግልጽ ነው፡፡ በዚያ መንገድ የእናንተ መልእክት እና የእናንተ ስብከት መንፈስንና ኃይልን በመግለጥ ይሆናል እንጂ በሚያባብል በሰው ጥበብ ቃላት ወይም በሽንገላ ንግግር አይሆንም፡፡

በመንፈሱ በተሞላችሁ ጊዜ መንፈስን ታገለግላላችሁ፤ ቃላቶቻችሁም የመለኮትን ኃይል የጸነሱ ናቸው፡፡ የእናንተም አገልግሎት ሰዎች ከእናንተ ጋር የነበራቸውን ግንኙነት ፈጽመው ሊረሱት ወይም ወደ ጎን ሊያደርጉት እንዳይችሉ የሚያደርጋቸው አይነት ነው፤ ከእናንተ ቃላት ውስጥ ከሚፈሰው እና ከሚወጣው የተነሳ፣ ሰዎች በከፍተኛ ደረጃ በኢየሱስ ፍቅርና ማንነት፤ በእርሱም ጥበብ፣ ኃይልና ጽድቅ ተጽዕኖ ስር ይወድቃሉ፡፡

2 ኛ ቆሮ 4፡5 “ክርስቶስ ኢየሱስን ጌታ እንደ ሆነ እንጂ ራሳችንን አንሰብክምና፥…” ይላል፤ ይህም ማለት ምንም ትንቢትን ብትናገሩ፣ ብትሰብኩ፣ ወይም ብታስተምሩ፣ የግድ ክርስቶስ ኢየሱስን መሆን አለበት፤ ደግሞም ያለ ክርስቶስ ኃይል፣ ያለ መንፈሱ ኃይል፣ ክርስቶስን ልትሰብኩም ሆነ ልታገለግሉ አትችሉም፡፡ እግዚአብሄር የሚናገርበት ሰው ትሆኑ ዘንድ፣ በመንፈስ ቅዱስ ውስጥ መንፈሳችሁን የበለጠ እየዘፈቃችሁ አንዳንድ ጊዜ

በመንፈሱ አማካኝነት ማገልገል

ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ነው፤ ሥጋ ምንም አይጠቅምም፤ እኔ የነገርኋችሁ ቃል መንፈስ ነው ሕይወትም ነው።

(ዮሐንስ 6፡63)

ማክሰኞ 22

Page 55: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - Christ Embassycedmvas.org/wp-content/uploads/2017/11/Rhapsody-Of... · እንደሆነ ያስባሉ፤ ምን ማለት እንደሆነ ከተረዳችሁ፣

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የዮሐንስ ወንጌል 10:22-42 & መጽሀፈ ነገስት ካልዕ 8-9

1ኛ ቆሮንጦስ 11:20-29 & መጽሀፈ ምሳሌ 18

1ኛ ጴጥሮስ 4:11; 1ኛ ቆሮንጦስ 2:4-5

ልትጸልዩና ልትጾሙ የሚገባችሁ ምክንያትም ይህ ነው፡፡ከመንፈሱ ጋር፣ በእኛ ውስጥና በእኛ በኩል በተገለጠው ከእርሱ ክብር

እና ኃይል ጋር ሁልጊዜ በአንድነትና በህብረት መራመድ ይጠበቅብናል፡፡ ነገር ግን እናንተ ለቃሉ ጥልቅ ጥናት እና ማሰላሰል እንዲሁም ከመንፈሱ ጋር ህብረት ለማድረግ እሰካልተሰጣችሁ ድረስ፣ ይህ የእናንተ ልምምድ ሊሆን አይችልም፡፡

ደግማችሁ፣ ደጋግማችሁ በመንፈሱ ተሞሉ! በግል ህይወታችሁ የመንፈሱን አገልግሎት አጠናክሩ፤ እናም ያኔ ሁኔታዎችን ለመቀየርና ፍጻሜዎችን ለመለወጥ ቃላቶቻችሁ ተግባራዊ፣ ውጤታማ እና በመለኮት ኃይል የታጨቁ ይሆናሉ፡፡

አባት ሆይ፣ የአንተ መንፈስ ቃላቶቼን በኃይል ስለሚሞላቸው፣ ስለዚህም ሁልጊዜ ህይወትን ስለምናገር አመሰግንሃለሁ፡፡ የአንተን ፍቅር፣ ጥበብ፣ ኃይል እና ጽድቅ በመሸከማቸው ቃላቶቼ ፍጻሜዎችን ይባርካሉ፤ ይለውጡማል፤ በኢየሱስ ስም፡፡ አሜን፡፡

ጸሎት

Page 56: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - Christ Embassycedmvas.org/wp-content/uploads/2017/11/Rhapsody-Of... · እንደሆነ ያስባሉ፤ ምን ማለት እንደሆነ ከተረዳችሁ፣

amharic

በመግቢያ ጥቅሳችን እንደምናየው ሐዋርያው ጳውሎስ በብሉይና አዲስ ኪዳን መካከል ያለውን አስደናቂ ልዩነት እያነጻጸረ ነው፡፡

ቃላት መሰንጠቅ ሳያስፈልገው፤ የብሉይ ኪዳን አገልግሎትን የሞት አገልግሎት ይለዋል፡፡ ይህ ግን ምን ማለት ነው?

እንግዲህ አሁን ስለ ህጉ አንድን ነገር ተረዱ፤ ህጉ የመጣው ኩነኔ እንዲጸና ነው፡፡ ህጉ ሲነበብ፣ ሞት ይገለገላል፤ ሰዎችም ይኮነናሉ፤ መንፈሳዊ ሞት አንድ አስተሳሰብ ሆነ፡፡ በሮሜ 7፡9 ላይ ያለውን የጳውሎስን ቃላት አስታውሱ፡- “እኔም ዱሮ ያለ ሕግ ሕያው ነበርሁ፤ ትእዛዝ በመጣች ጊዜ ግን ኃጢአት ሕያው ሆነ እኔም ሞትሁ፤” ኃጥያት በእርግጥም ምን እንደሆነ ይታይ ዘንድ፣ ህጉ የተሰጠው በኃጥያት ምክንያት ነው፡፡ “እንግዲህ በጎ የሆነው ነገር ለእኔ ሞት ሆነብኝን? አይደለም፥ ነገር ግን ኃጢአት ሆነ፤ ኃጢአትም በትእዛዝ ምክንያት ያለ ልክ ኃጢአተኛ ይሆን ዘንድ፥ ኃጢአትም እንዲሆን ይገለጥ ዘንድ በጎ በሆነው ነገር ለእኔ ሞትን ይሠራ ነበር።”፡፡

እንግዲህ፣ ብሉይ ኪዳን ለሰዎች ህይወትን መስጠት የሆነውን የእግዚአብሄርን ሃሳብ ሊያሟላ አልቻለም፡፡ ይልቁንም፣ ከስጋ ድካም የተነሳ ሞትን አመጣ፡፡ ማንም ቢሆን ህጉን ሊፈጽም አይችልም፤ ማንምበህጉ ወደሚያዘው ደረጃ ሊደርስ አልቻለም፡፡ ነገር ግን ምስጋና ለእግዚአብሄር ይሁን፡፡ ክርስቶስ ኢየሱስ የህጉ ፍጻሜ ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ በሙሴም ህግ ትጸድቁበት ዘንድ ከማይቻላችሁ ሁሉ ያመነ ሁሉ በእርሱ ጸድቀዋል ይላል። (የሐዋ 13፡39)፡፡

