በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ...

138
1 በድፍረት በኃይል እንነሣ ዶ/ር ኤላይጃህ ማስዋንጋኒ እና ብሩስ ብሪትን በኢየሱስ ስምና ኃይል፣ በአንድ ላይ እንነሣ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን መሠረት ያደረጉ መጻሕፍት የኤስ ኣይ ኤም ሥነ ጽሑፍ

Upload: others

Post on 01-Jan-2020

57 views

Category:

Documents


5 download

TRANSCRIPT

Page 1: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

1

በድፍረት በኃይልእንነሣ

ዶ/ር ኤላይጃህ ማስዋንጋኒእና ብሩስ ብሪትን

በኢየሱስ ስምና ኃይል፣በአንድ ላይ እንነሣ፡፡

መጽሐፍ ቅዱስን መሠረት ያደረጉ መጻሕፍትየኤስ ኣይ ኤም ሥነ ጽሑፍ

Page 2: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

2

Arise Boldly With Powerby Dr. Elijah Maswangani and Bruce Britten

Copyright © 2006 Oasis International Ltd.Fourth Edition

መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡ በአጭሩ በመጽሐፍ ለሚወሰዱ ጥቅሶች፣ እንዲሁምሒሳዊ ጽሑፍ ለማቅረብ ካልሆነ በቀር፣ የዚህ መጽሐፍ የቱም ክፍል ከአሳታሚውየጽሑፍ ፈቃድ ውጭ ፎቶ ኮፒ ማድረግን፣ በድምፅ መቅዳትን ወይም በሌሎች የፋይልማስቀመጫ እና ሲፈለግ አውጥቶ መጠቀሚያ ዘዴዎችን ጨምሮ በኤሌክትሮኒክስምሆነ ሜካኒካል መሣሪያዎች አማካይነት ሊበዛም ሆነ ሊሰራጭ አይገባም፡፡

Printed by SIM Press in Ethiopia 2011

የመጻሕፍት መደብሮች ይህን መጽሐፍ በሚከተለው የኢ.ሜይል አድራሻ ማዘዝይችላሉ info @ oasisint.net

Page 3: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

3

ማውጫከደራሲያኑ ጋር ተገናኙ 5ምዕራፍ 1፡ ኢየሱስ ሕዝቦችን ሁሉ ይባርካል................................................................................16ምዕራፍ 2፡ መጽሐፍ ቅዱስ በመጀመሪያ የት ሄደ? .....................................................................21ምዕራፍ 3፡ የሕዝቤን ልማዶች (ባህሎች) ሁሉ መተው ይኖርብኛልን? ...................................30ምዕራፍ 4፡ የተማሩ . . . ቀናዒ የሆኑ . . . ያልተደረሱ .....................................................38

ምዕራፍ 5፡ ኢየሱስ ‹‹ሂዱ . . . እኔ ከእናንተ ጋር ነኝ›› አለ................................ 47ምዕራፍ 6፡ መጸለይ . . . መላክ . . . መስጠት...................................................................61ምዕራፍ 7፡ እውነተኛ ታሪኮች .....................................................................................................70ምዕራፍ 8፡ ዘራችንም ሆነ ትምህርታችን ምንም አይፈይድም ...................................................74ምዕራፍ 9፡ ኢየሱስን እንዴት መቀበል እንደሚቻል ለጓደኞችህ

ልትነግራቸው ትችላለህ .........................................................................................78ምዕራፍ 10፡ ለቤተ ክርስቲያናችሁ የሚያስፈልጉ 24 ኃይለኛ አሳቦች .......................................88ምዕራፍ 11፡ ክርስቲያኖችን እንዲነሡ ልትረዱዋቸው ትችላላችሁ..............................................102ምዕራፍ 12፡ ሰላም ን የሚያወርድ ልጅ ........................................................................................108ተቀጽላዎች፡ የኢየሱስ መልኩ ምን ነበር?.....................................................................................114

ኢየሱስ ተስፋ የገባው ምንድን ነበር? ................................................................. 119የእኛ ተስፋ.............................................................................................................121ሌሎች ሃይማኖቶች...............................................................................................123ሌላ ቋንቋን ልትማር ትችላለህ ............................................................................124አንድ መጽሐፍን ጻፍ............................................................................................125እነዚህን ገጾች ፎቶ ኮፒ አድርግ ........................................................................127ልታነብባቸው የሚገቡ ሌሎች መጻሕፍት.........................................................132

በድፍረት በኃይል መነሣትየሚለው ይህ መጽሐፍ የተጻፈው ጣፋጭ የሆነ

አፍሪካዊ ጣዕምን በተላበሰበት ሁኔታበአፍሪካ ውስጥ ነው፡፡ በእያንዳንዱ አኅጉር

ያሉ አንባቢያን ጠቃሚናአነቃቂ ሆኖ ያገኙታል፡፡

Page 4: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

4

ይህ መጽሐፍ በቅርብም ሆነ ሩቅ ላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል ፍላጎትላላቸው አብያተ ክርስቲያናት እና የመጽሐፍ ቅዱስ ኮሌጆች በመታሰቢያነት ተሰጥቷል!

መቅድምበድፍረት በኃይል መነሣት የሚለው መጽሐፍ ሁለቱ ደራሲያን እያንዳንዳቸው

በግላቸው መጽሐፉን መጻፍ ይችላሉ፡፡ አብሮ መጽሐፍን የመድረሱ ሁኔታ ዓለምንበወንጌል ለመድረስ ንቁ የሆነ መተባበር አስፈላጊ መሆኑን ይነግረናል፡፡

አንድ ሕዝብ የቱንም ያህል ሀብትና ምሑራን ባለሙያዎች ቢኖሩትም፣ ብቻውንታላቁን ተልዕኮ መፈጸም አይችልም፡፡

መመሪያው በአንድ ላይ መሆን ነው!በበዓለ ኀምሳ ቀን የወረደው መንፈስ፣ ከሌሎች ችሎታዎች ሁሉ ጋር፣ በተግባር

ላይ ያለ የአንድነት መንፈስ ነው፡፡ ስለዚህ፣ ዓለምን ለክርስቶስ ለመድረስ በአንድ ላይእንነሣ!

ኤላይጃንና ብሩስን እንኳን ደስ አላችሁ እንላለን፣ ደግሞም ይህን መጽሐፍበመላው ዓለም ላለችው ቤተ ክርስቲያን ጠቃሚ ነው በማለት አስተያየታችንንእንሰጣለን፡፡ዶ/ር ቲ. አዲየሞ፣ ናይጄሪያ፡፡

ይህ መጽሐፍ በመላው ዓለም ባሉ አብያተ ክርስቲያናት እሳትን ይለኩሳል፡፡ የዶ/ርኤላይጃ ማስዋንጋኒ እና የብሩስ ብሪትን ልቦች ለጠፉ ነፍሳት በሥቃይ ይቃጠላሉ፡፡

መጽሐፉን እያነበባችሁ ሳለ፣ የእግዚአብሔር እሳት በልቦቻችሁ ውስጥ እንደዚሁይሰማችኋል፡፡

ፕሮፌሰር ሲ. ፒተር ዋግነር፣ ፉለር ሴሚነሪ፣ ፓሳዴና፡፡

Page 5: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

5

ከደራሲያኑ ጋር ተገናኙ

ኤላይጃ፡- በ18 ዓመቴ፣ በደቡብ አፍሪካውስጥ፣ እቤቴ አቅራቢያ፣ በአንድማክሰኞ ምሽት ከሴት ጓደኛዬ ጋር እሄድነበር፡፡ በመንገድ ላይ ቆመው የሚዘምሩወጣቶችን ለመስማት ቆምን፡፡ ከዝማሬውበኋላ፣ እያንዳንዳቸው የኃጢአትይቅርታንና ዘላለማዊ ሕይወትን እንዴትእንደ ተቀበሉ ተናገሩ፡፡ ሰዎች በኢየሱስእየተደሰቱ ሳይ ይህ ለእኔ የመጀመሪያጊዜዬ ነበር፡፡ ከዚያም ፍሪዳ ግሮሴንየተባለ አንድ ወጣት የወንጌል መልእክተኛ(ሚሲዮናዊ) ንግግር ለማድረግ ተነሣ፡፡

እያዳመጥሁ ሳለ፣ ስለ ኃጢአቶቼና ስለ ፍርሃቶቼ አሰብሁ፡፡ እናቴጠንቋይ ስለ ነበረች፣ ከእርሷ በኃይል የሚበረቱ ሌሎች ጠንቋዮችእንዳይደግሙብኝ ሁልጊዜ እፈራ ነበር፡፡ ከእንዲህ ያሉ ፍርሃቶች የተነሣ፣ዘወትር እንደ ማሪዋና (ዳጋ) ያለ አደንዛዥ ዕፅን ከፍ ባለ መጠን እወስድነበር፡፡ ነገር ግን፣ ዕፁ ሥራውን ከሠራ በኋላ ሲለቅቀኝ፣ በደሌና ፍርሃቶቼሁልጊዜም ተመልሰው ይመጣሉ፡፡

ደስተኛ ለመሆን እሞክር ነበር፡፡ በእግር ኳስ ቡድናችን ውስጥ ኮከብተጫዋች ነበርኩ፡፡

ሙዚቃ መሣሪያዎችን መጫወት እችል ነበር፡፡ እጅግ ታዋቂ የነበረ የገዛራሴ ባንድ ነበረኝ፡፡ ይሁንና፣ በልቤ ውስጥ አሳዛኝ ነበርሁ፡፡

ነገር ግን፣ በዚያ ምሽት መንፈስ ቅዱስ ኢየሱስን በእውነተኛ ማንነቱገለጠልኝ፡፡

ኢየሱስን እንዲቀበሉ ሰዎችን በሚጋብዙበት ጊዜ፣ ወደ ፊት ለመሄድ፣ለመንበርከክና ለመጸለይ በቅድሚያ ምላሽ የሰጠሁት እኔ ነበርኩ፡፡ ከኪሴውስጥ ጩቤዬንና ዳጋ የተባለውን አደንዛዥ ዕፅ አወጣሁ፡፡ ኃጢአቶቼን

ዶ/ር ኤላይጃህ ማስዋንጋኒ

Page 6: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

6

ተናዘዝሁ፡፡ ኢየሱስን ተቀበልሁ፡፡ ፍርሃቴ ደብዛው ጠፋ፡፡ እርሱ እንደሚጠብቀኝአውቄአለሁ፡፡

የዝማሬ አዝማቾችን እየዘመርሁ ወደ ቤቴ ሄድሁ፡፡ ምን ዓይነት ደስታ ነው!ምን ዓይነት ሰላም ነው!

በቤትም ወላጆቼን ‹‹ኢየሱስን ተቀብያለሁ›› አልኋቸው፡፡

ሁለቱም በአንድ ላይ፣ ‹‹አንተ አእምሮህን ስተሃል፣›› በማለት ተናገሩኝ፡፡

በሚቀጥለው ጠዋት፣ ‹‹እባክህ ይህን ትርጕም-የለሽ ኢየሱስ እርሳው፣››ልትለኝ የሴት ጓደኛዬ መጣች፡፡ እኔም የምትለውን አልተቀበልሁም፡፡ ስለሆነም፣ጥላኝ ሄደች፡፡

በአንድ የጥራጊ ክምር ላይ አንድ አሮጌ መጽሐፍ ቅዱስ አየሁ፡፡ ላነሣውምሮጥሁ፡፡ የእግዚአብሔርን ቃል ለማጥናት ያለኝ ምን ዓይነት ረሃብ ነበር! ብዙምሳይቆይ፣ ‹‹ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው›› (2ኛ ቆሮንቶስ 5፡17)የሚለውን ቃል ልብ አልሁ፡፡ ወዲያውም የሆነው ነገር ይሄ መሆኑን ተገነዘብሁ፡፡ እኔአዲስ ፍጥረት ነኝ!

ለመላው ቤተሰቤ፣ እንዲሁም በሙዚቃ ባንዱ እና በእግር ኳስ ቡድኑ ውስጥላሉ ጓደኞቼ ለመመስከር ያንን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ተጠቀምሁ፡፡

አንድ ቀን ከአንድ ትልቅ ዛፍ ሥር እየሰበክሁ ነበር፡፡ አባቴና እናቴ ሁለቱምተገኝተዋል፡፡ የአሥራ አንድ ዓመት ሽባ ልጅም እንዲሁ በዚያ ተገኝቶ ነበር፡፡ ይህንንልጅ ሁላችንም እናውቀዋለን፡፡ ከውልደቱ ጀምሮ አጥንቶቹ ተጣጥፈው ስለ ነበር፣መራመድ አይችልም፡፡ በየቀኑ በመንገዱ ላይ እየተሳበ ሲሄድ እንመለከተው ነበር፡፡

ከሰበክሁ በኋላ፣ ለዚህ ልጅ ጸለይሁ፡፡ እግዚአብሔር ተአምራት ይሠራል የሚልእምነት አልነበረኝም፡፡ ይገርመኝም ዘንድ፣ ብድግ ብሎ ቆመና፣ ‹‹ተፈውሼአለሁ!››በማለት ጮኸ፡፡

እያንዳንዱ ሰው ደነገጠ፡፡ እኔም እንዲሁ ደነገጥሁ!እናቴ እንባ በእንባ ሆነች፡፡ በዚያ ቀን ክርስቶስን ተቀበለች፡፡ አባቴም እንዲሁ፡፡እናቴ ወደ ቤት ሄደች፣ የጥንቈላ መሣሪያዎችዋን አመጣች፣ ከዚያም በፊት

ለፊቴ ዘረጋቻቸው - ትልቅ ክምር ሆነ፡፡ ክብሪት በእጄ ይዤ በዚያ ቆምሁ፡፡ ያንንክምር አቃጥለው እንደ ሆነ ለማየት እያንዳንዱ ሰው ዓይኖቹን በእኔ ላይ አደረገ፡፡

እኔም ለራሴ፡- በክርስቶስ እጅ ውስጥ በመሆን የተከለልሁ ነኝ (ቈላ. 2፡10)በማለት አስታወስሁት፡፡ እሳቱን ለኮስሁ፡፡ ጐረቤቶቻችን ይሞታል ብለው ይጠብቁኝነበር፡፡

Page 7: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

7

ከጥቂት ቀናት በኋላ፣ ብዙ ጠንቋዮች፣ በተለይም ከእናቴ በታች የነበሩትጠንቋዮች፣ ወደ ኢየሱስ መጡ፡፡ የጥንቈላ መሣሪያዎቻቸውንም እንዲቃጠሉአመጡዋቸው፡፡

አባቴ ወደ ጠጪነት ከቶ አልተመለሰም፣ ደግሞም እናቴ ሙሉ በሙሉ ጥንቈላንተወች፡፡ ከወንድሞቼ አንዱና ሁለት እኅቶቼም ክርስቶስን ተቀበሉ፡፡ ቤታችንመጽሐፍ ቅዱስ የሚጠናበት፣ መዝሙር የሚዘመርበትና ጸሎት የሚደረግበት ስፍራሆነ፡፡

ለመስበክ ያለኝ ፍላጎት አደገ፡፡ መስበክ ከሚወድዱ ከሌሎች አምስት ወጣትወንዶች ጋር ተገናኘሁ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን በማጥናትና በውይይት ብዙ ጊዜ አሳለፍን፡፡በአብያተ ክርስቲያናት፣ በገበያ ስፍራዎች፣ በመንገዶች፣ በአውቶብሶች፣ በባቡሮችውስጥ . . . ሰበክን፡፡ ፈውስ ላይ አጽንኦት አላደረግንም፤ ይሁንና፣ እግዚአብሔርአንዳንድ ሰዎችን ፈውሷል፡፡ ይሁን እንጂ፣ ስለ ተአምራት ብዙ አልተናገርንም፡፡ለምን? . . . ምክንያቱም እግዚአብሔር ተአምራትን በሚሠራበት በእያንዳንዱ ጊዜ፣

‹‹እግዚአብሔር ትልቅ ነው፡፡ እርሱ ሊልቅ ይገባል፡፡ እኛ ልናንስ ይገባል›› (ዮሐንስ

3፡30፣ መዝ. 115፡1) የሚለውን እንድንገነዘብ አድርጐናል፡፡

እንሰማውም ዘንድ በአካባቢው ላይ ወዳለ ወደ እያንዳንዱ የመጽሐፍ ቅዱስአስተማሪ ሄድን፡፡ እያንዳንዳቸውን ከሰማን በኋላ፣ ይህ ትምህርት በእውነትከእግዚአብሔር መጥቶ እንደ ሆነ ለማየት ከመጽሐፍ ቅዱሳችን ለመገንዘብ የጽሞናጊዜ ወሰድን፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ ኰሌጅ ገባሁ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናትንወደድሁ፤ ይሁንና፣ አንድ ችግር አገኘሁ፡- ለአንድ በመጽሐፍ ቅዱስ ኰሌጅ ላለተማሪ እሳቱን፣ ውስጣዊ መነሣሣቱንና ቀናዒነቱን መጠበቅ አስቸጋሪ ነው፡፡

በእነዚያ አራት ዓመታት ውስጥ እሳቴን እንዳይጠፋ ለማድረግ፣ ዘወትር መጸለይእንዲሁም አንድ ለአንድ በሆነ መልኩ ብዙ ጊዜ በመውሰድ ለግለሰቦች መመስከርነበረብኝ፡፡

ከተመረቅሁ በኋላ፣ ሬቨረንድ ጄ. ምላንግሔኒ የሚባል መጋቢ ያላትን ቤተክርስቲያን አገኘሁ፡፡ እርሱ የተቀባ የመጽሐፍ ቅዱስ አስተማሪ ነበር፡፡ በእያንዳንዱ ወርውስጥ ቢያንስ ቢያንስ ሁለት ‹‹የማስተማሪያ እሑዶች›› ነበሩት፡፡ በእነዚያ ሁለትየእሑድ አምልኮ መርሐ ግብሮች ለማስታወቂያና ለዝማሬዎች የሚሰጡ ጊዜያት አጭርነበሩ . . . ከዚያም ለአንድ ሙሉ ሰዓት ያህል ጊዜ ያስተምረን ነበር፡፡ ሁላችንምማስታወሻ እንጽፍ ነበር፡፡ ይህ ታላቅ ትምህርት ነበር!

Page 8: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

8

ከዚያም በምድር ላይ ያለን ምርጥ ሥራ ጀመርሁ፡- አብያተ ክርስቲያናትንእመሠርት ነበር፣ ከዛፍ ሥር እሰብክ ነበር፣ በራሪ ወረቀቶችን አድል ነበር፣ እንዲሁምከቤት ወደ ቤት በመሄድ እመሰክር ነበር፡፡ ሰዎች በሚድኑበት ጊዜ፣ ለመጽሐፍ ቅዱስጥናት ወደ አንድ ቤት እሰበስባቸው ነበር፡፡ አንዳንዶቹ የዚህ አዲስ ቤተ ክርስቲያንመሪዎች ሆኑ፡፡ ከእነዚያ ሽማግሌዎች ጋር ጠንከር ላለ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናትበሳምንት ለሁለት ምሽቶች እገናኝ ነበር፡፡ በአዳዲስ አካባቢዎች ላይ ቤተ ክርስቲያንንለመመሥረት ከእኔ ጋር እወስዳቸው ነበር፡፡ በአንድ ላይ ሆነን ቤቶችን እንጐበኝደግሞም በገበያ ስፍራዎች እንሰብክ ነበር፡፡ ብዙም ሳይቆዩ ቤተ ክርስቲያናትንመሠረቱ፤ እንዲሁም ቤተ ክርስቲያንን እንዲመሠርቱ ሌሎችን ማሠልጠን ጀመሩ፡፡እነዚያ አብያተ ክርስቲያናትም የቤተ ክርስቲያን - መሪዎች እና የወንጌል መልእክተኞችይሆኑ ዘንድ ሰዎችን ወደ መጽሐፍ ቅዱስ ኰሌጅ መላክ ጀመሩ፡፡ ምን ያህል አስደሳችነገር ነበረ!

በእነዚያ ዓመታት እኔ ድኻ ነበርሁ፡፡ ብዙ ጊዜ ቊርስ ወይም ምሳ አልበላምነበር፤ ከዚያም ጌታ ለእራት የሚሆን ነገር ያዘጋጅልኝ ነበር፡፡ የፈለግሁትን ሳይሆን፣የሚያስፈልገኝን ሁሉ አዘጋጀልኝ፡፡ ለእኔ በድኽነት ውስጥ መኖሩ ጥሩ ነበር፡፡ጽናትን ያስተምረኝ ዘንድ እግዚአብሔር ድኽነትን ተጠቀመ (ዮሐንስ 4፡34፤ 2ኛቆሮንቶስ 11፡27፤ የሐዋርያት ሥራ 20፡23-24)፡፡

ለጎሳዎች ሁሉ፡፡ በዚያን ጊዜ በደቡብ አፍሪካ፣ በልዩ ልዩ ጎሳዎች መካከል ክፍፍል(መለያየት) ነበር፡፡ በቤተ ክርስቲያን ስብሰባዎች (ኮንፍረንስ) እንኳ፣ ጥቁሮች በአንድአዳራሽ ውስጥ ይመገባሉ፤ ነጮች ደግሞ በሌላ አዳራሽ ውስጥ ይመገባሉ፡፡ ጥቁሮችለነጮች አይሰብኩም ነበር፡፡

እኔ ያንን ከቶ አልወደድሁትም፡፡ እግዚአብሔር ለሁሉም ሰዎች የሚሆን ፍቅርሰጠኝ፡፡ ስለዚህም አንድ አዲስ ነገር አደረግሁ፡፡ በደርባን በአንድ ታላቅ አዳራሽ ውስጥለአንድ ሳምንት ጊዜ ከሁሉም ጎሳ ለሆኑ ሰዎች ሰበክሁ፡፡

እግዚአብሔር ብዙዎቹን አዳነ፡፡ አንድ ነጭ የሆነ ነጋዴ ከአልኮል ነፃ በመውጣቱደስ አለው፤ ባለቤቱና ልጆቹ ክርስቶስን እንዲቀበሉ ወደ ቤቱ ወሰደኝ፡፡

ከዚያም ወደ ሆላንድ ሄጄ እንድሰብክ ገንዘብ ከፈለልኝ፡፡ከዚያም በኋላ እግዚአብሔር ወደ አውስትራሊያ፣ ብራዚል፣ ቻይና፣ ሕንድ፣

ጃፓን፣ ኬንያ፣ ማላዊ፣ ሞዛምቢክ፣ ሰሜን አሜሪካ፣ ሩሲያ፣ ስኮትላንድ፣ ስዊዚላንድ፣ዚምባቡዌ . . . ላከኝ፡፡

Page 9: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

9

ሰዎች ብዙ ገንዘብ እንዲሰጡኝ አልጠይቅም፡፡ ውድ የሆኑ ነገሮችን ለራሴአልገዛም፡፡ በቢሮዎች፣ በማስታወቂያ፣ እና በመሳሰሉት ላይ ብዙ ገንዘብ አላባክንም፡፡እግዚአብሔርን ለማገልገል ቊልፍ የሆኑት ነገሮች፡- የተቀደሰ ሕይወት መኖር፣ መጸለይእና ሰዎችን መውደድ ናቸው፡፡

ባለቤቴን፣ ታንዲን፣ እወዳታለሁ፡፡ እኛ ጓደኞች ነን፡፡ ለመግባባት ጊዜን እንወስዳለን፡፡እዚህ እቤት ውስጥ ያለውን ሥራ በተመለከተ አንዳችን ሌላውን ለመርዳት ፍቅራችንንእናሳያለን፡፡ ለሴት ልጃችንና ለሁለቱ ወንዶች ልጆቻችንም ብዙ ፍቅር እናሳያቸዋለን፡፡

በእያንዳንዱ ማለዳ ላይ ታንዲ እና እኔ ለሰዎች እንጸልያለን፡፡የእኛ ታላቁ ደስታ ሰዎችን ወደ ኢየሱስ ማምጣት፣ እናከዚያም እነርሱን መጽሐፍ ቅዱስ ማስተማር ነው፣ይኸውም እነርሱም ሌሎችን ማስተማር እንዲችሉ ነው (2ኛ ጢሞ. 2፡2)፡፡

ብሩስ፡- ልጅ በነበርሁበት ጊዜ፣ ከቤተሰባችንአንድም ሰው ቤተ ክርስቲያን የሚሄድአልነበረም፡፡ አባቴ፣ ‹‹ክርስቲያኖች ከእኛ

የሚሻሉ አይደሉም›› ይል ነበር፡፡

አንድ ቀን እውነተኛ አማኝ የሆነ ሰውለአባቴ መሰከረለትና መጽሐፍ ቅዱስ ሰጠው፡፡መጽሐፍ ቅዱስን ለሳምንታት ካነበበ በኋላ፣አባቴ፣ ‹‹ኢየሱስ ሆይ፣ አሁን ወደ ገሃነምእየሄድሁ እንደ ሆነ አያለሁ፡፡ እባክህንአድነኝ!›› ሲል ጸለየ፡፡

ብዙም ሳይቆይ በሕይወቱ ባየችው ታላቅ ለውጥ እናቴ ትገረም ነበር፡፡ እርሷምኢየሱስን ለመቀበል ወሰነች፡፡ እኛም ልጆቻቸው እንዲሁ አደረግን፡፡ ቤተሰባችን ወደቤተ ክርስቲያን ሲሄድ በመመልከታቸው ጐረቤቶቻችን ደነገጡ፡፡

አባቴ ለጓደኞቹ፣ ‹‹በእያንዳንዱ ሰኞ ዕለት ወደ ቤቴ ኑ፡፡ መጽሐፍ

ብሩስ ብሪትን

Page 10: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

10

ቅዱስን አንብበን እንወያይበታለን፣›› ብሎ ነገራቸው፡፡

ስድስት ሰዎች መጡ፡፡ ከጥቂት ወራት በኋላ፣ ሦስቱ ኢየሱስን ተቀበሉ፡፡

የአንዱ ሰውዬ ሚስት፣ ‹‹ባሌ መጠጣት አቁሟል፡፡ እኔን በመምታት ፈንታ

ለእኔም ሆነ ለልጆቻችን ቸር ሆኖአል፣›› ስትል ተናገረች፡፡

ሌላ ሰውዬ ደግሞ ዘላለማዊ ሕይወት በማግኘቱ እጅግ ደስተኛ ሆነ፤ ሥራውንአቆመ፤ መጽሐፍ ቅዱስ ኰሌጅ ተማረ፤ ከዚያም በሜክሲኮ ወንጌልን ለመስበክከሚስቱና ከልጆቹ ጋር ተጓዘ፡፡

በ17 ዓመቴ፣ ‹‹ለጓደኞቼ እመሰክራለሁ›› ስል ለኢየሱስ ቃል ገባሁለት፡፡ እኔዓይነ አፋር ልጅ ነበርሁ፡፡ ጓደኞቼ ስለ እኔ የሚያስቡትን ነገር ፈራሁት፡፡ ይሁንና፣ለጓደኛዬ ለኢዩኤል መጸለይ ጀመርሁ፡፡ ከዚያም አንድ ቀን ለእርሱ፣ ‹‹ስለ መንግሥተ

ሰማይና ስለ ኢየሱስ የሚናገሩ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን ላሳይህ?›› አልሁት፡፡ [ያንን

ለማለት እጅግ ፈራሁ፡፡]

እርሱም፣ ‹‹ብሩስ እኔ ጨዋታዎች (ቀልዶችን) እፈልጋለሁ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ

ቀልዶቼን ያበላሽብኛል፡፡››ከዚያም በኋላ፣ አንድ በአንድ እያደረግሁ፣ ለሌሎቹ ጓደኞቼ ሁሉ

መሰከርሁላቸው፡፡ ከእነርሱ አንዱ ክርስቶስን በተቀበለ ጊዜ ምን ያህል ደስታተሰምቶኛል መሰላችሁ!

በዩኒቨርስቲ ልጃገረዶች በጣም ፈታኝ ነበሩ፤ ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በንጽሕናእንድኖር ጠበቀኝ፡፡

በጋብቻችን ቀን፣ ካሮል ድንግል በመሆንዋ በጣም ተደስቼ ነበር፣ ደግሞምእኔም ድንግል በመሆኔ ካሮል ደስተኛ ነበረች፡፡ እግዚአብሔርን መታዘዝ ደስታንያመጣል፡፡

አንድ ቀን ካሮል፣ ‹‹ተመልከት፣ ጐረቤቶቻችን ከቤት ውጭ ተቀምጠዋል፡፡

እንሂድ እና እንተዋወቃቸው፣›› ብላ ተናገረችኝ፡፡

ቶም እና ራሔል ይባሉ ነበር፡፡ ብዙም ሳይቆዩ ችግሮቻቸውንይነግሩን ጀመር፡፡ ራሔል፣ ‹‹እኔ ሁልጊዜ እንደዚህ ስላሉ ችግሮች እጸልያለሁ››አለች፡፡ ነገር ግን ቶም፣ ‹‹እኔ አልጸልይም፡፡ እኔ ክርስቲያን አይደለሁም፡፡ መንግሥተ

ሰማያት ለመግባት መልካም ሰው አይደለሁም›› አለ፡፡

Page 11: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

11

ካሮል፣ ‹‹ልጃገረድ በነበርሁበት ጊዜ፣ መንግሥተ ሰማይ ለመግባት የምችለውንመልካም ነገር ሁሉ አደርግ ነበር - ከዚያም በወጣቶች ካምፕ ውስጥ ሳለን፣ አንድሰባኪ ‹‹ጻድቅ የሆነ (መልካምነቱ በቂ የሆነ) አንድም ሰው የለም፡፡ የመንግሥተ ሰማይ

መንገዱ፡- ኢየሱስን መቀበል ነው›› ብሎ ሲናገር ሰማሁ፡፡

ከአንድ ሰዓት ለሚበልጥ ጊዜ ቶምን፣ ‹‹ክርስቶስን ተቀበል›› ስንለው ቆየን፡፡

ነገር ግን እርሱ፣ ‹‹እኔ ብቁ አይደለሁም›› ይለን ነበር፡፡ከዚያ በኋላ በየቀኑ ለቶም ጸለይን፡፡አንድ ቀን መኪናውን በመጠገን እየረዳሁት ሳለ፣ በዓይኖቹ ውስጥ እንባዎችን

ተመለከትሁ፡፡ እርሱም፣ ‹‹ብሩስ፣ እኔ እጅግ ደስተኛ ነኝ! ትናንት ከባለቤቴ ጋር ቤተክርስቲያን ሄድሁ፣ ደግሞም ኢየሱስን ተቀበልሁ፡፡ አሁን ወደ መንግሥተ ሰማይየምሄደው፣ እኔ መልካም በመሆኔ አይደለም፤ ነገር ግን ኢየሱስ ስለ ኃጢአቶቼ መከራንበመቀበሉ ነው›› አለኝ፡፡

መጋቢያችን፣ እያንዳንዱ ሰውን፣ ‹‹ኢየሱስ እንግዲህ ሂዱና ወንጌልን ለፍጥረት ሁሉ

(ለሕዝቦች) ስበኩ›› የሚለውን (ማቴ. 28፡19) ማስታወስ ይወድዳል፡፡

ካሮልና እኔ ተወያየንና የበለጠ ነገር ለመስጠት ወሰንን፡፡ ከዚያ በኋላ በየወሩከገቢያችን ውስጥ ግማሽ የሚሆነውን ለቤተ ክርስቲያናችን ‹የወንጌል ማዳረስ ፈንድ›ለተባለው ሰጠን፡፡ ያንን ለማድረግ አስፈላጊ ያልሆኑ ነገሮችን ላለመግዛት ጠንቃቃመሆን ነበረብን (ማቴ. 6፡19)፡፡

ከቤት ወደ ቤት በመሄድ ከሚመሰክሩ አማኞችም ጋር እንደዚሁተቀላቀልን፡፡

ከዚያም አንድ ቀን መጋቢያችንን፣ ‹‹ወንጌልን ወደ አንድ ስፍራ መውሰድ

የምንችል ይመስልሃል?›› ስንል ጠየቅነው፡፡ ምላሽ ከመስጠቱም በፊት፣ ‹‹በእርግጥ፣

ቤታችንን መልቀቅ አንፈልግም፤ ነገር ግን፣ ለመሄድ ፈቃደኞች ነን›› የሚለውንአከልንበት፡፡

መጋቢው በጉዳዩ ላይ ከሽማግሌዎች ጋር ተወያየ፡፡ ከዚያም፣ ‹‹ቤተክርስቲያን፣ ኬምስትሪ እንድታስተምሩና በዚያ እንድትመሰክሩ ወደ ስዋዚላንድልትልካችሁ ትፈልጋለች›› ሲል ነገረን፡፡

ለመሄድም ተስማማን፡፡

Page 12: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

12

ለአለቃዬ በነገርሁት ጊዜ፣ ‹‹የኢንጂነርነት ሥራህን ትተህ ተራ አስተማሪ

ለመሆን እንዴት ትሄዳለህ?›› ሲል ጮኸ፡፡

ቶም ደግሞ፣ ‹‹አትሂዱ፡፡ እዚህ ያሉ ሰዎች ኢየሱስ ያስፈልጋቸዋል›› ብሎተናገረን፡፡

እኛም፣ ‹‹ቶም፣ እዚህ አንተ መስክር፡፡ እኛ እዚያ እንሄዳለን›› አልነው፡፡ቤተሰብና ወዳጆቻችንን እየተሰናበትን ሳለ ካሮል አለቀሰች፡፡

እንባዎቻችን፣ ከስዋዚላንድ ሰዎች ጋር በምንሠራበት ጊዜ ወደ ደስታ ተለወጡ፡፡ወደድናቸው፣ እነርሱም ወደዱን፡፡

ወዲያውም ሴት ልጃችንና ወንድ ልጃችን ተወለዱ፡፡ ከስዋዚላንዳውያን ልጆችጋር ይጫወቱና ሲስዋቲኛን ይናገሩ ጀመር፡፡ በትምህርት ቤት ውስጥ እነርሱ ብቻ ነጭልጆች መሆናቸውን ከቶ ልብ ያሉት አይመስሉም፡፡ ‹‹ስለ ምን ጫማችሁን

አትጫሙም?›› ብለን በምንጠይቃቸው ጊዜ፣ ‹‹እንደ ሌሎች ልጆች ልንመስል

እንፈልጋለን፣›› ሲሉ መለሱ፡፡

ሌላ አስተማሪ፣ ‹‹ብሩስ፣ አንተ፣ ባለቤትህና ልጆችህ ከከፍተኛው መደብ፣ከዝቅተኛው መደብ የኅብረተሰብ ክፍል እና ከእያንዳንዱ ጎሳ ጋር ወዳጅነት በመፍጠርረገድ ተሳክቶላችኋል፡፡ እንዴት ልታደርጉት ቻላችሁ?›› አለን፡፡

ከዚያም ከራሔል፣ ‹‹ቶም ሞቶአል›› የሚል ደብዳቤ ደረሰን፡፡ አለቀስን . . .

ይሁንና፣ አሁን ቶም በመንግሥተ ሰማያት፡- ‹‹እኔ መልካም አይደለሁም፤ ነገር ግንኢየሱስ ለእኔ ሞቶአል›› እያለ እንደሚዘምር እናውቃለን፡፡

አንድ ቀን ለተማሪዎቼ፣ ‹‹ዛሬ ለምን ኢየሱስን እንደ ወደድሁት ልነግራችሁ 10 ደቂቃ

እወስዳለሁ›› አልኋቸው፡፡

ብዙዎቹ ክርስቲያኖችን እንደሚንቁ አውቅ ነበር፡፡ እርስ በርሳቸው የማንሾካሾክምልክቶችን ማሳየት ይጀምራሉ፣ ከዚያም ማንም የሚያደምጥ አይኖርም ብዬ ፈርቼነበር፡፡

ነገር ግን እያንዳንዱ ሰው ያደምጥ ነበር!

