የአሜሪካ ሕገ መንግሥት -...

86
--------------------------------------------------------------- የአሜሪካ ሕገ መንግሥት The American Constitution ተርጏሚ:- ዶር ከፋል ገብረጊዮርጊስ Translated by: Georgis Kefale, M.D. February 2017 (የካቲት 2009 ..) እኛ የተባበሩት አሜሪካ ሕዝብ፣ ፍጹም የሆነ ሕብረት ለመመሥረት፣ ፍትህን ለማስፈን፣ የሀገር ውስጥ ጸጥታን ለማስከበር፣ የጋራ መከላከያን ለመገንባት፣ አጠቃላይ ደኅንነትን ለማሳደግና የነጻነትን ፀጋ ለራሳችንና ለሚመጣው ትውልድ ለማረጋገጥ ወስነን፣ ይህንን የተባበሩት አሜሪካ ሕገ መንግሥት መስርተናል። ።።።።።።። የዚህ መግቢያ ጽሁፍ ቁልፍ ቃል "እኛ የተባበሩት አሜሪካ ሕዝብ..." የሚለው ነው። "እኛ የአሜሪካ ክፍለ ግዛቶች" ሊል ይችል ነበር። ይህም የትብብሩን አንቀጽ (Article of Confederation) ብዙ ይመሳሰለው ነበር። "እኛ ሕዝብ" የሚለው፣ ፕሬዝደንት ሊንከልና ሰሜናውያኑ፣ ደቡባውያኑን ወደ ውህደቱ ለመመልስ የተጠቀሙበት ቃል ነው። ክርክራቸውም ማንኛውንም ክፍለ ግዛት የመገንጠል መብት የለውም ከሚል እምነት የመነጨ ነበር። ይህች አገር የሁሉንም አሜሪካኖች ትብብር Page 1

Upload: others

Post on 02-Feb-2020

40 views

Category:

Documents


0 download

TRANSCRIPT

---------------------------------------------------------------

የአሜሪካ ሕገ መንግሥት The American Constitution

ተርጏሚ:- ዶር ከፋል ገብረጊዮርጊስTranslated by: Georgis Kefale, M.D.February 2017 (የካቲት 2009 ዓ.ም.) እኛ የተባበሩት አሜሪካ ሕዝብ፣ ፍጹም የሆነ ሕብረት ለመመሥረት፣ ፍትህን ለማስፈን፣ የሀገር ውስጥ ጸጥታን ለማስከበር፣ የጋራ መከላከያን ለመገንባት፣ አጠቃላይ ደኅንነትን ለማሳደግና የነጻነትን ፀጋ ለራሳችንና ለሚመጣው ትውልድ ለማረጋገጥ ወስነን፣ ይህንን የተባበሩት አሜሪካ ሕገ መንግሥት መስርተናል።

።።።።።።።

የዚህ መግቢያ ጽሁፍ ቁልፍ ቃል "እኛ የተባበሩት አሜሪካ ሕዝብ..." የሚለው ነው። "እኛ የአሜሪካ ክፍለ ግዛቶች" ሊል ይችል ነበር። ይህም የትብብሩን አንቀጽ (Article of Confederation) ብዙ ይመሳሰለው ነበር። "እኛ ሕዝብ" የሚለው፣ ፕሬዝደንት ሊንከልና ሰሜናውያኑ፣ ደቡባውያኑን ወደ ውህደቱ ለመመልስ የተጠቀሙበት ቃል ነው። ክርክራቸውም ማንኛውንም ክፍለ ግዛት የመገንጠል መብት የለውም ከሚል እምነት የመነጨ ነበር። ይህች አገር የሁሉንም አሜሪካኖች ትብብር

Page �1

ፈጥራለች። የመግቢያ ጽሁፉ፣ የህብረት መንግሥቱንም (Federal government) ቁልፍ ሚና ይዘረዝራል፦ አንደኛ "የጋራ መከላከያ ሊያቀርብ"፤(ትንሽ ያተረጏጎም መዛባት ቢኖርበትም፣ ግልፅ ሚናው ይሄ ነው።) ሁለተኛው ሚና "ዐይን በሚስበው" ሐረግ-"የሕዝብን ደኅንነት ለማሳደግ" የሚለው ነው። ይህ ሐርግ ፣ ብዙ ነገሮችን ሊያጠቃልል ይችላል። መንገድ ከመስራት እስከ ዜጋን ማስተማር ሊያካትት ይችላል። የመጨረሻው ቁልፍ ሐረግ፣ ("የነጻነትን ፀጋ ለራሳችንና ለሚመጣው ትውልድ ለማረጋገጥ")፣ የሚለው ሁሉን አካታች ሐረግ፣ በተለያየ መንገድ ሊተረጎም ይችላል። ነገር ግን፣ ይህ ሐረግ በግልጽ የሚያስቀምጠው፣ የሕገ መንግሥቱ ተቃኞች (Framers) ቁልፍ ዓላማ፣ "ነፃነት" መሆኑን ነው።

።።።።።።።

አንቀፅ ፩

ክፍል 1

1.1. የሕግ አውጭ ስልጣን፣ ለተባበሩት አሜሪካ መንግሥት ተወካዮች ምክር ቤት ይሰጣል። ይህም አካል፣ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤትና (Senate) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት(House of Representatives) ይሆናል።