መጽሀፍ ቅዱስ እርሱ በወንጌል ህይወትንና አለመጥፋትን ወደ ብርሃን አውጥቷል ይላል፡፡ (2ኛ ጢሞ 1፡10)፡፡ ስለዚህ ዛሬ እውነተኛውን አዲስ

የህይወት አገልጋዮች

ዳሩ ግን የእስራኤል ልጆች ስለዚያ ስለ ተሻረው ስለ ፊቱ ክብር የሙሴን ፊት ትኩር ብለው መመልከት እስኪሳናቸው

ድረስ፥ ያ በፊደላት በድንጋዮች ላይ የተቀረጸ የሞት አገልግሎት በክብር ከሆነ፥ የመንፈስ አገልግሎት እንዴት

ይልቅ በክብር አይሆንም? (2ኛ ቆሮ 3፡7-8)

ረቡዕ 23

Page 57: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - Christ Embassycedmvas.org/wp-content/uploads/2017/11/Rhapsody-Of... · እንደሆነ ያስባሉ፤ ምን ማለት እንደሆነ ከተረዳችሁ፣

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የዮሐንስ ወንጌል 11:1-16 & መጽሀፈ ነገስት ካልዕ 10-12

1ኛ ቆሮንጦስ 11:30-34 & መጽሀፈ ምሳሌ 19

ኦሪት ዘህልቁ 6:23-26; መጽሀፈ መክብብ 8:4; ቆላስያስ 4:6

ኪዳን ስንሰብክ፣የህይወት መንፈስ የሆነውን መንፈሱን እያገለገልን ነው፡፡2ኛ ቆሮ 3፡6 እኛ የበቃን የአዲስ ኪዳን አገልጋዮች ነን ይላል፡- “…

በመንፈስ እንጂ በፊደል ለማይሆን …ፊደል ይገድላልና መንፈስ ግን ሕይወትን ይሰጣል።” ይህ የእናንተ ህልም እና ምኞት ሊሆን ይገባል፤ አገልግሎታችሁ የህይወት አገልግሎት፣ የመንፈስ አገልግሎት ሊሆን ይገባል፡፡

በእናንተ አገልግሎት የህይወት መንፈስ ከመለቀቁ የተነሳ፣ ደህንነትን፣ ፈውስን፣ ነጻ መውጣትን እና ሌሎች በረከቶችን የሚያነቃቃውን አገልግሎታችሁን ሰምቶ ገና እስካሁን ኢየሱስን የማያውቅ ሰው ሊቀየር ይገባል!

ውድ አባት ሆይ፣ ፍለጋ የሌለውን የክርስቶስን ባለጠግነት እንድሰብክና በወንጌሉም አማካይነት በዙርያዬ ላሉ ህይወትን እንዳገለግል ስለተሰጠኝ ከፍ ያለ ዕድል አመሰግንሃለሁ፡፡ በህይወታቸው ላይ ፍጹም ለውጥ የሚያመጣውን ወንጌል ዛሬ ብዙዎች ሲሰሙ ስለተለቀቀው የመንፈስ ኃይልና በቃልህ ውስጥ ስላለው ህይወት አመሰግንሃለሁ፤ በኢሱስ ስም፡፡ አሜን፡፡

ጸሎት

Page 58: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - Christ Embassycedmvas.org/wp-content/uploads/2017/11/Rhapsody-Of... · እንደሆነ ያስባሉ፤ ምን ማለት እንደሆነ ከተረዳችሁ፣

amharic

ዮሐንስ 1፡1 እንዲህ ይላል፡- “በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ።”

ቃል እግዚአብሄር ከነበረ፣ እናም እግዚአብሄር የሚለወጥ ካልሆነ፣ ይህ ማለት ቃል አሁንም እግዚአብሀር ነው ማለት ነው፡፡ በዚሁ ምዕራፍ ቁጥር 14 መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፡- “ቃልም ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ፥ አንድ ልጅም ከአባቱ ዘንድ እንዳለው ክብር የሆነው ክብሩን አየን።” (ዮሀንስ 1፡14)፡፡

ኢየሱስ ከመወለዱ በፊት መንፈስ ቅዱስ በማርያም ላይ መጥቶ እንደነበረ አስታውሱ፤ በመልአክ የተነገራት የነበረ ከእግዚአብሄር የተቀበለችው ቃል፣ በእርሷ ውስጥ ሥጋ ሆኖ ተገለጠ፡፡ ያ ቃል ህጻን ሆነ፣ ከዚያም አድጎ ክርስቶስ ኢየሱስን ሆነ፡፡ ስለዚህ ኢየሱስ በእርግጥ በስጋ የተገለጠው የእግዚአብሄር ቃል ነው፤ እርሱ ለማርያም የተነገረው ቃል ውጤት ነው፡፡

ዛሬ የእግዚአብሄር ቃል ወደ እናንተ ሲመጣ አሁንም ተመሳሳይ ተጽዕኖ ስላለው ውጤትን ያፈራል፡፡ የእግዚአብሄር ዓላማ፣ ቃሉ ከእናንተ ጋር አንድ እንዲሆን ማለትም በእናንተ ውስጥ ስጋ እንዲሆን ነው፡፡ ቃሉ የፈውስ ቃል ከሆነ፣ በሽታውን አጥፍቶ የእሱን ቦታ እንዲይዝ ነው፡፡

ቃሉ የተሰበረን ወይም የተቆረጠን ክንድ እንደገና መፍጠር ይችላል። ቃሉ ደማችሁን ይለውጣል፡፡ የኩላሊት ወይም የልብ ችግር ከነበረባችሁ፣ ቃሉ በእናንተ ውስጥ አዲስ ኩላሊቶች ሊሆን ይችላል፤ እና አዲስ ልብንም ይሰጣችኋል፡፡ የእግዚአብሄርን ቃል መቀበል ማለት፣ ወደ ህይወታችሁ የእግዚአብሄርን ኃይል ማለትም የእግዚአብሄርን የመፍጠር ኃይል መቀበል ማለት ነው፡፡

የቃሉ የመፍጠር ኃይል

አሁንም ለእግዚአብሔርና ያንጻችሁ ዘንድ በቅዱሳንም ሁሉ መካከል ርስትን ይሰጣችሁ ዘንድ ለሚችል ለጸጋው ቃል

አደራ ሰጥቻችኋለሁ። (የሐዋ 20፡32)

ሐሙስ 24

Page 59: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - Christ Embassycedmvas.org/wp-content/uploads/2017/11/Rhapsody-Of... · እንደሆነ ያስባሉ፤ ምን ማለት እንደሆነ ከተረዳችሁ፣

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የዮሐንስ ወንጌል 11:17-57 & መጽሀፈ ነገስት ካልዕ13-15

1ኛ ቆሮንጦስ 12:1-11 & መጽሀፈ ምሳሌ 20

መዝሙረ ዳዊት 107:20; ዕብራውያን 4:12 AMPC; ትንቢተ ኢሳያስ 55:11

ሁኔታችሁ ተስፋ የሌለው ነው ብላችሁ መቀበልን አሻፈረኝ በሉ፤ በገንዘብ ሁኔታችሁ የተነሳ ተስፋ አትቁረጡ ወይም አትከፉ፤ ነገሮችን በቃሉ ለውጡ፡፡ ማሰላሰል ጀምሩ፣ ቃሉን አላምጡ፤ የያዘውን መልእክት ቃል በቃል በእናንተ ውስጥ እሰኪፈጥር ድረስ ቃሉን አውጡና አውርዱ እና አስቡ፡፡ ሲሆን ታውቃላችሁ፡፡ ቃሉ ለእናንተ እና በእናንተ ውስጥ ለማፍራት የሚጠበቅበትን ውጤት ብቻ የሚያይ፣ የሚያስብ እና የሚቀበል እስኪሆን ድረስ አእምሯችሁ ይታደሳል፡፡