‹‹በምሞትበት ቀን፣ ሥጋዊ አካሌን እተውና በቀጥታ ወደ መንግሥተ ሰማይእሄዳለሁ (ሉቃስ 23፡43፤ ፊልጵ. 1፡21-24) በማለት ደመደምሁ፡፡ ለምን? ይህየሚሆነው ኢየሱስ ለኃጢአቶቼ በመሞቱ ብቻ ነው፡፡ አንዳንዶቻችሁ ስለዚህ ጉዳይ

Page 13: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

13

ከእኔ ጋር ልትነጋገሩ ትሹ ይሆናል፡፡ አሁን ለእያንዳንዳችሁ አንድ ወረቀትእሰጣችኋለሁ፡፡ በዚህም ላይ ሀ) ወይም ለ) ላይ አክብቡ፡፡

ስም _____________________ሀ) ሚስተር ብሪትን፣ ከአንተ ጋር ተቀምጬ በዚህ ጉዳይ ላይ መነጋገር

እፈልጋለሁ፡፡ለ) አይ፣ አመሰግናለሁ፤ በዚህ ጉዳይ ላይ መነጋገር አልፈልግም፡፡

ከዚያም እንደ ተለመደው፣ ሁሉ በቀሪው ክፍለ ጊዜ፣ በሙሉ ልቤ ኬሚስትሪንአስተማርሁ፡፡

ከክፍል (ትምህርት) በኋላ ወረቀቶቹን ተመለከትኋቸው፡፡ ሃያ ተማሪዎች "ለ"ላይ አክብበዋል፡፡

አንዱ ተማሪ፣ ‹‹ለገዛ ሕዝብህ ስበክ፣ ለእኛ አትስበክ፣›› ሲል ጽፎአል፡፡

ነገር ግን እግዚአብሔር ይመስገን ስድስቱ "ሀ"ን አክብበዋል፡፤ ደግሞም ከእነዚህአንዳንዶቹ ክርስቲያኖችን በንቀት የሚመለከቱ ነበሩ፡፡

ከእነዚያ ከስድስቱ ጋር በግል መገናኘት ጀመርሁ፡፡ ዛሬ ብዙዎቹ ክርስቶስንበማገልገል ላይ ናቸው፡፡ ከእነርሱ አንዱ በትምህርት ቤት ውስጥ ያስተምራል፡፡ እርሱአንዳንድ መምህራንን፣ ተማሪዎችንና ወላጆችን ክርስቶስን እንዲቀበሉ ረድቷቸዋል፡፡ ቤተክርስቲያን መሥርተዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት ያች ቤተ ክርስቲያን ሩቅ ወደ ሆኑ ስፍራዎችእንዲሰብኩ ሰዎችን ትልካለች፡፡

ወንድ ልጃችንና ሴት ልጃችን እያደጉ ሲሄዱ፣ እስከ ጋብቻ ድረስ በድንግልና እንዲቆዩማበረታታችንን ቀጠልን፡፡ ሁለቱም ይህን ስላደረጉት አመስጋኞች ነን፡፡ አሁን ወንዱ ልጃችንበኮምፒውተር ንግድ ሥራ ተሰማርቷል፡፡ እርሱና ባለቤቱ ክርስቶስን ይወድዳሉ፤ያገለግሉትማል፡፡ እንዲሁም ሴት ልጃችን አስደናቂ የሆነ መጋቢን አግብታለች፡፡ ክብርለእግዚአብሔር ይሁን!ድረ ገጻችንን ተመልከቱ፡- WWW. powerforvictory.com

ወዳጄ ኤላይጃ ማስዋንጋኒ መጽሐፍ መጻፍን በተመለከተ ለመወያየት ወደ ቤቴ በመጣ ጊዜ፣‹‹እኔ ግቤ አማኞች ማቴዎስ 28፡19ን እንዲታዘዙ የሚረዳ መጽሐፍን መጻፍ ነው››አልሁት፡፡

ኤላይጃም፣ ‹‹እኔም መጻፍ የምፈልገው በዚሁ ርእስ ላይ ነው ብሎ ጮኸ፡፡

መጽሐፉን በአንድ ላይ ሆነን እንጻፈው!›› አለ፡፡

ይህን መጽሐፍ መጻፍ ስንጀምር፣ ኤላይጃ፣ ‹‹ዕድሜህ ስንት ነው?›› ብሎ ጠየቀኝ፡፡

እኔም ‹‹51›› ነው ስል መለስሁ፡፡

Page 14: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

14

እርሱም ፈገግ አለና፣ ‹‹ደስ የማይል ነው! አንተ ከእኔ አንድ ዓመት ትበልጠኛለህ፡፡

እኔ በበለጥሁ፣ ስለዚህም በምንጽፍበት ጊዜ አለቃ በሆንሁ ብዬ እመኛለሁ›› አለ፡፡

እኔም እየሳቅሁ፣ ‹‹እኔ ሁልጊዜ ወጣት (አነስ ያልሁ) መሆንን እፈልጋለሁ፡፡ አንተ

እንዴት ታላቅ መሆን ፈለግህ?›› አልኩት፡፡

በወፍራም ድምፅና በፈካ ፈገግታው፣ ‹‹ምክንያቱም አጥንተ አፍሪካዊ ነኝ!›› ሲልተናገረ፡፡

እግዚአብሔር ይህን መጽሐፍ በመጠቀም በመላው ዓለም በልቦች (በነፍሳት) ውስጥእሳቱን እንዲያቀጣጥል በደስታ ጸለይን፡፡

ምዕራፍ 1

ኢየሱስ ሕዝቦችን ሁሉ ይባርካል

በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሁሉንም ነገር መልካም አድርጎ ፈጠረ፡፡ ይሁንና፣ ብዙሰዎች በእግዚአብሔር ላይ ምንም እምነት የላቸውም፡፡ ነገር ግን፣ አብርሃምበእግዚአብሔር ማመንን መረጠ፡፡

አብርሃም በዑር ተወለደ፡፡ በኋላምወላጆቹ ከእርሱ ጋር ወደ ካራን ተጓዙ፡፡ከዚያም እግዚአብሔር፣ ‹‹ከአገርህ፣ከዘመዶችህ ከአባትህም ቤት ተለይተህ እኔወደማሳይህ ስፍራ ውጣ›› ብሎ ተናገረው

(ዘፍጥ. 12፡1፤ ነህ. 9፡7-8)፡፡

ኋላ እግዚአብሔር ኢየሩሳሌም ወደሆነች ስፍራ መራው፡፡

ለምን ወደዚያ መራው?ምክንያቱም ኢየሩሳሌም በአፍሪካ፣

በአውሮፓ እና በእስያ መካከል ያለች ናት፡፡የእርሱ እምነት በእኩልነት ለእስያውያን፣ለአፍሪካውያንና ለአውሮፓውያን ይደርስ(ይሰራጭ) ዘንድ እግዚአብሔር አብርሃምንበዚያ አስቀመጠው፡፡

Page 15: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

15

‹‹እናንተ የምድር ዳርቻ ሁሉ፣ እኔአምላክ ነኝና ከእኔም በቀር ሌላ የለምናወደ እኔ ዞር በሉ ትድኑማላችሁ›› (ኢሳ.45፡22)፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ ‹‹የሕንድ አምላክ፣›› ‹‹የአፍሪካ

አምላክ፣›› ወይም ‹‹የአውሮፓ አምላክ›› ከሚለው አሳብ ጋርአይስማማም፡፡

አንድ እግዚአብሔር አለና በእግዚአብሔርና በሰውምመካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ እርሱምሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው (1ኛ ጢሞ. 2፡5)፡፡

እግዚአብሔር ሁሉንም ሕዝቦች በእኩልነት ይወድዳል (የሐዋርያት ሥራ

10፡34)፡፡ ለዚህ ነው አብርሃምን በመካከል ያስቀመጠው፡፡ ከዚያም ሁሉንም ሕዝቦችእንደሚባርክ ተስፋ ሰጠ፡፡ አዎን፣ ለአብርሃም ተስፋ ገባለት፡-

‹‹አሕዛብ ሁሉ›› እና ‹‹ዘርህ›› የሚሉትን ቃላት ልብ በሉ፡፡

‹‹አሕዛብ ሁሉም›› - ይህ ተስፋ ለሕዝቦች ሁሉ የተሰጠ ተስፋ ነው -ለእስያ ብቻ፣ ለአፍሪካ ብቻ፣ ወይም ለአውሮፓ ብቻ አይደለም፡፡

‹‹ዘርህ›› ማለት ልጅህ ማለት ነው፡፡ እግዚአብሔር ከአብርሃም ቤተሰብ

በሚሆን አንድ ልጅ አማካይነት ሕዝቦችን ሁሉ ለመባረክ የተስፋ ቃልን ሰጠ፡፡

ከመቶ ዓመታት በኋላ ኢየሱስ ተወለደ፡፡ እርሱ ያ የአብርሃም ‹‹ዘር›› ነበር

(ማቴ. 1፡1-16፤ ገላ. 3፡8 እና 16)፡፡

ኢየሱስ አውሮፓዊ ወይም አፍሪካዊ አልነበረም፡፡ እርሱ በኢየሩሳሌምአቅራቢያ፣ በመካከል ነበር የተወለደው፡፡ እርሱ ከሞላ

ጐደል በመካከል የሚገኝ ቡናማ ከለር ያለው ነበር፡፡በእነዚያ ቀናት፣ አንዳንድ አይሁዶች

(የአብርሃም ልጆች)፣ ‹‹የአብርሃም እምነትለእኛ ለአይሁዳውያን ብቻ ነው፡፡ አይሁድያልሆኑ ‹‹ንጹሕ አይደሉም›› ይሉ ነበር፡፡

(የሐዋርያት ሥራ 10፡28ን ተመልከት፡፡)

Page 16: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

16

አውሮፓውያንን በሙሉ ‹‹ንጹሕ

ያ ል ሆ ኑ ( የ ረ ከ ሱ ) › › ብ ለ ውይጠሩዋቸዋል፡፡

አፍሪካውያንን ሁሉ ‹‹ንጹሕ

ያልሆኑ›› ብለው ይጠሩዋቸዋል፡፡

የትኛውንም አይሁዳዊ ያልሆነ እስያዊ ‹‹ንጹሕ ያልሆነ›› ብለው ይጠሩታል፡፡

ነገር ግን፣ ኢየሱስ ያንን ከቶ አላደረገውም፡፡ የአብርሃም እምነት ለአሕዛብ ሁሉእንደ ሆነ አውቆ ነበር፡፡

አንዳንድ አይሁዶች ኢየሱስ የሁሉምጎሳዎችን ሕዝቦች የመውደዱን እውነታአልወደዱትም ነበር፡፡ ኢየሱስን ‹‹ሳምራዊ››

ነው ብለውታል (ዮሐንስ 8፡48)፡፡

እነርሱ፣ ‹‹ኢየሱስ እንደ እኛ አይሁዳዊነው፣ ደግሞም እኛ አይሁዳውያንአይሁዳውያን ካልሆኑት ጋር መደባለቅየለብንም፡፡ እኛ በአንድ ክፍል ውስጥከአውሮፓውያን፣ ወይም ከአፍሪካውያንወይም አይሁድ ካልሆኑ ከሌሎች ጋር አብረንልንበላ ከቶ አያስፈልግም›› (የሐዋርያትሥራ 11፡2-3) ብለው ያስባሉ፡፡

ነገር ግን ኢየሱስ ከመወለዱ 600ዓመታት በፊት፣ እግዚአብሔር አብ ተናገረ፡-

የአብርሃምን ሕዝብ ብቻ ማምጣትይህ ለአንተ [ለኢየሱስ] በጣም ትንሽነገር ነው፡፡ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስለመድኃኒት ትሆን ዘንድ ለአሕዛብብርሃን አድርጌ ሰጥቼሃለሁ ይላል(ኢሳ. 49፡6)፡፡

አፍሪካውያን ወደ አውሮፓ ወይም እስያ ሲጓዙበኢየሩሳሌም ሄዱ፡፡አውሮፓውያን እና እስያውያን ወደ አፍሪካለመጓዝ በኢየሩሳሌም በኩል አቋረጡ፡፡ከኢየሩሳሌም እምነት ወደ ደቡብ፣ ሰሜን፣ምሥራቅና ምዕራብ ሊሰራጭ ቻለ፡፡

አውሮፓ

ካራንኢየሩሳሌም

ዑር

እስያ

አፍሪካ

Page 17: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

17

አዎን፣ ኢየሱስ የመጣው ለሁሉም ጎሳዎች ነበር በዮሐንስ ምዕራፍ 4 ሴቲቱ ኢየሱስን፣ ‹‹አንተ የይሁዳ

ሰው ስትሆን ሳምራዊት ሴት ከምሆን ከእኔ መጠጥእንዴት ትለምናለህ?›› ስትል ጠየቀችው፡፡

ኢየሱስም፣ ‹‹እኔ ከምሰጠው ውኃ የሚጠጣ ሁሉ

ግን ለዘላለም አይጠማም›› ሲል መለሰ፡፡

በዮሐንስ 10፡11-16 ላይ እንዲህ አለ፡-

‹‹ነፍሴንም ስለ በጎቹ አኖራለሁ፡፡

ከዚህም በረት ያልሆኑ ሌሎች በጎች አሉኝ፤ እነርሱን ደግሞላመጣ ይገባኛል፡፡››

ይህም ማለት፣ ‹‹ለእናንተ ለአይሁዶች ደግሞም ለሌሎች ሕዝቦችም

ጭምር ሕይወቴን እሰጣለሁ፡፡ ሌሎች ሕዝቦችንም ላመጣ ይገባል፡፡››

ለምን ‹ይገባኛል› አለ?

ምክንያቱም፣ ‹‹ዘርህ ሕዝቦችን ‹ሁሉ ይባርካል››› ሲል እግዚአብሔር

ለአብርሃም ተስፋ ገብቶለታል፡፡ ማርቆስ11፡17፡- በእነዚያ ቀናት አይሁድ አውሮፓውያንን፣ አፍሪካውያንን ወይም

የትኞቹንም ሌሎች አይሁዳውያን ያልሆኑ ወገኖች ወደ መቅደሱ እንዲገቡአይፈቅዱላቸውም፡፡

እግዚአብሔር

ኢየሱስ

ሰዎች

የምድር አሕዛብ ሁሉም በዘርህ ይባረካሉ (ዘፍጥ. 22፡18)፡፡

Page 18: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

18

ምዕራፍ 2

መጽሐፍ ቅዱስ የት ተጻፈ?በመጀመሪያስ ወዴት ሄደ?

ኢየሱስ ነጭ ነበርን?ብዙዎቹ የኢየሱስ ሥዕሎች ነጭ የሆነ ሰው

ያስመስሉታል፡፡ ደግሞም በፊልም ሰማያዊ ዓይን፣ነጭ ቆዳ፣ እንዲሁም ሳሳ ያለ ቡናማ ጠጕር ያለውአድርገው ያሳያሉ፡፡

የአንድ ሰው ቀለም የሚፈይደው ነገር የለም፡፡ይሁንና፣ እውነቱን ነቅሰን ማውጣት አለብን፡፡እውነቱም፡- ኢየሱስ ነጭ ሰው አለመሆኑ ነው፡፡እርሱ ከዓለም መካከለኛ ስፍራ የመጣ ቡናማ ቀለምያለው ሰው ነበር፡፡

ጠጕሩ ጥቁር ነበር (ቡናማ አይደለም)፡፡ ዓይኖቹጥቁር ነበሩ (ሰማያዊ አይደሉም)፡፡ ቆዳው ከሞላጐደል ቡናማ ነበር፡፡ ገጽ 114ን ተመልከት

Page 19: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

19

ኢየሱስ ነጭ አልነበረም እንዲሁም ጥቁርአልነበረም - እርሱ በመካከል ነበር፡፡

መጽሐፍ ቅዱስስ?መጽሐፍ ቅዱስ በነጮች በአውሮፓ

ነበር ወይ የተጻፈው? ወይስ በአፍሪካ ነበርየተጻፈው? ወይስ በየት ስፍራ ተጻፈ?

መልስ፡-መጽሐፍ ቅዱስ በዓለም ላይ መካከለኛየሆነ ስፍራ ላይ ከሞላ ጐደል ጠይምቀለም ባላቸው ሰዎች በኢየሩሳሌምአቅራቢያ ተጽፎአል፡፡

እግዚአብሔር ኢየሩሳሌምን በዓለምዕምብርት ላይ አስቀምጬያለሁ አለ (ሕዝ.5፡5)፡፡ከኢየሩሳሌም ወዴት ሄደ?

የኢየሩሳሌም ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስንበመጀመሪያ ወደ አፍሪካ ወይስ ወደ አውሮፓወሰዱት?

መልሱ ከሐዋርያት ሥራ 1-16 ውስጥ ነው ያለው፡፡እስኪ አሁን እነዚያን ምዕራፎች እንመልከታቸው፡፡

የሐዋርያት ሥራ 1 እስከ 7፡፡ በሐዋርያት

ሥራ 1 ላይ ኢየሱስ፣ ‹‹በመንፈስ ቅዱስኃይል በኢየሩሳሌም እንዲሁም እስከ ዓለምዳርቻ ድረስ ትመሰክራላችሁ፡፡›› አለ፡፡ከዚያም ወደ ሰማይ ተመልሶ ሄደ፡፡

ከምዕራፍ 2 እስከ 7 ባለው ክፍል ላይአማኞች በኢየሩሳሌም መሰከሩ፡፡

የሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ8፣ ወደ አፍሪካ፡፡እግዚአብሔር ፊልጶስን፣‹‹ወደ ጋዛ›› እንዲሄድ ነገረው፡፡ ፊልጶስበመካከል የሚገኝ ቡናማ ቀለም የነበረው

Page 20: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

20

ሰው ነበረ፡፡ በጋዛም ኢትዮጵያዊ ከሆነ

የአፍሪካ ሰው ጋር ተገናኘ፡፡አፍሪካዊው አምኖ ተጠመቀ፡፡ ከዚያም

መጽሐፍ ቅዱስን ወደ ኢትዮጵያ ወሰደ (35ዓ.ም)

ስለዚህ፣ መጽሐፍ ቅዱስ በቅድሚያመኖር የጀመረው በዓለም ዕምብርትነበር፣ ከዚያም በመጀመሪያወደ ኢትዮጵያ ሄደ፡፡[ካርታ 1]

መጽሐፍ ቅዱስ ወደ አ ው ሮ ፓየገባው መቼ ነበር?

መልስ፡- ከ15 ዓመታት በኋላ (በ50ዓ.ም) ነበር፤ የሐዋርያት ሥራምዕራፍ 16 መጽሐፍ ቅዱስ እ ን ዴ ት

ወደ አውሮፓ እንደ ገባ ይነግረናል፡፡

የሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 1 6 ፣ ወ ደአውሮፓ፡፡

ሐዋርያው ጳውሎስ ጠይም ቀለም የነበረው የተርሴስ ሰውነበር፡፡ [ካርታ 2]

በሐዋርያት ሥራ 13 ላይ እርሱን ለሚመስሉ ሰዎች ሰበከ፡፡

ከ ዚ ያ ምበ ሐ ዋ ር ያ ት

ኢየሱስ ወደዚህ ምልክት እያመለከተ፣

በበሩ አቅራቢያ አይሁዳዊ ያልሆኑ (አውሮፓውያን ወይም አፍሪካውያን)በዚህ በር ከገቡ ይገደላሉ የሚል ጽሑፍ ያስቀምጣሉ፡፡

ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች (ማርቆስ 11፡17፤ ኢሳ. 56፡7) አለ፡፡

ቅድስተ

ቅዱሳን

ቅድስት

ኢየሱስ ሁሉም ሕዝቦች ነፃ ሆነው በአንድ ላይ ወደ ቤተ መቅደሱመግባታቸውን ፈለገው፡፡

አፍሪካውያን፣ አውሮፓውያን

እንዲሁም

አይሁዳውያን ያልሆኑ ሌሎች ወገኖች ሁሉ

ወደዚህ መግባት አይፈቀድላቸውም ነበር

ይህንን ገጽ በትልቁ ፎቶ ኮፒ አድርገው፡፡ ከለር ቅባው፡፡አስተምረው፡፡ * Davis Dictionary of the

Bible, 1973, p. 812.

አይሁዶች ብቻ

Page 21: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

21

ሥራ 16 ላይ፣ ‹‹ወደ አውሮፓ (መቄዶንያ) ና›› ብሎ የሚጠራን ሰው እግዚአብሔርበራእይ አሳየው፡፡

ስለዚህ፣ ጳውሎስ እና ሲላስ ወደ አውሮፓ ሄዱ፡፡ በዚያን ጊዜ አውሮፓውያን‹‹ኢየሱስ›› የሚለውን ቃል ከቶ አልሰሙም ነበር፡፡

‹‹እኛ ለአምላካችን 'ለዲያና' ፍየሎችንመሥዋዕት አድርገን አቅርበናል፡፡ እንዲሁምዲያናን እናመልካታለን፡፡ እንዴት? በዲያናመቅደስ ካሉ ሴቶች ጋር ሩካቤንበመፈጸም፡፡ ይህን በማድረጋች

ንም ዲያና ትባርከናለች፡፡››

ጳውሎስ ጠንቋይ ከነበረች አውሮፓዊት ልጃገረድ ጋር ተገናኘ [ዘዳግ. 18፡11ን

ተመልከት]፡፡ እርሱም፣ ‹‹በኢየሱስ ስም ውጣ›› ብሎ አስወጣው

(የሐዋርያት ሥራ 16፡18)፡፡አጋንንት ከውስጥዋ ወጡ፡፡ ከዚያም የአጋንንት ኃይል

አልመጣባትም፡፡ አውሮፓውያን ተቈጡ፡፡ ‹‹እኛ ነጮችልንቀበላቸው የማንችላቸውን ባህሎች (ልማዶች) ጳውሎስና ሲላስ ያስተምራሉ አሉ፡፡እነርሱ እንግዳ (ጠይም ቀለም ያላቸው) ሰዎች ናቸው፡፡ እነርሱ እየረበሹን ነው፡፡ እኛነጮች የእነርሱን ኢየሱስ አንፈልግም፡፡›› (የሐዋርያት ሥራ 16፡20-21 እና 17፡18)

እነርሱም ጳውሎስንና ሲላስን በእስር ቤት ከተቱዋቸው፡፡ ከዚያም እግዚአብሔርእስር ቤቱን ሲያናወጠው፣ የእስር ቤቱ ጠባቂ፣ ‹‹እድን ዘንድ ምን ማድረግይገባኛል?›› ሲል ጠየቀ (የሐዋርያት ሥራ 16፡30)፡፡

እርሱ ያንን ለምን ጠየቀ? መልስ፡- እርሱ የሚከተለውን ያስብ ነበር፣

ሁለት ጠይም ቀለም ያላቸው ሰዎች እዚህ መጥተው፣ ‹‹ዲያናን እንድንተው››ነገሩን፡፡ እኛም እምቢ አልን፡፡ ‹‹ኢየሱስ ለእነዚያ ጠይም ሰዎች ነው፣ ለእኛ ለነጮችአይደለም›› ብለን አስበን ነበር፡፡

ከዚያም እስር ቤታችንን ኢየሱስ አናወጠው (አነቃነቀው)፡፡ ይህም ማለትኢየሱስ ‹የእነርሱ› ብቻ አይደለም፡፡ እዚህ አውሮፓ ያለነው ሰዎችም ጭምርኢየሱስ ያስፈልገናል፡፡ እንዲያድነኝ እፈልገዋለሁ፡፡

በዚያ ማለዳ በመልኩ ነጭ የነበረው የወኅኒ ጠባቂ ጠይም ቀለም ከነበራቸውከሁለቱ የወንጌል መልእክተኞች (ጳውሎስና ሲላስ) ጀርባ ላይ የነበረውን ደም

አፍሪካ

አውሮፓ

ኢየሩሳሌም እስያ

መጽሐፍ ቅዱስ እንዲጻፍ እግዚአብሔርከ40 በላይ የሆኑ ሰዎችን ተጠቅሟል፡፡አንዱም እንኳ አውሮፓዊ አልነበረም፤አፍሪካዊም አልነበረም፡፡፡፡ ሁሉም ከሞላጐደል በመካከል የሚኖሩ ጠይም ቀለምያላቸው ሰዎች ነበሩ፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ የተወለደው በመሀል ነው

Page 22: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

22

አጠበ፡፡ ከዚያም ቀለማቸው ጠይም የነበረውሚስዮናውያን በመልኩ ነጭ የነበረውንሰውዬን አጠመቁት፡፡

ክርስትና ወደ አውሮፓ የደረሰበት ቀን ያኔ ነበር፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ፡፡ ጳውሎስ ከሞተ በኋላ፣ ክርስቲያኖች በ እ ር ሱየተጻፉ መጻሕፍትን፣ በሙሴ፣ በዳንኤል፣በማቴዎስ...እንዲሁም በብዙ ሌሎች ሰዎች የተጻፉትንመጻሕፍት ሰበሰቡዋቸው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስንሙሉ ለማድረግም 66 መጻሕፍትን በአንድ ላይአቀነባበሩ፡፡ከሁሉም ቀለም የተሰባሰቡ ክርስቲያኖች መጽሐፍ ቅዱስን ሩቅ ስፍራ ወሰዱት

የኢየሩሳሌም ክርስቲያኖች ወደ ሕንድ ወሰዱት፡፡ [ገጽ 27ን ተመልከት]ኢትዮጵያውያን መጽሐፍ ቅዱስን

አፍሪካዊ ወደ ሆነ ቋንቋ፣ ወደ ግዕዝተረጐሙት [250 ዓ.ም]፡፡ ኢትዮጵያክርስቲያን ንጉሥ የነበራት የመጀመሪያዋ አገርሆነች፡፡ የኢትዮጵያ እና የሱዳን ክርስቲያኖችንመጽሐፍ ቅዱስን ወደ ሰሜን አፍሪካ ወሰዱት[400 ዓ.ም]፡፡ ሰሜን አፍሪካውያን መጽሐፍቅዱስን ወደ ፖርቹጋል ወሰዱት፡፡

ሰሜን አፍሪካውያን መጽሐፍ ቅዱስንወደ ደቡብ፣ ኬንያ፣ ናይጄሪያ፣ ኡጋንዳ፣ታንዛኒያ፣ ማላዊ፣ ዛምቢያ፣ ዚምባቡዌ፣ቦትስዋና፣ ሌሴቶ፣ ስዋዚላንድ፣ ደቡብአፍሪካ . . . ለምን እንዳልወሰዱትአናውቅም፡፡

ሰሜን አፍሪካውያን መጽሐፍ ቅዱስንወደ ደቡብ ስላልወሰዱት፣ ነጮች እስከደረሱበት እስከ 1500ዓ.ም ድረስ በመካከለኛውና በደቡብ አፍሪካያሉ ሕዝቦች መጽሐፍ ቅዱስን አልተቀበሉምነበር፡፡

ጋዛ

አውሮፓ

ኢየሩሳሌም

1. መጽሐፍ ቅዱስ ወደ አፍሪካ

1

የሐዋርያት ሥራ 8 (35 ዓ.ም)

2. መጽሐፍ ቅዱስ ወደ አውሮፓ

የሐዋርያት ሥራ 16 (50 ዓ.ም)

አውሮፓ

መቄዶንያ

ጠርሴስኢየሩሳሌም

ኢትዮጵያአፍሪካ

ኢትዮጵያአፍሪካ

Ò³

Page 23: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

23

ስለዚህ፣ ሰሜን አፍሪካ መጽሐፍ ቅዱስን ከጥቁር እጆች ተቀብላለች፡፡መካከለኛውና ደቡብ አፍሪካ መጽሐፍ ቅዱስን ከነጮች እጅ ተቀብለውታል፡፡

ዛሬ በመካከለኛውና በደቡብ አፍሪካ ያሉ አንዳንድ ሰዎች ‹‹መጽሐፍ ቅዱስ

የነጮች መጽሐፍ ነው›› ብለው ያስባሉ፡፡

ነገር ግን እውነታዎቹ፡-

እውነታ 1፡- ጠይም ቀለም ያላቸው እጆች መጽሐፍ ቅዱስን ጻፉ [በኢየሩሳሌምአቅራቢያ]፡፡

እውነታ 2፡- ጠይም ቀለም ያላቸው እጆች ወደ ጥቁር እጆች ወሰዱት [ወደ

ኢትዮጵያ፣ የሐዋርያት ሥራ 8]፡፡ጠይም ቀለም ያላቸው እጆች ወደ ነጭ እጆች ወሰዱት፡፡ [ወደ አውሮፓ፣

የሐዋርያት ሥራ 16]፡፡

እውነታ 3፡- ጥቁር እጆች ወደ ነጭ እጆች ወሰዱት [ወደ ፖርቹጋል፣ 400 ዓ.ም]፡፡

እውነታ 4፡- ነጭ እጆች ወደ መካከለኛው እና ደቡብ አፍሪካ ወሰዱት [1500ዓ.ም]፡፡

እውነታ 5፡- ዛሬ የትኛውም ቀለምያላቸው እጆች ሁሉንምቀለም ወደ ያዙ እጆችእየወሰዱት ናቸው፡፡ [ገጽ42]

ሂዱና...በየስፍራው መስክሩ (የሐዋርያት ሥራ 1፡8)ዛሬ ብዙ ሕዝቦች ወንጌል ያስፈልጋቸዋል፡፡እዚህ ሦስት ምሳሌዎች አሉ፡-

ስዊድን፡- በስዊድን 96% የሚሆኑ ሰዎች ወደ ቤተክርስቲያን አይሄዱም፡፡ ቤተሰቦች በፍቺ፣አደንዛዥ ዕፅ፣ ራስን በማጥፋት . . .ተበታትነዋል፡፡ ከብዙ አገሮች ክርስቲያኖችወደዚያ በመሄድ መመስከር ይኖርባቸዋል፡፡

የዲያና መቅደስ

ከመቅደሱ ሴቶች ጋር ሩካቤን መፈጸም

Page 24: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

24

ሊቢያ፡- 97% የሚሆኑ ሰዎች ሙስሊሞች ናቸው፡፡ ብዙዎቹመጽሐፍ ቅዱስን ከቶ አላዩትም፣ ወይም ኢየሱስ ስለ ኃጢአታችን መሞቱን

አልሰሙም፡፡በሊቢያ ለመመስከር አማኞችን ለመላክ እግዚአብሔር በኃይሉ ሊሞላን

ይችላል (ማቴዎስ 28፡10-20)፡፡ሞዛምቢክ፡- በተለይ በሰሜናዊ ሞዛምቢክና በማፑቶ መጥተው የሚያስተምሩ

አማኞችን ትፈልጋለች፡፡ በዛምቢያ፣ ማላዊ፣ ስዋዚላንድ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ዚምባቡዌ፣ ኮሪያ ያሉ አብያተ ክርስቲያናት አንዳንድ መልእክተኞችን ልከዋል፡፡ተጨማሪ ሰዎችን መላክ ያስፈልጋል፡፡

መላው መጽሐፍ ቅዱስበእግዚአብሔር እስትንፋስየተሰጠ ነው (2ኛ ጢሞ.

3፡16)፡፡

Page 25: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

25

ኢትዮጵያዊው

Page 26: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

26

ምዕራፍ 3

የሕዝቤን ልማዶች (ባህሎች) ሁሉ መተው ይኖርብኛልን?

ዛሬ በሚሊዮን የሚቈጠሩ ሕዝቦች ይህየተሳሳተ አሳብ አላቸው፡፡

‹‹ኢየሱስን ለመቀበል እያንዳንዱንየሕዝቤን ባህል (ልማድ) መጣልናእንደ ባዕድ ሰው መመላለስይኖርብኛል፡፡››የመጀመሪያዎቹ የወንጌል መልእክተኞች

[ፊልጶስና ጳውሎስ] ያንን ስሕተት ከቶአልፈጸሙትም፡፡ ጳውሎስ ለእያንዳንዱ ሰው፣

የሰውየው ቀለም ምንምየሚፈይደው ነገር የለም፡፡(የሐዋርያት ሥራ 10፡34ን

ተመልከት፡፡)

ስዊድን

ሊቢያ

ሞዛምቢክ

Page 27: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

27

‹‹በኢየሱስ እመን፣ ሌሎችን የባዕድ ባህሎች

(ልማዶች) መቀበል አያስፈልግህም›› ብሎ

ይናገር ነበር (የሐዋርያት ሥራ 15፡1-2)፡፡

ነገር ግን ከ1500 ዓመታት በኋላ፣የፖርቹጋል ሚስዮናውያን ወደ ኮንጎ ሄደውለንጉሡ፣ ‹ ‹አሮጌ መንገዳችሁንየሚያስታውሱዋችሁ ልማዶቻችሁን(ባህላችሁን) ሁሉ ጣል›› ብለውነግረውታል፡፡

ብዙም ሳይርቅ ኮንጎ ፖርቹጋልን መምሰልዋን ጀመረች... አልባሳትጊዜም ፖርቹጋላዊ ስም

ይሰጥ ጀመር፤ የፖርቹጋላውያን የዝማሬና የሰርግ አደራረግ ስፍራውንያዘ፡፡

በኋላም ቤልጅየም ኮንጎን በቅኝ ግዛት ያዘች፡፡ ቤልጄማውያንምየሕዝቡን ቋንቋና ባህል ወደ ቤልጅየም ቋንቋና ባህል ለወጡት፡፡

እንግሊዛውያንም ይህንኑ አደረጉ፡፡ ለእስያውያንና ለአፍሪካውያን፣‹‹ከበሮዎቻችሁን ጣሉ፡፡ ልክ እንደ ትክክለኞቹ ሰዎች [እንግሊዛውያን] ዘምሩ››አሏቸው፡፡

አዎን፣ ከ1500 ዓ.ም በኋላ የአውሮፓውያን ሕዝቦች ሁለት ነገሮችን፡- መጽሐፍቅዱስንና የአውሮፓውያንን ባህል ወደ መላው ዓለም ወሰዱ፡፡

ስለዚህ፡- ክርስትና አውሮፓዊ ሆኖ መታየት ጀመረ፡፡ነጮች ሚስዮናውያን ይህን ሊሉ ይገባቸውነበር፡ - ‹‹የአውሮፓውያን ባህል

አያስፈልጋችሁም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ ተቀበሉ፡፡ከኢየሩሳሌም የሆኑ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን ወደ እኛ አመጡ- አሁን እኛ ወደ እናንተ አመጣነው፡፡ የምትለብሱበትንናየምትዘምሩበትን መንገድ መለወጥአያስፈልጋችሁም፡፡ ነገር ግ ን በ ም ድ ርላይ ያለ እያንዳንዱ ሰ ው የ ል ብ

1500 ዓ.ም

መጽሐፍ ቅዱስ የበቀለው በዓለም ዕምብርት ላይ ነበር . . . ከዚያም ወደተለያዩ ስፍራዎች

ተሰራጨ፡፡

እስያ

እዚህ በሁለተኝነት ደረሰ የሐዋ. 16መቄዶንያ

አውሮፓ

50ዓ.ም

ሕንድ

100 ዓ.ም35ዓ.

400ዓ.ም

አፍሪካኢትዮጵያ

በመጀመሪያእዚህደረሰ

የሐዋ. 8

ወደ አሜሪካ

1500 ዓ.ም

ፖርቹጋል

1500 ዓ.ም

1500

ዓ.ም

(1) እና (2) ትላልቆቹቀስቶች በሐዋርያት

ሥራ ክርስትና ወዴትእንደ ሄደ ያሳያሉ፡፡ትናንሾቹ ቀስቶች

መላው መጽሐፍ ቅዱስከተጻፈ በኋላ ወዴትእንደ ሄደ ያሳያሉ፡፡

ማስታወሻ፡- 35 ዓ.ም፣ 50 ዓ.ም፣ 400 ዓ.ም፣ 1500 ዓ.ም፡፡ እነዚያ ቁጥሮችመጽሐፍ ቅዱስ በመጀመሪያ፣ በሁለተኛ፣ በሦስተኛና በአራተኛነት የት እንደ ሄደ ይነግሩናል፡፡

1500 ዓ.ም

Page 28: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

28

መለወጥ ያስፈልገዋል፡፡ ሁላችንም ኢየሱስን እንፈልገዋለን፡፡ ደግሞም እርሱበሁላችንም ላይ ይፈርዳል›› (የሐዋርያት ሥራ 17፡30-31)፡፡

አንዳንድ ሰዎች እንዲህ ያስባሉ፡- ‹‹የአውሮፓውያን ባህል (ልማድ)

ክርስቲያናዊ ነው፡፡›› ነገር ግን እውነቱ፡- ብዙዎቹ የአውሮፓውያን ባህሎች

(ልማዶች) ከተሳሳተ እምነቶች የመጡ ናቸው፡፡ እዚህ ላይ አንድ ምሳሌ ቀርቧል፡-

የጋብቻ ቀለበቶች፡- ከ700 ዓመታት በፊት አውሮፓውያን ትልቁ የደም ሥር(ደም መልስ) ከልብ ወደ ሦስተኛው ጣት ይሄዳል ብለው ያስቡ ነበር፡፡ ስለዚህምበዚያ ጣት ላይ ‹‹የጋብቻ ቀለበት›› ማድረግ ጀመሩ፡፡

አሁን ይህ በጋብቻ ውስጥ ያለ ልማድ ከአውሮፓውያን ወደ ብዙ ሕዝቦችተዛምቶአል፡፡

እኛ ለእያንዳንዱ ሰው፣ ‹‹መጽሐፍ ቅዱስ፣ ‹የጋብቻ ቀለበትን አድርጉ› ከቶእንደማይል፣ ስለዚህም፣ እነዚህን ቀለበቶች ላለማድረግ ከወሰንህ፣ መልካም ነው፡፡ወይም ልታደርጋቸው ከመረጥህ፣ ያም እንደዚሁ መልካም ነገር ነው . . . ነገር ግንልትገነዘብ የሚገባህ፡- እነዚያ ቀለበቶች የአውሮፓውያን ባህል ብቻ መሆናቸውንነው፡፡ እኛ አማኞች ባዕድ ባህልን ለመተው ነፃነት አለን›› የሚለውን መንገርይኖርብናል፡፡

’@ T”U c¨< eK ¡`e„e ÁMcTv†¨< eõ^­‹

LÃ KSeu¡ ¾T>k×ÖM õLÔƒ ›K˜::

(aT@ 15:20)::

Page 29: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

29

የሕይወት እንጀራ በፕላስቲክ መያዣውስጥክርስቶስ፣ ‹‹የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ››ሲል አውጇል (ዮሐንስ 6፡48)፡፡

በአውሮፓ ያሉ ሰዎች ‹ኅብስቱን› ሲቀበሉ፣የራሳቸውን ባህል (ልማድ) አከሉበት፡፡ይህም ልክ እንደሚከተለው ነው፡-

"ኅብስቱን"፣ ‹‹በፕላስቲክ›› ውስጥ አስቀመጡት [የአውሮፓውያን ባህል]፡፡ከዚያም አውሮፓውያን ሚሲዮናውያንኅብስቱን [ከፕላስቲኩ ጋር] ወደ አፍሪካ፣

እስያ . . . ወደ ሁሉም ስፍራ፣ ወሰዱት፡፡

አሁን በመላው ዓለም ያሉ በሚሊዮንየሚቈጠሩ ሰዎች እንዲህ እያሉ ነው፡-

‹‹እኛ ከኅብስቱ ጋር ፕላስቲኩንበላነው፡፡ ፕላስቲኩ እንድንታመምአደረገን፡፡ እነዚያን ባዕድ የሆኑአደራረጎች አንፈልጋቸውም፡፡ እኛ

መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈው በዓለም ዕምብርትላይ ነበር፡፡

በሐዋርያት ሥራ 8 ላይ ወደ አፍሪካ ሄደ፡፡

በሐዋርያት ሥራ 16 ላይ ወደ አውሮፓሄደ፡፡

ዛሬ ክርስቲያኖች ከአፍሪካ፣ አውሮፓ፣እስያ . . . በአንድ ላይ በመሥራት

ወንጌልን በየስፍራው እየወሰዱት ነው፡፡

እግዚአብሔር አብልጦ የሚያየው ጎሳየለም፡፡

ከሁሉም ወገን የሆኑ ሕዝቦችን ይቀበላል(የሐዋ 10፡34-35)፡፡

ክርስቶ

ስ ሰላ

ማች

ን ነው

፡፡ እ

ርሱ አ

ንድአድ

ርጎናል

፡፡ እ

ርሱ በ

መካከ

ላችን

ያለው

ን ግድ

ግዳአፍ

ርሶታ

ል፡፡

በመ

ስቀሉ

ወደ

እግዚ

አብሔ

ርአመ

ጣን፣

ደግሞ

ም እ

ርስ በ

ርስ አ

ቀራረበ

ን፡፡

ስለዚ

ህ፣ በ

መካከ

ላችን

ያለው

ግድ

ግዳ በ

መስቀ

ሉላይ

ተወ

ግዷል

(ኤፌ

. 2፡14-

16)፡

‹‹መጽሐፍ ቅዱስ የነጮችመጽሐፍ ነው፡፡››

አንዳንድ ሰዎች እንዲህይላሉ፡-

እውነቱ ግን እንዲህነው፡-

Page 30: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

30

ኅብስቱን ብቻ ነው የምንፈልገው፡፡ እኛ ኢየሱስን/መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ ነውየምንፈልገው፡፡ ፕላስቲኩን እናስወግድና ኅብስቱን በደስታ እናጣጥመው፡፡››አዎን፣ ኅብስቱ አልተለወጠም፡፡ ኢየሱስ

አሁንም ያው ኢየሱስ ነው፡፡ እንዲሁም መጽሐፍቅዱስ የማይለወጥ ነው፡፡

ማንም ኢየሱስን ወደ አውሮፓዊነት ሊለውጠው አይችልም፡፡ አውሮፓዊ ያልሆነኢየሱስ አውሮፓዊ ያልሆኑ ልማዶችን . . .እግር ማጠብን፣ በምንጣፍ ላይ ተቀምጦመመገብን፣ ወዘተ . . . የተከተለ መሆኑን

መጽሐፍ ቅዱስ አሁንም ይናገራል (ሉቃስ7፡36-46)፡፡

ኢየሱስ፣ ‹‹እንግዲህ ሂዱና፣ያዘዝኋችሁን ነገር ሁሉ ለአሕዛብ ሁሉአስተምሩ›› አለ፡፡

እርሱ፣ ‹‹ሂዱና አሕዛብ ሁሉ የእናንተን

ባህል እንዲቀዱ አድርጉ›› ከቶ አላለም፡፡

ኢየሱስ በኅብስቱ ላይ ፕላስቲክእንዲታከልበት ከቶ አልፈለገም (ማርቆስ 7፡8)፡፡ ስለዚህ፣ እኛ መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ ለመውሰድ፣ እንዲሁም ባዕድ የሆነ ሙዚቃናአለባበስ ደግሞም እንዲህ ያሉ ‹‹ፕላስቲኮችን›› ለማስወገድ ነ ፃነን፡፡

ኢየሩሳሌም እስያ

አፍሪካ

አውሮፓ

ፊ ል ጶ ስ

አ ፍ ሪ ካ

እንደ ፊልጶስና ጳውሎስ ያሉ የወንጌል መልእክተኞች፣‹‹ኢየሱስን ስበኩ፣ ባዕድ የሆኑ ባህሎችን አትስበኩ››ይላሉ፡፡

አውሮፓ

እስያ

በኋላም አንዳንድ የወንጌል መልእክተኞች፣ ‹‹ኢየሱስን

እንዲሁም የአውሮፓ ባህሎችን›› ወደ ሌሎች ሕዝቦች

ውሰዱ አሉ፡፡

ጳውሎስ

Page 31: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

31

መልካም ባህሎችን (ልማዶችን) ያዙ፡፡ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ካልሆኑ ልማዶችራቁ፡፡

ሕዝባችሁ አንዳንድ መልካም ልማዶችና አንዳንድ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑባህሎች አሉት፡፡ [አዎን፣ እያንዳንዱ ሕዝብ አንዳንድ መልካም ባህሎች (ልማዶች) እናአንዳንድ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ልማዶች አሉት፡፡]ሀ) መልካሙን ልማዶቻችሁን አትጣሉ፡፡ ለጥሩ ልማዶች ሁለት ምሳሌዎችን መውሰድ

ይቻላል፡፡ እነዚህም፣ ‹‹የቤተሰብ ፍቅር፣›› እና ‹‹በዕድሜ አነስ ያሉ ሰዎች

ሽማግሌዎችን የሚያከብሩበት›› ሁኔታ ናቸው (ዘሌዋ. 19፡32)፡፡

ለ) መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ልማዶችንመጣል (2ኛ ጢሞ. 3፡16)፡፡መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ልማዶችምሳሌዎች፡-

እነሆ፡

መፋታት . . . እንደገና ማግባት . . . መፋታት . . . (ማቴ. 19፡3-9

ተመልከት፡፡)

ከሙታን እርዳታን ለማግኘት መፈለግ፡፡ (ኢሳ. 8፡19-20 ተመልከት፡፡)

ባልን አለማክበር፡፡ (ኤፌ. 5፡21-25 ተመልከት፡፡)

ሚስትህን እንደ ገረድ መቊጠር፡፡ (1ኛ ጴጥ. 3፡7 ተመልከት፡፡)

ወንዶች፣ ለልጆቻቸው በቂ ፍቅር አለማሳየት፡፡ (ሚል. 4፡6 ተመልከት፡፡)

Page 32: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

32

ይህ የታሪክ አሳዛኝ እውነታ ነው፡- ለመቶ ዓመታት ብዙ ነጮች ሕዝቦች የአፍሪካንሕዝብ በጭቈና ገዝተዋል፡፡

ዛሬ፣ ብዙ ክርስቲያኖች ይህን ሲናዘዙ ማየት የሚያስደስት ነው፡፡ ‹‹በቀለም ላይ

የተሳሳተ አስተሳሰብ ነበረኝ፡፡ አዝናለሁ፡፡ ደግሞም ለመለወጥ ቈርጫለሁ፡፡››

ይሁንና፣ ዛሬም እንኳ አንዳንድ ‘ክርስቲያኖች’ የተሳሳተ አስተሳሰብን የያዙበት

ሁኔታ አለ፡፡ ያ ደግሞ ሙሉ በሙሉ የእግዚአብሔርን ቃል የሚቃረን ነው (ኤፌ. 2፡14

-16)፡፡

አሁንም እየተጠየቀ ያለው ጥያቄ፡- ከክርስቶስ ሊመልሱን አንዳንዶች‘ክርስቲያኖች’ እያካሄዱት ያለውን ዘረኝነት ልንፈቅደው

ይገባልን? የሚል ነው፡፡በፍጹም፡፡ ዶ/ር ቢ. ካቶ ክርስቶስ ከየትኛውም ክፍለ ዓለም ጋር እንደ ሆነ

ሁሉ እንዲሁ በአፍሪካም ከእኛ ጋር ነው የሚለውን ሊያስታውሱን ይወድዳሉ፡፡እንዲህም ይላሉ፡-

1) ክርስትና ለምንድን ነው የነጮች ሃይማኖት መስሎ የሚታየው? [አንዳንድ ሰዎችክርስትናን ከአውሮፓውያን ልማዶች (ባህል) ጋር በመቀላቀላቸው ምክንያትነው፡፡]

ለሰዎች፣ ‹‹ባዕድ ልማዶችን ተከተሉ›› ብለህ ከቶ አትናገር፡፡ በዚህ

ፈንታ ለእያንዳንዱ ሰው፣ ‹‹መጽሐፍ ቅዱስን ታዘዝ›› ብለህ ተናገር፡፡

ኢየሱስ ለሰዎች፣ ‹‹እናንተ ተሳስታችኋል፡፡ የእግዚአብሔርን ትእዛዛትአትከተሉም፡፡

በዚህ ፈንታ የሰውን ሥርዓት ተከትላችኋል›› ብሎ ተናግሮአል (ማርቆስ7፡8-9)፡፡

Page 33: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

33

2) በባህላችን ውስጥ ያሉ አንዳንድ መልካም ልማዶችን ጥቀስ፡፡ [1ኛ ተሰ. 5፡21][ምሳሌ፣ እኛ አዛውንት የሆኑ ሰዎችን መርዳት እንወድዳለን፡፡ 1ኛ ጢሞ. 5፡1-8

እና 16]እነዚያን የሕዝባችንን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ልማዶች እንከተል፡፡

3) በባህላችን ውስጥ ያሉ አንዳንድ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ልማዶችን ጥቀስ፡፡4) መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ አንዳንድ የውጭ አገር ልማዶችን ጥቀስ፡፡

ምሳሌ፡- ‹‹ሴቶች፣ ወንዶችን የሚፈትኑ ስሜት - ቀስቃሽ ልብሶችን

ይለብሳሉ›› (1ኛ ጢሞ. 2፡9፤ ማቴ. 5፡28)፡፡

‹‹አትጋቡ፤ ዝም ብላችሁ አብራችሁ ኑሩ›› (ዕብ. 13፡4)፡፡

‹‹ገንዘብ ለማግኘት፣ መንግሥትን አታልሉ፣ ሰዎችን አታልሉ፣ ጉቦ

ተቀበሉ›› (2ኛ ዜና 19፡7)፡፡

‹‹ግብዣ፣ መስከር›› (ኢሳ. 5፡11-12)፡፡

‹‹በምድር ላይ ሀብትን ለመሰብሰብ ጊዜህን አጥፋ›› (ማቴ. 6፡19)፡፡

ሌሎች ብዙ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ልማዶችን ልታስብ ትችላለህ፡፡

5) ኢየሱስ፣ ‹‹ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ . . . ደቀ መዛሙርቴ አድርጓቸው›› (ማቴ.

28፡19)፡፡ ይህንን ትእዛዝ በመታዘዝ ረገድ እዚህ [በሕዝባችን መካከል] ያለን

ክርስቲያኖች እንዴት የተሻለ መሥራት እንችላለን? [ተወያዩበት . . . ከዚያም

የሚቀጥለውን ምዕራፍ ተመልከቱ፡፡]

በባህልህ ውስጥ ያለውን መልካም ነገር ተከተል፡፡ደግሞም መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑትን የባዕዳንም ሆነ የአገር በቀልልማዶችን ጣል፡፡

Page 34: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

34

ምዕራፍ 4

የተማሩ . . . ቀናዒ የሆኑ. . . ያልተደረሱ ሰዎች

ዛሬ በምድር ላይ በእውነቱ ሦስት ዓለማት አሉ፡-‹‹የተማሩ ሰዎች ዓለም፣››‹‹ቀናዒ የሆኑ ሰዎች ዓለም፣››እና ‹‹ያልተደረሱ ሰዎች ዓለም›› ናቸው፡፡

1) የተማሩ ሰዎች ዓለምእኔ [ኤላይጃ] አውሮፓ፣ አሜሪካ፣ አውስትራሊያ... በነበርሁበት ጊዜ፣ በተማሩ

ሰዎች ዓለም እንደ ነበርሁ ይሰማኝ ነበር፡፡በዚያ ያሉ ክርስቲያኖች በመጽሐፍ ቅዱስ እውቀት የበረቱ ናቸው፡፡

ችግሩ፡- ብዙዎቹ ገንዘብን...ምቾትን...ደስታን ለማግኘት እጅግ የሚለፉናቸው፡፡ ስለዚህ ስለ ራሳቸውም ሆነ ስለ ሌሎች ሰዎች ነፍስ እምብዛም ደንታአልነበራቸውም፡፡

በአሜሪካ፣ በአውስትራሊያና በአውሮፓ እየሰበክሁ ሳለሁ፣ አንዳንድ ሰዎችከከተማ ከተማ እኔን ይከተሉ ነበር፡፡ እነርሱ፣ ‹‹አንተ አንድ ነገር አለህ፡፡ እግዚአብሔር

ለአንተ እውነት ሆኖልሃል! እኛም ያንን እንፈልገዋለን!›› ብለው ነገሩኝ፡፡

ኅብስት

ኢየሱስ/መጽሐፍ ቅዱስ

ፕላስቲክ

አውሮፓ ኅብስቱን በፕላስቲክውስጥ አደረገው፡፡

ከ1500 ዓ.ም በኋላ፣ አውሮፓ ወደአፍሪካ፣ እስያ፣ . . . ኅብስት + ፕላስቲክ›› ላከች፡፡

አውሮፓ ፕላስቲክአከለችበት

የአውሮፓውያን ባህል

ኢየሱስም እንዲህ አለ፣ ‹‹እናንተስ ስለወጋችሁ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ስለ ምንትተላለፋላችሁ?››

(ማቴ. 15፡3)

Page 35: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

35

እኔም፣ በኢየሱስ ያለውን እውነተኛ ሕይወት ለማግኘት፣ እናንተ መጽሐፍቅዱስን መታዘዝ ይኖርባችኋል፣ እንዲሁም ለመመስከር መንፈስ ቅዱስ ኃይሉንይሙላችሁ!›› አልኋቸው፡፡

2) ቀናዒ የሆኑ ሰዎች ዓለም

በአፍሪካና በእስያ፣ ክርስቲያኖች በቀናዒነት ረገድ ጠንካሮች ናቸው፡፡ ብዙዎችበድፍረት ይመሰክራሉ፡፡ በሚዘምሩበት ጊዜ ሕያውነት (የተነቃቃ ነገር) አለ፡፡ሕይወት አላቸው!

ድክመታቸው፡- ያላቸው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርት ትንሽ ነው፡፡ቀናዒ በሆኑ ሰዎች ዓለም ውስጥ ምእመናን ስሜታቸው ከፍተኛ መጠን ላይ

እስኪደርስ ድረስ አዝማቾችን ይዘምራሉ...ከዚያም ደግሞ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርትን

አይፈልጉም...ለምን?...ትምህርት ደስታቸውን ያበላሽባቸው ይሆናል፡፡

ውጤቱም፡- በቀናዒ ሰዎች ዓለም ያሉ ብዙዎች ለኢየሱስ አስደናቂ ፍቅርይኖራቸዋል፣ ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱሳዊ መርሖዎች ላይ መሠረታቸው ደካማ ነው፡፡

በዚህ በቀናዒያን ሰዎች ዓለም ብዙ አማኞችለአንድ ሰው ክርስቶስን የሚቀበልበትን እናበክርስትና ሕይወት የሚያድግበትን መንገድ

ለማሳየት መጽሐፍ ቅዱሳቸውን እንዴት መጠቀም እንዳለባቸው አያውቁም፡፡ [ገጽ

78-87 ተመልከቱ፡፡]በአፍሪካ እና እስያ - በቤተ ክርስቲያን፣ በቤቶች፣ በጋብቻ ሥነ ሥርዓት፣ በቀብር

ሥነ ሥርዓት . . . መጽሐፍ ቅዱስን በማስተማር ብዙ ጊዜን መውሰድ ይገባናል፡፡

ኢየሱስ፣ ‹‹እንግዲህ ሂዱና ደቀ መዛሙርቴ አድርጉ . . . አስተምሩ››ብሎአል (ማቴ. 28፡19-20)፡፡

በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ሐዋርያት በማስተማር ላይ ብዙ ጊዜን ያሳልፉ ነበር(የሐዋርያት ሥራ 2፡42፤ 5፡21፤ 5፡42፤ 15፡35፤ 18፡11፤ 28፡31)፡፡

ደስ የሚያሰኙ አዝማቾች መልካም ናቸው [መዝሙር 95፡1]፣ ነገር ግን እኛየመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶችም ያስፈልጉናል፡፡

1) ክርስቶስን ተቀበል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስህን አንብብ፡፡ ከዚያም መጽሐፍቅዱሳዊ ያልሆኑ የሕዝብህን ልማዶች አስወግድ (ገላ. 5፡19-21)፡፡

2) ባዕድ ልማዶችን ለመቀበል አትገደድም (ቈላ. 2፡8፣ 22)፡፡

Page 36: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

36

አንዳንድ አማኞች በደንብሊያስተምሩ ይችላሉ፡፡ የማስተማርስጦታ አላቸው [ኤፌ. 4፡11]፡፡

ስለዚህ፣ በአብያተ ክርስቲያናችንየማስተማር ስጦታ ያላቸውን ሰዎችእንፈልግ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስንበትክክል ወደሚያስተምር የመጽሐፍቅዱስ (ት/ቤት) ኮሌጅእንላካቸው፡፡ ከዚያም በቤተክርስቲያን እና በቤት ለቤትፕሮግራሞች እንዲያስተምሩ ዕድሉን

እንስጣቸው፡፡ የዮሐንስ ወንጌል ን፣ ፊልጵስዩስን፣ ጢሞቴዎስን እና የመሳሰሉትንመልእክታት ክፍል በክፍል ወይም ምዕራፍ በምዕራፍ አድርገው ሊያስተምሩንይገባል፡፡ (ኤፌ. 4፡12-15 ተመልከት፡፡)

የቀናዒ ሰዎች ዓለም የተማሩ ሰዎች ዓለምን ትሻለችእኛ በቀናዒ ሰዎች ዓለም ያለን፣ ከተማሩ ሰዎች ዓለም መጽሐፍ ቅዱስን

የሚያስተምሩ ሰዎችን እንዲመጡና በእስያና በአፍሪካ ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስአስተማሪዎችን ለማሠልጠን በሚደረገው ሥራ እንዲረዱን እየጠየቅን ነው፡፡

ነገር ግን እነዚያ የሚመጡ ሰዎች እዚህ ጠቃሚና ተግባራዊ የሚሆን ሥነመለኮት ማስተማር ይኖርባቸዋል፡፡ ይህም ልክ በናይሮቢ ያሉ የሥነ መለኮት ምሁራንእንዳሉት ነው፡-

ክርስትና እንግሊዝ ወይም አሜሪካ ከመድረሱ በፊት በዚህ በአፍሪካ ውስጥጠንካራ መሠረት ይዞ ነበር፡፡ ክርስትና የነጮች ሰዎች ሃይማኖት ነው ብሎ ማለትአመክንዮታዊ አይደለም፡፡ ኢየሱስን ላለመቀበል የሚፈልግ የትኛውም ሰው፣‹‹ኢየሱስ የነጮች ነው›› የሚለውን ምክንያት (ሰበብ) መጠቀም አይችልም፡፡

ተወያዩበት

Page 37: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

37

‹‹የምዕራባውያን ሥነ መለኮት በአብዛኛው ለዘብተኛ (ሊብራሊዝም)የተባለውን የክርስትና ክፍል ለመቃወም የሚዘጋጅ ነው፡፡ በዚህምምክንያት፣ በአፍሪካም ሆነ በእስያ ያልተጠየቁ ጥያቄዎችን ወደ መመለሱያዘነበለ ነው፡፡ በዚህ የዓለም ክፍል የሚጠየቀውን ጥያቄ መመለስ ይችልዘንድ ሥነ መለኮትን ካለንበት ተጨባጭ ሁኔታ ጋር የተገናዘበ ማድረግይኖርብናል፡፡›› [ከማስዋንጋኒ፣ ኤላይጃ፣ 1994፣ ሆፕ ፎር ዘ ሴቭድዋይፍ ኦፍ አን አንሴቭድ ሀዝባንድ ኤንድ ዘ ሴቭድ ሀዝባንድ ኦፍ አንአንሴቭድ ዋይፍ፣ ታንዛኒያ፣ ኢኮን፣ ገጽ 3፡፡]

የተማሩት ሰዎች ዓለም የቀናዒ ሰዎች ዓለም ያሻዋልእኛ የእነርሱን ርዳታ እንፈልጋለን፤ እነርሱም የእኛን ርዳታ ይፈልጉታል፡፡ለብዙ ዓመታት፣ እኛ በቀናዒ ሰዎች ዓለም ያለን፡- የምንሰጠው ነገር የለንም

ብለን አስበናል፡፡ዛሬ ይህን ተገንዝበናል፡- በአውሮፓ፣ በአሜሪካ እና በአውስትራሊያ ያሉ

ወንድሞቻችን የእኛ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል፡፡ የጠፉ ነፍሶችን ወደ ኢየሱስ ለማምጣትያለን ደስታ እና ቀናዒነታችንን ይፈልጉታል፡፡

ኤኢ በአፍሪካ እንዲህ አለ፡-

ያም አሁን እየሆነ ነው! ከቀናዒ ሰዎች ዓለም የሆኑ ወገኖች ወደ ተማሩ ሰዎችዓለም በመሄድ ላይ ናቸው፡፡

በጋና ያሉ አብያተ ክርስቲያን ወደ እንግሊዝ የወንጌል መልእክተኞችን(ሚስዮናውያንን) ልከዋል፡፡

ዛየር የወንጌል መልእክተኞችን ወደ ፈረንሳይ እየላከች ነው፡፡ናይጄሪያ እና ኮሪያ መልእክተኞችን ወደ አሜሪካ እየላኩ ነው፡፡

Page 38: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

38

ብራዚል መልእክተኞችን ወደ ፖርቹጋል እየላከች ነው፡፡

ይህ የሚስዮናውያን ልውውጥ እኛን ሁላችንንም ጠንካራ ጎኖቻችንንእንድንካፈል ይረዳናል፡፡

3) ያልተደረሱ ሰዎች ዓለምበቀናዒ ሰዎች ዓለም እና በተማሩ ሰዎች ዓለም ያሉ አማኞች ሊገነዘቡት

የሚገባው ነገር፡- ያልተደረሱ ሰዎች ያሉበት ዓለም እንዳለ ነው፡፡ያልተደረሱ ሰዎች ዓለም ስለ ኢየሱስ ትንሽም ሆነ ምንም ያልሰሙ በሚሊዮን

የሚቈጠሩ ሰዎች አሉ፡፡ ሃይማኖታቸው [እስልምና፣ ሂንዱይዝም፣ ወይም

ቡድሒዝም፣ ወይም...] ኢየሱስ ስለ ኃጢአታችን ሞተ ብሎ አያስተምርም፡፡

በተጨማሪ ገጽ 123 ን ይመልከቱ

በወንጌል ያልተደረሱ ሰዎች ባሉበት ዓለም አንዳንድ አገሮች በመላውግዛታቸው ከ40 የሚያንሱ ክርስቲያኖችን ይዘው ይገኛሉ፡፡

እንደ ቱኒዚያ፣ ሳውዲ ዐረቢያ፣ የመን፣ ወዘተ . . . ባሉ አገሮች፣መንግሥት ዜጎቹ ቤተ ክርስቲያን እንዲሄዱ አይፈልግም፡፡ ስለዚህ አብያተ

Page 39: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

39

ክርስቲያን የሚያገለግሉት የውጭ አገር ሰዎችን ብቻ ነው፣ አገልግሎቱምየሚካሄደው በእንግሊዘኛ ቋንቋ ብቻ ነው፡፡

ውጤቱም፡-በወንጌል ባልተደረሱ ሰዎች ዓለም የሚገኙ በሚሊዮን የሚቈጠሩ ሰዎች

ቋንቋቸውን የምትናገር ቤተ ክርስቲያን ከቶ አይተው አያውቁም፡፡ መጽሐፍቅዱስን ከቶ አይተው አያውቁም፡፡ በኢየሱስ ከቶ አምነው አያውቁም . . .

ለምን?ስለ እርሱ ማንም አልነገራቸውምና፡፡

ይህም ሊያስለቅሰን ይገባል፡፡እንድንጸልይም ሊያደርገን ይገባል!ተግባራዊ እርምጃም እንድንወስድ ሊያደርገን ይገባል!

አዎን፣ አብያተ ክርስቲያናችንሰባኪዎችን ካልላኩ በቀር፣ ሰዎች ሊሰሙአይችሉም፡፡

ከሁሉም ጎሳዎች (ሕዝቦች)ሰባኪዎችን መላክ ይኖርብናል፡፡

ባለፉት ጊዜያት አንዳንድ ምዕራባውያን የወንጌል መልእክተኞች(ሚሲዮናውያን) ጥቁሮችን እንደ የወንጌል መልእክተኛ (ሚስዮናውያን)አይቀበሉዋቸውም ነበር፡፡ እነርሱ የነጮችን ቡድን ብቻ ነበር የሚልኩት፡፡

ያ በጣም ስሕተት ነበር፡፡

ክርስቶስ ከሁሉም ቀለም አማኞችን የወንጌልመልእክተኞች እንዲሆኑ ጠርቷቸዋል፡፡

ሕዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሣጠፍቶአልና(ሆሴዕ 4፡6)፡፡

Page 40: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

40

ዛሬ አውሮፓውያንን፣ አሜሪካውያን ን፣እስያውያንን፣ አፍሪካውያንን . . . በአንድ ላይወንጌል ወዳልደረሳቸው ሰዎች ዓለም ሲሄዱ ስናይእንደሰታለን፡፡

ይህንን በብዛት እንሻዋለን፡፡ከዚህ በበለጠ እንፈልገዋለን!ልክ ዶ/ር ቲ. አዲየሞ እንዳሉት፡-

‹‹እኛ (ከሁሉም ጎሳዎች የመጣን አማኞች) መላው ምድሪቱ መልካሙን የምሥራችእስክትሰማ ድረስ፣ ጨለማው እስኪገፈፍ ድረስ፣ እንዲሁም ክርስቶስ የነገሥታት

ንጉሥ ሆኖ እስኪገለጥ ድረስ፣ ልናርፍ አይገባንም!››

1) ቤተ ክርስቲያናችን በቀናዒነት ደካማ ናትን? . . . ወይም በማስተማር ደካማ

ናትን? እንዴት በጥንካሬ እያደግን መሄድ እንችላለን? [ገጽ 38-42 ተመልከት፡፡]2) ቤተ ክርስቲያናችን በወንጌል ወዳልተደረሱ ሰዎች ዓለም ወንጌልን እንዴት መውሰድ

ትችላለች? [ይህን በቤተ ክርስቲያናችሁ እና በቤታችሁ ተወያዩበት፡፡ ከዚያም

ቀጣዩን ምዕራፍ አንብቡ፡፡]

በምትሰብክበት ጊዜ፣ እያንዳንዱ ሊሰማው ይችል ዘንድ መጽሐፍ ቅዱስንጮክ ብለህ አንብብ፡፡ ከዚያም መጽሐፍ ቅዱስን ግልጽ በሆነ መንገድ

አስተምር፡፡(1ኛ ጢሞ 4፡13 ተመልከት፡፡)

ተጠንቀቁ፡፡ አንዳንድ የቤተ ክርስቲያንአባላት ከመንፈስ ቅዱስ ሳይሆን፣ ነገር ግንከርኩሳን መናፍስት የሆነ ቀናዒነትሊኖራቸው ይችላል፡፡

የእኛ የአፍሪካውያን ልማድ እንዲህየሚል ነው፡- የ‹መንፈስ› ኃይል ሲሰማህ፣ሰውነትህ ይንቀጥቀጥና ውደቅ፡፡

የትኛው ኃይል ከመንፈስ ቅዱስ፣እንዲሁም የትኛው ኃይል ከአጋንንት እንደሆነ ለማወቅ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርትያስፈልገናል (ማቴ. 7፡15-20)፡፡

Page 41: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

41

ምዕራፍ 5

ኢየሱስ፣ ‹‹ . . . ሂዱ ... እኔ ከእናንተ ጋር ነኝ›› አለ፡፡

‹‹እንግዲህ ሂዱና፣ አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስምእያጠመቃችኋቸው፣ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ

መዛሙርት አድርጓቸው፡፡ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋርነኝ›› (ማቴ. 28፡18-20)፡፡

‹‹ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኃይልን ትቀበላላችሁ፡፡በኢየሩሳሌም፣ በይሁዳም ሁሉ በሰማርያም እስከ ምድር ዳርም ድረስ ምስክሮቼ

ትሆናላችሁ አለ›› (የሐዋ. 1፡8)፡፡

‹‹እናንተ፡- ገና አራት ወር ቀርቶአል መከርም ይመጣል ትሉ የለምን? እነሆ እኔእላችኋለሁ፣ ዓይናችሁን አንሡ እነሆ አዝመራውም አሁን እንደ ነጣ እርሻውን

ተመልከቱ››(ዮሐ. 4፡35)፡፡

‹‹በዚያን ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን፡- መከሩስ ብዙ ነው፣ ሠራተኞች ግን ጥቂቶች ናቸው፤

የመከሩን ጌታ ወደ መከሩ ሠራተኞችን እንዲልክ ለምኑ አላቸው›› (ማቴ. 9፡37-38)፡፡

Page 42: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

42

‹‹ብልና ዝገት በሚያጠፉት፣ ሌቦችም ቈፍረው በሚሠርቁት ዘንድ ለእናንተ በምድር

ላይ መዝገብ አትሰብስቡ›› (ማቴ. 6፡19)፡፡

‹‹በስሙም ንስሐና የኃጢአት ስርየት ከኢየሩሳሌም ጀምሮ በአሕዛብ ሁሉ

ይሰበካል›› (ሉቃስ 24፡47)፡፡

ኢየሱስ እነዚህን ቃሎች ከ2000 ዓመታት በፊት ተናገራቸው፡፡ ከዚያንጊዜ ጀምሮ ባሉት 2000 ዓመታት፣ ክርስቲያኖች ለብዙ ሕዝቦች ወንጌልንአድርሰዋል፣ ነገር ግን ለሁሉም አላደረሱም፡፡

ኢየሱስ እንደሚያድን ያልሰሙ ሕዝቦች ያሉባቸው አገሮች ዛሬም እንኳአሉ፡፡ ገጽ 48-55 ተመልከቱ፡፡

‹‹ከ300 ዓመታት በላይ አውሮፓ በአፍሪካ ውስጥ ታላቅ የሚሲዮናዊነትን(የወንጌል መልእክተኝነትን) ሥራ አከናወነች፡፡ አሁን እኛ አፍሪካውያንክርስቲያኖች በአውሮፓ ላሉት ወንድሞቻችን በትሕትና ወንጌልንና ‘በኢየሱስ

ያለውን ደስታ’ ይዘንላቸው ልንሄድ እንሻለን፡፡ አዎን፣ በአውሮፓም ሆነ

ከዚያም በስቲያ ለመስበክ ለአፍሪካውያን ሰባኪዎች ጊዜው አሁን ነው!››

Page 43: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

43

በቅርቡ 12 የምንሆን መጋቢዎች ማቴ. 28፡19ን እንዴት መታዘዝ እንችላለን በሚለው አሳብ ላይ ለመወያየት ተገናኘን፡፡

ከአፍሪካ ጀምረን ወደ ምዕራብ አውሮፓ ለመሄድ ወሰንን፡፡ አፍሪካንየመረጥንበት ምክንያት የብዙዎቻችን መኖሪያ ቤት ስለ ሆነች ነበር፡ አውሮፓን

ሳውዲዐረቢያ፣የመን

ቡድሒስትሒንዱ

ቱኒዚያሙ ስ ሊ ም

Page 44: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

44

የመረጥንበት ምክንያት በውስጥዋ ያሉት አገሮች አፍሪካን በወንጌል ለመድረስ ከብዙዓመታት በፊት ብዙ ሥራ ስለ ሠሩ ነበር፡፡

ምርምር አደረግን፣ ከዚያም በእያንዳንዱ አገር ያለ የእውነተኛ ክርስቲያኖችንፐርሰንታይል (መቶኛውንም) በግምት አስቀመጥን፡፡ ፐርሰንታይሉንም

(መቶኛውንም) በካርታው ላይ አስቀመጥን፡፡ [ገጽ 52]

በካርታችን ላይ ያለው ፐርሰንታይል (መቶኛ) ፍጹም ትክክል ላይሆንይችላል፡፡ ነገር ግን፣ ሁለት ነገሮችን እናውቃለን፡-

1. ብዙ ሕዝቦች (አገሮች) ከ10 በመቶ በታች የሆኑ እውነተኛ ክርስቲያኖችአሉዋቸው፣ እንዲሁም አንዳንድ አገሮች

ወደ 0% የቀረቡበት ሁኔታም አለ፡፡

1. ኢየሱስ፣ ‹‹ሂዱና . . . ለሕዝቦች ሁሉ መስክሩ›› ብሎ ነግሮናል፡፡ያንን ሥራ አልጨረስነውም፡፡ አሁንም ብዙ የሚሠራ ሥራ አለን፡፡

ስንጸልይ ሳለን፣ የተገነዘብነው ነገር ነበር፡- ካርታውን [ገጽ 52 ላይ] ለአብያተ

ክርስቲያን ማሳየት፣ እና ‹‹ተግባራዊ እርምጃዎችን›› እንዲወስዱ ማደፋፈርነበረብን፡፡

‹‹የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናልና፡፡ እንግዲህ ያላመኑበትን እንዴትአድርገው ይጠሩታል? ካልሰሙትስ እንዴት ያምናሉ? ያለ ሰባኪስ

እንዴት ይሰማሉ? መልካሙን የምሥራች የሚያወሩ እግሮቻቸው እንዴትያማሩ ናቸው ተብሎ እንደ ተጻፈ ካልተላኩ እንዴት ይሰብካሉ? (ሮሜ

10፡13-15)

Page 45: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

45

የናይጄሪያው ዶ/ር ቢ. ካቶ እንዲህ ብለዋል፡-ብዙ ሰዎች ግራ ተጋብተዋል፡፡ የወንጌል

መልእክተኛ ነጭ መሆ አለበት፡፡ በእርግጥ፣‹‹ሚስዮናዊ›› የሚል ቃል በምንሰማበት

ጊዜ፣ ብዙዎቻችን አንድ ነጭ ቀለም ያለውሰው ጥቊር የቆዳ ቀለም ላላቸው ሰዎችለመስበክ ሲሄድ እናስባለን፡፡

ነገር ግን፣ ታሪክ ይህን አረጋግጦአል፡-ኢየሱስ ‹‹ሂዱ›› ካለበት ቀን ጀምሮ፣

ብዙዎች ጥቁሮችና ነጮች የወንጌልመ ል እ ክ ተ ኞ ች ( ሚ ስ ዮ ና ው ያ ን )

እግዚአብሔርን በታማኝነት አገልግለዋል፡፡ዛሬ ያ ማደግ አለበት፡፡

ናይጄሪያዊው ዶ/ር ኤስ. ኦዱኔኬ እንዲህብለዋል፡-

አፍሪካዊ አያቶቻችን ለክርስትና የከበረአስተዋጽኦ አበርክተዋል፡፡

በጥንት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ብዙዎቹታላላቅ አፍሪካውያን መሪዎች፣ እንደሊቢያዊው ሳይፕሪያን፣ እና አልጄሪያዊውአውግስጢኖስ ያሉት ሰዎች ነበሩ፡፡

አውሮፓውያንን ሃያማኖታቸውንሲያስፋፉ እየረዳናቸው ብቻ እንዳለንአድርገን ልናስብና ልንመላለስ አይገባንም፡፡ክርስትና የእኛም የእነርሱም ነው፡፡ ስለዚህ፣ልናሰራጨው መብቱም ሆነ ኀላፊነቱምአለብን፡፡

Page 46: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

46

የእውነተኛ ክርስቲያኖች አኀዝ በመቶኛ ተጠጋግቶ ሲቀመጥ

ተወያዩበት

Page 47: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

47

ዓለም ወደ 200 የሚጠጉ አገሮች እና ወደ 6000 የሚጠጉ ቋንቋዎች አሉባት፡፡ብዙዎቹ አገሮች ከደርዘን በላይ ‹‹ቋንቋዎች›› ይነገሩባቸዋል፡፡

ችግሩ፡- በእያንዳንዱ አገር ማለት ይቻላል፣ ስለ ክርስቶስ ጥቂት የሚያውቁወይም ምንም የማያውቁ አንዳንድ ወገኖች መኖራቸው ነው፡፡

እዚህ አሥር ምሳሌዎች አሉ፡፡

1. ጀርመን 20 የተለያዩ ቋንቋዎችን የሚናገሩ ሕዝቦች(ወገኖች) አሉዋት፡፡ ብዙዎቹ ጀመርናውያንተርኪሽ (ቱርካዊ) የሚባሉትን ወገኖች

አ ይ ወ ዱ ዋ ቸ ው ም ፡ ፡ [ገጽ 55ን ተመልከት፡፡]ይሁንና፣ ያ ወገን ኢየሱስ ያስፈልገዋል፡፡ክ ር ስ ቲ ያ ኖ ች ሊ ወ ድ ዷ ቸ ው ናሊመሰክሩላቸው ይገባል፡፡

2. ፈረንሳይ ሁለት ዋነኛ ቋንቋ፡- ‹‹ፍሬንች›› እና ‹‹ባስኩ›› ተናጋሪ ወገኖች

አሉዋት፡፡ ፈረንሳይኛ (ፍሬንች) ተናጋሪ ወገኖች ክርስቶስ ያስፈልጋቸዋል፡፡

ብዙዎቹ ወጣቶቻቸው መጽሐፍ ቅዱስን ከቶ ነክተው አያውቁም፡፡ ብዙዎቹራሳቸውን ይገድላሉ፡፡

3. በፈረንሳይ ውስጥ 700,000 ሰዎች ባስኩ የሚባለውን ቋንቋ ይናገራሉ፡፡ብዙዎቹም ዘላለማዊ ሕይወት እንዴት እንደሚገኝ አያውቁም፡፡ ክርስቲያኖች እዚያሊሄዱ፣ ባስኩኛን ሊማሩ እና ለእነርሱ ሊመሰክሩላቸው ይገባል፡፡

4. ሱዳን 132 ቋንቋዎች አሏት፡፡ ከእነዚህ ቋንቋዎች በ10ሩ መጽሐፍ ቅዱስተተርጉሞአል፡፡ ስለሆነም፣ 122 በሚሆኑ ቋንቋዎች የሚናገሩ ወገኖች መጽሐፍቅዱስ የላቸውም፡፡ ፉር የሚባሉትና ሌሎችም ብዙ ወገኖች የአንተን ርዳታይፈልጋሉ፡፡

5. ኢትዮጵያ 86 በሚሆኑ ልዩ ልዩ ቋንቋዎች የሚናገሩ ወገኖች አሉባት፡፡ እንደሶማሊ ጎሳ ያሉ ወገኖች መልካሙን የምሥራች መስማት ያስፈልጋቸዋል፡፡

6. ሞዛምቢክ 21 ልዩ ልዩ የሆነ ቋንቋዎችን የሚናገሩ ወገኖች አሉባት፡፡ ለ470ዓመታት ፖርቹጋላውያን ወደ ሞዛምቢክ እንዲገቡ የፈቀዱት ለጥቂት የወንጌልመልእክተኞች (ሚሲዮናውያን) ነበር፡፡ ነገር ግን አሁን በሩ ተከፍቶአል፡፡ማክሁዋ [እና ሌሎች ወገኖች] ኢየሱስ ያስፈልጋቸዋል፡፡ በመላው ሞዛምቢክመጽሐፍ ቅዱስን እንዲያስተምሩ በአፍሪካም ሆነ በየትም ስፍራ የሚገኙ አብያተክርስቲያናት ወንዶችና ሴቶችን እንዲልኩ ጸልዩ፡፡

Page 48: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

48

7. በማላዊ፣ የያኦ እና ሌሎች ወገኖች የክርስቶስ ፍቅር ያስፈልጋቸዋል፡፡

8. አሜሪካ (ዩ. ኤስ. ኤ) 20 ሚሊዮን ስፓኒሽ ተናጋሪዎች አሉዋት፡፡ ብዙአሜሪካውያን አይወድዱአቸውም፡፡ እውነተኛ ክርስቲያኖች ሊወድዱዋቸው፣ሊረዱዋቸውና ወደ ኢየሱስ ሊጋብዟቸው ያስፈልጋል፡፡

9. በእስራኤል ዕብራይስጥ፣ ዓረብኛ፣ አማርኛ . . . ይናገራሉ፡፡ ወደ አብርሃም

አምላክ ይጸልያሉ፤ ነገር ግን፣ ብዙዎቹ ኢየሱስ መሢሑ መሆኑን ይጠራጠራሉ፡፡አማኞች እንዲሆኑ (እንዲያምኑ) ልንረዳቸው ይገባል፡፡ [ሮሜ 10፡1-15ይመልከቱ፡፡]

10. ሕንድ 1652 የሚሆኑ በልዩ ልዩ ቋንቋዎች የሚናገሩ ወገኖች አሉዋት፡፡ብዙዎቹ ኢየሱስን አያውቁትም፡፡ አንድ ምሳሌ የሚሆነን፣ 20,000,000የሚሆኑት የሲንድሂ ሰዎች ናቸው፡፡ወደ ሌላ ቋንቋ ተናጋሪ ወገኖች መሄድ ቀላል ነገር አይደለም፡፡ እኛ ሰዎች በገዛ

ወገናችን ዘንድ መኖርን እ ን ወ ዳ ለ ን ፡ ፡ስ ለ ዚ ህ ፣ ጥ ቂ ት

ክርስቲያኖችን ወደ ሌላ ቋንቋ ተናጋሪ ወገኖች የመላክንስሕተት እንሠራለን፡፡

ርዳታ የሚያስፈልጋቸው ቡድኖች 10 ምሳሌዎች

Page 49: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

49

‹‹የገንዘብ ኃይል›› ወይስ ‹‹የመንፈስ ቅዱስ ኃይል››?