የተባረክህ አባት ሆይ፡- በህይወቴ ውስጥ ስላለው የቃልህ ውጤታማነት አመሰግንሃለሁ፡፡ ቃሉን በማሰላሰል፣ በህይወቴና በሁኔታዎቼ ላይ ቃሉ የያዘውን መልእክት እያፈራ ቃሉ ከመንፈሴ፣ ከነፍሴ እና ከአካሌ ጋር ተዋህዷል፡፡ ዛሬና ሁልጊዜም የአንተ መለኮታዊ ኃይል ሙሉ በሙሉ በእኔ ውስጥ እየሰራ ነው፤ በኢየሱስ ስም፡፡ አሜን፡፡

ጸሎት

Page 60: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - Christ Embassycedmvas.org/wp-content/uploads/2017/11/Rhapsody-Of... · እንደሆነ ያስባሉ፤ ምን ማለት እንደሆነ ከተረዳችሁ፣

amharic

ክርስትና ማለት መለኮት በሰው ልጅ ሲሰራ ማለት ነው፤ ክርስቶስ በእናንተ ውስጥ መገለጥ ማለት ነው፡፡ አንድ ክርስቲያን ማለት

ክርስቶስ ቃል በቃል በእርሱ ውስጥ የሚኖር ሰው ማለት ነው፤ እና ክርስቶስ ማነው? እንደ ሰው ክርስቶስ ማለት በኢየሱስ ውስጥ ተወክሎ የአምላክ መገለጫ፤ የእግዚአብሄር ሙላት ነው፡፡ እና መጽሐፍ ቅዱስ ሲናገር እርሱ ከሁሉም በላይ ነው፤ እርሱ የሁሉም ኃይላትና ስልጣናት ራስ ነው፤ እናም እርሱ በእናንተ ውስጥ ይኖራል፡፡

እንግዲህ ይህ እውነት ከሆነ፣ እግዚአብሄር ይመስገን ደግሞም እውነት ነው፤ ማንኛውም ክርስቲያን አጋንንትን ይፈራል? እንዲያውም አንዳንዶች ከአጋንንትና ከሰይጣናዊ ጭቆናዎች ነጻ ለመውጣት ከቤተክርስቲያን ወደ ቤተክርስቲያን ይጓጓዛሉ፡፡ እንዴት ያሳዝናል! በሆሴእ 4፡6 ላይ ጌታ እንዲህ ብሏል፡- “ሕዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሣ ጠፍቶአል…” አንድም ክርስቲያን ከሠይጣን ነጻ መውጣት አያስፈልገውም፡፡ ከሠይጣን ነጻ መውጣት እንደሚያስፈልገው/እንደሚያስፈልጋት የሚያምን/የምታምን አንድ/አንዲት ክርስቲያን፣ እውነተኛውን የክርስቲያን ህይወት እየኖረ/እየኖረች አይደለም፡፡

ክርስቲያን ከሠይጣን የበላይ ነው፤ እናም ከአጋንንቶች የተነሳ ምንም ችግር ሊኖረው አይገባም፡፡ እንደ ክርስቲያን አንዴ የአንድ ችግር ወይም ሁኔታ መንስኤ ሰይጣን መሆኑ ከታወቀ፣ ያንን ችግር መፍታት ቀላል ይሆናል፤ አስወጡት በቃ! ኢየሱስ በማርቆስ 16፡17 ላይ እንዲህ ብሏል፡- “ያመኑትንም እነዚህ ምልክቶች ይከተሉአቸዋል፤ በስሜ አጋንንትን ያወጣሉ፤ …”፣ ይህ እርሱ ከተናገራቸው በስሙ ማድረግ የምንችላቸው ነገሮች የመጀመሪያው ነው፡፡

በተጨማሪ መጽሐፍ ቅዱስ ሲናገር “አብን እያመሰገናችሁ፥ … እርሱ ከጨለማ ሥልጣን አዳነን፥ ቤዛነቱንም እርሱንም የኃጢአትን ስርየት

እውነተኛውን የክርስቲያን ህይወት ኑሩ

ለእነርሱም እግዚአብሔር በአሕዛብ ዘንድ ያለው የዚህ ምሥጢር ክብር ባለ ጠግነት ምን እንደ ሆነ ሊያስታውቅ

ወደደ፥ ምሥጢሩም የክብር ተስፋ ያለው ክርስቶስ በእናንተ ዘንድ መሆኑ ነው። (ቆላስይስ 1፡27).

አርብ 25

Page 61: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - Christ Embassycedmvas.org/wp-content/uploads/2017/11/Rhapsody-Of... · እንደሆነ ያስባሉ፤ ምን ማለት እንደሆነ ከተረዳችሁ፣

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የዮሐንስ ወንጌል 12:1-19 & መጽሀፈ ነገስት ካልዕ 16-17

1ኛ ቆሮንጦስ 12:12-21 & መጽሀፈ ምሳሌ 21

የሉቃስ ወንጌል 10:17-19; 1ኛ ዮሐንስ 4:4; ሮሜ 5:17

ወዳገኘንበት ወደ ፍቅሩ ልጅ መንግሥት አፈለሰን።” (ቆላስይስ 1፡12-14)። ዳግም ከመወለዳችሁ አስቀድሞ፣ ከጨለማ ሥልጣን ድናችሁ ወደ ፍቅሩ ልጅ መንግሥት ፈልሳችኋል፤ ኢሱስ ይህንን ለዓለም በሙሉ ስላደረገ፤ በህግ ተፈጽሟል፡፡ አሁን ዳግም ተወልዳችኋልና፣ ይህ ለእናንተ ህያው እውነታ ሆኗል፡፡ ሰይጣን ወይም ጨለማ በእናንተ ላይ ምንም ስልጣን የለውም፤ እናንተ በእነሱ ተጽዕኖ ስር አይደላችሁም፡፡

ይሁን እንጂ፣ ለጌታ እየኖራችሁ ካልሆነ፣ እና በሠይጣን ተጽእኖ ስር ለመኖር ከመረጣችሁ፣ ችግር ይገጥማችኋል፡፡ አንድ ሰው “ወደ ሰይጣን ግዛት ሄዳችሁ፣ አሁን በሰይጣን ጭቆና እየተቸገራችሁስ ከሆነ?” ብሎ ሊጠይቅ ይችላል። ነገር ግን ያ ችግር የለውም፡፡ ይህንን ብቻ በሉ፡- “ኢየሱስ ክርስቶስ የህይወቴ ጌታ ነው፤ እናም ከሰይጣን ጋር ምንም ጉዳይ የለኝም፡፡” ይህንን ብቻ ማድረግ ነው! ለእግዚአብሄር ክብር ይሁን!