ኢ የ ሱ ስ ፣‹‹እምነትን ለማስፋፋት፣ ብዙ ገንዘብ

ያስፈልጋችኋል?›› ብሏልን? አላለም፡፡ እርሱ ለድኾች ሰዎች ያለው፡-

ወደ ቅርብም ሆነ ወደ ሩቅ እንዲሄዱ እንዴት እንደሚመሰክሩ፣ ከመንፈስቅዱስ በሆነ ኃይል እንዲመሰክሩ፣ መከራ ለመቀበል ዝግጁ እንዲሆኑ ነው፡፡(የሐዋርያት ሥራ 1፡8፤ ሉቃስ 9፡23 ተመልከት፡፡)ኢየሱስ እነዚህን ቃሎች በኢየሩሳሌም ተናግሮአቸዋል፡፡

በንጉሥ ዳዊት ዘመን፣ ኢየሩሳሌም ሀብታም ነበረች - ነገር ግን በኋላሮማውያን ከተማይቱን በሚያስተዳድሩበት ጊዜ ኢየሩሳሌም ደኸየች፡፡ እንዲያውም፣በዚያ ያሉ ሰዎች እጅግ ድኻ ከመሆናቸው የተነሣ፣ ጳውሎስ በሌላ ስፍራ ያሉ አብያተክርስቲያንን፣ ‹‹በኢየሩሳሌም ላሉ ሰዎች እባካችሁን ምግብ ግዙ፤›› ብሎተናግሮአቸዋል (ሮሜ 15፡26፤ 1ኛ ቆሮ. 16፡1-3)፡፡

Page 50: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

50

አ ዎ ን ፣ በኢየሩሳሌምያ ሉ ሰ ዎ ች ድ ኾ ችነ በ ሩ ፤ ነገር ግን ኢየሱስ፣ ‹‹ሂዱና ሩቅ ስፍራዎች

መስክሩ›› ብሏቸዋል፡፡

እነርሱም ታዝዘዋል፡፡ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል፣ እና ያለ ምንም ማጕረምረምመከራን በመቀበል እነዚያ ድኻ አማኞች ወንጌልን ወደ ሩቅ ስፍራ ወስደዋል፡፡

ለመጀመሪያዎቹ 1500 ዓመታት፣ ክርስትና የተሰራጨው

‹‹ያለ ገንዘብ ኃይል›› ነበር፡፡ከኢየሱስ ዘመን ጀምሮ እስከ 1500 ዓ.ም ክርስትና ከኢየሩሳሌም ወደ

ኢትዮጵያ - - ከዚያም ከኢትዮጵያ ወደ ሱዳን፣ ሊቢያ፣ አልጄሪያ፣ፖርቹጋል...[ገጽ 27] ተሰራጭቷል፡፡

ክርስትና የ ተ ሰ ራ ጨ ውለኢየሱስ የሚቀጣጠል ፍቅር በነበራቸው ተራ የሆኑ ድኾች ሰዎችነበር፡፡

አንዳንዶቹ በበሽታ ምክንያት ሞቱ፡፡ አንዳንዶቹ ተገደሉ፡፡ ነገር ግን መልካሙየምስራች ተሰራጨ፡፡

ከ1500 ዓ.ም እስከ አሁን ድረስ፣ አንዳንድ የወንጌል መልእክተኞች (ሚስዮናውያን)በአያሌው በገንዘብ ላይ የተደገፉ ሆኑ፡፡

ጋናዊው ዶ/ር ጂ. ኦሴይ-ሜንሳህ የሚከተለውን ይናገራሉ፡-

Page 51: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

51

ይህን አድርግ፡- በገጽ 47 ላይ ያለውን ክፍል በቤተ ክርስቲያናችሁ ላሉት ሰዎችአሳይ፡፡ ከዚያም

ቤተ ክርስቲያናችሁ ለአገሮች፣ [ገጽ 52] እንዲሁም በልዩ ልዩ ቋንቋ

ለሚናገሩ ወገኖች መጸለይን መጀመር ትችላለች፡፡ [ገጽ 55]ምናልባት አንተ እንድትሄድ እግዚአብሔር ይጠራህ ይሆናል፡፡ ከሆነም፣

ለቤተ ክርስቲያናችሁ መሪዎች ንገራቸው፡፡ አክብሮት ባለበት ሁኔታ ንገራቸው፡፡‹‹እግዚአብሔር ጠርቶኛል፤ እናንተ በገንዘብ ልትረዱኝ ይገባል፣›› አትበል፡፡

በዚህ ፈንታ፣ ‹‹በልዩ ልዩ ቋንቋ ተናጋሪ ወደ ሆኑ፣ የተጠሙ ወገኖች ሄጄእንድመሰክር እግዚአብሔር ጥሪውን እያስተላለፈልኝ ነው፡፡ ምናልባትእግዚአብሔር ሌሎችንም ይጠራ ይሆናል - ከዚያም በቡድን ሆነን አብረን መሄድእንችላለን፡፡ ምናልባት ቤተ ክርስቲያን የሚያስፈልገንን ሥልጠና፣ እናየምንሄድበትን ገንዘብ በተመለከተ ልትረዳን ትችል ይሆናል፣›› በል፡፡

ከአንተ ጋር የሚሄድ አንድም ሰው ከሌለ፣ ቤተ ክርስቲያናችሁ ምንም ገንዘብካልሰጠችህ፣ አሁንም መሄድ ትችላለህ፡፡ እንዲጸልዩልህና በገንዘብ እንዲረዱህጓደኞችህን ጋብዛቸው፡፡ ከዚያም በልዩ ልዩ ቋንቋ ወደሚናገሩና ወንጌልወደሚያስፈልጋቸው ወገኖች ሂድ፡፡ የገንዘብ እጥረት በሚገጥምህ ጊዜ ሁሉ፣

ልብስ ስፋ፣ ወይም አትክልት ትከል፣ አልያም ልክ ድንኳን ይሰፋ እንደ ነበረው እንደጳውሎስ ማንኛውንም ሥራ ሥራ፡፡

ነገር ግን ሩጫዬንና ከጌታ ከኢየሱስ የተቀበልሁትን አገልግሎት እርሱምየእግዚአብሔርን ጸጋ ወንጌልን መመስከር እፈጽም ዘንድ ነፍሴን በእኔዘንድ እንደማትከብር እንደ ከንቱ ነገር እቈጥራለሁ፡፡ እነዚህ እጆቼ

ደረጃ 1 . . . መጸለይ፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን ለአገራችን ብቻ በመጸለይ

ልትረካ አትችልም፡፡ ለሁሉም አገሮች፣ በተለይም ደግሞ እውነተኛክርስቲያኖች በመቶኛ አናሳ ለሆኑባቸው አገሮች እንጸልያለን፡፡

ደረጃ 2 . . . መላክ፡፡ በገዛ አገራችን ያሉ የተለያዩ ቋንቋዎችን የሚናገሩ

ጥቂት ሕዝቦችን በወንጌል ለመድረስ የቤተ ክርስቲያናችን አባላትንለአራት ሳምንታት ጕዞ በመላክ እንጀምራለን፡፡ የትኞቹ አባላት የተሻለሥራ እንደ ሠሩ እንመለከታለን፡፡ እነዚያን ሰዎች ነው አሠልጥነንበሞዛምቢክ፣ ወይም ኒጀር፣ ወይም ቤልጅየም፣ ወይም . . .

አብያተ ክርስቲያንን በመመሥረት 5 ዓመታት ወይም ከዚያም በላይ

ዓመታት እንዲያገለግሉ የምንልካቸው፡፡ደረጃ 3 . . . መስጠት፡፡ በገንዘብ እንረዳቸዋለን፡፡ ያንን ለማድረግ፣ እኛ

አማኞች ‹‹ፍላጎቶቻችንን መሥዋዕት እናደርጋለን››፣ ስለዚህም

‹‹በልግስና እንሰጣለን›› (2ኛ ዜና 31፡5-6)፡፡

K}Óv^© `UÍ › UaI” ›²ÒÏ (1— â?Ø. 1:13)

K}Óv^©

`UÍ ›

UaI” ›

²ÒÏ

K}Óv^©

`UÍ ›

UaI” ›

²ÒÏ

K}Óv^© `UÍ › UaI” ›²ÒÏ (1— â?Ø. 1:13)

‹‹ተግባራዊ እርምጃዎቻችን››

Page 52: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

52

በሚያስፈልገኝ ነገር ለእኔና ከእኔ ጋር ላሉት እንዳገለገሉ እናንተታውቃላችሁ (የሐዋርያት ሥራ 20፡24 እና 34)፡፡

1. በአገራችን ብዙ ሰዎች፣ ‹‹ወንጌልንለማዳረስ ብዙ ገንዘብና ምቹ የሆነ መኪና

ያ ስ ፈ ል ጉ ኛ ል ? › › ብ ለ ውያስባሉን?

2. ‹ ‹ ም ቾ ት ን

መሥዋዕት አድርገን ወንጌልን እ ን ድ ና ደ ር ስ › ›የሚያበረታቱን የትኞቹ የመጽሐፍ ቅዱስ

ክፍሎች ናቸው? [እያንዳንዱ ሰው የመጽሐፍ ቅዱስክፍሎችን እንዲጠቁም ፍቀድ፡፡ ከዚያም ደግሞ1ኛ ቆሮ. 4፡11፤ 2ኛ ጢ ሞ .

1፡8፤ ፊልጵ. 4፡18፤ ማቴ.26፡39፤ ማር. 8፡34-35፤ሉ ቃ ስ 17፡7-10፤ 1ኛ ዮሐ. 3፡16ን

አንብብ፡፡]

3. ከ ገ ጽ 52 እስከ 55

ስንመለከት፣ ቤተ ክርስቲያናችን ሰዎችን ልትልክ የሚገባው ወደየትኞቹ ጎሳዎች ወይም አገሮች ነው? [በዚህ ጠቃሚ በሆነ ጥያቄ

ላይ ብዙ ጊዜ ውሰዱ፡፡]

እንግሊዝ 12% ኔዘርላንድስ 9%ቤልጅየም 3%ጀርመን 8%ስዊዘርላንድ 10%ፈረንሳይ

ስፔንፖርቱጋል

ቱኒዚያ 0%ሞሮኮ 0.1%

ሴኔጋል 1 %

ሞሪታንያ 0%

አልጄሪያ0.1% ሊቢያ 0%

ግብፅ 7% ኤርትራ18%

ጅቡቲ 0%ማሊ 0.5% ኒጀር 0.1%

ቻድ 9% ሱዳን 3%

ኢትዮጵያ26%ኮት

ዲቯ Ò“

c?^K=Ä”

ጊኒ ቢሳው

ጋምቢያ

Ñ>’>

„Ô

u?’>”

"T@a”

›="D„]ÁM Ñ>’>

Òx”

Åu<w ›õ]"

“T>u=Áxƒeª“

²=Uvu<«

³Uu=Á

”³’>Á

ÈV¡. ]. ¢”Ô

›”ÔL

¢”Ô

ማዕከላዊ አፍሪካ

“ÃÎ]Á

fTK=Á

Ÿ?’>Á

\ª”Ç

TL©

u<\ӂ=

TÇÒe"`

V³Uu=¡

eª²=L”É

K?f„

ይህን ካርታ በትልቁ ፎቶ ኮፒ አስደርገው፡፡ ዝቅተኛፐርሰንት (መቶኛ) ያላቸውን አገሮች ቀይ ቀለም ቀባ፡፡ለቤተ ክርስቲያናችሁ አሳየው፡፡ ‹‹ተግባራዊ

እርምጃዎችን›› በተመለከተ ውይይት አድርጉ፡፡

×K=Á”

ቡርኪናፋሶ

›<Ò”ÇLÃu?]Á

Page 53: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

53

‹‹ተግባራዊ እርምጃዎችን›› እንጻፍ፡፡ [ገጽ 51 ላይ ካለው ጋር ተመሳሳይይሁኑ፡፡]

4. ለእያንዳንዱ የተግባራዊ እንቅስቃሴው ደረጃ ኀላፊነት የሚወስዱ ሰዎችንመምረጥ እንችላለን? እያንዳንዱን ደረጃ በየትኛው ቀን እንጀምረው?

ምዕራፍ 6

መጸለይ... መላክ... መስጠት

አንዳንድ ክርስቲያኖች፣ ‹‹ብቸኛው ኀላፊነቴ ቤተ ክርስቲያን መሄድና

ኮንፍረንሶችን (ጉባኤዎችን) መሳተፍ ነው፣›› ብለው ያስባሉ፡፡

ነገር ግን ክርስቶስ ከዚያ የበለጠ እንድናደርግ ነግሮናል፡፡ እርሱ፣‹‹እግዚአብሔር ሠራተኞችን እንዲጠራ ጸልዩ . . . በቅርብም ሆነ በሩቅ ወዳሉ

የጠፉ ሰዎች ሰዎችን ላኩ . . . እነርሱንም ለመርዳት ገንዘብ ስጡ፣›› ብሏል፡፡

Page 54: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

54

አንዳንድ ሰዎች ለገዛ ሕዝባቸው በመጸለይ ረገድ መልካም ያደርጋሉ፤ ነገር ግን፣ለሌሎች አገሮች በመጸለይ ረገድ ደካሞች ይሆናሉ፡፡ በተሻለ ሁኔታ መጸለይእንድትችል ቤተ ክርስቲያናችሁን መርዳት ትችላላችሁ፡፡ እንዴት? በቤተ ክርስቲያኒቱአገልግሎት ወንጌል ስለሚያስፈልጋቸው ለአንድ ቋንቋ ተናጋሪ ወገኖች ለመናገር ጥቂትደቂቃዎችን መውሰድ ትችላላችሁ፡፡ ከዚያም በአገራችሁ እንዲሁም በሌሎች አገሮችስላሉ በልዩ ልዩ ቋንቋዎች ስለሚናገሩ ጎሳዎች እንዲጸልዩ እያንዳንዳቸውንአበረታቷቸው፡፡ [ገጽ 58]

መንግሥተ ሰማያት በምንገባበትና በጸሎታችን በኩል እግዚአብሔርያደረጋቸውን ታላላቅ ነገሮች በምናይበት ጊዜ፣ ‹‹ቴሌቪዥን የበለጠ በተመለከትሁ

እና በጥቂቱ በጸለይሁ›› ከቶ አንልም፡፡ደፋሮች ሁኑ፡፡ በየቤቱ ይመሰክሩ ዘንድ የቤተ ክርስቲያን አባላትን ከአንተ ጋርውሰድ፡፡ ያንን ዘወትር አድርግ፡፡ ከትንሽ ጊዜ በኋላ የቤተ ክርስቲያን መሪዎችህ

Page 55: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

55

ለአንዳንዶቹ፣ ‹‹በደንብ እንደምትመሰክር ልብ ብለናል፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን ወደ ሌላ

ቋ ን ቋ ተ ና ጋ ሪወገኖች አ ራ ትአባላት ያሉትን አንድ ቡድን መላክትፈልጋለች፡፡ ቡድኑ በዚያ ሆኖ ቤተ ክርስቲያንለመመሥረት ጥቂት ዓመታትን ያሳልፋል፡፡ቤትህን ትተህ ከቡድኑ ጋር ለመሄድ ፈቃደኛነህን? ከሆንህ፣ ቤተ ክርስቲያናችን ሥልጠናእንድታገኝ ትረዳሃለች፡፡ እንዲሁም አንተንበጸሎትና በሚያስፈልግህ ገንዘብ ለመርዳት

በመቶ የሚቈጠሩ በልዩ ልዩ ቋንቋ የሚናገሩወገኖች ወንጌል ያስፈልጋቸዋል፡፡ እነዚህ አሥርምሳሌዎች ብቻ ናቸው፡፡

በጀርመን ያሉ ተርኪሾች

በፈረንሳይ ያሉ ፍሬንች ተናጋሪዎች

በፈረንሳይ ያሉ ባስኩዎች

በሱዳን ያሉ ፉር ተብለውየሚጠሩ ሕዝቦች

በኢትዮጵያ ያሉ ሶማሊዎች

በሞዛምቢክ ያሉ ማክሁዋተብለው የሚጠሩሕዝቦች

በማላዊ ያሉ ያኦ ተብለውየሚጠሩ ሕዝቦች

በዩ. ኤስ. ኤ ያሉስፓኒሾች

ዕብራይስጥ፣ ዓረብኛና አማርኛየሚናገሩ በእስራኤል ያሉሕዝቦች

በፓኪስታንና በሕንድ ያሉሲንድሂ ተብለው የሚጠሩሕዝቦች

አፍሪካ 2110 ቋንቋዎች የሚናገሩ ወገኖችአሉባት፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ 160በሚሆኑት ተተርጉሟል፡፡

Page 56: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

56

የምንችለውን ሁሉ እናደርጋለን›› (የሐዋ. 13፡2-

ማቴ. 9፡37

ብዙ ክርስቲያኖች በገዛ ወገናቸው ዘንድተቀምጠዋል፡፡

ጥቂቶች ይሄዱና ለሌሎች ቋንቋ ተናጋሪወገኖች ኢየሱስን ይሰብካሉ፡፡

እምነታቸው በእኔ በመሆኑ፣ ኃጢአታቸውከታጠበላቸው የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ጋር

ይቀላቀላሉ (የሐዋ. ሥራ 26፡18)፡፡

ጳውሎስ፡- ‹‹በሌላው ሰው መሠረትላይ እንዳልሠራ የክርስቶስ ስም

በተጠራበት ስፍራ ሳይሆን ወንጌልንለመስበክ ተጣጣርሁ›› ብሏል

(ሮሜ 15፡20)፡፡

በምድር ላይ የትም ብትኖር፣ ዓይኖችህንክፈት፣ ይህን ካደረግህ ክርስቶስ እንዴትዘላለማዊ ሕይወት እንደሚሰጥ መስማት

የሚፈልጉ ልዩ ቋንቋ ተናጋሪ የሆኑወገኖችን ታገኛለህ፡፡ ሄደው

መልካሙን የምሥራች የሚነግሩዋቸውአማኞችን እንድትልክና እንድትጸልይላቸው

ቤተ ክርስቲያናችሁ ልትረዳ ትችላለህ፡፡

ኢየሱስ ለጳውሎስ፣ ‹‹ዓይናቸውን እንድትከፍት፣ከሰይጣንም ኃይል ወደ እግዚአብሔር፣

እንዲሁም ከጨለማ ወደ ብርሃንእንድትመልሳቸው እልክሃለሁ›› ብሎ

ተናግሮታል፡፡

Page 57: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

57

3)፡፡ያ ሁሉ አስቸጋሪ ነው፡፡ ‹‹የሚሄዱት››

ሰዎች ቤታቸውን በመተውና ሥራቸውንበመልቀቅ መሥዋዕትነት ይከፍላሉ፡፡‹‹በቤት

የሚቀሩት›› ሰዎች ደግሞ በመጸለይና በመስጠት ረገድ መሥዋዕትነትን ይከፍላሉ፡፡

ወንጌልን ማዳረስ ከቶ ቀላል አይደለም፡፡መሥዋዕትነትን ይጠይቃል፡፡ እግዚአብሔርልጁን መሥዋዕት አድርጓል፣ ደግሞምሕይወታችንን መሥዋዕት እንድናደርግይጠራናል (ሮሜ 12፡1)፡፡

ወንጌልን ማዳረስና መሥዋዕት መክፈል አብረው የሚሄዱ ነገሮች ናቸው፡፡

እያንዳንዱ ክርስቲያን፣ ‹‹በተሰጥኦዎቼ ሁሉ [ስብከት፣ ወጣቶችን መርዳት፣ ወይምባለኝ በየትኛውም ስጦታ] እግዚአብሔርን አገለግላለሁ፣ ደግሞም በገንዘቤም ጭምርእርሱን አገለግለዋለሁ፣›› ብሎ መወሰን አለበት፡፡ ‹‹ገንዘብን ለራሴ በሚሆን ምድራዊመዝገብ ላይ በማዋል ፈንታ፣ ሠራተኞችን ለመላክ መሥዋዕትነት በመክፈልእሰጣለሁ››መዝ. 37፡21፤ማቴ. 6፡19 እና 33፤ሮሜ 15፡24፤1ኛ ቆሮ. 16፡2

አንዳንድ ክርስቲያኖች እንዲህ ይላሉ፡-

‹‹ክርስቶስን የማያውቁ ሰዎች ወዳሉበት ስፍራ እሄዳለሁ . . . ቤተ ክርስቲያን

መመሥረት፣ መጽሐፍ ቅዱስ ማስተማር፣ ወላጅ - አልባ ልጆችን መርዳትእፈልጋለሁ፡፡ ነገር ግን መሄድአልችልም፡፡ ለምን? በገንዘብ ችግር ምክንያት፡፡ ሥራዬንአቁሜ የምሄድ ከሆነ፣ በምግብና/በገንዘብ የሚረዳኝ ይኖራል?

Page 58: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

58

ይህን እጠራጠራለሁ፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን ድኻ ናት፣ እኔንወዴትም ለመላክ እጅግ ድኻ ናት፡፡ ስለዚህ መሄድአልችልም፡፡››

ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ ሁለት እውነታዎችን ይነግረናል፡-

የመጽሐፍ ቅዱስ እውነታ 1፡- እግዚአብሔር ሄጄ እንድሰብክ፣ወይም ልጆችን እንድረዳ፣ ወይም የቱንም ነገር እንዳደርግየጠራኝ ከሆነ . . . ቤተ ክርስቲያናችን ምንም ገንዘብባትሰጠኝ እንኳ፣ ልሄድና ላደርገው ይገባኛል፡፡

የመጽሐፍ ቅዱስ እውነታ 2፡- መጽሐፍ ቅዱስን ለማስተማርና ችግረኞች ሰዎችንለመርዳት ጠንክረው የሚሠሩትን ሰዎች ቤተ ክርስቲያን በገንዘብልትረዳቸው ይገባል፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ ይህንን የሚለው የት ነው? በገጽ 65-66 ላይ ባሉት የመጽሐፍቅዱስ ክፍሎች ውስጥ ነው፡፡ እነዚያን ጥቅሶች ለማጥናት ጊዜ ውሰድ፣ መንፈስቅዱስም ዓይኖችህን ይከፍትልሃል፡፡

እነዚያ ጥቅሶች፡- ቤተ ክርስቲያናችን ወንጌልን የሚያደርሱ ሰዎችን በገንዘብመደገፍ ትችል ዘንድ እኔ ገንዘብ ልሰጥ ይገባኛል ይላሉ፡፡

እግዚአብሔር ‹‹ሥራህን አቁምና ሂድ›› ካለኝ፣ ‹‹ገንዘብ ስለ ሌለ መሄድ

አልችልም፣›› ማለት አይኖርብኝም፡፡ ምንም እንኳ ቀለቤን ለማግኘት ‹ድንኳን

መስፋት› የሚያስፈልገኝ ቢሆንም እንኳ፣ እርሱ ወደ ላከኝ ስፍራ መሄድይኖርብኛል፡፡

በኬንያ [ለምሳሌ ያህል] በኬንያ ወዳሉ በልዩ ልዩ ቋንቋ ወደሚናገሩ ወገኖች፣

እንዲሁም ወደ ሶማሊያ፣ ሱዳን፣ ወዘተ . . . አብያተ ክርስቲያን ለመመሥረት፣አብያተ ክርስቲያን ወንዶችንና ሴቶችን የወንጌል መልእክተኞች እየላኩ ናቸው፡፡እነዚያ ወንዶችና ሴቶች እንዲህ ይላሉ፡-

ለቤተ ክርስቲያናችሁ የሚሆኑ ሁለት አሳቦች እዚህ ቀርበውልሃል፡-1) በቤተ ክርስቲያናችሁ፣ ‹‹ለሁሉም ቋንቋ ተናጋሪ ወገኖች ቡድንን›› ምረጥ፡፡

ይህ ቡድን [ከ5 እስከ 8 ሰዎች ያሉበት] ለቤተ ክርስቲያን፣ ‹‹በወንድሞችጉባኤ፣ በእኅቶች ጉባኤ፣ በሰንበት ትምህርት ቤት እና በወጣቶች አገልግሎትውስጥ መዝ. 96፡3-10፤ ማቴ. 9፡37-38፤ ማቴ. 28፡18-20፤ ሉቃስ 24፡45-

ከ500 ዓመታት በፊት አውሮፓ የወንጌል መልእክተኞችን መላክ ጀመረች፡፡ወዲያውም እኛ የአፍሪካና የእስያ ሰዎች፣ ‹‹ክርስትና ከነጮች ሰዎችና ከገንዘብ ጋር የተገናኘ

ነው›› ስንል ማሰብ ጀመርን፡፡

ዛሬም እንኳ ‹‹ክርስትናን›› በምታነሣበት ጊዜ፣ የእኛ ሰዎች ባህላቸውን ትተው ልክ

እንደ ነጮቹ እንዲመላለሱ የምትፈልግ እንደ ሆንህ አድርገው ያስባሉ፡፡ ደግሞም፣ ‹‹እኔ

በእግዚአብሔር ሥራ ላይ የምጠመድ ከሆነ፣ ብዙ ገንዘብና ምቹ መኪና ሊኖረኝ ይገባል፣››ሲሉ ያስባሉ፡፡

በኢየሱስ ዘንድ ግን እንዲህ አልነበረም፡፡ እርሱ በገንዘብና በምቾት አልመጣም፡፡ዛሬ፣ እኛ አፍሪካውያን አማኞች (በቊሳዊ ባለጠግነት ሳይሆን፣ ነገር ግን ራስን

መሥዋዕት በማድረግ) ወንጌልን ወደ ጠፉ ሰዎች የምንወስድ ከሆነ፣ ሰዎች ልብ ይላሉ፤ያደምጡንማል፡፡

በዚህ ጊዜ በአውሮፓና በአሜሪካ ካሉ አብያተ ክርስቲያን ይልቅ፣ አፍሪካዊ አብያተክርስቲያናችን የበለጠ ቀናዒነት (መነሣሣት) አላቸው፡፡ ምንም እንኳ እኛ በገንዘብ ረገድደካሞች ብንሆንም፣ በክርስቶስ ጠንካሮች ነን፡፡ በየአብያተ ክርስቲያናችን፣ ‹‹በብዙ ገንዘብሳይሆን፣ ነገር ግን በመነሣሣትና ምቾቶችን በመሠዋት፣ ወንጌልን ማድረስ እንችላለን›› ብለን

እናውጅ (ዕብ. 10፡32-39)፡፡

ዶ/ር ጂ. ኦሴይ - ሜንሳህ

Page 59: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

59

47፤ ዮሐ. 17፡18፤ የሐዋ. 1፡8፤ የሐዋ. 13፡47፤ ሮሜ 10፡13-15፤ ሮሜ 15፡20ን

እናስተምር እና ጥቅሶቹ የሚሉንንም እናድርግ›› በማለት መጀመር ይቻላል፡፡

ከዚያም ቡድኑ ቤተ ክርስቲያንን እንድትጸልይ፣ እንድትሰጥ እና ወንዶችናሴቶችን ወንጌል ወደሚያስፈልጋቸው ጎሳዎች ለመላክ የሚያበረታታበትን መንገድያገኛል፡፡

2) በእያንዳንዱ ዓመት ‹‹ሁሉንም ሕዝቦች በወንጌል የመድረስ ኮንፍረንስን››አዘጋጅ፡፡የኮንፍረንሱ ግብ፡- በመጸለይ፣ በመስጠት ወይም በመሄድ እያንዳንዱን አማኝበማሳተፍ ረገድ ለመቀስቀስ ነው፡፡

በኮንፍረንሳችሁ ላይ፡-

ሀ) ማቴ. 28፡18-20ን አስተምር፡፡ ከዚያም፣ ‹‹ወንጌል የሚያስፈልጋቸው አንዳንድ

ጎሳዎች የት ናቸው?›› ብለህ ጠይቅ፡፡ [የገጽ 52ን እና 55ን ትልቅ ፎቶ ኮፒአሳያቸው፡፡]

ለ) ቤተ ክርስቲያን ለመመሥረትና ችግረኞችን ለመርዳት ወደ ሌሎች ጎሳዎች ሄደውለሚያውቁ ሰዎች ቃለ መጠይቅ አድርግላቸው፡፡

ሐ) ‹‹የቤተ ክርስቲያን አባላት እንዴት ሊረዱ ይችላሉ?›› በሚለው ላይ ውይይትአድርግ፡፡

ገንዘብ ያለህ ብትሆን ኖሮ፣ ለእግዚአብሔር ምን ታደርግለታለህ;

ያለ ብዙ ገንዘብ፣ አሁኑኑ ያንኑ ሂድና አድርገው (ፊልጵ. 4፡12-13)፡፡

Page 60: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

60

1) ለገዛ ሕዝባችን ብቻ ሳይሆን፣ ለሌሎች ሕዝቦችም ጭምር እንድትጸልይ ቤተ

ክርስቲያናችንን እንዴት ማበረታታት እንችላለን? [ገጽ 62]

2) ቤተ ክርስቲያናችን ሰዎችን መላክ ያለበት ወዴት ስፍራ ነው? [ገጽ 55]

3) አማኞችን እንዲሰጡ እንዴት ማበረታታት እንችላለን? [ገጽ 63 -66]

4) ዓመታዊ የሆነ ‹ለሁሉም ቋንቋ ተናጋሪ ሕዝቦች ኮንፍረንስ› ቤተክርስቲያናችንን ሊረዳ ይችል ይሆን? ወይስ የተሻለ መንገድ ይኖራል?

5) ‹ለሁሉም ቋንቋ ተናጋሪ - ቡድን› ቤተ ክርስቲያንን እንዴት ሊረዳ ይችላል?

ቤተ ክርስቲያናችሁ የቤተ ክርስቲያን መሪዎችን በምትመርጥበት ጊዜ፣

ቤተ ክርስቲያን ማቴዎስ 28፡19ን እንድትታዘዝ የሚፈልጉ መሪዎችን ምረጡ፡፡

ተወያዩበት

ቤተ ክርስቲያናችን ክርስቲያኖችን ቅርብም ሆነ ሩቅ ስፍራ ትልካለች፡፡ እኛ አሁኑኑይህን እናደርገዋለን፡፡ ‹‹ቤተ ክርስቲያናችን ትልቅና ሀብታም እስክትሆን ድረስ

እንቆይ፣›› አንልም፡፡

Page 61: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

61

ምዕራፍ 7

እውነተኛ ታሪኮች (ስሞች ተለውጠዋል)

ናይጄሪያዊው ኢዩኤል አዎኒዪ እንዲህ አለ፡- መጋቢያችን ብዙ ጊዜ እንዲህይላል፣ ‹‹ሥራ ያላችሁ ሁሉ አድምጡኝ፡- ‹የዓመት ፈቃዳችሁን› ክርስቶስን

ለማገልገል ተጠቀሙበት፡፡››

ስለዚህ ለባለቤቴ፣ ‹‹በዚህ ዓመት ያለኝን የዓመት ፈቃድ ወንጌልን ወደ ቤኒንለመውሰድ እንደምጠቀምበት ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ወደዚያ በአውሮፕላን ሄጄ ለ30ቀናት እሰብካለሁ፡፡ ምን ይመስልሻል?›› አልኳት፡፡

በመጀመሪያ፣ ‹‹ወደ ቤኒን የምትሄድበት ቲኬት በመግዛት ገንዘብ ከምናባክን፣

ምድጃ (ስቶቭ) ልንገዛበት እንችላለን፡፡ ከዚያም በከሰል ማብሰሌን እተዋለሁ››አለች፡፡

ከዚያ በኋላ ግን፣ ፈገግ ብላ እንዲህ አለች፣ ‹‹እግዚአብሔር ወደ ላከህ ቦታ

ሂድ፡፡››

በእነዚያ 30 ቀናት ውስጥ ቤተ ክርስቲያንን በመመሥረት ረገድ አንድ መጋቢንረዳሁት፡፡ እኔና ባለቤቴ እንዴት ባለ ግሩም ሁኔታ እግዚአብሔርን አመሰገንን!