ውድ አባት ሆይ፣ ከጨለማ ሥልጣን አድነህ ወደ ፍቅሩ ልጅ ኢየሱስ መንግሥት ስላፈለስከኝ አመሰግንሃለሁ፡፡ እኔ አሁን በመንግስቱ ውስጥ ነኝ፤ በእኔ ያለው በዓለም ካለው ስለሚበልጥ፣ ሰይጣን በህይወቴ ውስጥ ምንም ስፍራ አያገኝም፡፡ ለህይወቴ ወንጌሉ ከሚሰጠኝ ማንኛውም አቅርቦት ጋር የተጻረረ ነገር ላይ፣ የበላይነትና ስልጣን አለኝ፤ በኢየሱስ ስም፡፡ አሜን፡፡

ጸሎት

Page 62: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - Christ Embassycedmvas.org/wp-content/uploads/2017/11/Rhapsody-Of... · እንደሆነ ያስባሉ፤ ምን ማለት እንደሆነ ከተረዳችሁ፣

amharic

አጋንንትን ለማስወጣት በተለየ ሁኔታ የተቀቡ ወይም ሥጦታ ያላቸው ክርስቲያኖች የሉም፡፡ ኢየሱስ እንዲህ ብሏል፡

- “ያመኑትንም እነዚህ ምልክቶች ይከተሉአቸዋል፤ በስሜ አጋንንትን ያወጣሉ፤…” (ማርቆስ 16፡17)፡፡ እናንተ አጋንንትን ማስወጣት እንድትችሉ ሊኖራችሁ የሚገባ ብቃት ቢኖር፣ ማመን ማለትም በክርስቶስ ውስጥ መሆን ብቻ ነው፡፡ እያንዳንዱ ክርስቲያን፣ ከደቂቃዎች በፊት ዳግም የተወለደውንም ጨምሮ፣ አጋንንትን ለማስወጣት ሥልጣን አለው፡፡

አንድ ሰው “ይህ እንዴት ይሆናል? አጋንንትን ከማስወጣታችን በፊት ራሳችንን ማዘጋጀት እና ኃይለኛ ጸሎትን መጸለይ የለብንም እንዴ?” እንደዚህ አይደለም! ኢየሱስ ስለ ሠይጣን እንድንጸልይ እንኳን አልተናገረንም፡፡ እርሱ ያለው “አስወጡት!” ነው፡፡ ሠይጣን በተመለከተ አንድ ነገር እንዲያደርግ ለእግዚአብሄር መንገር ያለባችሁ ምንም ነገር የለም፤ እርሱ አስቀድሞ ስለ ሠይጣን እና የጨለማው አጋንንቶች ማድረግ የሚያስፈልገውን ሁሉ አድርጓል፤ እናም በእነሱ ላይ ሥልጣንን ሰጥቷችኋል፡፡

በማርቆስ 6፡7 መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፡- “አስራ ሁለቱንም ወደ እርሱ (ወደ ኢየሱስ) ጠራ… በርኵሳን መናፍስትም ላይ ሥልጣን ሰጣቸው፥”:: “ኃይል” ለሚለው ቃል የግሪኩ ቃል “ኤክሱዝያ” ነው፤ ትርጉሙም ‘ሥልጣን’ ማለት ነው:: ኢየሱስ በርኵሳን መናፍስት ላይ ሥልጣን ሰጥቶናል፡፡ እርሱ በሲኦል እነሱ ላይ ምን እንዳደረገ አንብቡ፡- “አለቅነትንና ሥልጣናትን ገፎ፥ ድል በመንሣት በእርሱ እያዞራቸው በግልጥ አሳያቸው።” ኢየሱስ ሠይጣንና ጭፍሮቹን ችሎታ፣ ኃይልም ሆነ ጥቅም የሌላቸው አድርጓቸዋል፡፡ ይህ ምን ማለት እንደሆነ መገመት ትችላላችሁ? እርሱ ይህንን ሲያደርግ እናንተ በእርሱ ውስጥ ነበራችሁ::

በሉቃስ 10፡19 ላይ እርሱ እንዲህ ብሏል፡- እነሆ፥ እባቡንና ጊንጡን ትረግጡ ዘንድ፥ በጠላትም ኃይል (ችሎታ) ሁሉ ላይ ሥልጣን ሰጥቻችኋለሁ፥ የሚጐዳችሁም ምንም የለም። ሠይጣንና ጭፍሮቹን ቁጥጥር

በአጋንንት ላይ የበላይነት

ያመኑትንም እነዚህ ምልክቶች ይከተሉአቸዋል፤ በስሜ አጋንንትን ያወጣሉ፤ (ማርቆስ 16፡17)

ቅዳሜ 26

Page 63: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - Christ Embassycedmvas.org/wp-content/uploads/2017/11/Rhapsody-Of... · እንደሆነ ያስባሉ፤ ምን ማለት እንደሆነ ከተረዳችሁ፣

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የዮሐንስ ወንጌል 12:20-50 & መጽሀፈ ነገስት ካልዕ 18-19

1ኛ ቆሮንጦስ 12:22-31 & መጽሀፈ ምሳሌ 22

የማቴዎስ ወንጌል 10:7-8; የሉቃስ ወንጌል 10:17-19

ሥር ለማዋል ሥልጣን አላችሁ፡፣ ያም ሥልጣን የተሟላና ፍጹም ነው፡፡ የትኛውም አጋንንት ሊቋቋመው አይችልም፡፡

በመክፈቻ ጥቅሳችን ላይ ያነበብነውን አስታውሱ “ያመኑትንም እነዚህ ምልክቶች ይከተሉአቸዋል፤ በስሜ አጋንንትን ያወጣሉ፤…”፤ ይህ በመንፈስ ዓለም ሕግ ነው፡፡ በኢየሱስ ስም አንድ አጋንንት እንዲወጣ ስታዙት፣ ልክ ኢየሱስ ራሱ እንደተናገረ ይቆጠራል፡፡ በስሙ ሥልጣን ውስጥ ኑሩ፡፡ በአካባቢያችሁ ሠይጣን እንዲጨፍር አትፍቀዱለት፡፡ ሃሌሉያ!

የተባረክህ አባት ሆይ፣ ኢየሱስ ስለእኔ በሠይጣንና በጨለማው ኃይላት ላይ ስላገኘው ድል አመሰግንሃለሁ፡፡ እኔ አሁን በኢየሱስ ክርስቶስ ድልና ሥልጣን ውስጥ እኖራለሁ፤ ለእኔ ስኬት፣ ሠይጣንና የእርሱ ጭፍሮች ምንም ለውጥ አያመጡም፡፡ በየዕለቱ በአሸናፊነት እኖራለሁ፤ በኢየሱስ ስም፡፡ አሜን፡፡

ጸሎት

Page 64: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - Christ Embassycedmvas.org/wp-content/uploads/2017/11/Rhapsody-Of... · እንደሆነ ያስባሉ፤ ምን ማለት እንደሆነ ከተረዳችሁ፣

amharic

ክርስቲያኖች እንደመሆናችን መጠን ሁላችንም እግዚአብሔርን ማስደሰት እንፈልጋለን፤ ፍቃዱን በማድረግ ለእርሱ ስኬታማ

መሆን እንፈልጋለን። በህይወታችን ያለውን ጥሪ ለማወቅና ለማሳካት እንዲሁም ለእርሱ ክብር ማምጣት እንፈልጋለን።

ነገር ግን ይህ ሁሉ እውን እንዲሆን፣ ቃሉን መከተልና ፍጹም እውነት እንደሆነ አምነን መቀበል አለብን፤ ምክንያቱም የእግዚአብሔር ቃል የተገለጠው የእግዚአብሔር ፍቃድ ነው። በቃሉ አማካይነት የእግዚአብሔርን እቅድና ዓላማ እንዲሁም ልንከተለው የሚገባንን መርህ በማወቅ በትክክለኛው መንገድ እናገለግለዋለን።

በክርስትና ውስጥ ዋናው ነገር ጥሩ ስራ መስራት ሳይሆን የምንሰራውን በእግዚአብሔር መንገድ ለእግዚአብሔር ዓላማ መስራት ነው። በመክፈቻ ጥቅሳችን ላይ ያነበብነውን ልብ ብላችሁ ተመልከቱ፤ ሙሴ ድንጋዩን በመናገር ፋንታ መታው። ውሀው ፈልቋል፣ ሕዝቡም እስኪረኩ ድረስ ጠጥተዋል፤ ይሁንና እግዚአብሔር ደስተኛ አልነበረም፡፡ በሙሴም ተቆጥቶ ነበር።

በድጋሚ በዘፍጥረት መጽሐፍ ላይ መጽሀፍ ቅዱስ ሁለቱ ወንድማማቾች ቃየልና አቤል መባቸውን ለእግዚአብሔር ስላቀረቡበት መንገድ ይነግረናል። ቃየል ራሱ የፈለገውን መባ አቀረበ፣ አቤል ግን እግዚአብሔር እንዲቀርብ የመረጠውንና የጠየቀውን አቀረበ።

ቃየል የጊዜውን መመርያ ስላልተከተለና እግዚአብሔር የፈለገውን ስላላቀረበ፣ መስዋእቱ ተቀባይነት አጣ። መስዋእቱ ተቀባይነትን ስላጣ ቃየል መበሳጨቱን ተመልክቶ፣ እግዚአብሔር እንዲህ አለው፡- “መልካም ብታደርግ ፊትህ የሚበራ አይደለምን?” (ኦሪት ዘፍጥረት 4:7)

የእርሱን ፍቃድ፣ አላማና እቅድ ተከተሉ

ሙሴም እጁን ዘርግቶ ድንጋዩን ሁለት ጊዜ በበትሩ መታው፤ ብዙም ውኃ ወጣ፥ ማኅበሩም ከብቶቻቸውም ጠጡ፤ እግዚአብሔርም ሙሴንና አሮንን፣ በእስራኤል ልጆች

ፊት ትቀድሱኝ ዘንድ በእኔ አላመናችሁምና ስለዚህ ወደ ሰጠኋቸው ምድር ይህን ጉባኤ ይዛችሁ አትገቡም አላቸው።

(ዘኍልቍ ምዕ. 20፡11-12)

እሁድ 27

Page 65: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - Christ Embassycedmvas.org/wp-content/uploads/2017/11/Rhapsody-Of... · እንደሆነ ያስባሉ፤ ምን ማለት እንደሆነ ከተረዳችሁ፣

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የዮሐንስ ወንጌል 13:1-30 & መጽሀፈ ነገስት ካልዕ 20-22

1ኛ ቆሮንጦስ 13:1-13 & መጽሀፈ ምሳሌ 23

መጽሀፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 15:22; ሮሜ 12:2; ዕብራውያን 8:5

ውድ አባት ሆይ እኖርበት እና ክብርህን እገልጥበት ዘንድ ቃልህን ስለሰጠኸኝ አመሰግንሀለሁ። እኔ ቃሉን አድራጊ ነኝ። በቃሉ መሰረትና በቃሉ ውስጥ እኖራለሁ፤ ለስምህ ምስጋናና ክብር ይሆን ዘንድ ለእኔ ያለህን መለኮታዊ አላማና ሀሳብ እየፈጸምኩ በጥበብ እመላለሳለሁ። ሀሌሉያ!

ጸሎት

ስለዚህ እግዚአብሔር ገና ከመጀመሪያው በእኛ ሳይሆን በእርሱ እቅድ መሰረት ማገልገል እንደሚገባን አሳይቶናል፡፡ የእናንተ እቅድ ምንም ያህል መልካም ቢሆን፣ ጥያቄው እግዚአብሔር የሚፈልገው ያንን ነው ወይ? የሚለው ነው።

እግዚአብሔርን ማክበር የምትችሉት ቃሉን በማድረግ ነው። ኢየሱስ እንዲህ ብሏል፡- “እኔ ላደርገው የሰጠኸኝን ሥራ ፈጽሜ በምድር አከበርሁህ፤ አሁንም፥ አባት ሆይ፥ ዓለም ሳይፈጠር በአንተ ዘንድ በነበረኝ ክብር አንተ በራስህ ዘንድ አክብረኝ።” (ዮሐንስ ወንጌል 17:4) ኢየሱስ አብን ያከበረው በዚህ መንገድ ነው። በአብ ፍቃድ፣ ዓላማና እቅድ መሰረት አብን አገልግሏል። በየትኛውም ሌላ መንገድ ልትሰሩት አትችሉም!

Page 66: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - Christ Embassycedmvas.org/wp-content/uploads/2017/11/Rhapsody-Of... · እንደሆነ ያስባሉ፤ ምን ማለት እንደሆነ ከተረዳችሁ፣

amharic

በመክፈቻው ጥቅስ ላይ ጌታ ኢየሱስ አብን እንዴት ማክበር እንዳለብን አሳይቶናል። እርሱ አብ የሚፈልገውን በማድረግ

አክብሮታል፤ ስለዚህ እኛም እንዴት እግዚአብሄርን ማክበር እንዳለብን ምሳሌ ሰጥቶናል። “አባት ሆይ አከብርሀለሁ” ማለት ብቻ በቂ አይደለም፤ አይደለም! የምታከብሩት ቃሉን በማድረግና በቃሉ ላይ የተመሰረተ ውጤትን በማስገኘት ነው።

አንድ ሰው ቃሉን እስካላደረገ ድረስ “ጌታ ሆይ ክብርን እሰጥሀለሁ” እያለ መዘመሩ ለውጥ አያመጣም፤ ጌታ አይከብርም። በአንድ ሰው ፊት ለፊት ቆማችሁ “ምግብ እሰጥሀለሁ” ብትሉት ሰውየው ከእናንተ ምግብ አግኝቷል ማለት አይደለም። ይህ የሚከተለውን አይነት ምስክርነት ከመስጠት ጋር ይመሳሰላል፤ ለምሳሌ “ፓስተር ክሪስ እንደባረከኝ መመስከር እፈልጋለሁ፤ ጌታ ይመስገን!” ልትሉ ትችላላችሁ፡፡ ይህን አላችሁ ማለት የሰማችሁ ሰው የተናደራችሁት ገብቶታል ማለት አይደለም። ነገር ግን እኔ ምን አድርጌ እንደባረኳችሁ መናገር ብትጀምሩ፣ የሚያዳምጧችሁ ሁሉ ይረዷችኋል።

ይህ ማለት ግን “ጌታ ሆይ ክብርን እሰጥሀለሁ” ብሎ መናገር ችግር አለበት ማለት አይደለም፤ እንደዛ ማለቴ አይደለም! ሊተኮርበት የተፈለገው ነጥብ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ማድረግ ከሁሉም የበለጠ ጌታን የማክበሪያ መንገድ እንደሆነ ነው። ቃሉን ካደረጋችሁ በኋላ “ጌታን አከብረዋለሁ” ወይንም “ለጌታ ክብርን እሰጣለሁ” ስትሉ መንፈሳዊ ትርጉም የሚሰጥ ነገር ነው፤ ምክንያቱም ለጌታ ክብር በእርግጥ የሚያመጣ ድርጊትን ፈጽማችኋልና! እግዚአብሄር በፍጹም እንዳልተቀበለውና እንዳልደረሰው የምታውቁትን ክብር፣ ለእርሱ መስጠት አትፈልጉም፡፡

ኢየሱስ እንዲህ ብሏል፡- “እንድሰራ ያዘዝከኝን ሰርቻለሁ፣ አንተም

ቃሉን በማድረግ አክብሩት

እኔ ላደርገው የሰጠኸኝን ሥራ ፈጽሜ በምድር አከበርሁህ። (ዮሐንስ ወንጌል 17:4)