በሚቀጥለው ዓመት 4000 ኪሎ ሜትር ተጕዤ ወደ ሞዛምቢክ ሄድሁ፡፡

ወደ ናይጄሪያ በተመለስሁ ጊዜ፣ ባለቤቴን፣ ‹‹የኔ ቆንጆ፣ በሞዛምቢክ ያሉ ሰዎችመጽሐፍ ቅዱስ ያስፈልጋቸዋል፡፡ ሥራችንን እናቁም፣ ልጆቻችንንም ይዘን ወደዚያውእንሂድ›› አልኋት፡፡

የመጀመሪያው ምላሽዋ፣ ‹‹ሞዛምቢክ? በዚያ ያሉ ሰዎች እንግሊዝኛ እንኳ

መናገር አይችሉም፡፡ ደግሞስ ልጆቻችን...???›› የሚል ነበር፡፡

ነገር ግን በነጋታው፣ ‹‹አዎን፣ መሄድ እንችላለን፡፡ እግዚአብሔር

ይጠነቀቅልናል›› አለች፡፡

ለመሄድ ፈቃደኞች በመሆናችን ቤተ ክርስቲያናችን ተደሰተች፡፡ አባላቱ፣በየዓመቱ የተወሰነ ገንዘብ ሊሰጡን ቃል ገቡልን፡፡ ምንም እንኳ እኛ ሠርተንከምናገኘው በእጅጉ ያነሰ ቢሆንም፣ እግዚአብሔርን አመሰገንነው፡፡

መከሩስ ብዙ ነው፣ ሠራተኞች ግን ጥቂቶች ናቸው፡፡እንግዲህ የመከሩን ጌታ ወደ መከሩ ሠራተኞቹን እንዲልክ

ለምኑ/ጸልዩ

(ማቴ. 9፡37-38)፡፡

መጸለይ፡-

መንፈስ ቅዱስ ለቤተ ክርስቲያን መሪዎች፣‹‹በርናባስንና ሳውልን ለጠራኋቸው ሥራ ለዩልኝ

(ላኩ) አለ›› (የሐዋርያት ሥራ 13፡2-3)፡፡መላክ፡-

Page 62: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

62

ሁለታችንም ሥራችንን ለማቆም ሥጋት ተሰማን፡፡

ሞዛምቢክ በደረስን ጊዜ፣ ሰዎቹ፣ ‹‹እናንተ ሚሲዮናውያን ናችሁን?›› ብለው

ጠየቁን፡፡ ከዚያም፣ ‹‹ታዲያ ስለ ምን ጥቊር ሆናችሁ?›› አሉን፡፡ ትንሽ ቤትተከራየንና ምስክርነታችንን ቀጠልን፡፡ አሁን ስድስት እያደጉ ያሉ አብያተ ክርስቲያንተመሥርተዋል፡፡

በየዕለቱም፣ ‹‹ጌታ ሆይ፣ እዚህ በሞዛምቢክ ያገለግሉህ ዘንድ ከብዙ አገሮች

ክርስቲያኖችን እባክህን ላክ፣›› እያልን እንጸልያለን (ማቴ. 9፡37)፡፡

አውስትራሊያዊው ዳን ሆቭ እንዲህ ይላል፡- ልጅ ሆኜ ራሴን

እንዲህ አልኩኝ፡- ‹‹እኔ ጥቅመ ቢስ ነኝ! እንደ ወንድሜ ለእይታየምስብ አይደለሁም፡፡ በስፖርትም ጥሩ ውጤት የለኝም፡፡

በየትኛውም ነገር ከቶ አይሳካልኝም፡፡››ከኮሌጅ ከተመረቅሁ በኋላ፣ በከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት

እንግሊዝኛ የማስተምርበት የሥራ ዕድል አገኘሁ፡፡ ሥራውን ወደድሁት፡፡ ደግሞምተማሪዎቼ የማስተምርበትን መንገድ ወደዱት፡፡

ከዚያም አንድ ክርስቲያን ሰውዬና ባለቤቱ ኢየሱስን እንድቀበል ረዱኝ፡፡መጽሐፍ ቅዱስን አስተማሩኝ፣ ከዚያም በምሳ ሰዓት ተማሪዎችን አስተምረው ጀመር፡፡ሕይወቴ እንደዚህ ደስተኛ ሆኖ ከቶ አያውቅም ነበር!

ከሁለት ዓመታት በኋላ፡- በመጽሐፍ ቅዱስ ኮሌጅ እንድማር እግዚአብሔርእንደሚፈልግ ተሰማኝ፡፡

ቤተሰቦቼ፡- ‹‹የእኛ ልጅ፣ ዲግሪ የማይሰጥ ኮሌጅ ውስጥ ለምን ትገባለህ?የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ዲፕሎማ ከፍ ያለ ደመወዝአያስገኝልህም›› ሲሉ ተናገሩኝ፡፡

ይሁንና፣ እግዚአብሔርን ለመታዘዝ ወሰንሁ፡፡

ማስተማርን ማቆም እንዲሁም ተማሪዎቼን ደኅና ሁኑ ብሎ መሰናበትምን ያህል አሳዛኝ እንደ ሆነ ተሰማኝ!

በእምነታችሁ፣ በስብከታችሁ፣ በቅንዓታችሁ እናበፍቅራችሁ መልካም አድርጋችኋል፡፡ በመስጠትምረገድ እንዲሁ መልካም ማድረጋችሁን እርግጠኞች ሁኑ(2ኛ ቆሮንቶስ 8፡7)፡፡

መስጠት፡-

መጸለይ

በልዩ ልዩ ቋንቋዎች የሚናገሩ ወገኖችሁሉ እግዚአብሔርን እንዲያመሰግኑ

እንጸልያለን (መዝ. 67፡3)፡፡

ቃሉን በየስፍራው ሁሉ ስናደርስሳለን ስለ እኛ ጸልዩ(2ኛ ተሰ. 3፡1)፡፡

መላክ

Page 63: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

63

ለኮሌጅ ትምህርት ክፍያ ገንዘብ ለማግኘት መኪናዬን ሸጥሁ፡፡ ከዚያም ወደኮሌጁ በአውቶቡስ ሄድሁ፡፡

ዲፕሎማዬን ከተቀበልኩኝ በኋላ፣ ቤተ ክርስቲያናችን፣ ‹‹እባክህ ወደ ደቡብ

አፍሪካ ሂድ . . . በዚያም አስተምር፣

መስክርም›› አለችኝ፡፡

በእርግጥም ቤተሰቦቼ፣ ‹‹ስለ ምንአውስትራሊያን ለቅቀህ ትሄዳለህ? እዚሁ ብዙገንዘብ ማግኘት ትችላለህ!›› አሉኝ፡፡

ወንድሜ፣ ግን ‹‹መሄድ ትችላለህ፡፡ እኔ

ለወላጆቻችን እንክብካቤ አደርጋለሁ›› ብሎተናገረኝ፡፡

አሁን እንደ እኔ ‹ጥቅመ ቢስ› የሆነውንሰው፣ ለሕዝቦች ሁሉ ፍቅሩንና ደኅንነትንለማምጣት እግዚአብሔር እንዴት ተጠቀመበት!ስል እገረማለሁ (ኤር. 29፡11)፡፡

ስዋዚላንዳዊቷ ሚስ ጃቡ ሴሌ፡፡ ከአሥር ዓመታት በፊት ቤተ ክርስቲያናችንለዞስዋ ሰዎች እንድንመሰክር ስድስት የምንሆን ወጣቶችን ላከችን፡፡ 600 ኪሎሜትሩን በአውቶቡስ ተጓዝን፤ ከዚያም በዚያ ቤተ ክርስቲያን መሠረትን፡፡

ወደ አገራችን ከተመለስን በኋላ፣ እኔ፣‹‹ጌታ ሆይ፣ የዞስዋ ልጆችን ለማስተማር አንድ

ሰው ላክ፡፡ ነገር ግን እኔን አትላከኝ!›› እያልሁ

መጸለዬን ቀጠልሁ፡፡ ‹‹በዚያ ሆኜ የሰንበትትምህርት ቤት አስተማሪዎችን በማሠልጠን ተግባርተጠምጄያለሁ፡፡ በዚያ ላይ፣ እናቴን ትቼ መሄድአልችልም!›› ብዬ መጸለዬን ቀጠልኩ፡፡

ይሁንና፣ የማውቀው ነገር አለ፣ ይህም፡- እግዚአብሔር እኔን እየጠራኝ መሆኑነው፡፡ከእናቴ ጋር በጕዳዩ ላይ ለመወያየት ወሰንሁ፡፡ እጅግ ፈርቼ ነበር!እርሷ፣ ‹‹አይሆንም፣ ልጄ ሆይ፣ እፈልግሻለሁ፡፡ እዚሁ ሁኚ፡፡

አግቢ፡፡

ቤትህን ለቅቀህ እንድትሄድእግዚአብሔር ጠርቶህ ይሆናል፡፡

ዘፍጥ. 12፤1፤ 1ኛ ነገሥ. 19፡20፤ ማቴ.10፡37፤

ማር. 1፡20

በወንጌል ለመድረስመሥዋዕትነት መክፈል

አለብን፡፡

መስጠት

Page 64: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

64

ልጆችን ውለጂ፡፡›› እንደምትለኝ አውቅ ነበር፡፡

ነገር ግን እርሷ ይህን ከቶ አልተናገረችም፡፡ በዚህ ፈንታ እንዲህ አለችኝ፣ ‹‹ልጄሆይ፣ ከዚህ ቀደም ለማንም ያልነገርሁትን አንድ ነገር ልነግርሽ ይገባኛል፡፡ ልጃገረድበነበርሁበት ጊዜ፣ ‹አላገባም፤ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ እግዚአብሔርን አገለግላለሁ›ብዬ ወሰንሁ፡፡ ነገር ግን፣አ ገ ባ ሁ ፡ ፡ ይ ሁ ን ና ፣ለእግዚአብሔር፣ ‹ከልጆቼመካከል አንዱን/አንዷንውሰድና ያገልግልህ/ታገልግልህ›ስል ነገርሁት፡፡ አሁን፣ ልጄሆይ፣ አንቺ እግዚአብሔርን የምታገለግዪ እንደ ሆንሽ አያለሁ፡፡››

በሚያስገርም ሁኔታ ተቃቀፍን፣ አለቀስን፣ ደግሞም እግዚአብሔርን አመሰገንን!አንድ ደስ የሚል ሰው፣ ‹‹እንዳገባሽ እግዚአብሔር ተናግሮኛል›› አለኝ፡፡

‹‹አይሆንም፣›› አልሁ፣ ‹‹እኔ የወንጌል መልእክተኛ ልሆን ነው፡፡››እግዚአብሔር እንደ ጠራኝ ለሰዎች ነገርኋቸው፡፡ ‹‹እግዚአብሔር ይመስገን፡፡

እንረዳሻለን፤›› ይሉኛል ብዬ ተስፋ አድርጌ ነበር፡፡ ነገር ግን፣ በዚህ ፈንታ፣ ‹‹ሥራሽን

የምታቆሚ ከሆነ፣ እንዴት ልትኖሪ ነው?›› ብለው ጠየቁኝ፡፡

ተስፋ መቁረጥ በጣም ተሰማኝ፡፡ነገር ግን፣ ከዚያ በኋላ በየወሩ ለእኔ ጥቂት ገንዘብ ልትልክልኝ ቤተ ክርስቲያናችን

ቃል ገባች፡፡ አንዳንድ ጓደኞቼም እንዲሁ አደረጉ፡፡ ከዚያም የቤተ ክርስቲያን መሪዎችእጃቸውን ከጫኑብኝ በኋላ ላኩኝ (የሐዋርያት ሥራ 13)፡፡

ለዞሳ ልጆች የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮችን ልነግራቸው ስጀምር፣ የዞሳን ቋንቋበትክክል መናገር ባለመቻሌ ልጆቹ ሁሉ ሳቁ፡፡

ምዕራፍ 8

ዘራችንም ሆነ ትምህርታችንምንም አይፈይድም

እግዚአብሔር በደስታ የሚሰጠውን ይወዳልናእያንዳንዱ በልቡ እንዳሰበ ይስጥ፡፡ (2ኛ ቆሮ.

9፡7)

Page 65: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

65

ወደ የትኛውም ቤተ ክርስቲያን ስንገባ፣ ልናገኘው የሚገባ ነገር፡- ቀለማችንምሆነ በኅብረተሰቡ ውስጥ ያለን ከፍተኛም ሆነ ዝቅተኛ ደረጃ ከቁም ነገር ሳይገባ፣ በዚህያሉ ክርስቲያኖች ሞቅ ባለ ሁኔታ ይቀበሉናል፡፡

ነገር ግን እውነታው፡- ዛሬ አንዳንድ አብያተ ክርስቲያን ‹‹ከእኛ በታች ለሆኑ

ሰዎች›› የሚያሳዩት ፍቅር ትንሽ መሆኑ ነው፡፡

17በመልካም የሚያስተዳድሩ ሽማግሌዎች፣ይልቁንም በመስበክና በማስተማርየሚደክሙት እጥፍ ክብር ይገባቸዋል፡፡18 መጽሐፍ፡- ‹‹የሚያበራየውን በሬ አፉን

አትሰር፣›› ደግሞ ‹‹ለሠራተኛ ደመወዙ

ይገባዋል›› ይላልና (1ኛ ጢሞ. 5፡17-18)፡፡6ልንዞር መብት የለንም? ወይስ ሥራንለመተው መብት የሌለን እኔና በርናባስ ብቻነን?10የሚያርስ በተስፋ ሊያርስ የሚያበራይምእንዲከፍል በተስፋ ሊያበራይ ስለሚገባውበእውነት ስለ እኛ ተጽፎአል፡፡

እነዚህ እጆቼ በሚያስፈልገኝ ነገር ለእኔናከእኔ ጋር ላሉት እንዳገለገሉ እናንተታውቃላችሁ (የሐዋርያት ሥራ 20፡34)፡፡

በአንድ ላይ ሠሩ፣ ሥራቸው ድንኳንመስፋት ነበረና (የሐዋርያት ሥራ 18፡3)፡፡

ከእናንተ በአንዱ ስንኳ እንዳንከብድበትሌሊትና ቀን እየሠራን፣ የእግዚአብሔርንወንጌል ለእናንተ ሰበክን፡፡ (1ኛ ተሰ. 2፡9-13ተመልከት፡፡)12መዋረድንም አውቃለሁ መብዛትንምአውቃለሁ፣ በእያንዳንዱ ነገር፣ በነገርም ሁሉመጥገብንና መራብንም መብዛትንና መጕደልንተምሬአለሁ፡፡

የመጽሐፍ ቅዱስ እውነታ 2፡-የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት በመስበክጠንክረው ለሚሠሩ ሰዎች አብያተ

ክርስቲያናት በገንዘብ ሊደግፏቸው ይገባል፡፡

የመጽሐፍ ቅዱስ እውነታ 1፡-እግዚአብሔር እንድሄድና እንድሰብክከጠራኝ፣ አብያተ ክርስቲያን ገንዘብ

የማይሰጡኝ ቢሆንም እንኳ፣ ላደርገውይገባኛል፡፡

Page 66: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

66

ኢየሱስ እንዲህ ያለውን አድሎአዊነት ከቶ አልፈለገውም፡፡ እርሱ በዝቅተኛደረጃ ያሉትን ሰዎች (ማርቆስ 10፡42-52)፣ በከፍተኛ ደረጃ ያሉትን ሰዎች (ማቴ. 9፡18-19)፣ እንዲሁም በሁሉም ጎሳዎች ያሉትን ሰዎች (ዮሐንስ 4፡9፤ ማቴ. 8፡5)እንድንወድድ አስተምሮናል፡፡

የጌጥ ልብስም የለበሰውን ተመልክታችሁ፡- አንተስ በዚህ በመልካምስፍራ ተቀመጥ ብትሉት ድሃውንም፡- በዚያ ቁም ወይም ከእግሬመረገጫ በታች ተቀመጥ ብትሉት፣ ራሳችሁን መለያየታችሁአይደለምን? ክፉ አሳብ ያላቸው ዳኞች መሆናችሁ አይደለምን? (ከያዕ.2፡3-4)፡፡

የሐዋርያት ሥራ በሚጻፍበት ጊዜ፣ የነበረው ልማድ፡- ጌታና ባሪያ በአንድ ክፍልውስጥ ሆነው ሊመገቡ አይችሉም፤ እንዲሁም የተለያዩ ጎሳዎች በአንድ ላይ ሊበሉአይገባም የሚል ነበር፡፡

13በመቅደስ ነገር የሚያገለግሉ ከመቅደስየሆነውን ነ ገ ር እንዲ መገቡ፣በመሠዊያውም የሚጸኑከመሠዊያውእንዲካፈሉ ...፡፡14እንዲሁ ደግሞ ወንጌልን የሚሰብኩ

ከወንጌል ቀለብ እንዲቀበሉ ጌታደንግጐአል (1ኛ ቆሮ. 9፡6-14)፡፡

ወደ እስጳኝ በሄድሁ ጊዜ ሳልፍእናንተን እንዳይ አስቀድሜም ጥቂትብጠግባችሁ ወደዚያ በጕዞዬ እንድትረዱኝተስፋ አደርጋለሁ (ሮሜ 15፡24)...የዘላለም

እግዚአብሔር እንደ አዘዘው ለእምነትመታዘዝ ይሆን ዘንድ ለአሕዛብ ሁሉየተገለጠው ምሥጢር (ሮሜ 16፡26)፡፡

13 ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉንእችላለሁ፡፡ እርሱ ኃያል ያደርገኛልና፡፡

14ሆኖም በመከራዬ ከእኔ ጋር ስለ ተካፈላችሁ

መልካም አደረጋችሁ፡፡

15 የፊልጵስዩስ ሰዎች ሆይ፣ ወንጌልበመጀመሪያ ሲሰበክ ከመቄዶንያ በመጣሁ ጊዜከእናንተ ብቻ በቀር ሌላ ቤተ ክርስቲያንበመስጠትና በመቀበል ስሌት ከእኔ ጋርእንዳልተካፈለች እናንተ ደግሞ ታውቃላችሁ፡፡

16በተሰሎንቄ እንኳ ሳለሁ አንድ ጊዜና ሁለት

ጊዜ ያስፈለገኝን ሰድዳችሁልኝ ነበር፡፡

17በስሌታችሁ የሚበዛውን ፍሬ እንጂ

ስጦታውን ፈላጊ አይደለሁም (ፊልጵ. 4፡12-

17)፡፡

Page 67: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

67

ነገር ግን የሐዋርያት ሥራ እንዲህ ይላል፡- ያንን ልማድ መከተልንየመጀመሪያይቱ ቤተ ክርስቲያን እምቢ አለች፡፡ በዚህ ፋንታ፣ ከሁሉም ቀለምና ጎሳየሆኑ ክርስቲያኖች በአንድ ላይ አመለኩ፣ እንዲሁም በየቤታቸው አብረው ተመገቡ

(የሐዋርያት ሥራ 2፡9-11 እና 46)፡፡

ይህ አዲስ ነገር ነበረ!እንዲህ ያለውን መደባለቅ (መቀላቀል) ዓለም ከቶ አላየችውም፡፡

ከዚያም በቤተ ክርስቲያን ጠብ ነበር . . . ይህም ጠብ በግሪክኛ ተናጋሪአይሁድ እና በዕብራይስጥ ተናጋሪ አይሁድ መካከል የተከሰተ ነበር [የሐዋርያት ሥራ6፡1-7]፡፡ ነገር ግን፣ ጠቡን አበረዱት፡፡ ውጤቱም፡- ‹‹ክርስቶስ ኃይል እንዳለው . . .

ግሪኮችን እንዲወድ ዕብራውያንን በፍቅር ማስታጠቅ ይችላል፣›› የሚለውን በዚያከተማ የነበሩ እያንዳንዳቸው ተገነዘቡ፡፡ ከዚያም ብዙ የማያምኑ ሰዎች ወደ ክርስቶስተመለሱና ከቤተ ክርስቲያን ጋር ተቀላቀሉ፡፡

የሐዋርያት ሥራ 13 የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ከአንድ ጎሳ የተገኙ አልነበሩም፣ነገር ግን እጅግ አስደናቂ ድብልቆች ነበሩ፡፡ እነርሱም፡-

በርናባስና ጳውሎስ [አይሁዳውያን]፣

ስምዖንና ሉስዩስ [አፍሪካውያን]፣

ማናኤን [አውሮፓዊ] ነበሩ፡፡

ከኬንያ ለመላው ዓለም

‹‹ቤታችንን ለቅቀን ስንሄድ ሳለ፣ ራብንና ምቾት ማጣትንም እንታገሣለን፡፡ በሰዎቹ

መካከል እንኖራለን፡፡ ቋንቋቸውን እንማራለን፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን እናስተምራለን፡፡አንዳንድ ጊዜ ገንዘብ ለማግኘት ጊዜን እንወስዳለን - ነገር ግን አብዛኛውን ገንዘብ

የምናገኘው በዚህ በኬንያ ካሉ ክርስቲያኖች ነው፡፡ ባህር ማዶ ካሉ አብያተ ክርስቲያንእምብዛም ገንዘብ አንጠይቅም፡፡ የኬንያ ክርስቲያኖች ወንጌልን ለማዳረስ ገንዘብአላቸው ብለን እናምናለን፡፡››

Page 68: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

68

እነዚህን ሰዎች እርስ በርስ ያያያዟቸው ተፈጥሮአዊ ኃይላት አልነበሩም፡፡ ዓለምልታየው የምትችለው፡- ኅብረታቸው ከክርስቶስ የሆነ ተአምር መሆኑን ነው! [ኤፌ.

2፡14-16] [ገጽ 29]

ዛሬ . . . ?ዛሬ በአብያተ ክርስቲያናችን የዘረኝነት አስተሳሰቦችን ሰዎች ዘወትር ማየታቸው

በእውነቱ የሚያሳስተን ነው፡፡ ከዚያም፣ ‹‹የእነዚያ ሰዎች ክርስትና ልክ እንደ ክርስቶስ

አይደለም›› ይላሉ፡፡

ልጆች እንኳ፣ ‹‹ከሁሉም ዝርያዎች የተውጣጡ ሕዝቦች በሰማይ እንዴት በአንድላይ ይሆናሉ? ሲሉ ይጠይቃሉ፡፡ እዚህ በምድር ላይ በቤተ ክርስቲያን በአንድ ላይአይቀመጡም፡፡››

እንለወጥ!በክርስቶስ ኃይል፣ ቀለማችን፣ ጎሳችን ወይም ትምህርታችን ምንም ይሁን፣ አንድ

እንሁን፡፡

‹‹ይህ ችግራቸው ነው - ሊለወጡ ይገባል፣›› ከቶ አንበል፡፡

‹‹ልንለወጥ ይገባናል - እኔ ልለወጥ ይገባኛል፣›› የሚለውን አምነን እንቀበል፡፡

‹‹ክርስቶስን ከተቀበልሁ በኋላ፣›› ትላለች ደቡብ አፍሪካዊቷ ጆይስ እስኮት፣

‹‹እግዚአብሔር በባህሌ ምክንያት፣ በቀለሜ ምክንያት የበላይ እንደ ሆንሁ በማሰቤምን ያህል ተሳስቼ እንደ ነበረ አሳየኝ፡፡ አሁን እኔ ከከንቱ አስተሳሰብ ነፃ መሆንን

እያጣጣምሁ ነኝ፡፡››

ከቤቴ ርቄ . . . ወይም በቤቴ አቅራቢያ . . . እግዚአብሔርን አገለግላለሁ፡፡

ከቤቴ ርቄ፡- ጌታ ሆይ፣ ቤቴን ትቼ ሩቅ ስፍራ ሄጄ እንዳገለግልህ ጠርተኸኝ ከሆነ -አደርገዋለሁ፡፡ በጸሎትና በገንዘብ እንዲረዱኝ አብያተ ክርስቲያናትን እና ወዳጆቼንእጠይቃለሁ፡፡ ገንዘብ በማልቀበልበት ጊዜም፣ ጠንክሬ በመሥራት ጥቂት ገንዘብ አገኛለሁ፡፡ምንም የሚያቆመኝ ነገር የለም፡፡ ወደምትልከኝ ስፍራ እሄዳለሁ፡፡

በቤቴ አቅራቢያ፡- ጌታ ሆይ፣ እቤቴ አካባቢ እንዳገለግልህ የምትፈልግ ከሆነ፣ አደርገዋለሁ፡፡ሰዎችን የምረዳበትን መንገድ እፈልጋለሁ፡፡ በድፍረት እመሰክራለሁ፡፡ ደግሞም ወደ ሩቅ ቦታለላክሃቸው አማኞች ብዙ ገንዘብ እሰጣለሁ፡፡

እግዚአብሔር ሠራተኞችን እንዲልክጸልዩ

(ማቴ. 9፡38)፡፡

መልካሙን የምሥራች

እንዲሰብኩ ሰዎችን ላኩ (ሮሜ10፡13-15)፡፡

በደስታ ስጡ(2ኛ ቆሮ. 9፡7)፡፡

çMÃL¡eØ

^eI

H>ɨÃUK?KA‹”

Page 69: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

69

አዎን፣

የመጀመሪያው ጸሎታችን፣‹‹ጌታ ሆይ፣ ለውጠኝ››የሚል ሊሆን ይገባል፡፡

ከዚህም በኋላ፣ ‹‹አብያተ ክርስቲያናችንን፣ ሕዝባችንን . . . ›› ለውጥ ብለንመጸለይ እንችላለን፡፡

አዲስ አማኝ ወደ ቤተ ክርስቲያናችን በሚቀላቀልበት ጊዜ፣ ‹የተለያዩ› መስለውከሚታዩት ሰዎች ጋር ሲደባለቅ ምቾት ላይሰማውይችላል፡፡

ይህን ሰው ልንረዳው እንችላለን፡፡እንዴት? ምሳሌ በመሆን፡፡ክርስቶስን በአንድ ላይ ስናገለግል፣ለእርስ በርሳችን ስንጸልይ፣በአንድ ላይ ስንመገብ፣በአንድ ላይ ሆነን እየተጫወትንስንሳሳቅ፣

በሚመለከትበት ጊዜ፡- ‹‹ሁሉም ሰዎች ወንድሞቼና እኅቶቼ ናቸው፣››የሚለውን ይገነዘባል፡፡

1) በአገራችን፣ ሰዎች አንዳንድ ጎሳዎችን በንቀት ይመለከታሉን? የተለያዩ ቋንቋተናጋሪ የሆኑ ጐሳዎችን ጭምር በንቀት ይመለከታሉን? አንዳንድ ምሳሌዎችንስጥ፡፡

2) በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ፣ የቱም ዓይነት ቀለም፣ መደብ፣ ቋንቋ . . .ላላቸው ሰዎች እውነተኛ የሆነ ፍቅር አለን? ይህን እንዴት ልናሻሽለው እንችላለን?

3) በከተማችን እኛ ክርስቲያኖች ከሌሎች ጎሳዎች/መደቦች ጋር ወዳጅነትንመመሥረት እንችላለን? በቤታችን እና በቤተ ክርስቲያናችን ከእኛ ጋር ኅብረትእንዲያደርጉ ልናበረታታቸው እንችላለን?

እዚህ ላይ ዘረኝነትም ሆነ መደብ የለም፡፡በክርስቶስ እናንተ ሁለችሁ አንድ ናችሁ (ቈላ. 3፡11)፡፡

ተወያዩበት

Page 70: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

70

እግዚአብሔር የሚያዳላው ዘር የለውም (የሐዋ. 10፡34)፡፡

ምዕራፍ 9

ኢየሱስን እንዴት መቀበል እንደሚቻል ለወዳጆችህልትነግራቸው ትችላለህ

‹‹ለጓደኞቼ ስለ ኢየሱስፈጽሞ ልነግራቸው አልችልም፡፡እንዴት እንደ ሆነ አላውቅም፡፡ደግሞም እፈራለሁኝ፣›› ብለህታስብ ይሆናል፡፡

እንንገርህ፡- አትጨነቅ፡፡ ልታደርገው ትችላለህ፡፡ እነዚህን 4 ደረጃዎችን ብቻተጠቀም፡፡

ደረጃ 1ቅን ክርስቲያን ሁን

Page 71: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

71

ክርስቶስን ተቀበል - ከዚያም ከክርስቲያን እንደሚጠበቅበት ባለ ሁኔታተመላለስ፡፡

ኢዩኤል ለእኅቱ ሊመሰክርላት በሞከረ ጊዜ፣ እርሷ ‹‹እንዴት እንደምትመላለስ

ስላየሁህ አንተን ላደምጥህ አልችልም!›› ስትል መለሰችለት፡፡

ያ በአንተ ላይ ከቶ አይፈጸም፡፡ ምሳሌ ሁን፡፡ ሰዎችን ውደድ፡፡ ደግሞም ንጹህየሆነ ሕይወት ይኑርህ (ቲቶ 2፡7)፡፡በቤት ውስጥ፡- ለእያንዳንዱ በቤት ውስጥ ላለ ሰው የምትረዳ ሰው ሁን፡፡ አንድን ሰው

ከጐዳኸው፣ ይቅር እንዲልህ/እንድትልህ ጠይቅ፡፡በሥራ ስፍራ፡- ሥራህን እጅግ በደንብ ሥራ፡፡ እነዚያ ያልተማሩትንም ሰዎች ጨምሮ፣

ለሁሉም ሠራተኞች ሩኅሩኅ ሁን (ሮሜ 12፡16)፡፡

ለአንድ ጓደኛህ በምትመሰክርበት ጊዜ፣ ‹‹አንተ በታማኝነት ኢየሱስን ስትከተል

ስላየሁህ፣ ላደምጥህ እችላለሁ፣›› የሚልህ ከሆነ፣ እጅግ በጣም ግሩም ይሆናል፡፡

ደረጃ 2ለጓደኞችህ መልካሙን የምሥራች ንገራቸው

ለጓደኛህ ከመመስከርህ በፊት፣ ለእርሱ በየቀኑ ጸልይለት፡፡ ደግሞምበሚያስፈልጉት ነገሮች እርዳው፡፡ ቸር ሁን፡፡

ከዚያም አንድ ቀን፣ ‹‹ዘላለማዊ ሕይወት እንዴት እንዳገኘሁ ልንገርህ?››በማለት በቀላሉ ጠይቀው፡፡

እርሱም ‹አዎን፣› ካለህ፣ ይህትልቅ ነገር ነው፡፡ ነገር ግን ወደመንግሥተ ሰማያት እንዴት እንደሚኬድልትነግረው ትችላለህ? አዎን፣ ትችላለህ፡፡ለጓደኞችህ ልታሳያቸው የሚገቡ ሁለትነገሮች ብቻ አሉ፡፡

ሀ) ችግሮቹን አሳየውለጓደኛህ እንዲህ በለው፡- እግዚአብሔር ይወድድሃል፡፡ ከእርሱ ጋር በመንግሥተ

ሰማይ እንድትኖር ይፈልጋል፡፡ ነገር ግን ችግሩ፡- አንተ ኃጢአተኛ ነህ፡፡ አዎን፣የሰው ልጆች ሁሉ ኃጢአተኞች ናቸው፡፡ ኃጢአትህ ከእግዚአብሔርለይቶሃል፡፡ እርሱ ቅዱስ ነው፡፡ ኃጢአት መንግሥተ ሰማያት እንዲገባ ሊፈቅድአይችልም፡፡

Page 72: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

72

ምን ይመስልሃል? መንግሥተ ሰማያት ትገባ ዘንድ ኃጢአቶችህን እንዴትማስወገድ ትችላለህ?

ጓደኛህ ምናልባት ይህን ይመልሳል፡- የእግዚአብሔርን ትእዛዛት ለመታዘዝ ከተጋሁ፣ምናልባት ወደ መንግሥተ ሰማይ እንድገባ ይፈቅድልኛል፡፡

አንተም እንዲህ ትለዋለህ፡- ሮሜ 3፡23ን እናንብብ፡፡ ሮሜ 3፡23 ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋል፡፡ ሁሉም ቅዱስ ከሆነው

እግዚአብሔር ርቀዋል ይላል፡፡ያም ማለት፡- የእግዚአብሔርን ሕጎች ለመታዘዝ የጣሩ ሁሉ - እነርሱምእንደዚሁ ኃጢአትን ሠርተዋል፡፡ስለዚህ፣ የእግዚአብሔርን ሕጎች በመጠበቅ አሁንም መንግሥተ ሰማይመግባት የምትችል ይመስልሃልን?[‹‹በኃጢአቶቼ ምክንያት ወደ መንግሥተ ሰማይ ሳይሆን፣ ወደ ገሃነም መሄድ

ይኖርብኛል፣›› የሚለውን ማየት እስኪችል ድረስ ከጓደኛህ ጋር ተነጋገር፡፡

ያንን ካየ በኋላ፣ መልካሙን የምሥራች አሳየው፡፡]

ለ) መልካሙን የምሥራች አሳየውአንተ፡- ውድ ጓደኛዬ፣ አንተ ተስፋ የሌለህ እንደ ሆንህ ታስባለህ፣ ነገር ግን መልካም

የሆነው የምሥራች እዚህ አለ፡፡ መንግሥተ ሰማይ እንድትገባ ኢየሱስለአንተ መንገድን አበጅቶአል፡፡

. ኢሳይያስ 53፡5-6 የእግዚአብሔርን ሕጎች ተላልፈናል፡፡ ልንቀጣ ይገባናል፡፡ ነገርግን እግዚአብሔር ቅጣታችንን በልጁ ላይ አደረገ፡፡ ሕጉንበመተላለፋችን ምክንያት አካሉ ተወጋ፡፡

. ዮሐንስ 3፡16 እግዚአብሔር እጅግ ይወድድሃል፤ ልጁን፣ ኢየሱስን ሰጥቶሃል፡፡በኢየሱስ ለማመን ከመረጥህ፣ ወደ ገሃነም አትሄድም፣ ነገር ግንዘላለማዊ ሕይወት ይኖርሃል፡፡

ወዳጄ ሆይ፣ ይህ መልካሙ የምሥራች ነው! አዎን፣ ኢየሱስን እንደ ጌታህ እናየግል አዳኝህ አድርገህ ለመቀበል ከመረጥህ፣ አዎን፣ ዛሬ እግዚአብሔር ኃጢአትህንያስወግዳል ደግሞም መንግሥተ ሰማያት የምትገባበትን ተስፋ ይሰጥሃል፡፡

ደረጃ 3ዛሬ ኢየሱስን እንዲቀበል ጓደኛህን ጋብዘው

Page 73: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

73

‹‹ወዳጄ ሆይ፣ ዛሬ ኢየሱስን ልትቀበል ትችላለህ፡፡ አሁን እርሱን እንደ ጌታህና

የግል አዳኝህ አድርገህ ልትቀበለው ትመርጣለህ?›› በለው፡፡

‹አዎን፣› ካለ፣ ‹‹ብልሃት ያለበት ምርጫ ነው! አሁኑኑ እርሱን ለመቀበል እንደ

መረጥህ ንገረው፣›› በለው፡፡ ‹‹እንዴት ልትነግረው ትችላለህ? እንደዚህ ያለ ጸሎት

አድርግ››፡-

‹‹ለእግዚአብሔር ልትነግረው የምትፈልገው ያንን ከሆነ፣ አሁኑኑ እንደዚያ

አድርገህ ጸልይ፡፡ የገዛ ራስህን ቃሎች ተጠቀም፡፡››ከጸለየ በኋላ፣ እንደዚህ ባለ ሁኔታ ከእርሱ ጋር ተነጋገር፡-

አንተ፡- ወዳጄ ሆይ፣ አሁን ብትሞት፣ ወደ መንግሥተ ሰማያት ነው ወይስ ወደ ገሃነምየምትሄደው?

ጓደኛ፡- እኔ አላውቅም . . . ምናልባት ወደ መንግሥተ ሰማያት እገባ ይሆናል???

አንተ፡- 1ኛ ዮሐንስ 5፡13ን አንብብ፡፡ እንዲህ ይላል፡- በኢየሱስ ክርስቶስ የሚያምኑአማኞች ዘላለማዊ ሕይወት እንዳላቸው ያውቃሉ፡፡

ዛሬ በኢየሱስ ለማመን መርጠሃል፡፡ ስለዚህ፣ ምን ታውቃለህ?

ጓደኛ፡- እኔ ወደ መንግሥተ ሰማይ እንደምሄድ አውቃለሁ - ወደ ገሃነም አይደለም፡፡ያ ትክክል ነው?