ሰኞ 28

Page 67: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - Christ Embassycedmvas.org/wp-content/uploads/2017/11/Rhapsody-Of... · እንደሆነ ያስባሉ፤ ምን ማለት እንደሆነ ከተረዳችሁ፣

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የዮሐንስ ወንጌል 13:31-14:1-14 & መጽሀፈ ነገስት ካልዕ 23-25

1ኛ ቆሮንጦስ 14:1-9 & መጽሀፈ ምሳሌ 24

Á°qw 1:25; የዮሐንስ ወንጌል 15:8

በዚህ ከብረሀል እኔም በአንተ ውስጥ ከብሬያለሁ”፡፡ ኢየሱስ አብን ያከበረው በዚህ አኳኋን ነው። እርሱ የሚፈልገው ምን እንደሆነ ለማወቅ ቃሉን ማጥናት ያለባችሁም በዚህ ምክንያት ነው። ምክንያቱም በፍርድ ቀን በአብ ፊት የሚቆመው ብቸኛው ነገር፣ እንደቃሉ የኖራችሁት ህይወት ብቻ ነው።

ውድ ጌታ ሆይ፣ ቃልህ ህያው ስለሆነና በእኔም ውስጥ እየሰራ እንዲሁም በማይነገር ሀሴትና ክብር እየሞላኝ ስለሆነ አመሰግንሀለሁ። ቃሉን በማድረግና በቃሉ መሰረት የሆነ ውጤትን በማስመዝገብ፣ ለክብርህ ለመኖር ወስኛለሁ፤ በኢየሱስ ስም፡፡ አሜን።

ጸሎት

Page 68: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - Christ Embassycedmvas.org/wp-content/uploads/2017/11/Rhapsody-Of... · እንደሆነ ያስባሉ፤ ምን ማለት እንደሆነ ከተረዳችሁ፣

Te ¨h

Te ¨

h

amharic

Page 69: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - Christ Embassycedmvas.org/wp-content/uploads/2017/11/Rhapsody-Of... · እንደሆነ ያስባሉ፤ ምን ማለት እንደሆነ ከተረዳችሁ፣

Te ¨h

Te ¨

h

Page 70: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - Christ Embassycedmvas.org/wp-content/uploads/2017/11/Rhapsody-Of... · እንደሆነ ያስባሉ፤ ምን ማለት እንደሆነ ከተረዳችሁ፣

amharic

የክርስቲያን ህይወት መለኮታዊ ፍቅር ማሳየት ነው። 1ኛ ዮሐ 4:8 “ፍቅር የሌለው እግዚአብሔርን አያውቅም፥ እግዚአብሔር ፍቅር

ነውና” ይላል፡፡ እግዚአብሔር በስብእና የተገለጠ ፍቅር ነው። ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል። (ሮሜ 5:8)

ዳግም የተወለዳችሁ ስለሆነ፣ የእግዚአብሔር ልጆች ሆናችኋል፤ እናም እናንተን የወለዳችሁ ፍቅር የሆነው እግዚአብሔር ከሆነ፣ ያ ማለት እናንተ የፍቅር ልጆች ማለትም በአካል የተገለጠ ፍቅር ናችሁ ማለት ነው። መለኮታዊ ፍቅር እግዚአብሔርን ስጠኝ ብላችሁ የምትጸልዩበት ጉዳይ አይደለም፤ መለኮታዊ ፍቅር ዳግም የተወለደው መንፈሳችሁ መገለጫ ነው፤ “የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥…” (ገላ 5፡22)፡፡ ከእናንተ የሚጠበቀው በልባችሁ ውስጥ የተከማቸውን ያንን ፍቅር በማሳየት ለአለማችሁ በረከት መሆን ነው። በዚህ በተቸገረ ዓለም ውስጥ፣ ልዩ የፍቅር ቦታ ሁኑ።

ጌታ በዮሀ 14፡15 ላይ “ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ” ብሏል። ከትእዛዛቱ አንዱ ደግሞ ወንጌልን ለአለም ሁሉ መስበክ ነው (ማርቆስ 16፡15)፡፡ የክርስቶስን ወንጌል ይዛችሁ ላላችሁበት ዓለም ስትደርሱ፣ የእግዚአብሔርን ፍቅር እየገለጣችሁ ነው ማለት ነው።

2 ኛ ቆሮ 5:14 “የክርስቶስ ፍቅር ግድ ይለናል…” ይላል። ልክ እርሱ ስለሀጢያተኞች ወደ መስቀሉ ለመሄድ ያነሳሳው ፍቅር እንደሆነ ሁሉ፣ እኛም ወንጌልን ለመስብክ ለእርሱ ያለን ፍቅር ያነሳሳናል። እርሱ የእግዚአብሔር ፍቅር መግለጫና ማሳያ ነበር።

የበረከትን ቃል ለህዝቡ መናገር ብቻ ሳይሆን፣ ይነካቸውና ከእነርሱ ጋር በፍቅር ህብረትን ያደርግ ነበር። እርሱ እነርሱን የወደደበትን ፍቅር በማሳየት፣ አብ እንደሚወዳቸው እንዲያውቁ ረድቷቸዋል። በእርሱ መገኘት ውስጥ በሆናችሁበት ጊዜ ሁሉ፣ መለኮታዊ ፍቅርን ተለማምዳችኋል።

ፍቅሩን ማሳየት

በተሰጠንም በመንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ፍቅር በልባችን ስለ ፈሰሰ ተስፋ አያሳፍርም። (ሮሜ 5:5)

ማክሰኞ 29

Page 71: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - Christ Embassycedmvas.org/wp-content/uploads/2017/11/Rhapsody-Of... · እንደሆነ ያስባሉ፤ ምን ማለት እንደሆነ ከተረዳችሁ፣

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የዮሐንስ ወንጌል 14:15-31 & መጽሀፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ 1-2

1ኛ ቆሮንጦስ 14:10-19 & መጽሀፈ ምሳሌ 25

1ኛ ዮሐንስ 4:11-12; 1ኛ ዮሐንስ 4:16; 2ኛ ቆሮንጦስ 5:14-15

በሚናገራቸው ቃላት ውስጥ ፍቅርን ስለሚሰሙና ስለሚያዩ፣ ሰዎች እርሱን ሊሰሙትና ከእርሱ ጋር ሊሆኑ ሰዎች ከየስፍራው ይመጡ ነበር። እንደ ክርስቲያንና እና የወንጌል አገልጋይ መሻታችሁ የክርስቶስን ፍቅር ለዓለም ሁሉ መግለጥ ሊሆን ይገባዋል።

መንፈስ ቅዱስ በህይወታችሁ ከሚገልጣቸው ነገሮች ውስጥ አንዱ ይህ ነው፤ እርሱን ባወቃችሁት መጠን፣ እግዚአብሔርን ይገልጥላችኋል፤ ፍቅሩም ይቆጣጠራችኋል። ይህም የሚሆነው አብልጣችሁ በወደዳችሁት ቁጥር፣ በይበልጥ እርሱን እየመሰላችሁ ትሄዳላችሁ።

አባት ሆይ፣ መንፈሴን በፍቅርህ መገለጥ ስለሞላኸውና ለእኔ ባለህ ታላቅ ፍቅር መሰረት እንድመላለስ ብቻ ሳይሆን ይህንን ፍቅር እንድገልጸውና ላለሁበት ዓለም በረከት እንድሆን ስለረዳኸኝ አመሰግንሀለሁ፤ በኢየሱስ ስም፡፡ አሜን።

ጸሎት

Page 72: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - Christ Embassycedmvas.org/wp-content/uploads/2017/11/Rhapsody-Of... · እንደሆነ ያስባሉ፤ ምን ማለት እንደሆነ ከተረዳችሁ፣

amharic

አንዳንድ ክርስቲያኖች የእግዚአብሔር የመንፈሱ ሙላት ያለበት ኢየሱስ ብቻ ነው፤ የቀረነው ግን መንፈሱ ያለን በተወሰነ ልክ

ብቻ ነው ይላሉ። ነገር ግን በእግዚአብሔር ቃል መሰረት፣ ይህ እውነት አይደለም።

በመጀመሪያ ደረጃ፣ መጽሐፍ ቅዱስ ስለኢየሱስ ሙላት ሲናገር እኛ ሁላችን ከሙላቱ ተቀብለን በጸጋ ላይ ጸጋ ተሰጥቶናልና (ዮሐ 1፡16) ይላል። ከዚህም በተጨማሪ ዳግም ተወልዳችሁ ከሆነ፣ መንፈስ ቅዱስ በስብእናውና በሙላቱ በእናንተ ውስጥ ይኖራል።

እንግዲህ መንፈሱ በሙላት የተሰጠው ለኢየሱስ ብቻ ነው የሚለውን ሀሳብ የሚያስፋፉ ሰዎች የግራ የመጋባታቸው ምንጭ በኪንግ ጄምስ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም በዮሀ 3፡34 ላይ የተቀመጠው ነው። እንዲህ ይላል፡- “እግዚአብሔር የላከው የእግዚአብሔርን ቃል ይናገራልና፤ እግዚአብሔር መንፈሱን ሰፍሮ (ለእርሱ) አይሰጥምና።” የተሰመረበት ቃል በኪንግ ጄምስ ቅጂ የተቀመጠው በቅንፍ ውስጥ ነው፤ ያም ማለት በዋናው (በኦሪጅናሉ) የግሪክ መጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ የሌለና በተርጓሚዎች የተጨመረ ነው፤ እናም ያሳስታል፤ ምክንያቱም ጥቅሱ የሚያወራው ስለ ኢየሱስ እንደሆነ አድርጋችሁ እንድታስቡ ያደርጋችኋል፣ ይሁንና ግን እንደዛ አይደለም።

ትክክለኛው ትርጉም እንደሚከተለው ነው፡- “እግዚአብሔር የላከው የእግዚአብሔርን ቃል ይናገራልና፤ እግዚአብሔር መንፈሱን ሰፍሮ አይሰጥምና።” ኢየሱስ በአብ እንደተላከ እናንተም ተልካችኋል:- “ኢየሱስም …፤ አብ እንደ ላከኝ እኔ ደግሞ እልካችኋለሁ አላቸው ይህንም ብሎ እፍ አለባቸውና መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ። (ዮሐ 20፡21-22) እናንተ የመንፈስ ቅዱስ “ሁለንተና” በሙላት አለባችሁ።

ኤፌ 3፡17-19 እናንተ በእግዚአብሔር ፍጹም ሙላት እንደተሞላችሁ

የእርሱ ሙላት አለን

እግዚአብሔር የላከው የእግዚአብሔርን ቃል ይናገራልና፤ እግዚአብሔር መንፈሱን ሰፍሮ አይሰጥምና። (ዮሐ 3:34)

ረቡዕ 30

Page 73: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - Christ Embassycedmvas.org/wp-content/uploads/2017/11/Rhapsody-Of... · እንደሆነ ያስባሉ፤ ምን ማለት እንደሆነ ከተረዳችሁ፣

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የዮሐንስ ወንጌል 15:1-17 & መጽሀፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ 3-4

1ኛ ቆሮንጦስ 14:20-30 & መጽሀፈ ምሳሌ 26

የዮሐንስ ወንጌል 1:16; 1ኛ ዮሐንስ 4:17; ኤፌሶን 1:22-23

ይናገራል። ቆላስይስ 1፡19 ደግሞ ይኸንኑ ነገር ስለኢየሱስ ተናግሯል፡- “እግዚአብሔር ሙላቱ ሁሉ በእርሱ እንዲኖር፥ ፈቅዶአል”፡፡ ይሄ በደስታ የሚያስፈነድቅ ነው ብላችሁ ካሰባችሁ፣ ሌላ ጥቅስ ልጨምርላችሁ፡- “…በእርሱ ሆናችሁ ተሞልታችኋል።” (ቆላ 2:10) በማነው የተሞላችሁት? ከዚህ የቀደመው ቁጥር 9 በማን እንደሆነ ይነግረናል፡- “በእርሱ (ኢየሱስ ክርስቶስ) የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና።” (ቆላ 2:9)። እግዚአብሔር የተባረከ ይሁን!

የመለኮት፣ የአምላክ ሙላት በውስጡ በሚኖረው በእርሱ ተሞልታችኋል፤ በእርሱ ፍጹማን ሆናችኋል። ይህም ማለት እናንተ በእግዚአብሔር ሙላት ተሞልታችኋል፤ እናንተ የሚራመድና ህያው የሆነ የእግዚአብሔር ቤተ-መቅደስ ናችሁ። ሀሌሉያ!

ደግና የተባረክህ አባት ሆይ፣ አንተ እንዴት ታላቅ ነህ! በውስጤ በሙላት ስለሚኖረውና ወደ ህይወቴ የዘላለም ክብር ስላስገኘልኝ ስለ መንፈስ ቅዱስ አመሰግንሀለሁ። አንተን ለመውደድ፣ ለማክበር እና በህይወቴ ዘመን ሁሉ ፍቃድህን ላደርግ እኖራለሁ። በኢየሱስ ስም፡፡ አሜን!!!

ጸሎት

Page 74: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - Christ Embassycedmvas.org/wp-content/uploads/2017/11/Rhapsody-Of... · እንደሆነ ያስባሉ፤ ምን ማለት እንደሆነ ከተረዳችሁ፣

amharic

ብዙ ሰዎች ህይወት በእርግጥ መንፈሳዊ መሆኑን አይረዱም። ያለው ነገር ይህ የምንኖርበት ፍጥረታዊ ዓለም ብቻ

አይደለም፤ እንዲያውም ይህ ፍጥረታዊው ዓለም በመንፈሳዊው ዓለም ቁጥጥር ስር ነው።

በዚህ ፍጥረታዊ ዓለም ዙሪያ መላእክት አሉ፤ ነገር ግን በፍጥረታዊው ዓይናችሁ ልታይዋቸው አትችሉም፤ እነርሱን ለማየት ወደ መንፈሳዊው ዓለም ግዛት ውስጥ መግባት አለባችሁ። አሁን የዚህ ነገር ዋናው ነጥብ ይህ ነው፤ እግዚአብሔር የነገረን ነገሮች በሙሉ በመንፈስ አለም እውን ናቸው፤ ነገር ግን በህይወታችሁ እውን እንዲሆኑ ልትናገሯቸው ይገባል። የእግዚአብሔር ቃል ለመስራት የሚነቃቃው በእናንተ ቃል አማካይነት ነው።

ቃላቶቻችሁ “የመንፈስ ቃላቶች” ናቸው፣ ስትናገሩ ከመንፈስ ዓለም ጋር ትገናኛላችሁ። ቃሎቻችሁ ምድራዊውን ዓለምና መንፈሳዊውን ዓለም የሚያገናኙ ድልድዮች ናቸው። ሁልጊዜ ስትናገሩ፣ የተናገራችሁት ምንም ይሁን ምን በመንፈስ ዓለም እውን ሆኗል። በእምነት የተሞሉ አዎንታዊ ቃላት ከተናገራችሁ የእምነትን ውጤት ያስገኛሉ። የፍርሀት፣ ተስፋ የመቁረጥ እና የሽንፈት ቃላት ከሆኑ ደግሞ የተናገራችሁትን ዐይነት አሉታዊ የሆኑ ውጤቶችን ያስገኛሉ።