የክርስቶስ ፍቅር ግድ ይለናል (2ኛ ቆሮንቶስ 5፡14)

Page 74: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

74

አንተ፡- አዎን፣ 1ኛ ዮሐንስ 5፡13 የሚለው ይህንኑ ነው፡፡ ዛሬ ኢየሱስ ዘላለማዊ

ሕይወት ሰጥቶሃል! ዛሬ ኢየሱስ በመንግሥተ ሰማይ መንገዱ ላይእንዳስቀመጠህ ለአንድ ሰው ንገር፡፡

አሁን አንተ ክርስቲያን ነህ፤ ስለዚህም ሕይወትህ በእንደዚህ ያለ ሁኔታይለወጣል፡-

"ክ" እና "እ" የሚባሉ ሁለት ወንድማማቾች በአንድ ላይ ይኖሩ ነበር፡፡

"ክ" መልካም የሆነ ወጣት ነበር፡፡ ስሕተት ፈጽሞ አያውቅም፡፡

"እ" በኃጢአት ውስጥ የሆነ ነበር፡፡ አንድ ቀን "እ" ሰክሮ ሳለ፣ ሰውን ለመግደልጩቤውን ተጠቀመ፡፡ ከዚያም ወደ ቤቱ እየሮጠ ሄደ፡፡ በዚያም ወንድሙን፣‹‹እርዳኝ፡፡ ፖሊሶች እየመጡ ናቸው፡፡ እባክህ ይህን ጩቤ ውሰድ፡፡ እባክህን በደም

የተጨማለቀውን ሸሚዜን ልበስ›› ብሎ ለወንድሙ ነገረው፡፡

ፖሊሶች "ክ"ን ከጩቤውና በደም ከተለወሰው ሸሚዙ ጋር አዩት፡፡ ወደ እስር

ቤትም ወሰዱት፡፡ በኋላም ዳኛው "ክ" መሞት አለበት አለ፡፡

"እ" በጣም አዘነ፡፡ "ክ"ን ለዳኛው መሞት የሚገባኝ እኔ እንደ ሆንሁ

ንገረው›› አለው፡፡

"ክ" ሲመልስ፣ ‹‹በፍጹም፣ እኔ የአንተን ሞት እወስዳለሁ፡፡

አንተ የእኔን ሕይወት ልትኖርልኝ ይገባል›› አለው፡፡

"ክ" ተገደለ፡፡

በሚቀጥለው ቀን "እ" ፣ ‹‹ወንድሜ ስለ እኔ ሞቷል፡፡ እኔ ስለ እርሱ ልኖር

ይገባኛል፣›› ሲል ወሰነ፡፡ ‹‹ዛሬ ወንድሜ ምን ያደርግ ነበር? አይሰክርም ነበር፡፡

ሰዎችን ይረዳ ነበር፡፡››

ስለዚህ፣ "እ" ወላጅ የሌላቸውን ልጆች መርዳት

ጀመረ፡፡ ደግሞም የሴት ጓደኛውን ‹‹ከጋብቻ በፊት በፍጹምየግብረ ሥጋ ግንኙነት

አላደርግም፣›› አላት፡፡ ከዚያም የሠረቀውን ሬዲዮ መለሰ፡፡

Page 75: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

75

ደረጃ 4

የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶችን ለጓደኛህ አሳየውሀ) በአዲሱ ሕይወትህ ሳለህ፣ ለኢየሱስ፣ ‹‹በኃይልህ የበለጠ ርኅሩኅ፣ ሰዎችን

የምረዳ፣ ታጋሽ እና ራስ ወዳድ ያልሆንሁ እሆናለሁ፡፡ ለኃጢአት ‹አይሆንም›፣ለአንተ ‹እሺ› እላለሁ›› በሉት (ዮሐንስ 12፡46፤ ገላ. 5፡22-23)፡፡

በኃጢአት ከወደቅህ፣ ተናዘዘውናከእርሱ ተመለስ፡፡

ሰይጣን፣ ‹‹በዚህ ኃጢአት ምክንያት፣አንተ በመንግሥተ ሰማይ መንገድ ላይአይደለህም›› ይልሃል፡፡

ነገር ግን እግዚአብሔር፣ ‹‹ኢየሱስ ስለኃጢአትህ ተሠቃይቷል፡፡ ስለዚህ፣ አሁንም

አንተ በመንግሥተ ሰማይ መንገድ ላይ ነህ፡፡ ከኃጢአት ሽሽ፡፡

እኔ አባትህ ነኝ፡፡ ታዘዘኝ፣›› ይልሃል (ሮሜ 6፡1-2፤ 1ኛ ዮሐንስ 1፡9፤ ኤፌ. 4፡17-

32፤ 1ኛ ጴጥ. 1፡14-19፤ 4፡3-5፤ ቈላ. 3፡1-21፤ ዘዳግ. 28)፡፡ሰይጣን ‹‹ተመልሰህ ና፣ ኃጢአት ደስታን ይሰጣል›› ብሎ ይነግርሃል፡፡

እግዚአብሔር፣ ‹‹ኃጢአት ደስ የሚል ይመስላል፡፡ ነገር ግን፣ ኃጢአትን

የተከልኸው ከሆነ፣ ችግሮችን ታጭዳለህ፣ [በአካልህ ላይ መከራ፣ ወይም በአንተና

በምትወድዳቸው ጓደኞችህ መካከል ችግር፣ ወይም ሌሎች ችግሮች ይመጣሉ]፡፡ኃጢአት በምድር ላይ በአንድ ሰው ሕይወት ውስጥ ተጨማሪ ችግሮችን ሁልጊዜያመጣል›› (ገላ. 6፡7-8)፡፡

Page 76: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

76

አንዳንድ ሰዎች፣ ‹‹እኔ ኢየሱስን እወድዳለሁ፣›› ይላሉ፤ ይሁንና፣ ሐሰት

መናገርን፣ መስከርን፣ ዝሙት መፈጸምን . . . ይቀጥላሉ፡፡እ ው ነ ተ ኞ ች ክ ር ስ ቲ ያ ኖ ች

ይመለሳሉ፡፡ ኃጢአትን መተው ይወድዳሉ(2ኛ ጢሞ. 2፡19)፡፡

ክርስቶስን መታዘዝ ወደ ኑሮአችን እናቤቶቻችን ደስታንያመጣል (ኤፌ. 5፡33፤ ምሳሌ

5፡18-23)፡፡

ለ) መጽሐፍ ቅዱስ፡- መጽሐፍ ቅዱስንበደንብ የምታስተምር ቤተ ክርስቲያን አባልሁን፡፡ በተጨማሪም፣ መጽሐፍ ቅዱስህንበቤትህ አጥና፡፡ ከዮሐንስ ወንጌልጀምር፡፡ እያነበብህ ሳለህ፣ ማስታወሻዎችንጻፍ፣ ‹‹በዚህ ምዕራፍ ውስጥ ምን ተማርሁ?እንዲሁም ሕይወቴ እንዴት ሊለወጥይገባል?›› የሚሉትን በተመለከተ ማስታወሻዎችን ጻፍ፡፡

[የኢየሱስ ኃይል የሚለው መጽሐፋችን ሊረዳህይችላል፡፡ ገጽ 127ን ተመልከት፡፡]

ሐ) የስሕተት ትምህርቶችን አስወግድ፡- አንዳንድ ሰባኪያን መልካም መስለውይታያሉ፤ ነገር ግን፣ ሙሉውን መጽሐፍቅዱስን አያስተምሩም፡፡ በዚህ ፋንታ፣የሚወድዷቸውን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችመዝዘው ያወጣሉ፡፡ በእያንዳንዱ እሑድ፣‹‹እምነት ካላችሁ፣ ሀብታም ትሆናላችሁ፣››ወይም ‹‹መንፈስ ቅዱስ በውስጣቸውያደረባቸው ሰዎች ትንቢት የሚናገሩና በልሳንየሚናገሩ ሰዎች ብቻ ናቸው፤›› ሊሉይችላሉ፡፡

እውነቱ፡- ከኦሪት ዘፍጥረት እስከዮሐንስ ራእይ ባለው ክፍል ውስጥ

በክርስቶስ አማኞች እንደሆናችሁ፣ ሁሉንም እኩልውደዱ (ያዕ. 2፡1)፡፡

በአኗኗርህ፣በአነጋገርህ፣በፍቅርህለአማኞቹ

ምሳሌ ሁን(1ኛ ጢሞ. 4፡12)፡፡

Page 77: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

77

መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረው ዋናውጉዳይ፡- ክርስቶስን ከተቀበልህ በኋላ፣በመንፈስ ቅዱስ ፍሬዎችእደግ የሚለው ነው (ገላ. 5፡22-23፣ 2ኛ ጴጥ. 1፡5-9)፡፡

እነዚያ ፍሬዎች በጣም ጠቃሚ ናቸው፡፡ አንድ ሰው የጸጋ ስጦታዎች ካሉት[1ኛ ቆሮ. 12፡10]፣ ነገር ግን ፍሬ ከሌለው [ገላ. 5፡22]፣ ስጦታዎቹን ለራሱ ጥቅምሲል ለታይታ ያውላቸዋል፡፡ በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ክፍለ ጊዜ፣ አንድ ሰውወድቆ እንግዳ በሆነ መንገድ ቢናገር፣ ምናልባት እናንተ፣ ‹‹እርሱ መንፈሳዊ ነው››ብላችሁ ታስቡ ይሆናል፡፡ ነገር ግን መጠየቅ ያለበት፡- ከሰኞ እስከ ዓርብ በቅንነት፣ራስን በመግዛት፣ እንዲሁም በሌሎች የመንፈስ ፍሬዎች የተሞላ ነውን? ካልሆነ፣ በዚያሰው ውስጥ ተግባራቱን የሚፈጽመው መንፈስ ቅዱስ አይደለም፡፡

ይህን አድርግ፡- የበለጠ ክርስቶስን እየመሰልህ እንድትሄድ፣ መጽሐፍ ቅዱስንአጥና፣ ደግሞም በመንፈስ ፍሬዎች እደግ፡፡

መ) ጓደኞችህ፡- ጓደኞችህ ወደ ኃጢአት እንዲጎትቱህ አትፍቀድላቸው፡፡ በዚህ ፈንታለእያንዳንዳቸው፣ ‹‹አንድ ቀን በኃጢአቶቼ ምክንያት እኔ ወደ ገሃነም እየሄድሁእንደ ሆነ ሊያሳየኝ እግዚአብሔር መጽሐፍ ቅዱስን ተጠቀመ፡፡ እኔም ወደኢየሱስ ጸለይሁ፡፡ እርሱ ከገሃነም አዳነኝ፡፡ አሁን ሕይወቴ አዲስ ነው! እናንተምእንደዚሁ ኢየሱስን መቀበል ትችላላችሁ፡፡ ዮሐንስ 3፡16 እንዲህይላል . . . ›› በላቸው፡፡

ሠ) ቤተ ክርስቲያን ቤተሰብህ ናት፡፡ ትምህርታችንም ሆነ ዘራችን ምንም ይሁን ምን፣እኛ የቤተ ክርስቲያን አባላት ወንድምና እኅት ነን፡፡በየእሑዱ በአንድ ላይ ሆነን እግዚአብሔርን ማምለክ እንወድዳለን፡፡ በቤት

ለቤት ኅብረት (ሴል ግሩፕ) ስብሰባዎች [ገጽ 89]፣ መጽሐፍ ቅዱስን እያጠናንበደስታዎቻችንና በኀዘኖቻችን ላይ እንወያያለን፡፡ ችግረኛ ለሆኑት በደስታ ምግብን/ገንዘብን እንሰጣለን፡፡

ለፍቅርና ለመልካም ሥራ እንድንነቃቃ እርስ በርሳችን እንተያይ፡፡መሰባሰባችንን አንተው (ዕብ. 10፡24-25)፡፡

ረ) በውኃ ተጠመቅ፡፡ ጥምቀት ማለት፣ ‹‹ወደ ክርስቶስ ተመልሻለሁ፡፡ አዲስ ሕይወት

ጀምሬአለሁ፣›› ማለት ነው፡፡

ተወያዩበት

Page 78: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

78

በምትጠመቅበት ጊዜ፣ ቤተ ክርስቲያን እንዲህ የሚል ወረቀት ልትሰጥህትችላለች፡-

1) አማኞችን አንድ ለአንድ እንዲመሰክሩ እንዴት ማበረታታት እንችላለን?2) በምትመሰክርበት ጊዜ፣ ደረጃ ሀ) እና ለ) ምንድን ነው?

ደረጃ ሀ) ‹‹በኃጢአቶቼ ምክንያት፣ ወደ መንግሥተ ሰማይ ሳይሆን፣ ወደ ገሃነም

መሄድ ይገባኝ ነበር››የሚለውን እንዲያይእርዳው (ገጽ 83)፡፡

ደረጃ ለ) ‹‹ኢየሱስ ኃጢአትህንይቅር ሊል፣ ደግሞምበመንግሥተ ሰማይመ ን ገ ድ ላ ይሊያስቀምጥህ ይችላል›› የሚለውን መልካሙን የምሥራች አሳየው

(ገጽ 83)፡፡

ነገር ግን መንፈስቅዱስ በእናንተ ላይበወረደ ጊዜ ኃይልንትቀበላላችሁ . . .

ምስክሮቼትሆናላችሁ

(የሐዋ. 1፡8)፡፡

Page 79: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

79

ምዕራፍ 10

ለቤተ ክርስቲያናችሁ የሚሆኑ24 ኃይለኛ አሳቦች

ኢየሱስ እንዲህ አለ፣እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ፣ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም

እያጠመቃችኋቸውያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው

(ማቴ. 28፡19-20)፡፡

ቤተ ክርስቲያናችሁን ይህን በትክክልእንድታከናወን የሚረዷት 24 አሳቦችእዚህ ቀርበዋል፡፡

1. ግባችንን ማጕላትግባችን፡- ሰዎችን ወደ ኢየሱስ

ማምጣት ነው (ዮሐንስ 1፡40-46)፡፡

በቤተ ክርስቲያን ያሉ ሴቶች የጠፉሰዎችን እንዴት ወደ ክርስቶስ ማምጣት ይቻላል በሚለው ላይ ዕቅድ ማውጣትይኖርባቸዋል፡፡ ወንዶች ብዙ ወንዶችን ወደ ክርስቶስ እንዴት ማምጣት ይቻላልበሚለው ላይ ዕቅድ ማውጣት ይኖርባቸዋል፡፡ የሰንበት ትምህርት ቤት እንዴት ማደግአለብኝ በሚለው ላይ ዕቅድ ማውጣት አለበት፡፡ ሁላችንም ከሰዎች ጋር ጓደኝነትንልንመሠርትና ኢየሱስን እንዲቀበሉ ልንጋብዛቸው ይገባል፡፡ [ገጽ 78-87]

በሌሎች ነገሮች እጅግ የተወጠርንና የተዋከብን አንሁን፡፡ ሰዎችን ወደ ኢየሱስማምጣት! የሚለውን እናጕላ፡፡

2. አባላትን ማሠልጠንእያንዳንዱ ቤተ ክርስቲያን አንድ የሥልጠና ኮርስ ሊኖረው ይገባል፡፡ የትምህርቱ

አሰጣጥ ዝርዝር የሚከተሉትን ሊያካትት ይችላል፡-

አንተ ወንድ ከሆንህ እና ለሴትየምትመሰክር ከሆነ፣ በእርሷ ላይ ያለህፍላጎት ወሲባዊ መሆኑን የሚያሳይአንዳችም ነገር አታድርግ፡፡

ለወንዶች የሚመሰክሩ ሴቶችም እንደዚሁሊሆኑ ይገባል፡፡

Page 80: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

80

ሀ) እንዴት ቅዱስና ኃይለኛ ልትሆን ትችላለህ? (ቈላ. 3፤ ገላ. 5፡19-23)፡፡ለ) እንዴት መዳን ይቻላል የሚለውን ለማሳየት መጽሐፍ ቅዱስህን እንዴት

እንደምትጠቀም፡፡ [ገጽ 78-87]ሐ) ቤተ ክርስቲያናችን በአገራችን ውስጥ ያሉ ሌሎች ቋንቋዎችን የሚናገሩ

ወገኖችን እንዴት በወንጌል ልትደርሳቸው ትችላለች? [ገጽ 48-61]

መ) ቤተ ክርስቲያናችን ወንጌልን ወደ ሌሎች ሕዝቦች እንዴት ልትልክ ትችላላች?[ገጽ 61-69]

3. የቤት ለቤት ኅብረት ቡድኖችን መጀመርብዙዎቹ ያልዳኑ ሰዎች ቤተ ክርስቲያን መግባት አይፈልጉም፣ ነገር ግን በቤት

ውስጥ የሚካሄዱ ስብሰባዎችን ለመካፈል ፈቃደኞች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ስለዚህ በ5 ቤቶች ውስጥ የቤት ለቤት ኅብረት ቡድን ስብሰባዎችን ጀምሩ፡፡

በየማክሰኞም [ሆነ በሌላ ቀን] መገናኘትን ጀምሩ፡፡ በእያንዳንዱ የቤት ለቤት ኅብረት

ቡድን ውስጥ ‹‹የቤት ለቤት ኅብረት ቡድን አስተማሪ›› መኖር አለበት፤ ከእርሱምጋር ጥቂት የቤተ ክርስቲያን አባላትና ጥቂት ያልዳኑ በቤቱ አቅራቢያ ያሉት ሰዎችአብረው መኖር አለባቸው፡፡

የሚያስተምሩትን ያሳያቸው ዘንድ አንድ መጋቢ ወይም ዲያቆን ከአምስቱ የቤትለቤት ኅብረት ቡድን አስተማሪዎች ጋር መገናኘት አለበት፡፡ ለመጀመርም አንዱመንገድ፡-የኢየሱስ ኃይል በሚለው መጽሐፋችን ላይ ያሉትን ትምህርቶችማስተማር ነው፡፡ ያም ወደ 25 ሳምንታትን ይፈጃል፡፡

4. ቤት- ለቤት መመስከርአንዳንድ ሰዎች ቤተ ክርስቲያንም ሆነ በቤት ለቤት የሚደረጉ

ስብሰባዎችን መካፈልን የማይፈልጉ ናቸው፡፡ ለምን?ምክንያቱም ክርስቶስ ምን ያህል አስደናቂ መሆኑን አያውቁም፡፡

ስለዚህ፣ ሰዎችን በቤታቸው ሳሉ ለመጐብኘትየቤተ ክርስቲያን አባላት ሁለት ሁለት ሆነው መሄድይኖርባቸዋል (የሐዋ. 20፡20)፡፡ ይህ ከባድ ሥራ ነው፡፡ብዙ ቤተሰቦች ክርስቲያኖችን አይቀበሉም፡፡ ስለዚህ፣እርስ በርስ ተበረታቱ በጽናትም ጸልዩ (1ኛ ተሰ. 5፡11)፡፡

Page 81: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

81

5. በየስፍራው ስለ ኢየሱስ ተናገሩ (የሐዋ. 8፡4)ሰዎችን ወደ ኢየሱስ በማምጣት ረገድ የማይሳካላቸው ምን ዓይነት አማኞች

ናቸው? መልስ፡- በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ቆመው የሚመሰክሩ፣ ነገር ግን ከዚያ ሕንጻውጭ ለማንም ስለ ኢየሱስ የማይናገሩ ሰዎች ናቸው፡፡

ሰዎችን ወደ ኢየሱስ በማምጣት ረገድ የሚሳካላቸው አማኞች ምን ዓይነትናቸው? በየሄዱበት ስፍራ ሁሉ ስለ እርሱ የሚናገሩ አማኞች ናቸው፡፡

በሆስፒታል ያለ ጓደኛቸውን በሚጐበኙበት ጊዜ፣ ስለ ኢየሱስ ለሌሎችሕሙማን ለመናገር ጊዜን ይወስዳሉ፡፡

ከጐረቤቶቻቸው ጋር ወዳጅነትን ይመሠርታሉ፣ ደግሞም ወደ ቤት ለቤትኅብረት ቡድን ይጋብዙዋቸዋል፡፡

በሥራ ስፍራ ክርስቲያን ሊመላለስበት በሚገባ መልኩ ይመላለሳሉ፣ ደግሞምበምሳ ጊዜ መጽሐፍ ቅዱስን ለማጥናት ሰዎችን ይጋብዛሉ፡፡

በቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ ሰዎችን ያጽናናሉ፣ ደግሞም በገሃነም ፈንታ ወደመንግሥተ ሰማይ መንገድ ላይ እንዴት መገኘት እንደሚቻል ለእያንዳንዱ ሰውይናገራሉ [ገጽ 81-82] (2ኛ ቆሮ. 5፡20)፡፡

6. በአንድ ጊዜ ለአንድ ሰው መስክርሰዎችን ወደ ክርስቶስ ለማምጣት ስብከት ኃይለኛ መንገድ ነው፡፡ ሌላው

ኃይለኛ መንገድ፡- ምስክርነት ነው፡፡‹‹ምስክርነት›› ማለት፡- ከጓደኛህ ጋር ተቀምጠህ፣ ‹‹ኢየሱስ ዘላለማዊ

ሕይወት እንዴት እንደ ሰጠኝ ልነግርህ ትፈቅዳለህ?›› ማለት ነው፡፡[እያንዳንዱ ክርስቲያን ሊመሰክር ይችላል፡፡ ገጽ 83-87 ስለ ምስክርነት ያሠለጥንሃል፡፡]

ኢየሱስን ለመቀበል የሚሆን ጸሎት

ጌታ ኢየሱስ ሆይ፣ እኔ ኃጢአተኛ ነኝ፡፡ ስለ ኃጢአቶቼ መሠቃየት የሚገባኝ ነኝ፡፡ ነገርግን፣ ወደ ምድር መጥተህ በእኔ ቦታ ተሠቃየህ፡፡ ዛሬ እንደ አዳኜ አድርጌእቀበልሃለሁ፡፡ በምሞትበት ጊዜ፣ ስለ ሠራኋቸው መልካም ሥራዎች ሳይሆን፣ ስለኃጢአቴ በመሞትህ ምክንያት ወደ መንግሥተ ሰማይ ትወስደኛለህ፡፡

ከዛሬ ጀምሮ፣ አንተ ጌታዬ ነህ፡፡አንተን ልታዘዝህና ላገለግልህ እፈልጋለሁ፡፡

Page 82: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

82

7. አዳዲስ አማኞችን ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዲቀላቀሉ አድርግአንድ ሰው፣ ‹‹በስታዲዮም በሰበክሁ ጊዜ 1000 ሰዎች እጃቸውን አነሡ፣››

ብሎ ሪፖርት ሊያደርግ ይችላል፡፡ነገር ግን፣ ሦስቱ ብቻ በቤተ ክርስቲያን ታቅፈው ታገኝ ይሆናል፡፡አንዳንድ ሰዎች በድንኳን ወደሚደረጉ ስብሰባዎች ተአምራትን ለማግኘት

ይሄዳሉ . . . ነገር ግን ከዚያ በኋላ ኢየሱስን አይከተሉም [

በርጠሜዎስ ኢየሱስን ተከትሎታል፡፡ ማር. 10፡52]፡፡

ግባችን የተአምራት መሠራት ወይም የእጆች መነሣት ጉዳይ አይደለም፡፡ ግባችን፡- ሰዎችን ክርስቶስን እንዲቀበሉ፣ በቤተ ክርስቲያን እንዲታቀፉ፣ አዲስ ሕይወትእንዲኖሩ፣ ወንጌልን ወደ ሕዝቦች ሁሉ ለመውሰድ ከእኛ ጋር እንዲሠሩ ማድረግነው፡፡

8. ሁሉንም ሰዎች በቤተ ክርስቲያን ውስጥመቀበልቤተ ክርስቲያናችሁ በእግዚአብሔር ኃይል፣ ‹‹እስከ አሁን ድረስ ለሕዝባችን

ብቻ ወንጌልን ስንመሰክር ነበርን - ነገር ግን ከዛሬ ጀምሮ፣ ለየትኛውም ወገን ወይምባህል እንመስክር፡፡ ወደ ቤተ ክርስቲያን እናምጣቸው ልትል ትችላለች፡፡ ይህ ቀላልላይሆን ይችላል፡፡ አንዳንድ ሰዎች፣ ‹‹በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ ‹እነርሱን

አንፈልጋቸውም› የሚል ስሜት ሊሰማቸው ይችላል፡፡ ነገር ግን ኢየሱስ ለሁሉምበሚሆን ፍቅር ሊሞላን ይችላል (የሐዋ. 11፡19-21)፡፡

Page 83: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

83

9. ወደ ከተማ የሚፈልሱትን ሰዎች መርዳትበየቀኑ በደርዘን የሚቈጠሩ ሰዎች ከገጠር አካባቢዎች አንተ ወደምትኖርበት

ከተማ ይፈልሳሉ፡፡ ‹‹የገጠር ሕይወትን›› ትተው፣ ‹‹የከተማ ሕይወት››ይጀምራሉ፡፡ ብዙዎቹ ወንጌልን ለመስማት በተለይ በከተማ ውስጥ በሚኖራቸውበመጀመሪያው ዓመት ቆይታቸው ወቅት፣ ዝግጁዎች ናቸው፡፡

ቤተ ክርስቲያናችሁ እነርሱንመፈለግ፣ በሚያስፈልጋቸው ነገሮችመርዳት፣ እንዲሁም ኢየሱስንእንዲቀበሉ ማበረታታት ትችላለች(ማቴ. 25፡35)፡፡

10. መገልገያ ቊሳቊሶችንበትንሹ ...እግዚአብሔርንበይበልጥ ታመንእኔ [ኤላይጃ] ለመስበክ ከወጣቶች ጋር በምጓዝበት ጊዜ፣ ማይክራፎኖችና

የድምፅ ማጕሊያ መሣሪያዎችን ይፈልጉዋቸዋል፡፡ እነርሱ፣ ‹‹ወንጌልን ለመስበክ፣ነጮች ሚስዮናውያን ያሉዋቸው ቊሳቊሶች ሁሉ ሊኖሩን የግድ እንደ ሆነአድርገው›› ያስባሉ፡፡

‹‹ለመገልገያ ቊሳቊሶች መግዣ የሚሆን ገንዘብ ባይኖረንም እንኳ፣የእግዚአብሔር ኃይል ይሠራል፡፡ ንጹሕ ሕይወት የምንኖር ከሆነ፣ የምንጸልይና ሰዎችንየምንወድድ ከሆነ፣ የእርሱ ኃይል ይሠራል፣›› በማለት እነግራቸዋለሁ፡፡

11. መስከር - ምንም ነገር አያስቁምህአንድ ቀን እኔ [ብሩስ] በስዋዚላንድ የመንግሥት መሥሪያ ቤት ቢሮ ቪዛ

እንዲሰጠኝ እየጠበቅሁ ነበር፡፡ እዚያ ተቀምጬ ሳለ፣ አእምሮዬ ስለ ሴት ልጃችንሕመም ማሰብ ጀመረ፡፡ ብዙ ባሰብሁ መጠን፣ በጣም እጨነቅ ነበር፡፡

ከዚያም ስዋዚላንዳዊ ሰው ወደ ክፍሉ ገባ፣ ተቀመጠ፣ ከዚያም መጽሐፍ ቅዱሱንማንበብ ጀመረ፡፡ ከአሥር ደቂቃ በኋላ በሲስዋቲኛ እንዲህ አለኝ፣ ‹‹እነዚህ ጥቅሶች

ታላቅ ናቸው! ‹በመከራ ጊዜ፣ በእግዚአብሔር ታመን› ይላሉ›› ሲል ተናገረኝ፡፡

ጮክ ባለ ድምፅ ብዙ ጥቅሶችን ለእኔ አነበበልኝ፡፡እያነበበልኝ ሳለ፣ ዓይኖቼ በዕንባ ተሞሉ፡፡

"እ" = እኔ

"ክ" = ክርስቶስ

እንዲህ ብለህ ተናዘዝ፡- ‹‹ጌታሆይ፣ አንተ ቅዱስ ነህ፡፡ እኔኃጢአተኛ ነኝ፡፡ እባክህኃጢአቴን ይቅር በለኝ . . .ኢየሱስ ጌታዬ ነው፡፡ ስለዚህኃጢአትን ማድረግ አልፈልግም(መዝ. 32፡4-5፤ ቲቶ 2፡14)

ክርስቶስ ለአንተሞቶልሃል፡፡ ስለዚህ ከአሁንጀምሮ ለራስህ አትኖርም፡፡

በዚህ ፈንታ፣ ለእርሱ ኑርለት(2ኛ ቆሮ. 5፡15)፡፡

እንግዲህ ማንም በክርስቶስቢሆን፣ እርሱ አዲስ ፍጥረትነው፡፡ አሮጌው አልፎአልና

(2ኛ ቆሮ. 5፡17)፡፡

Page 84: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

84

በዚያ ቢሮ ያሉ ሌሎች ሰዎች፣ ‹‹ያንን ስዋዚላንዳዊ ሰው ተመልከቱት፤ ለነጩ

ሰውዬ በድፍረትና በፍቅር ይናገራል...ደግሞም ነጩ ሰውዬ እያነባ ነው!››እንደሚባባሉ እርግጠኛ ነኝ፡፡

ምናልባት ሰይጣን፣ ‹‹ከሌላ ጎሳ ለሆነ ለማንኛውም ሰው አትመስክር፣›› ብሎ

ሳይነግረው አልቀረም፡፡ ነገር ግን እርሱ መሰከረ... ሰይጣን እንዲያስቆመውአልፈቀደለትም፡፡

እኛም እንደዚያ ሰው እንሁን፡፡ ሰይጣን እንዲያስቆመን አንፍቀድለት፡፡

12. መጽሐፍ ቅዱስን አስተምር! (የሐዋ. 2፡42፤ 5፡21፤ 5፡42፤15፡35፤ 18፡11፤ 28፡31)

ከቤተ ክርስቲያን አገልግሎት በፊት፣ የመጽሐፍ ቅዱስ አስተማሪ ትላልቅሰዎችንና ወጣቶችን የዮሐንስ ወንጌልን፣ የኤፌሶን መልእክትን፣ ትንቢተ ዳንኤልን . .. ሊያስተምር ይገባል፡፡ ሌሎች አስተማሪዎች የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮችን ለልጆችሊነግሩ ይገባል፡፡

በአገልግሎቱ ጊዜ፣ ሰባኪው መጽሐፍቅዱስን ሊያስተምር ይገባል፡፡

የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት መሠረት ነው፡፡

13. ሥራውን ሥራ...ማዕረግን (መጠሪያ ስምን) አትፈልግእኔ [ኤላይጃ]፣ እኛ አፍሪካውያን በየስፍራው በምስክርነት ጠንክረን እየሠራን

ሳለ - ሰዎች ሰባኪ፣ ወንጌላዊ፣ ወይም ጳጳስ ብለው ቢጠሩን ግድ እንዳልነበረንአስታውሳለሁ፡፡ ነገር ግን፣ ዛሬ ሰዎች ወደ አውሮፓ ወይም አሜሪካ ይሄዳሉ፣ዲግሪዎችን ያገኛሉ፣ ተመልሰው እዚህ ይመጣሉ፣ እንዲሁም ሐዋርያ፣ ጳጳስ፣ ነቢይ . .. ለመባል ይፈልጋሉ፡፡ ይሁንና፣ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡-

ትሑታን ሁኑ (1ኛ ጴጥ. 5፡1-6)፡፡

ለሰው ሳይሆን ለጌታ እንደምታደርጉ የምታደርጉትን ሁሉ በትጋት አድርጉ (ቈላ.3፡23)፡፡

14. ልጆችን ወደ ኢየሱስ አምጣ/ምራወንዶችም ሆኑ ሴቶች ልጆችን መጽሐፍ ቅዱስ ማስተማር ይኖርባቸዋል፡፡

የእግዚአብሔር ጸጋ ሰዎችን በዓለማዊምኞትና በኃጢአተኝነት ላይ አርነትያወጣቸዋል (ቲቶ 2፡ 11-12)፡፡

የኢየሱስ

ኃይል

Page 85: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

85

በቤት፣ በጐረቤትህ ላሉ ልጆች የመጽሐፍ ቅዱስን ታሪኮች ንገራቸው፡፡ በቤተክርስቲያን፣ መልካም የሆነ ትልቅ የእሑድ ትምህርት ቤት ይኑራችሁ (መዝ. 78፡3-6)፡፡

በቤትና በቤተ ክርስቲያን፣ የሚሠቃዩ ልጆችን እርዳ፡፡ ዛሬ በምድር ላይ፣ 200ሚሊዮን ልጆች ወላጅ የላቸውም፡፡ አንዳንዶቹን ትላልቅ ሰዎች የወሲብ መጠቀሚያያደርጉዋቸዋል፡፡ ሕፃናትን እንርዳ (ሉቃስ 18፡16)፡፡

15. ስደተኞችን በወንጌል ድረስ‹‹በአገራችን ስደተኞችን አንፈልግም፤›› ከቶ አትበል፡፡ስደተኞችን ውደድ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን አስተምራቸው፡፡ ልብስ፣

መድኃኒት...በመስጠት እርዳቸው (ያዕ. 2፡15-16)፡፡

16. ልዩ ፍላጎት ያላቸውን ሰዎች በወንጌል መድረስበከተማችሁ ውስጥ መስማት የተሳናቸው በመሆናቸው ምክንያት ብቻ ከቶ ቤተ

ክርስቲያን ሄደው የማያውቁ ሰዎች አሉ፡፡መስማት የተሳናቸው ሰዎችን መርዳት ትችላለህ፡፡እንዴት? በእጆቻችሁ መናገርን (የምልክት ቋንቋን) ተማር፡፡ አዎን፣ ‹የምልክት

ቋንቋን› የሚያውቅ ሰው ፈልግ፡፡ በእያንዳንዱ ቀን ትንሽ ነገር እንዲያስተምርህጠይቀው፡፡

ከዚያም፣ መስማት የተሳናቸው ሰዎችን ሻይ እንዲጠጡ ወደ ቤትህ ጋብዛቸው፡፡ከእነርሱም ጋር ወዳጅ ሁን፡፡ በቤተ ክርስቲያን፣ ሰባኪው የሚለው ነገር ምን እንደሆነ ስትነግራቸው እጆችህን ተጠቀም፡፡

በተጨማሪም ማየት የተሳናቸውን፣ የተራቡትን፣ የታመሙትን፣ በእስር ቤትያሉትን፣ የአካል ጕዳተኞችን. . .በወንጌል ድረሳቸው (ኢዮብ 29፡12-16፤ ማቴ. 25፡31-40)፡፡

17. ትምህርትህን በምትከታተልበት/በምትሠራበት ስፍራ መስከርመንግሥት፣ ‹‹ወደ እንግሊዝ አገር ሄደህ ተማር፣›› ካለህ፣ ወይም

የንግድ ድርጅት፣ ‹‹ወደ የመን ሄደህ፣ በዚያ ሥራህን አከናውን››ካለህ...እንግዲያው፣ ‹‹እግዚአብሔር እዚህ ላከኝ፡፡ ጥናቴን/ሥራዬን አከናውናለሁ፣ደግሞም በአንድ ቤተ ክርስቲያን ታቅፌ በዚያ ካሉ አማኞች ጋር ለመመስከርእተጋለሁ፡፡ ወይም ይህች አገር ቤተ ክርስቲያን እንዲኖር የምትፈቅድ ካልሆነች፣በመኖሪያ አፓርትመንቴ (ቤቴ) ለመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ሰዎችን እጋብዛለሁ፡፡

የመንፈስም ፍሬ ፍቅር፣ ትዕግሥት፣ ለጋስነት፣ትሕትና የዋህነት እና ራስን መግዛት ነው (ገላ.5፡ 22-23)፡፡

Page 86: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

86

እግዚአብሔር በዚህ ያስቀመጠኝ ስለ እርሱ እንድናገር ነው›› የሚለውን መገንዘብያስፈልግሃል፡፡

18. በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በሐዋርያት ሥራ 1፡8 ላይ ተወያዩበት1. የሐዋርያት ሥራ 1፡8 አራት ነገሮችን

ይነግረናል፡፡2. በከተማህ ውስጥ [ኢየሩሳሌም] መስከር፣

3. ደግሞም ለገዛ ሕዝብህ [ይሁዳ] መስከር፣

4. እንዲሁም ለማይወደዱ ሕዝቦች [ሰማርያ] መስከር፣

ብዙዎቹ አብያተ ክርስቲያናት 3ኛውንና 4ኛውን አያከናውኑም፡፡ በቤተክርስቲያናችሁ ውስጥ ይህን ተወያዩበት፡- ቤተ ክርስቲያናችን በአጠቃላይ 4ቱንምትእዛዛት እንዴት መፈጸም ትችላለች?