ቃላቶቻችሁ አንድም ለእናንተ እየሰሩ ነው፤ አለበለዚያ በእናንተ ላይ በተቃውሞ እየሰሩ ነው፤ የምትናገሩትን መጠንቀቅ ያለባችሁም በዚህ የተነሳ ነው። ይህ ጌታ በማቴዎስ 12፡37 ላይ የተናገረውን ያስታውሰናል፡- “ከቃልህ የተነሣ ትጸድቃለህ ከቃልህም የተነሣ ትኰነናለህ።” በመክፈቻ ጥቅሳችን ላይ የተናገረውን አስታውሱ።

“የመንፈስ ቃላትን” ተናገሩ

ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ነው፤ ሥጋ ምንም አይጠቅምም፤ እኔ የነገርኋችሁ ቃል መንፈስ ነው

ሕይወትም ነው። (ዮሐንስ ወንጌል 6:63)

ሐሙስ 31

Page 75: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - Christ Embassycedmvas.org/wp-content/uploads/2017/11/Rhapsody-Of... · እንደሆነ ያስባሉ፤ ምን ማለት እንደሆነ ከተረዳችሁ፣

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የዮሐንስ ወንጌል 15:18-16:1-16 & መጽሀፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ 5-6

1ኛ ቆሮንጦስ 14:31-40 & መጽሀፈ ምሳሌ 27

ሮሜ 10:6-8; 1ኛ ቆሮንጦስ 2:12-13

እኛ፣ እርሱን እንድንመስል ብቻ ሳይሆን ሳይሆን፣ እንደ እርሱም እንድንሰራም ጭምር ተደርገናል፡፡ በቃላቶቻችን ህይወትና መንፈስን እንለቃለን፡፡ በቃላቶቻችን የምንለቀው ኃይል፣ ወይ ህይወትን ይሰጣል፣ ወይም ደግሞ ሞትን ያፈራል። መጽሀፍ ቅዱስ በምሳሌ 18፡21 ላይ “ሞትና ሕይወት በምላስ እጅ ናቸው፤” የሚለው ለዚህ ነው።

በቃላቶቻችሁ የህይወት ሀይልን ልቀቁ፡፡ በዙሪያችሁ ባለው ነገር ላይ፣ በቤተሰባችሁ፣ በስራችሁ፣ በአገልግሎታችሁ፣ በገንዘባችሁ ወዘተ... ላይ ህይወትን ተናገሩ። በሚመለከታችሁ ጉዳይ ላይ ሁሉ፣ ህይወትን ተናገሩ። በሁኔታዎች ላይ ሁሉ የእግዚአብሔርን ቃል አውጁ። የምታገኙት የተናገራችሁትን ነው (ማር 11:23)፤ ይህንን ፈጽሞ አትርሱ፡፡ ህይወትን ብቻ ተናገሩ፤ ሁልጊዜም እምነት የተሞሉ “የመንፈስ ቃላትን” ተናገሩ።

በዓለም ዙርያ ላሉ ሀገሮች ሁሉ ሰላምና ብልጽግናን አውጃለሁ፣ የክርስቶስ ወንጌል ይከብራል፣ በነጻነትም ይሰበካል፤ በሀገራት መሀከል የእግዚአብሔር ጽድቅ ከፍ ከፍ ይላል፤ እያልኩ አውጃለሁ፤ በኢየሱስ ስም፡፡ አሜን።

ጸሎት

Page 76: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - Christ Embassycedmvas.org/wp-content/uploads/2017/11/Rhapsody-Of... · እንደሆነ ያስባሉ፤ ምን ማለት እንደሆነ ከተረዳችሁ፣

በዚህ መጸሐፍ እንደተባረካችሁ እናምናለን፡፡ ክርስቶስ ኢየሱስን በሕይወታችሁ ጌታ እንድታደርጉ እንጋብዛችኋለን፡፡

ጌታ እግዚአብሔር ሆይ ኢሱስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ፤ በሙሉ ልቤ አምነለሁ ፡፡ ለእኔ ሲል እንደሞተ እና እግዚአብሔርም ከሞት እንዳስነሳው አምናለሁ፡፡ ዛሬ ሕው እንደሆነ አምናለሁ፡፡ ከዛሬ ጀምሮ ኢየሲስ ክርስቶስ የሕይወቴ ጌታ እንደሆነ በአፌ አውጃለሁ፡፡ በእርሱ በኩል እና በስሙ ዘላለማዊ ሕይወት አለኝ፡፡ዳግም ተወልጃለሁ፡፡ ጌታሆይ ነብሴን ስላዳንካት አመሰግንሀለሁ! አሁን የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ፡፡ ሀሌሉያ!

እንኳን ደስ ያልዎት፤ አሁን የእግዚአብሔር ልጅ ኖት፡፡ እንደክርስቲያን በመንፈሳዊ ሕይወትዎ እንዲያድጉ ከኋላ በተጻፈውን ስልክ ቁጥር ይደውሉ፡፡

የደህንነት ጸሎት

united kingdom: +44 (0)1708 556 604

nigeria:+234 812 340 6547+234 812 340 6791

canada:+1-647-341-9091+1-416-746 5080

usa:+1 (0) 980-219-5150+1-281-759-5111+1-281-759-6218

south africa: +27 11 326 0971

amharic

Page 77: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - Christ Embassycedmvas.org/wp-content/uploads/2017/11/Rhapsody-Of... · እንደሆነ ያስባሉ፤ ምን ማለት እንደሆነ ከተረዳችሁ፣

Pastor Chris Oyakhilome, the President of Believers’ LoveWorld Inc., a dynamic, multifaceted, global

ministry, is the author of Rhapsody of Realities, the world’s #1 daily devotional, and more than 30 other books. He’s a dedicated minister of God’s Word whose message has brought the reality of the divine life to the hearts of many.

Millions have been affected by his television broadcast, “Atmosphere For Miracles,” which brings God’s divine presence right into people’s homes. The scope of his television ministry extends throughout the world with LoveWorld satellite television networks, delivering qualitative Christian programming to a global audience.

A t the wor ld - renowned Hea l ing Schoo l , he manifests the heal ing works of Jesus Christ and has helped many receive healing through the operation of the gifts of the Spirit.

Pastor Chris has a passion to reach the peoples of the world with God’s presence—a divine commission he’s fulfilled for more than 30 years through various outreaches, crusades, as well as several other platforms that have helped millions experience a victorious and purposeful life in God’s Word.

ስለ ፀሐፊው

Page 78: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - Christ Embassycedmvas.org/wp-content/uploads/2017/11/Rhapsody-Of... · እንደሆነ ያስባሉ፤ ምን ማለት እንደሆነ ከተረዳችሁ፣

Te ¨h

Te ¨

h

amharic

Page 79: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - Christ Embassycedmvas.org/wp-content/uploads/2017/11/Rhapsody-Of... · እንደሆነ ያስባሉ፤ ምን ማለት እንደሆነ ከተረዳችሁ፣

Te ¨h

Te ¨

h

Page 80: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - Christ Embassycedmvas.org/wp-content/uploads/2017/11/Rhapsody-Of... · እንደሆነ ያስባሉ፤ ምን ማለት እንደሆነ ከተረዳችሁ፣

Te ¨h

Te ¨

h

amharic