በደቡብ ቻድ የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት እንዲመሰክሩ 4500 አማኞችንአሠልጥነዋል [ገጽ 78-87]፡፡ ከዚያም ከታኅሣሥ 25-31 አንድ ለአንድ በሆነመልኩ በሰሜን ቻድ ላሉ ግለሰቦች መስክረዋል፡፡

ውጤቱም፡- በሰሜን ቻድ ያሉ አብያተ ክርስቲያናት በ140% ማደጋቸውነበር፡፡

19. በንጽሕና የምትኖር ላጤ፣ ወይም ባለትዳር ሰው ሁን

ውድ አዲሱ አባላችን፣

መጽሐፍ ቅዱስን እንድታጠናና እንድትታዘዝ እንረዳሃለን፡፡

ለጓደኞችህ እንድትመሰክር እናደፋፍርሃለን፡፡

ወንጌልን ቅርብም ሆነ ሩቅ ስፍራ በመውሰድ ረገድ አብረኸን ሥራ፡፡ለክርስቶስ ለመሠቃየት ዝግጁ ሁን፡፡

ለመመስከር አትፈር፡፡ ስለ ወንጌል አብረኸኝመከራን ተቀበል (2ኛ ጢሞ. 1፡8)፡፡

Page 87: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

87

እግዚአብሔርን ለማገልገል፣ ወሲባዊ ለሆነኃጢአት ‹እምቢ› ማለት ይኖርብሃል፡፡ እንደዚህያለውን ኃጢአት ባለፉት ጊዜያት ሠርተህ ከሆነ፣ተናዘዘው፡፡ ከእርሱም ተመለስ (ምሳሌ 28፡13)፡፡

ከዚያም፡-

ላጤ ከሆንህ፣ ከማንም ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት አታድርግ፡፡ በቅንዓትና በደስታ

ለእግዚአብሔር ሥራለት (1ኛ ተሰ. 4፡3-5፤ 2ኛ ጢሞ. 2፡22፤ 1ኛ ቆሮ. 7፡34-35)፡፡

ያገባህ ከሆንህ፣ ከትዳር ጓደኛህ ጋር ብቻፍትወትን ፈጽም፤ ከማንም ጋር አትፈጽም፡፡

ባልሽን አክብሪ፡፡ለእርሷ መልካም የሆኑ ነገሮችን በማድረግ ሚስትህን አስደንቃት፡፡ እስከ

ጋብቻቸው ድረስ በድንግልና እንዲኖሩ ልጆቻችሁን አስተምሩ (ቈላ. 3፡5-19፤ 1ኛቆ ሮ .1 3 ፡ 4 -

7)፡፡

ለሚስትህ/ለባልሽ ታማኝከ ሆ ን ህ / ከ ሆ ን ሽ ፣ጸሎቶቻችሁ የበለጠ ኃይልይኖራቸዋል (1ኛ ጴጥ. 3፡7)፡፡

ተወያዩበት

የኢየሱስ

ኃይል

በቤትህና በቤተ ክርስቲያናችሁ ውስጥ፣ ሰዎችንልትረዳ ትችላለህ፡፡ እንዴት? በዚህ መጽሐፍ ከገጽ78-87 ያለውን አስተምራቸው፡፡ በተጨማሪም

የእኛን ሌላውን መጽሐፍ፣ ‹‹የኢየሱስ ኃይል››የሚለውን መጽሐፍ አስተምራቸው፡፡

Page 88: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

88

20. ለሕዝቦች ሁሉ እንክብካቤ እንዲያደርጉ ልጆችህን እርዳቸውወንጌልን በቅርብም ሆነ በሩቅ የሚያደርሱ አንዳንድ አማኞችን ሻይ እንዲጠጡ

በቤትህ ጋብዛቸው፡፡ ከልጆችህ ጋር በመሆን፣ ታሪኮቻቸውን አድምጥ፡፡ ከዚያም፣አንተ እና ልጆችህ በየዕለቱ ልትጸልዩላቸው ትችላላችሁ፡፡ በተጨማሪም፣ ልጆችህንአታክልቶችን በመትከል፣ የምርት ውጤቶችን በመሸጥ፣ ወንጌልን ለሚያዳርሱ ሰዎችገንዘብን እንዲሰጡ እርዳቸው፡፡

21. ቤትህን ትተህ ለመሄድ ፈቃደኛ ሁንቤትን ትቶ መሄድ አስቸጋሪ ነገር ነው፡፡ እኛ ሰዎች የቤታችንን ዋስትና

እንፈልገዋለን፡፡ ይሁንና፣ እግዚአብሔር ቤታቸውን ትተው እንዲሄዱ ለሰዎች ዘወትርጥሪ ያደርጋል!

እግዚአብሔርም አብርሃምን አለው፡- ከአገርህ ከዘመዶችህም ከአባትህም ቤትተለይተህ እኔ ወደማሳይህ ምድር ውጣ (ዘፍጥ. 12፡1)፡፡

ከእኔ ይልቅ አባቱን ወይም እናቱንየሚወድድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም(ማቴ. 10፡37)፡፡

ስለ እኔና ስለ ወንጌል ቤትን ወይምወንድሞችን ወይም እኅቶችን ወይምአባትን ወይም እናትን ወይም ሚስትንወይም ልጆችንወይም እርሻን የተወ፣ አሁን በዚህ ዓለም ከስደት ጋር መቶ ዕጥፍ የማይቀበልማንም የለም (ማር. 10፡29-30)፡፡

እንደ ክርስቲያን ልታደርገው የሚገባው ነገር እነሆ፡-

ሀ) ወላጆችህን/ዘመዶችህን በፍላጎቶቻቸው (በሚያስፈልጓቸው ነገሮች) እርዳ (1ኛጢሞ. 5፡8)፡፡

ለ) እግዚአብሔር ወደሚልክህ ስፍራ ለመሄድ ወላጆችህንናዘመዶችህን ትተህ ለመሄድ ፈቃደኛ ሁን (ማቴ.19፡29፤ ማር. 1፡20)፡፡

Page 89: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

89

ተወያዩባቸው፡- እግዚአብሔር ወደሚልከኝ ስፍራ እንዴት መሄድ እችላለሁ፣ደግሞስ በዚህ ሁሉ ውስጥ እያለሁ ወላጆቼንና ዘመዶቼን እንዴት መርዳትእችላለሁን?

22. ሴቶችን አበረታታብዙ ሴቶች ከአፍሪካ፣ አውሮፓ፣ እስያ. . .አስቸጋሪ ወደ ሆኑ

ቦታዎች ወንጌልን ወስደዋል፡፡ ወንጀልና በሽታበሚያሠጋበት ስፍራ ይኖራሉ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስንይተረጕማሉ፣ በሽተኞችን ያክማሉ፣ በወሲብ ንግድ ላይየተሰማሩ ሕፃናትን ያድናሉ፣ ወላጅ-አልባ ልጆችን

ይረዳሉ፣ መጽሐፍ ቅዱስን ያስተምራሉ . . .እንደዚህ ያሉ ሴቶችን እንባርካቸው፣ እንርዳቸውም፡፡

23. ላጤዎችን አበረታታብዙ ሰዎች፣ ‹‹ላጤ ሆኖ በሚኖር ሰው ሕይወት ውስጥ አንድ የሆነ ችግር

አለ፣›› ብለው ያስባሉ፡፡

ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፡- አንድ ሰው ለማግባትም ሆነ ላጤ ሆኖለመኖር ነፃ ነው፡፡ በእርግጥ፣ አንድ ሰው፣ ‹‹አላገባም፡፡ ከማንም ጋር ፍትወትአልፈጽምም፡፡ ባል/ሚስት እንዲሁም አሳቤን የሚወስድብኝ ነገር ሳይኖር፣እግዚአብሔርን አገለግላለሁ ብሎ ከወሰነ መልካም ነው›› (1ኛ ቆሮ. 7፡28፣ 32-35፣ 40)፡፡

ወንጌልን ለማስፋፋት ላጤዎችን እናበረታታ፡፡ እነርሱንም ለመደገፍ ገንዘብእንስጥ፡፡ [ገጽ 72-73]

24. ‹የተጠሩ› ሰዎችን ጥሩ ወደ ሆነ የመጽሐፍ ቅዱስ ኮሌጅ ላክአንድ ሰው ለቤተ ክርስቲያን መሪዎች፣ ‹‹በሱዳን [ወይም በየትኛውም ስፍራ]

ቤተ ክርስቲያን ለመመሥረት እግዚአብሔር ጠርቶኛል›› ብሎ ለቤተ ክርስቲያን

መሪዎች በሚነግርበት ጊዜ፣ መሪዎቹ ‹‹እርሱ/እርሷ ንጹሕ የሆነ ሕይወትን እየኖሩነው? ደግሞም ሰውየው/ሴትየዋ እዚሁ ከሽማግሌዎች ሥር ሆነው እግዚአብሔርንእያገለገሉ ነበር ወይ?›› ብለው መጠየቅ አለባቸው፡፡

የኢየሱስ

ኃይል

Page 90: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

90

መልሱ እውነት ከሆነ፣ እርሱን/እርሷን የመጽሐፍ ቅዱስ ሥልጠና እንዲያገኙእርዷቸው፡፡

‹‹ሥልጠና አስፈላጊ አይደለም፣›› አትበሉ፡፡ሥልጠና አስፈላጊ ነው፡፡ ሙሴ ኢያሱን አሠልጥኖታል፣ደግሞም ጳውሎስ ጢሞቴዎስን አሠልጥኖታል፡፡

ማቴዎስ 28፡19-20ን ለመታዘዝ ሰዎችን የሚያዘጋጅየመጽሐፍ ቅዱስ ኮሌጅን ምረጡ፡፡

1) ከእነዚህ 24 አሳቦች፣ ቤተ ክርስቲያናችን አሁኑኑ ልትጀምራቸው የሚገቡ 5አሳቦችን ማግኘት እንችላለን? ከ5ቱ፣ ለእያንዳንዱ መሪ ያስፈልገናል፡፡ 5ቱንመሪዎች ዛሬ መምረጥ እንችላለን? ይህ ዓመት ከማለቁ በፊት እነዚህ 5ቱ መሪዎች5ቱን አሳቦች ቤተ ክርስቲያናችን እንድትጀምራቸው መርዳት ይችላሉ?

2) 2) ከእነዚህ 24 አሳቦች ባሻገር፣ ልናስባቸው የሚገቡ ሌሎች አሳቦች ይኖራሉን?

ለእነዚህ ለእያንዳንዳቸው ማን መሪ ይሆናል? [ኢያሱ 1፡6-8]

Page 91: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

91

ይህንን ገጽ በትልቁ ፎቶ ኮፒ አድርገውና በቤተ ክርስቲያናችሁ ውስጥ ለጥፈው፡፡

ምዕራፍ 11

ክርስቲያኖችን እንዲነሡ ልትረዱዋቸው ትችላላችሁ

የእግዚአብሔርን ሥራ የምትሠራ ከሆንህ [ቤት ለቤት የምትመሰክርም ይሁን፣ ወደ ሩቅ ቦታ ሄደህ

የምትሰብክ ቢሆን]፣ ምሳሌ ሁን፡፡ ከቶ አትስከር ወይም ከጋብቻ ውጭ ከማንኛዋም ሴት ጋርየግብረ ሥጋ ግንኙነት አታድርግ፡፡ በገንዘብ ረገድ ታማኝ ሁን፡፡ ሚስትህን/ባልሽን እና ልጆቻችሁንውደጂ/ድ፡፡ ቈላስይስ 3፡1-24ን ታዘዝ፡፡

ኢየሱስ መስክሮአል ደግሞም ኢየሱስ ሰብኳል

ኢየሱስ የመሰከረው፡-ለናትናኤል (ዮሐንስ 1፡47)

ለዘኬዎስ (ሉቃስ 19)ለኒቆዲሞስ (ዮሐንስ 3)ለማርታ (ዮሐንስ 11፡25)ለሌዊ (ማርቆስ 2፡14)

በጕድጓዱ አጠገብ ላገኛት ሴት(ዮሐንስ 4)

ለዕውሩ ሰው (ዮሐንስ 9፡35)ለጋለሞታይቱ ሴት (ሉቃስ 7፡37)ለሀብታሙ ሰው (ሉቃስ 18፡18)ለሕግ አዋቂው (ሉቃስ 10፡37)

ኢየሱስ የሰበከው፡-በምኵራብ ውስጥ (ማርቆስ 1፡21)

በተራራ ላይ (ማቴ. 5-7)በታንኳ ላይ ሆኖ (ማርቆስ 4)ለ5000 ሰዎች (ማርቆስ 6፡34)

ለ4000 ሰዎች (ማርቆስ 8)

Page 92: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

92

ክርስቲያኖችን እንዲነሡ እንዴት ልትረዱዋቸው ትችላላችሁ?መልስ፡- መዝሙር 67 እና የሐዋርያት ሥራ 10ን ልታስተምሩዋቸው ትችላላችሁ፡፡

እንዲህ ባለ መልኩ አስተምሩዋቸው፡-

መዝሙር 67፡1 እና 2ን አንብቡ፡፡ እነዚህ ሁለት ቊጥሮች እንዲህ ይላሉ፡-

1 እግዚአብሔር ይማረን ይባርከንም . . .2 በአሕዛብ ሁሉ መካከል ማዳንህን፣ መንገድህንም በምድር እናውቅ ዘንድ፡፡እነዚህን ሁለት ቁጥሮች በጥንቃቄ ተመልከቱ፡፡ አሁን ይህን ጥያቄ እንመልስ፡-

እንዲባርከን እግዚአብሔርን መጠየቅ የሚገባን ለምንድን ነው?

[ሰዎች መልሳቸውን እንዲሰጡ ጊዜ ስጣቸው፡፡]

ትክክለኛው መልስ፡- እግዚአብሔርን እንዲባርከን እንጠይቀዋለን . . . ለምን?

‹‹የእርሱ ማዳን በአሕዛብ ሁሉ መካከል የታወቀ ይሆን ዘንድ›› ነው፡፡

በሌላ አነጋገር፣ 67፡1 እና 2 የሚነግሩን፡-እግዚአብሔርን በገንዘብ እንዲባርከን በምንጠይቀው ጊዜ፣የሚሰጠንን ገንዘብ ሁሉ ለራሳችን አንጨርሰው፡፡

እግዚአብሔር በጤንነት እንዲባርከን በምንጠይቀው ጊዜ፣ለራሳችን ብቻ አንኑር፡፡ ጤናማ ሕይወታችንን የእግዚአብሔርንማዳን ለአሕዛብ ሁሉ ለማድረስ እንጠቀምበት፡፡

ራስ ወዳድ አንሁን፡፡ ራሳችንን የተመቸው ለማድረግ የእግዚአብሔርን በረከቶችአንጠቀም፡፡

በረከቶቻችሁን ቊጠሩ፡፡ ከዚያም፣ ‹‹የእርሱን ማዳን ለሕዝቦች ሁሉ ለማድረስ

እያንዳንዱን በረከት እንዴት መጠቀም እችላለሁ?›› የሚለውን ጠይቁ፡፡

67፡3 እና 67፡4፣ ‹‹አሕዛብ ሁሉ ያመስግኑህ›› በሉ፡፡

ይህም ማለት፡- ከሁሉም ቋንቋ የተገኙ ‹ወገኖች› ያመስግኑህ ማለት ነው፡፡

ዛሬ ሁሉም ‹ሰዎች› እግዚአብሔርን ያመሰግኑታልን? አይደለም፡፡ እንደ

‹ማኩዋ› እና ‹ያኦ› ያሉ ቋንቋ ተናጋሪዎች ስለ ክርስቶስ የሚያውቁት ኢምንት ነው፡፡

[ገጽ 55]

መዝሙር 67 እንዲህ ይላል፡- ባርከን... ለምን?...ደኅንነት ለሁሉም ሕዝቦች

ይደርስ ዘንድ...እንዲሁም በልዩ ልዩ ቋንቋ ወደሚናገሩ ‹ወገኖች› ይደርስ ዘንድነው፡፡

Page 93: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

93

እግዚአብሔር እንዴት ባርኮሃል? ምናልባት መኪናዎችን ለመጠገን በሚያበቃችሎታ፣ ወይም የንግድ ችሎታ፣ ወይም አታክልት በመትከልና በመንከባከብ ችሎታ፣ወይም ጥሩ አድርጎ በመጻፍ ችሎታ፣ ወይም በደንብ አድርጎ በማስተማር ችሎታ፣ወይም በሌላ ችሎታ...ባርኮህ ይሆናል፡፡

ሁሉም ‹ሰዎች› የደኅንነት ወንጌልን ይሰሙ ዘንድ... በረከቶችህን ተጠቀም፡፡

ሁሉም የኢየሱስ ተከታዮች በረከቶቻቸውን በዚያ መንገድ ይጠቀማሉን?በፍጹም አይጠቀሙም፡፡ አንዳንዶች የእግዚአብሔርን በረከቶች ‹‹ለራሳቸው››ለማዋል መርጠዋል፡፡

ሌሎች፣ ‹‹የእርሱን የደኅንነት ወንጌል ለማድረስ በረከቶቼን እጠቀማለሁ›› ሲሉወስነዋል፡፡

አንተም መምረጥ ይኖርብሃል፡፡መዝሙር 67 እንዲህ ይላል፡- በጥበብ ምረጥ፡፡ እንዲባርክህ እግዚአብሔርን

ጠይቀው፤ ከዚያም በልዩ ልዩ ቋንቋ ለሚናገሩ ወገኖች ሁሉ እና ‹ለሕዝቦች› ሁሉመልካሙን የምሥራች ለመላክ በረከቶችህን ለመጠቀም ወስን፡፡

Page 94: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

94

1) ያሉን በረከቶች ምንድን ናቸው? በልዩ ልዩ ቋንቋ ለሚናገሩ ወገኖች ሁሉ ደኅንነትንለማድረስ እነዚያን በረከቶች እንዴት ልንጠቀምባቸው እንችላለን?

2) ‹‹በረከቶችን በራስህ ላይ አውላቸው፣›› የሚለውን ሰይጣን የሚነግረን እንዴት

ነው? [ለምሳሌ፣ ቴሌቪዥን እና መጽሔቶች፣ ‹‹ይህን ግዛ . . . ትፈልገዋለህ . . . ስለ ራስህ

አስብ፡፡›› ይላሉ፡፡]

የሐዋርያት ሥራ 10 ጴጥሮስ ከሁሉም ቀለምና ዝርያ የሆኑ ሰዎችን መውደድመጀመሩን ይነግረናል፡፡

ጴጥሮስ ልጅ በነበረበት ጊዜ፣ አስተማሪው፣ ‹‹እኛ አይሁዳውያን አይሁዳውያንካልሆኑት ጋር በአንድ ጠረጴዛ ላይ ተቀምጠን አንመገብም፡፡ ከአውሮፓውያን ጋር ከቶበአንድ ላይ አንመገብም፡፡ እነርሱ ንጹሕ አይደሉም፡፡ ከአፍሪካውያን ጋር ከቶ በአንድላይ አንመገብም፡፡ ንጹሐን አይደሉም፡፡ አይሁዳዊ ያልሆኑ ሁሉ ንጹሐን አይደሉም፤››ሲል ነግሮታል፡፡

ነገር ግን በሐዋርያት ሥራ 10 ላይ እግዚአብሔር ለጴጥሮስ፣ ‹‹ማንንም ንጹሕ

ያልሆነ አትበል ብሎ ተናግሮታል፡፡ ‹‹ሂድና ለቆርኔሌዎስ...ስበክ›› ብሎታል

(የሐዋርያት ሥራ 10፡15-20)፡፡

ቆርኔሌዎስ መልኩ ነጭ የሆነ ሰው ነበር [ኢጣሊያዊ ነበር] (የሐዋ. 10፡1)፡፡

ጴጥሮስ መልኩ ቡናማ የሆነ ሰው ነበር [ከመካከለኛው ምሥራቅ የሆነ ነበር]፡፡

መልኩ ነጭ ለሆነው ሰውዬ፣ ‹‹ልማዳችን እንዲህ ነው፡- እንደ እኔ ያለ አይሁዳዊእንዳንተ ያለ አይሁዳዊ ያልሆነ ሰው ቤት ከቶ አይገባም፡፡ ነገር ግን፣ እግዚአብሔር‹ማንንም ንጹሕ ያልሆነ› ብለህ አትጥራ ብሎ ተናገረኝ፡፡ ስለዚህ ወደ ቤትህ

ገባሁ›› (የሐዋ. 10፡28-29)፡፡

[በሌላ አነጋገር፣ ጴጥሮስ፡- በሕይወት ዘመኔ ሁሉ አውሮፓውያንንና አፍሪካውያንን ንጹሕ ያልሆኑ

በማለት እጠራቸው ነበር፡፡ ነገር ግን ያንን ከዚህ በኋላ አላደርግም፡፡]

ከዚያም ጴጥሮስ ‹‹አሁን፣ እግዚአብሔር ሁሉንም ሕዝቦች እና የቱንም ቀለም

የተላበሱ ሰዎችን [እናንተን ነጮችን እንኳ] እንደሚቀበል ተገንዝቤያለሁ›› አለ

(የሐዋ. 10፡34-35)፡፡

ቆርኔሌዎስ በክርስቶስ አመነ ደግሞም ተጠመቀ፡፡

¾SêNõƒU

I`ƒ

Page 95: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

95

ጴጥሮስ ወደ ቤት በተመለሰ ጊዜ፣ የእርሱ ጓደኞች ተቈጥተው አገኛቸው፡፡እነርሱም፣ ‹‹አይሁዳዊ ያልሆነ ሰው ቤት ጴጥሮስ ሆይ ስለ ምን ትገባለህ?›› አሉት

(የሐዋ. 11፡1-3 ተመልከት፡፡)

ጴጥሮስ፣ ‹‹እግዚአብሔር፣ ‹ማንንም ንጹሕ አይደለም› አትበል ብሎ

ተናገረኝ›› አለ፡፡ ደግሞም እግዚአብሔር ቆርኔሌዎስ ለሚባል ነጭ ቀለም ያለው ሰው፣

‹ጴጥሮስ መልእክት ያደርስላችኋል› ብሎ ተናገረው›› አለ (የሐዋ. 11፡9-14)፡፡

የጴጥሮስ ጓደኞች ያንንበመስማታቸው ተገረሙ፡፡እነርሱም እንዲህ ብለው ነበር፡-ኢየሱስ አይሁዳዊ ለሆንን ለእኛብቻ ነው፡፡

ነገር ግን ጴጥሮስየእግዚአብሔርን መልእክትከነገራቸው በኋላ፣ እነርሱ፣‹‹ማለትም፣ አይሁዳዊ ያልሆኑ

[አውሮፓውያን፣ አፍሪካውያን እና

ሌሎች አይሁዳዊ ያልሆኑ ወገኖች]

ንስሐ ሊገቡና ሕይወትን ሊቀበሉ ይችላሉ›› አሉ [የሐዋ. 11፡18]፡፡ያንንም ወዲያው ሊገነዘቡት ይገባ ነበር፡፡ ወደ ኋላ ተመልሰን ስንመለከት፣

በሐዋርያት ሥራ 8 ላይ እግዚአብሔር ፊልጶስን ወደ አፍሪካዊው ሰው ልኮታል፡፡ደግሞም ኢየሱስ፣ ‹‹ለሁሉም ሕዝቦች›› መስክሩ ብሎ ነግሮአቸዋል (ማቴ. 28፡19)፡፡

ዛሬ እኛም እንደዚሁ መገንዘብ የሚገባን ነገር አለ፡- ወንጌልን ወደ ሕዝቦች ሁሉየመውሰድ ኀላፊነት አለብን፡፡ ከዚያም በመንግሥተ ሰማይ በአንድ ላይ እንዲህበማለት እንዘምራለን፡-

በደምህም ለእግዚአብሔርከነገድ ሁሉ

ከቋንቋም ሁሉከወገንም ሁሉከሕዝብም ሁሉ

ሰዎችን ዋጀህ (ራእይ 5፡9)፡፡

Page 96: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

96

1) አንዳንድ የቤተ ክርስቲያን አባላት የተወሰኑ ወገኖችን ‹ከእኛ በታችናቸው›...‹ንጹሕ አይደሉም› ብለው ያስባሉን?

2) በሐዋርያት ሥራ ላይ የትኞቹ ጥቅሶች ናቸው የሚከተለውን ልናደርግ ይገባናልየሚሉት፡-

ሀ) ማንኛውም ሰው (ወገን) ‘ንጹሕ አይደለም’ ማለት አይኖርብንም? [የሐዋ.10፡19-23]

ለ) ለሁሉም ሰዎች ወንጌልን ማድረስ አለብን? [የሐዋ. 8፡35፤ 10፡34-35፤11፡8]

3) አንዳንድ ክርስቲያኖች፣ ‹‹‘ከእኔ በላይ’ ለሆኑ ወይም ‘ከእኔ በታች’ ለሆኑወይም ‘ከእኔ ለተለዩ’ ሰዎች መመስከር አልችልም ሲሉ ያስባሉ፡፡ ስለዚያጕዳይ የሐዋርያት ሥራ 10 ምን ይላል? (10፡27-29፣ 39-43)

4) መዝሙር 67 እና የሐዋርያት 10 ረድተውሃልን?

እነዚህን ሁለት ምዕራፎች የት ልታስተምራቸው ትችላለህ?

[በቤት ውስጥ ለትልልቅ ሰዎችም ሆነ ለልጆችመዝሙር 67 እና የሐዋርያት ሥራ 10ን ል ታ ስ ተ ም ራ ቸ ውትችላለህ፡፡ ከዚያም በቤተ ክርስቲያን ውስጥ፣ በ ሴ ቶ ችስብሰባዎች፣ በወጣቶች ስብሰባዎች፣ በእሑድትምህርት ቤቶች፣ በፋሲካ በዓል አከባበር ወቅት፣በገና (በኢየሱስ የልደት) በዓል...ልታስተምራቸው ትችላለህ፡፡

የአመራር ሥልጠና ሴሚናሮችን በማዘጋጀት በዚያ ልታስተምራቸው ትችላለህ፡፡መሪዎችን ሊያስተምሩ የሚችሉት ከባህር ማዶ የሚመጡት ብቻ ናቸው ብለህአታስብ፡፡ 2ኛ ጢሞ. 2፡2፤ የሐዋ. 20፡20-21 ተመልከት፡፡]

ምዕራፍ 12

¾T@Ç=ƒ

^’>Á”

vI`

¾ÑK=LvI`

cT`Á

›=¾\dK?U

ÃG<ÇS<ƒ vI`

Page 97: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

97

ሰላም አውራጅ ልጅ

ዶን እና ካሮል ሪቻርድሰን፣ በካናዳ የመጽሐፍ ቅዱስ ኰ ሌ ጅውስጥ በነበሩበት ጊዜ፣ ‹‹ጌታ ሆይ፣ አንተን ለማገልገል አደገኛ የሆነ ቦታ እንኳ ቢሆን

ወደምትልከን ሁሉ እንሄዳለን፣›› እያሉ ይጸልዩ ነበር፡፡

ከዚያም ቤተ ክርስቲያናቸው፣ ‹‹ወደ ኢሪያንጃያ ልንልካችሁ እንፈልጋለን፡፡ችግሩ፡- በዚያ ያሉ ሰዎች ከሌላ ጐሳ የሆነ የማንኛውንም ሰው አንገት መቅላትንመውደዳቸው ነው፡፡ እንደዚህ ወዳለው አደገኛ ቦታ ለመሄድ ፈቃደኞች ናችሁን?››ስትል ተናገረቻቸው፡፡

ዶን እና ካሮል ለመሄድ ተስማሙ፡፡ ኢሪያን በደረሱ ጊዜ፣ ዶን ካሮልን፣‹‹ሰዎቹ የሰፈሩበትን እስካገኝ ድረስ በትንሽ ጀልባ በወንዝ ወደ ላይ እሄዳለሁ፡፡በዚያም ቀለል ያለ ቤት እሠራለሁ፡፡ ከዚያም አንቺንና ሕጻኑን ልጃችንን ለመውሰድእመለሳለሁ፣›› ሲል ተናገራት፡፡

ወንዙን ይዞ 5 ኪ.ሜ. ርቀት ላይ ዶን አንድ ሰው ተመለከተና፣ ‹‹እባክህን ቤትእንድሠራ እርዳኝ ሚስቴን አመጣለሁ፡፡ እዚህ እንቆያለን፡፡ ከእያንዳንዱም ሰው ጋርየምንካፈለው መልካም የምሥራች አለን፣›› ሊለውም እጆቹን ተጠቀመ፡፡

በአንድ ላይም ከሣርና ከእንጨት ቤት ሠሩ፡፡ ከዚያም ዶን ካሮልንና ሕፃንልጃቸውን ለማምጣት ሄደ፡፡ በወንዙ አድርገው ወደ ላይ እየተጓዙም ሳለ፣ እርሱ፣‹‹በቅርቡ ቤታችንን ታዪዋለሽ፣ ደግሞም ሰውየውን እዚያው እናገኘዋለን ብዬ

ተስፋ አደርጋለሁ፣›› አላት፡፡

ነገር ግን፣ በአንድ ሰው ፈንታ ከ400 ሰዎች በላይ በዚያ ነበሩ፡፡ ሰዎቹጀልባዋን በተመለከቱበት ጊዜ፣ ሁሉም በቋንቋቸው አንድ ነገር እየተናገሩይጮኹ ነበር፡፡

ዶን እና ካሮል እነርሱ የሚጮኹት ‹‹እንኳን ደኅና መጣችሁ›› ወይም

‹‹እነዚያን ጭንቅላቶች!›› ተመልከቱ እያሉ እንደ ሆነ አያውቁም ነበር፡፡

ዶን ጀልባዋን መሬት አስይዞ ወጣ፡፡ ከዚያም እርስዋ ከጀልባው መውጣት ትችልዘንድ ሕፃኑን ከካሮል ተቀብሎ ወሰደው፡፡ ይህንን በሚያደርግበት ጊዜ፣ እያንዳንዱሰው መጮኹን አቆመ፡፡ ሕፃኑን እንደ ያዘ ዶንን መመልከት ጀመሩ፡፡

Uu=

ለባሎቻችሁ ተገዙ፡፡ ጸሎቶቻችሁእንዳይከለከሉ፣ አብረው ደግሞየሕይወትን ጸጋ እንደሚወርሱአድርጋችሁ አክብሩዋቸው

(ከ1ኛ ጴጥ. 3፡1-7)፡፡

Page 98: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

98

በዚያ ምሽት ዶን እና ካሮል በሰላም አንቀላፉ፡፡ ነገር ግን በማለዳ አስፈሪድምፅን ሰሙ፡፡ ዶን ወደ ውጪ ሮጦ ሄደ፣ ነገሩም ጦርነት እንደ ሆነ ደረሰበት!ሁለት ነገዶች እርስ በርሳቸው ጦር ይወራወሩ ነበር፡፡ እያንዳንዱ ሰው የጠላቱንጭንቅላት ለመቅላት ተስፋ አድርጎ ነበር፡፡

ዶን ፍልሚያው ወደሚደረግበት መካከል ሮጠ፡፡ በእጆቹም ጦሮቻቸውንእንዲያስቀምጡ ለመናቸው፡፡ ...እስከሚቀጥለው ማለዳ ድረስ...ፍልሚያው አቆመ፡፡ከዚያም ያው ነገር እንደገና ተከሰተ፡፡

በእያንዳንዱ ማለዳ ጦርነት ነበር፡፡ ካሮል ከጦሮቹ አንዱ ባሌን ይገድላል ስትልፈራች፡፡

በየምሽቶቹ፣ ዶን በእሳት ዙሪያ ተቀምጠው ሳሉ ታሪኮችን በሚናገሩ ሰዎችመካከል መቀመጡን ሁልጊዜ ይወድደዋል፡፡ ዶንን ወደዱት፤ ቋንቋቸውንም ለእርሱማስተማርን ደስ ተሰኙበት፡፡ ከዚያም ታሪኮችን እንዲነግራቸው እርሱን ጠየቁት፡፡ስለዚህ፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮችን ነገራቸው፡፡

ከስድስት ወራት በኋላ፣ ‹‹ከነገርኋችሁታሪኮች ሁሉ ውስጥ፣ እጅግ የወደዳችሁት ሰውማንን ነው?›› ብሎ ይጠይቃቸዋል?፡፡

‹‹ይሁዳ!›› ብለው ሲመልሱ በአያሌውይገረማል፡፡

‹‹ኢየሱስን አትወድዱትም?›› ሲል

ጠየቃቸው፡፡››

‹‹አንወደውም፣›› ብለው መለሱ፡፡ ‹‹እኛ ይሁዳን እንወድደዋለን፡፡ እኛ ልክ

በአሳማዎች ላይ እንደምናደርገው ያለውን እርሱ በሰው ላይ አድርጓል፡፡››

‹‹አሳማ...?›› ሲል ዶን ጠየቀ፡፡

‹‹እናብራራልህ፣›› አሉት፡፡ ‹‹አየህ፣ ለማዳ ያልሆኑአሳማዎችን በምናድንበት ጊዜ፣ ዘወትር እናት አሳማንእንገድላለን፣ ነገር ግን ሕፃን አሳማን ከቶ አንገድልም፡፡ ትንሿንአሳማ እቤት እንወስዳታለን፡፡ በቤታችን ትተኛለች፡፡እንመግባታለን፡፡ ከጥቂት ወራት በኋላ፣ ዋስትናና መተማመንይሰማታል፡፡ ከዚያም እንገድላትና ግብዣ እናደርጋለን!

እግዚአብሔርም፣ ‹‹ማንን ልላክ

ማንስ ይሄድልናል?›› አለ፡፡

ኢሳይያስ ሲመልስ፣ ‹‹እነሆኝ፣

እኔን ላከኝ›› አለ (ኢሳ. 6፡8)፡፡

Page 99: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

99

‹‹በሰዎችም ላይ እንዲሁ ማድረጉን እንወድዳለን፡፡ አንዳንድ ጊዜ ከሌላ ጎሳ

የሆነ ሰው ወደ እኛ ይመጣና፣ ‹ወገኔ ሊገድለኝ ይፈልጋል፡፡ ከእናንተ ዘንድ መቀመጥ

እችላለሁን?› ይለናል

‹‹እኛ ሁልጊዜ፣ ‹እንኳን ደኅና መጣህ፣ ወንድማችን›እንለዋለን፡፡ ከጥቂት ወራት በኋላ ዋስትናና ደኅንነትይሰማዋል፡፡ ከዚያም ራሱን በምንቀላው ጊዜ ፊቱ በመገረምይሞላል፡፡ እኛም ግብዣ እናደርጋለን! ሁላችንምእንዘምራለን፡፡ ‹ልክ በአሳማዎቹ ላይ የምናደርገውን ነገር

በሰውም ላይ አናደርጋለን፡፡›

‹‹ይሁዳን የምንወድበት ምክንያት ይህንን በኢየሱስ ላይ በማድረጉ ነው፡፡››

በዚያ ምሽት በአልጋ ላይ ሳሉ፣ ‹‹በጣም አዝኛለሁ! እኛ ጥሩ የወንጌል

መልእክተኞች አይደለንም፡፡ ሰዎቹ ይወድዱናል...እኛም ደግሞ እንወዳቸዋለን...ነገርግን ኢየሱስ አዳኝ መሆኑን ለእነርሱ በመንገር ረገድ አልተሳካልንም፣›› ሲል ዶንለካሮል ነገራት፡፡

እንዴት ያለ ጸሎት ጸለዩ መሰላችሁ!

በሚቀጥለው ቀን ዶን ከጐሳ መሪዎቹ ለአንዱ፣ ‹‹በእያንዳንዱ ቀን ጦርነት አለ፡፡

ሰላም ማውረጃ መንገድ ይኖራልን?›› ሲል ጠየቀው፡፡

‹‹አዎን፣›› ሲል የጎሳ መሪው መለሰ፡፡ ‹‹ሁላችንም. . .ጦርነቱን ማስቆሚያ አንድ

መንገድ እንዳለ እናውቃለን፡፡››

‹‹ምንድን ነው መንገዱ?›› ሲል ዶን ፈካ እያለ ጠየቀው፡፡

‹‹ሰላምን የሚያወርድ ልጅ፣›› ሲል የጐሳ መሪው መለሰ፡፡ ‹‹አንድ ሰው ከእኛጐሳ ልጁን ለሌላው ጐሳ ቢሰጥ፣ ሰላም ይሰፍናል፡፡ ሌላው ጐሳ ያ ልጅ ሰላምንየሚያወርድ ልጅ በመሆኑ ምክንያት ልጁን በፍጹም አይገድለውም፡፡ ደግሞም ሰላምየሚያወርደው ልጅ በሕይወት እስካለ ድረስ የእኛም ጐሳ በፍጹም አይዋጋም፡፡ ነገርግን እርሱ በሚሞትበት ጊዜ፣ ጦርነት እንደገና ይጀመራል፡፡››

‹‹ኧረ፣ እባካችሁ አድርጉት!›› ሲል ዶን በጩኸት ተናገረ፡፡ ‹‹እባካችሁ

ከልጆቻችሁ አንዱን ስጡዋቸው!››

Page 100: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

100

‹‹በእያንዳንዱ ቀን እንዲያደርጉት ሕዝቤን ለምኛለሁ፣›› አለ የጎሳ መሪው

እያዘነ፡፡ ‹‹ነገር ግን፣ ሁሉም፣ ‹‹‘ልጄን መስጠት አልችልም፡፡ ሌላ ሰው ልጁን ይስጥ

ይላሉ፡፡’››ስለዚህ ጦርነት፣...ሮል ከዕለታት አንድ ቀን በአትክልት ስፍራዋ እየሠራች ሳለ፣

አንድ ሰው ልጁን ይዞ ሲሮጥ በማየት እስከ ተገረመችበት ቀን ድረስ ቀጠለ፡፡ የገዛልጁን ይዞ እየሮጠ የነበረው የጎሳው መሪ ራሱ ነበር!

ሚስቱ ከኋላው ልትይዘው እየሞከረች ትሮጣለች፡፡ ተሰናከለችና ጭቃው ላይወደቀች፣ ከዚያም ለልጅዋ እየጮኸች፣ ተነሥታ እንደገና ሮጠች፡፡

የጎሳው መሪበ ቀ ጥ ታ

ወደ ሌላው ጎሳ ሮጠ፣ ሰላም አውራጅ የሆነውን ልጁን ሰጣቸው፡፡በማግሥቱ ዶን እና ካሮል ከእንቅልፋቸው ሲነቁ፣ ሁሉም ነገር ሰላም ነበር . . .

ጦርነት አልነበረም፡፡

በዚያ ምሽት ወንዶች በእሳት ዙሪያ ተቀምጠው ሳለ፣ ዶን፣ ‹‹ፈጣሪ ከቶኃጢአትን አያደርግም፡፡ ነገር ግን እኛ የሰው ልጆች ኃጢአት እንሠራለን፡፡ ኃጢአታችንየፈጣሪ ጠላቶች ያደርገናል›› [ሮሜ 1፡29-32፤ ቈላ. 1፡21-22] ማለትን ጀመረ፡፡

‹‹እናውቃለን፣›› አሉ፡፡ ‹‹አንተ ከመምጣትህ በፊት፣ ሁላችንም፡- ፈጣሪ

መልካም እንደ ሆነ...እኛ መጥፎ እንደ ሆንን...እኛ እርሱን መናገርም እንደማንችል

እናውቃለን፡፡››

ፍክት ባለ ፈገግታ ዶን፣ ‹‹እኔ መልካም የምሥራች አለኝ፡፡ እናንተ ፈጣሪያችሁንማናገር ትችላላችሁ! ለምን? እርሱ ሰላም የሚያወርደውን ልጅ ልኳል፣ የገዛ ልጁንልኳል፡፡››

አንድ ሰው፣ ‹‹ሰላም የሚያወርድ ልጅ አለ!›› ሲል ጮኸ፡፡

ነገር ግን የጎሳው መሪ አሁንም እንዳዘነ ይታያል፡፡ እርሱም ዶንን፣ ‹‹ባለፈው

ሳምንት...ሰዎች ልጁን በመስቀል ላይ ገደሉት ብለህ ነግረኸናል፡፡ ይህም ማለት ሰላም

አውራጁ ልጅ ሞቶአል፡፡ የነበረው ሰላምም አልፏል፣›› ማለት ነው አለው፡፡

ዶን በፈገግታው ገፍቶበት፣ ‹‹ልጁ እንደ ተነሣ፣ ለዘላለምም ሕያው እንደ ሆነ

አስታውሱ፣›› አለ፡፡

ተወያዩበት

Page 101: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

101

እያንዳንዱም፣ ‹‹ሰላም አውራጁ ልጃችን ሕያው ነው! ከፈጣሪያችን ጋር ሰላም

ሊኖረን ይችላል!›› እ ያ ለይጮኽ ጀመር፡፡

ደግሞም የጎሳ መሪው፣ ‹‹ይሁዳ ጀግና አይደለም፡፡

ሰላም አውራጁ ልጃችንን ከድቶታል፣›› ሲል ጮኸ፡፡

ወንዶች፣ ‹‹ፈጣሪ ሰላም አውራጅ ልጁን ልኳል›› ብለው ለሌሎች ጎሳዎች

ለመንገር ሮጡ፡፡በሺህዎች የሚቈጠሩ በኢየሱስ አመኑ፡፡

ከዚያም ሰዎቹ፣ ‹‹በዚያ በመጀመሪያው ቀን ራሳችሁን ባለመቅላታችን

ደስተኞች ነን፣›› በማለት ለዶንና ለካሮል ነገሩአቸው፡፡

ካሮልም በመገረም፣ ‹‹ይህንን ዐቅዳችሁት ነበር?›› ስትል ጠየቀች በመገረም፡፡

ወደ ቤተ ክርስቲያናችን ቅጥር ግቢ ለሚመጡት ሰዎች ብቻ በመስበክ ብዙሰዎችን ወደ ኢየሱስ ማምጣት አንችልም፡፡ ወደ መኖሪያ ቤቶች፣ ሆስፒታሎች፣

እስር ቤቶች . . . እንሂድ፡፡

በውስጥ ተቀምጠህ ጊዜ ከማሳለፍ ይልቅ፣ ከቤተ ክርስቲያን ውጭ ወንጌልበማዳረስ ላይ ጊዜውን አውለው፡፡

Jeú M e` u?ƒ

ኢየሱስ ከቶ ዓለምን ወደ ቤተ ክርስቲያን እንድትመጣ አልጠራትም፡፡

ወደ ዓለም እንድንሄድ ነው የተናገረን!

S•]Á u?„‹

Page 102: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

102

‹‹አዎን፣ በእርግጥም ዐቅደን ነበር፡፡ በጀልባችሁ ላይ በነበራችሁበት ጊዜ፣

‹የተከበራችሁ ራሶች ሆይ፣ ኑ፣› ብለን እየጮኽን ነበር፡፡ አታስታወሱትምን?››

‹‹ጩኸቱን እናስታውሰዋለን፣›› አለች ካሮል ‹‹ነገር ግን በዚያን ጊዜ ቋንቋችሁንአንረዳውም ነበር፡፡ ስለዚህ፣ እባካችሁ፣ ራሶቻችንን ከመውሰድ ምን እንዳገዳችሁንገሩን፡፡››

የጎሳ መሪው፣ ‹‹ዶን ከጀልባው ውስጥ በወጣ ጊዜ፣ ልጁን ይዞ ነበር፡፡ ሕፃን

ልጅ የያዘን ሰው አንገድልም፡፡ ሰላም አውራጅ ልጅ ሊሆን ይችላልና፣›› ሲል ነገራት፡፡

ተቀጥላ

የኢየሱስ ቀለም ምን ዓይነት ነበር?

Page 103: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

103

እንደ ደራሲያን የምናውቀው፡- የአንድ ሰው ቀለም ምንምፋይዳ እንደ ሌለው ነው፡፡

ነገር ግን በሚሊዮንየሚቈጠሩ ሰዎች የኢየሱስን

የቆዳ ቀለም በተመለከተየተሳሳተ አሳብ አላቸው፡፡ስለዚህ እውነተኛውን ነገርልንፈጽመው ይገባል ፡፡

ብዙ ሰዎች፣ ‹‹አይሁዶች ነጮች ናቸው...ኢየሱስ ነጭ ነበር... ሙሴም፣

ጴጥሮስም ሆነ ጳውሎስ እንዲሁ ነጭ ቀለም ያላቸው ሰዎች ነበሩ፣›› ብለው ያስባሉ፡፡

ደግሞም ሰዎች በኢየሱስ ሕይወት ዙሪያፊልም በሚሠሩበት ጊዜ፣ ብዙውን ጊዜ ሰማያዊዓይኖች ያሉትንና ነጭ ቀለም ያለውን ሰው‘ኢየሱስ’ እንደ ሆነ አድርገው ያቀርባሉ፡፡

እውነቱ፡- አብርሃም [የአይሁዶች ሁሉ አባት]አውሮፓዊ አልነበረም፡፡ የተወለደው በዑር ነበር[ገጽ 16]፡፡ የዑር ሰዎች የነበራቸው፡-

ጥቁር ፀጕር፣ጥቁር ዓይኖች፣

ይነስም ይብዛም ቡናማ (ጠይም) ቆዳ ነበር፡፡

ሙሴ፣ ጴጥሮስ፣ ኢየሱስም...እንደዚሁ ይህን ሊመስሉ ግድ ነበር፡፡

ዛሬ አይሁዶች ሁሉም ዓይነት መልኮች (ቀለሞች) አሏቸው፡፡አዎን፣ ዛሬ በአብርሃም ቤተሰብ

ውስጥ፣ አንዳንዶች አሁንም ጠይም(ቡናማ) ቀለም አላቸው፡፡ ነገር ግንሌሎች ነጮች እንዲሁም ሌሎች ጥቁርሆነዋል፡፡

እንዴት ተለወጡ?

Page 104: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

104

መልስ፡- መቼም ቢሆን ጦረኞችእስራኤልን በወረሩ ጊዜ፣ ብዙአይሁዳውያን ወደ ሩቅ ስፍራዎችሸሽተዋል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ፣ ‹‹አይሁድከኢትዮጵያ እስከ ሕንድ ድረስ በ127አገሮች ነበሩ››ይለናል (አስቴር 8፡9)፡፡

ኢየሱስ ከሞተናወ ደ ሰማይ

ከተመለሰ በኋላ፣የሮማ ጦር

እስራኤልን ወረረ [በ70 ዓ.ም]፡፡ከዚያም አይሁዶች፣ አንዳንዶቹ ወደአፍሪካ እንዲሁም ሌሎች ወደአውሮፓ ሸሹ . . . ጥቂቶቹ ብቻበእስራኤል ቀሩ፡፡ [ካርታ ሀን ተመልከት፡፡]

ብዙ መቶ ዓመታት አልፈዋል፡፡ከዚያም፣ በ1948 ዓ.ም (እ.ኤ.አ)አይሁድ ወደ እስራኤል መመለስንጀመሩ [ካርታ ለ]፡፡ እንደ ደረሱ፣የተገነዘቡት፡-

ከ70 ዓ.ም እስከ 1948 ዓ.ምድረስ በአፍሪካ የኖሩት አይሁዶች፣አሁን ጥቊሮች ናቸው፡፡ ለምን?አፍሪካውያንን አግብተዋልና፡፡

ለእነዚያ ሁሉ መቶ ዓመታትበአውሮፓ የኖሩት አይሁዶች አሁን

በረከቶችህንበራስህ ላይአውል፡፡

የደኅንነትወንጌልንለሁሉም‹ሰዎች›ለማድረስ

በረከቶችህንተጠቀም

(መዝሙር 67)፡፡

ምረጥ

ሕዝቦች ሁሉ ደኅንነትህን ያውቁ ዘንድ ባርከን (መዝሙር 67)፡፡

ተወያዩበት

ሀብታም ሆንክ ድኻ፣ለእግዚአብሔር ቃል

ግባለት፡፡

‹‹ደኅንነትህን ወደ ሰዎችሁሉ ለመላክ በረከቶቼንለመጠቀም መንገዶችን

እፈልጋለሁ፡፡››

Page 105: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

105

ነ ጮ ች ና ቸ ው . . . ም ክ ን ያ ቱ ምአውሮፓውያንን አግብተዋልና፡፡

ለእነዚያ ሁሉ ዓመታት በእስራኤል የኖሩት ጥቂት አይሁዶች -አልተለወጡም፡፡አሁንም ከሞላ ጐደል ጠይም የቆዳ ቀለም ያላቸው ናቸው፡፡

ስለዚህ፣ ዛሬ አይሁዶች ሁሉንም የቀለም ዓይነት ይይዛሉ፡፡ ነገር ግን ጥያቄው፡-በኢየሱስ ዘመን የአይሁዶች የቆዳ ቀለም ምን ዓይነት ነበር የሚለው ነው?

መልሱ፡- እነርሱ ከሞላ ጐደል ጠይም ነበሩ፣ [ልክ እስራኤልን ለቅቀው

ወጥተው እንደማያውቁት አይሁዶች ነበሩ]፡፡ስለዚህ እኛ በእውነት የምንለው፡- ኢየሱስ ጠይም ሰው ነበር፡፡ ጠጕሩ ጥቁር

[ቡናማ ያልሆነ] ነበር፡፡ ዓይኖቹ [ሰማያዊ ሳይሆኑ] ጥቁር ነበሩ፡፡ የቆዳው ቀለም

ከሞላ ጐደል ጠይም ነበር፡፡ እርሱ ጥቁርም ሆነ ነጭ የቆዳ ቀለም (መልክ)አልነበረውም፡፡ መካከለኛ ነበር፡፡

ይህ ፋይዳ አለውን? የለውም፡፡ ቀለም ከቶም ፋይዳ አይኖረውም፡፡ለዚህም ነው መጽሐፍ ቅዱስ በፍጹም የቆዳ ቀለሙን የማይጠቅሰው፡፡ዛሬ በአፍሪካ አገሮች፣ አንዳንድ አብያተ ክርስቲያናት የጥቁር ኢየሱስ ሥዕል

አላቸው፤ ደግሞም በምዕራባውያን አገሮች፣ ብዙ አብያተ ክርስቲያናት ነጭ የቆዳቀለም ያለው የኢየሱስ ሥዕል አላቸው፡፡ ለምን? ምናልባት ሕዝባቸው ኢየሱስን‘በእንግድነት ስሜት እንዳይመለከቱት’ አስበው ይሆናል፡፡

ነገር ግን፣ እውነቱን መናገር ይሻላል፡፡ እውነቱም፡- አብርሃም፣ ሙሴ፣ ማርያም፣ኢየሱስ...ቡናማ የቆዳ ቀለም ያላቸው ሰዎች የነበሩ መሆናቸው ነው፡፡

ልጆች፣ ‹‹የኢየሱስ የቆዳ ቀለም ምን ዓይነት ነበር?›› ብለው በሚጠይቁ ጊዜ፣

ምላሻችን፣ ‹‹የእርሱ የቆዳ ቀለም ቡናማ ነበር፤ ነገር ግን የቆዳ ቀለም ምንም ፋይዳ

Page 106: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

106

የለውም፡፡ እርሱ ሁላችንንም በእኩልነት ይወድደናል፡፡ እኛም እርስ በርሳችንበእኩልነት እንዋደዳለን፤›› የሚል ነው፡፡

ለእግዚአብሔር የተመረጠ ዝርያ የለም(የሐዋ. 10፡34)፡፡

1) የቆዳ ቀለምን አስመልክቶ ያለን ትምክሕተኝነት ለማስወገድ ልጆችን/ትላልቅ ሰዎችን እንዴት መርዳት እንችላለን?

2) በአገራችን፣ የኢየሱስን የቆዳ ቀለም አስመልክቶ ሰዎች የተሳሳተአሳብ አላቸውን? እነዚህን አሳቦች ከየት አገኙዋቸው?

በሐዋ. 10 ላይ ለአውሮፓዊው ሰውእንዲመሰክር እግዚአብሔር ጴጥሮስን

ልኮታል፡፡

በሐዋ. 8፡26-38 ለአፍሪካዊ ሰውእንዲመሰክር እግዚአብሔር ፊልጶስን

ልኮታል፡፡

ጴጥሮስ

ፊልጶስ

የሐዋ. 10፡47

የሐዋ. 8፡38

Page 107: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

107

ኢየሱስ፣ ‹‹ወንጌልን ወደ ቅርብም ሆነ ሩቅ ስፍራ ስትወስዱ፣ በገንዘብየበለጠጋችሁ ትሆናላችሁ፣›› ብሎአልን?

አላለም፡፡ እርሱ የነገረን፣ ‹‹ሂዱ...እኔ ከእናንተ ጋር ነኝ፤›› የሚለውን ብቻ

ነው (ማቴ. 28፡19-20)፡፡

ጳውሎስ፣ ‹‹አንዳንድ ጊዜ እበለጥጋለሁ፡፡ በሌላ ጊዜያት ያለ ምግብ፣ የሚሞቅልብስ በሌለበት በድኽነት ውስጥ እኖራለሁ አለ፡፡ ያ ፋይዳ የሌለው ነገር ነው፡፡ኢየሱስ የሰጠኝን ሥራ ለመጨረስ እፈልጋለሁ፤›› ይላል (ፊልጵ. 4፡12፤ 2ኛ ቆሮ.11፡27፤ የሐዋ. 20፡24)፡፡

የዕብራውያን መጽሐፍ እንዲህ ይላል፡-ሀ) አንዳንድ የእምነት ሰዎች ከአንበሳ አፍና ከእሳት ዳኑ (ዕብ. 11፡34)፡፡

ለ) ነገር ግን ሌሎች የእምነት ሰዎች ድኾች ነበሩ (ዕብ. 11፡37-38)፡፡

ሐ) ሁሉም የእምነት ሰዎች በሰማይ ያላቸውን ብድራት ይመለከቱ ነበር (ዕብ.11፡13-16 እና 11፡26)፡፡

ኢየሱስ፣ ‹‹በሽታዎቻችሁን ሁልጊዜ እፈውሳለሁ፣›› ብሎአል?

አላለም፡፡ እርሱ ያንን ከቶ አላለም፡፡ አማኞች ወንጌልን ወደ ሩቅ ስፍራዎችእየወሰዱ ሳለ፣ ብዙውን ጊዜ ይታመማሉ [ለምሳሌ፣ ወባ፣ ወዘተ... ]፡፡አንዳንዶቹ አልተፈወሱም (2ኛ ጢሞ. 4፡20)፡፡ አንዳንዶች ከበሽታ የተነሣ ሞተዋል(2ኛ ነገሥ. 13፡14)፡፡

ተወያዩበት

Page 108: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

108

ኢየሱስ ፍቅሩን...ለመመስከር የሚሆን ኃይሉን...እንዲሁም በሰማያት የሚኖሩሽልማቶችን ተስፋ ሰጥቶአል?

አዎን፡፡ እርሱ ተከታዮቹን፣ ‹‹ስፍራ አዘጋጅላችሁ ዘንድ እሄዳለሁሀ...ሂዱ፣

በኃይል መስክሩለ... መከራ ትቀበላላችሁሐ...ነገር ግን በምድር ላይ

ስላደረጋችሁት ነገር እያንዳንዳችሁን እሸልማችኋለሁ፣››መ ብሎተናግሮአቸዋል፡፡

ሀዮሐ. 14፡1-3፤ ለየሐዋ. 1፡8፤ ሐዮሐ. 16፡33፤ መማቴ. 16፡27፤ 1ኛ ቆሮ. 3፡8፤ 2ኛቆሮ. 5፡10፤ 2ኛ ጢሞ. 4፡8፤ 1ኛ ጴጥ. 5፡4፤ ራእይ 22፡12፡፡

ዓይን ያላየው፣ ጆሮም ያልሰማው...ነገር ግን እግዚአብሔር ለሚወድዱት ያዘጋጀው(1ኛ ቆሮ. 2፡9)፡፡

Page 109: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

109

ውዱ ኢየሱስ ሆይ፣ እንጸልያለን፡፡ እንመሰክራለን፡፡በሩቅ ባሉ ቦታዎች ወዳሉ ሕዝቦች መልካሙን የምሥራች ይዘው እንዲሄዱወንዶችንና ሴቶችን እንልካለን፡፡እነርሱን ለመርዳትም ገንዘብ እንሰጣለን፡፡

ደግሞም ውዱ ኢየሱስ ሆይ፣ እንድንሄድ የምትጠራን ከሆነ፣ እንሄዳለን፡፡የሚያስፈልገንን ሥልጠና እንወስዳለን፡፡

ቋንቋችንን መናገር ወደሚችሉትም ሆነ. . .

ሌላ ቋንቋ ወደሚናገሩ ሰዎች. . .ወደ ምትልከን ወደ የትም ስፍራ እንሄዳለን፡፡

ውድ የሆኑ ቤቶችም ሆነ የቤት ውስጥ መገልገያ ቊሳቊሶች የሌሉን ቢሆንም፣ከእነዚህ አንዳቸውም ለኢየሱስ አልነበሩትም፡፡

በወጣትነታችን የምንሞት ቢሆንም፣ኢየሱስም እንዲሁ ገና በወጣትነቱ ነበር የሞተው፡፡

በእስር ቤት ብንጣል፣ በዚያ የምሥጋና ዝማሬዎችን እንዘምራለን፡፡

ጊዜያችንን፣ ገንዘባችንን . . . ውድ የሆነ ሕይወታችንን እንሠዋለን፡፡

ያንን ቃልኪዳን ዛሬ ትገባለህን? ቃል የምትገባ ከሆነ፣ እዚህ ላይ ስምህን ጻፍ ፡፡

ከዚያም ይህን መጽሐፍ አንብበው ስማቸውን እዚሁ ላይ እንዲጽፉ ሌሎችን ጋብዝ(ነህ. 9፡38)፡፡

1)------------------- 4)----------------- 7)----------------2)------------------- 5)----------------- 8)----------------3) ------------------- 6)----------------- 9)----------------

ስምህን ከጻፍህ በኋላ፣ ብዙ መጸለይን ጀምር፡፡ በፍቅርና በድፍረት መስክር፡፡ፍላጎት ባላቸው ስፍራዎች ላይ ስለ ክርስቶስ እንዲናገሩ መልእክተኞችንእንድትልክ ቤተ ክርስቲያናችሁን አበረታታ፡፡ ለወንጌል ሥራ ለሚሄዱት ሰዎችበልግሥና ስጥ፡፡እግዚአብሔር አንተ እንድትሄድ ከመረጠህ፣ በደስታ ሂድ፡፡

የክርስቶስ ፍቅር ወደ ተግባር ይመራል፡፡

Page 110: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

110

(2ኛ ቆሮ. 5፡14 እና 20ን ተመልከት፡፡)

Page 111: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

111

ሌላ ቋንቋ ልትማር ትችላለህቤተ ክርስቲያናችሁ ‹ቡቦ› የሚባል ቋንቋ የሚናገር ሕዝብ ወዳለበት ስፍራ

ትልክሃለች እንበል፡፡ ያንን ቋንቋ ለመማር ትችላለህን? አዎን፣ ትችላለህ፡፡ እንዴት?ልክ እንደዚህ፡-

አንድ ረዳት ፈልግ፡፡ ‹ረዳት› ማለት ቋንቋውን እንድትማር ሊረዳህ በየቀኑየምታገኘው ሰው ነው፡፡

ረዳትህን በጥንቃቄ ምረጥ፡- ልትፈልግ የሚገባህ ሰው፡-ሀ) በዚያ የተወለደና በልጅነቱም በቡቦ ቋንቋ አፍ የፈታ፣

ለ) በተጨማሪም አንተ የምታውቀውን ቋንቋ [ለምሳሌም፣ እንግሊዝኛ]የሚያውቅ መሆን አለበት፡፡

የትምህርት ቤት አስተማሪን ረዳትህ እንዲሆን አትምረጠው፡፡ አስተማሪ ክፍልውስጥ ያስቀምጥህና በዚያ ያስተምርሃል፡፡ ያ ቋንቋ ለመማር መልካም መንገድአይደለም፡፡ ከክፍል ውጪ ሆኖ፣ ከሰዎቹ ጋር ብዙ በመነጋገር፣ ጊዜን መጠቀምይሻላል፡፡

Page 112: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

112

የመጀመሪያው ቀን፡፡ በቡቦ ቋንቋ፣ ‹‹እንደ ምን አደርህ? ቡቦኛንእየተማርሁ ነው፡፡ ዛሬ ልናገረው የምችለው ይህን ብቻ ነው›› የሚለውንእንዴት እንደሚባል ረዳትህን ጠይቀው፡፡

እነዚህን 3 ዓረፍተ ነገሮች በቡቦኛ ተለማመዳቸው፡፡ ስትሳሳት እንዲያርምህረዳትህን ጠይቀው፡፡ ረዳትህ፣ ‹‹አዎን፣ ሰዎች የምትለውን ይረዳሉ፣›› እስኪልህድረስ ተለማመድ፡፡

ከዚያም ረዳትህን ትተኸው ወደ ጐዳናዎች ሂድ፡፡ በገበያ ቦታ ላሉ፣ ለልጆች፣እንዲሁም ለእያንዳንዱ ሰው እነዚያን ሦስት ዓረፍተ ነገሮች ተናገር፡፡

በሚቀጥለው ቀን፣ ሦስት ተጨማሪ ዓረፍተ ነገሮችን እንድትማር ረዳትህንጠይቀው፡፡ ከዚያም ወደ ጐዳና ሄደህ እነዚያን ዓረፍተ ነገሮች ለብዙ ሰዎችተናገራቸው፡፡

በየቀኑ፣ ተጨማሪ 3 ዓረፍተ ነገሮችን ተማር...ከዚያም በጐዳና ለሚገኙሰዎች ብዙ ጊዜ ተናገራቸው፡፡

ስሕተት በምትሠራበትና ሰዎች በሚስቁበት ጊዜ፣ አትጨነቅ፡፡ከሰዎቹ ጋር ሳቅ፡፡ እንዲያርሙህ ፍቀድላቸው፡፡ ውደዳቸው፡፡ እነርሱም

ይወድዱሃል፡፡

ከጥቂት ወራት በኋላ ከእነርሱ ጋር በቋንቋቸው መነጋገር የመቻልን ደስታታጣጥመዋለህ!

መጽሐፍ እንደምትጽፍ ተስፋ እናደርጋለንእውነተኛ ክርስቲያን ከሆንህ እና የመጽሐፍ ቅዱስ ኰሌጅ ትምህርትህን

ካጠናቀቅህ፣ መጽሐፍ እንድትጽፍ እናበረታታሃለን፡፡

ጥቂት ሰዎች ብቻ ሊረዱት በሚችሉት

ለመረዳት አስቸጋሪ በሆኑ ቃላት አትጻፍ፡፡

እኛ በዚህ መጽሐፍ እንዳደረግነው፣

ጥልቀት ያላቸው እውነታዎችን ለመጻፍ ቀላል ቃላትን ተጠቀም፡፡

እኛ [ኤላይጃ እና ብሩስ] የአንተመጽሐፍ ከእኛ ይልቅ ታዋቂ የመሆኑ ጕዳይአያስጨንቀንም፡፡ እግዚአብሔር እኛንከባረከበት በላይ አንተን ቢባርክህ ደስተኞችነን፡፡

Page 113: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

113

ÄN”e 3:16

የዚህን መጽሐፍ የተወሰነ ክፍል ለመውሰድና በመጽሐፍህ ውስጥ ለማስፈርትጽፍልንና ፈቃድ ትጠይቀን ይሆናል፡፡ ምንም ገንዘብ አናስከፍልህም፡፡ እኛ አንተንማበረታታት ብቻ ነው የምንፈልገው፡፡

መጽሐፍ ከመጻፍህ በፊት፣ ንጹሕ ሕይወት የምትኖር ስለ መሆንህ እርግጠኛ ሁን፡፡እግዚአብሔር በኃጢአት ጸንተው የሚኖሩ ሰዎችን አይጠቀምም፡፡

ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋእግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ

ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልናዮሐንስ 3፡16፡፡

Page 114: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

114

›¨<aû

›<`

›õ]"

ጌታ እስከ ምድር ዳር ድረስመድኃኒት ትሆን ዘንድ፣ለአሕዛብ ብርሃን አድርጌሰጥቼሃለሁ ፡፡

(ኢሳይያስ 49፡6 እናየሐዋርያት ሥራ 13፡47)

ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጠኝ፡፡ እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ፣በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፣ ያዘዝኋችሁንም እንዲጠብቁእያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው ፡፡

(ማቴዎስ 28፡18-20)

እናንተ፡- ገና አራት ወር ቀርቶአል፣ መከርም ይመጣል ትሉ የለምን? እነሆእላችኋለሁ፣ ዓይናችሁን አንሡ አዝመራውም አሁን እንደ ነጣ እርሻውን ተመልከቱ ፡፡

( ዮ ሐ ን ስ4፡35)

መከሩስ ብዙ ነው፣ ሠራተኞች ግን ጥቂቶች ናቸው፤ እንግዲህ የመከሩን ጌታ ወደመከሩ ሠራተኞች እንዲልክ ለምኑት፡፡

(ማቴዎስ 9፡37-38)

ኤላይጃህ ማስዋንጋኒ

ብሩስ ብሪትን

Page 115: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

115

ልጄ ሆይ፣ ዛሬ ሂድናበወይኔ አትክልት ሥራ አለው፡፡

(ማቴዎስ 21፡28)

ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኃይልን ትቀበላላችሁ፣በኢየሩሳሌምምበይሁዳም ሁሉ በሰማርያም እስከ ምድር ዳርም ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ

(የሐዋርያት ሥራ 1፡8)፡፡

ስለ ስሜም ቤቶችን ወይም ወንድሞችን ወይም እኅቶችን ወይም አባትን ወይም እናትንወይም ሚስትን ወይም ልጆችን ወይም እርሻን የተወ ሁሉ መቶ እጥፍ ይቀበላል(ማቴዎስ 19፡29)፡፡

በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፤ ነገር ግን አይዞአችሁ፤ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ(ዮሐንስ 16፡33)፡፡

ለእናንተ በምድር ላይ መዝገብ አትሰብስቡ (ማቴዎስ 6፡19)፡፡በስሙም ንስሐና የኃጢአት ስርየት ከኢየሩሳሌም ጀምሮ በአሕዛብ ሁሉ ይሰበካል(ሉቃስ 24፡47)፡፡

ሐዋርያው ጳውሎስ እንዲህ አለ፡-

እንዲሁም በሌላው ሰው መሠረት ላይ እንዳልሠራ የክርስቶስ ስምበተጠራበት ስፍራ ሳይሆን ወንጌልን ለመስበክ ተጣጣርሁ ፡፡ (ሮሜ 15፡20)

ካርታሀ

በ70 ዓ.ም አብዛኞቹ አይሁዶችእስራኤልን ትተው ሄዱ

አውሮፓ

እስራኤል

እስያ

ሕንድ

ኢትዮጵያ

አፍሪካ

Page 116: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

116

በድካምና በጥረት ብዙ ጊዜም እንቅልፍ በማጣት፣ በራብና በጥም፡፡ (2ኛቆሮንቶስ 11፡27)

ነገር ግን ሩጫዬንና ከጌታ ከኢየሱስ የተቀበልሁትን አገልግሎት እርሱምወንጌልን መመስከር እፈጽም ዘንድ ነፍሴን በእኔ ዘንድ እንደማትከብር እንደከንቱ ነገር እቈጥራለሁ፡፡ (የሐዋርያት ሥራ 20፡24)

እንግዲህ በጌታችን ምስክርነት ወይም በእስረኛው በእኔ አትፈር፣ ነገር ግንእንደ እግዚአብሔር ኃይል መጠን ስለ ወንጌል አብረኸኝ መከራን ተቀበል፡፡(2ኛ ጢሞቴዎስ 1፡8)

እንግዲህ ያላመኑበትን እንዴት አድርገው ይጠሩታል? ባልሰሙትስ እንዴትያምናሉ? ያለ ሰባኪስ እንዴት ይሰማሉ? መልካሙን የምሥራች የሚያወሩእግሮች እንዴት ያማሩ ናቸው ተብሎ እንደ ተጻፈ ካልተላኩ እንዴትይሰብካሉ? (ሮሜ 10፡14-15)

ወደ እስጳንያ በሄድሁ ጊዜ . . . በጕዞዬ እንድትረዳኝ ተስፋ አደርጋለሁ ፡፡(ሮሜ 15፡24)

እግዚአብሔር በደስታ የሚሰጡትን ሰዎች ይወዳል፡፡ (2ኛ ቆሮንቶስ9፡7)

ዛሬ በዓለም ላይ ቋንቋቸውን የምትናገዮንየሚቈጠሩ ሰዎች አሉ፡፡ ደግሞምክርገራቸውምና፡፡

ከአንድ አንባቢ የተላከ ደብዳቤ

ከ1948 ዓ.ም በኋላ አይሁዶች ተመለሱ

ካርታ ለ

አውሮፓ

እስያእስራኤል

አፍሪካ

የዛሬዎቹ አይሁዶች ሁሉም ዓይነት የቆዳ ቀለም (መልክ) አላቸው

Page 117: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

117

በኤላይጃህ እና ብሪትን በጋራ የተጻፉ መጻሕፍት1. በድፍረት በኃይል እንነሣ

2. የኢየሱስ ኃይል፣ 1ኛ መጽሐፍ

በብሩስ እና ኮሮል ብሪትን የተጻፉ መጻሕፍት1. የጋብቻ እንቆቅልሾችና መፍትሔዎቻቸው

2. Answers for Your Marriage

Page 118: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

118

3. በወጣቶች የሚነሡ ጥያቄዎች

4. ጣፋጭዋ ልጅተወያዩበት

Page 119: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

119

ኢየሱስ ተስፋ የገባው ምንድን ነበር?

Page 120: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

120

Page 121: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

121

የእኛ ተስፋ

Page 122: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

122

Page 123: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

123

የእስል

ምና

ሃይማ

ኖት

፣‹ ‹

ኢየሱ

ለኃ

ጢአ

ትአል

ሞተ

ም፣››

ይላል

፡፡

የሂንዱ

ሃይ

ማኖ

ት፣

‹‹ብ

አማል

ክትን

ያመል

ካል፡፡››

የቡድ

ሒስት

ሃይ

ማኖ

ት፣

‹‹ሙ

ታን

ከሆኑ

ወላጆ

ችና

ዘመዶ

ች ጋ

ር ይ

ነጋገራ

ል፡፡››

ሌሎ

ች ሦ

ስት ሃ

ይማ

ኖቶ

Page 124: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

124

Page 125: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

125

ጕዳዩ ስለ እኛ አይደለም፤ስለ ክርስቶስ እንጂ፡፡

ለElijiah and Bruce, powerforvictoryBox 249, Mbabane, Swazilandemail: [email protected] ብለህ ጻፍ፡፡

Page 126: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

126

ለራስህና ለትምህርትህ ተጠንቀቅ፣በእነዚህም ጽና፣ ይህን ብታደርግ፣

ራስህንም የሚሰሙህንም ታድናለህ (1ኛ ጢሞ. 4፡16)፡፡

ከጋብቻ በፊትየግብረ ሥጋግንኙነትን፣‹አላደርግም›በል (1ኛ ተሰ.4፡3-5)

በጋብቻ ውስጥከሚስትህ ጋርበሚሆንየፍትወትሕይወት ተደሰት(1ኛ ቆሮ. 7፡3-9)

ከሚስትህ በቀርከማንም ጋርየግብረ ሥጋግንኙነትአታድርግ

(ዕብ. 13፡4)፡፡

Page 127: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

127

Page 128: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

128

(ማቴ. 28፡19)

Page 129: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

129

Page 130: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

130

በሊቢያ ያሉ የበርበር ሰዎች፣

በሞሮኮ፣ በሞሪታኒያ፣ አልጄሪያ. . . ያሉ

በሚሊዮኖች የሚቈጠሩ ዐረቦች

አንድ ጊዜ እንኳ ሳይሰሙት፣

ወንጌል በዓመት 52 ጊዜ ሲሰበክ ለመስማት

ምን መብት አለን?

ብዙ ገንዘብን በራሳችን ላይ ከማዋላችን በፊት፣ ለወንጌልማዳረስና ለሚሲዮናዊነት

ሥራ በልግሥና እንስጥ!

ናይጄሪያዊው ዶ/ር ቲ. አዲዬሞ

³_ u¯KU Là s”s†¨<”

¾Uƒ“Ñ` u?} ¡`e+Á””

Ád¿ uT>K=Ä” ¾T>rÖ\ c

­‹ ›K<:: ÅÓVU ’²=I c

­‹ u¡`e„e ›ÁU’<U'

U¡”Á~U T”U ¨”Ñ@M

¾’Ñ^†¨< ¾KU“::

Page 131: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

131

ውድ ወንድሞቼ፣ ማስዋንጋኒ እና ብሪትን፣‹‹በድፍረት በኃይል ተነሣ›› እንደሚለው ያለ መጽሐፍ ከዚህ በፊት ከቶ

አላነበብሁም፡፡በውጭ ስላለው ዓለም ምንም ዓይነት እውቀት ሳይኖረኝ፣ በቤተ ክርስቲያን

ውስጥ ከሚቀመጡት ሰዎች መካከል አንዱ መሆኔን ልተንፍሰው፡፡ መጽሐፋችሁዓይኖቼን ከፍቶታል፡፡

ምን ያህል ሰዎች ያለ ክርስቶስ እንደ ሆኑ በእውነቱ እንድገነዘብ በማድረጉልቤን ነክቶታል፡፡

ውሳኔ አድርጌአለሁ፡፡ እጸልያለሁ፡፡ ገንዘብ እሰጣለሁ፡፡ ደግሞምእግዚአብሔር ከላከኝ፣ እሄዳለሁ፡፡

ቀድሞውኑ መመስከር ጀምሬያለሁ፡፡አሁን መጋቢያችን እሑድ እሑድ ከምዕራፍ 1-11 ያለውን በቤተ ክርስቲያን

እንዳስተምረው ፈልጓል፡፡ ከእያንዳንዱ የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት በፊት ይህንለ40 ደቂቃዎች ያህል አከናውነዋለሁ፡፡

በአገልግሎቶቹ፣ መጋቢው ራሱ በመጽሐፋችሁ ካሉት ጥቅሶች ውስጥይሰብካል፡፡

ከአገልግሎቱ በፊት፣ምዕራፍ 1-6 እና 8-11ን ከመጽሐፉ

አስተምር፡፡

በአገልግሎቱ ወቅት፣ በገጽ 16-29፣32- 47፣ 51-69፣ 74-77፣ 88-107፣119፣ 127- 129 ካሉት ውስጥ

ስበክ፡፡

Page 132: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

132

የኤስ ኣይ ኤም ሥነ ጽሑፍየፖሣ.ቁ. 127፣ አዲስ አበባብለው ይጻፉልን፡፡

[email protected]ኢ-ሜይል ያድርጉልን፡፡

Page 133: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

133

Page 134: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

134

Page 135: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

135

Page 136: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

136

Page 137: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

137

Page 138: በድፍረት በኃይል እንነሣcdn.good-amharic-books.com/arise.pdf · ይህ መጽሐፍ በቅርብምሆነ ሩቅላሉ ወንጌልን ለማዳረስ የሚቀጣጠል

138