።።።።።።።።

ይህ ሐረግ፣ የአስተዳደር ስርዓታችንን ያካትታል(bicameral system)። አሜሪካ፣ ሁልት ክፍል ባለው ምክር ቤት፦ የሕዝብ ተወካዮች የሕግ

Page �2

አውጭና የሕግ መወስኛ ምክር ቤት - ትተዳደራለች። ይህም ስርዓት፣ በሕዝብ ብዛት የሚወከል ምክር ቤት የፈለጉትን ትላልቅ ክፍለ ግዛቶችና ሁልም ግዛቶች እኩል እንዲሆኑ የፈለጉትን ትናንሽ ግዛቶች፣ ለማስማማት የተደረገ የ"ታላቅ አስታራቂ ሀሳብ" ውጤት ነው። ይህም አስታራቂ ሀሳብ፣ ሁልት አካላትን ፈጠረ--አንዱ የግዛቶቹን ሕዝብ ቁጥር የሚያንጸባርቅ አባላትን የያዝ፣ ሁለተኛው ደግሞ የግዛቶቹን እኩልነትን የሚያንጸባርቅ አባላትን ያካተተ ነው። ይህ ክፍል፣ "የሕግ አውጭው ስልጣን ...ይሰጣል" የሚሉ ቃላትን ይጠቀማል። አንዳንድ የሕገ መንግሥቱ ተርጏሚዎች፣ ይህንን ሐረግ ትልቅም ውሱንም ነው ብልው ይገልጹታል። ሕገ መንግሥቱ እነዚህን ቃላቶች የሚጠቅሰው፣ የሕግ አውጭ ምክር ቤቱን ስልጣን በሚገልጽበት ጊዜ ብቻ እንጂ ሌሎች ሕግ አውጭ ሀይሎችን አይመለከትም።

።።።።።።።

ክፍል 2

1.2.1. የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤቱ አባላት፣ ከየክፍለ ግዛቱ በየሁለት ዓመት፣ በሕዝቡ የሚመረጡ ሰዎች ይሆናሉ። እያንዳንዱ ተመራጭም፣ ለሌሎች የክፍለ ግዛቱ ልዩ ልዩ ሕግ አውጭ አካል አባልነት ለሚደረጉ ምርጫዎች የሚያስፈልገው ብቃት፣ ለዚህም እንዲኖረው ይጠበቅበታል።

።።።።።።።።

ይሄም የሚያመለክተው፣ የምክር ቤቱን አባላት የሚመርጠው የክፍለ ግዛቱ ሕዝብ እንጅ የሕግ አውጭው ክፍል እንዳልሆነ ነው።

።።።።።።።።

Page �3

1.2.2. ሀያ አምስት ዓመት ያልሞላውና ለሰባት ዓመታት የአሜሪካ ዜጋ ያልሆነና በሚመረጥበት ክፍለ ግዛት ነዋሪ ያልሆነ ሰው፣ የሕዝብ ተወካይ ምክር ቤት እጩ ሊሆን አይችልም።

።።።።።።።

ይህ የሚጠቅስው፣ የተመራጩ ዕድሜ 25 ዓመት መሆን እንዳለበት ነው። ከፍትኛው ፍርድ ቤትም፣ በክፍለ ግዛቶች ሌላ መለኪያ መደረግ እንደማይቻል ወስኗል።

።።።።።።።

1.2.3. የተወካዮች ቁጥርና ቀጥተኛ ታክስ፣ በአባል ክፍለ ግዛት ውስጥ በሚኖሩ ነጻ ዜጎች ቁጥር መጠን ይደለደላል። በተጨማሪም፣ አገልግሎታቸውን ያልጨረሱ ግለ ሰቦችን ያጠቃልላል። ታክስ የማይክፍሉ ቀይ ሕንዶችን የማይጨምር ሆኖ፣ ለሌሎች ሰዎች በሙሉ በወከፍ ሶስት አምስተኛ ቁጥር ይሰጣቸዋል። ትክክለኛው አቆጣጠር፣ የአሜሪካ ምክር ቤት አባላት በተሰበሰቡ በሶስት ዓመት ጊዜ ውስጥና ከዛም በየአሥር ዓመቱ፣ ሕግ በሚፈቅደው መልኩ መከናወን ይገል። የተወካዩ ቁጥር፣ ከአንድ ሰው ለሰላሳ ሺህ ሕዝብ መብለጥ የለበትም። ነገር ግን፣ እያንዳንዱ ክፍለ ግዛት ቢያንስ አንድ ተወካይ ይኖረዋል። አስፈላጊው ቁጥር እስኪከናወን ድረስ፣ የኒው ሀምፕሸር ክፍለ ሀገር ሶስት፣ ማሳቹሰትስ ስምንት፣ ሮድ አይላንድና የፕሮቪደንስ እርሻ አንድ አንድ፣ ከኔክቲከት አምስት፣ ኒው ዮርክ ስድስት፣ ኒው ጀርሲ አራት፣ ፔንሲልቬኒያ ስምንት፣ ዴለወር አንድ፣ ሜሪላንድ ስድስት፣ ቨርጅንያ አስር፣ ሰሜን ካሮላይና አምስት፣ ደቡብ ካሮላይና አምስት እና ጆርጂያ ሶስት ተወካይ ይሆናል።

።።።።።።።

Page �4

ይህ ሐረግ፣ የተወካዮቹ ቁጥር በሕዝቡ ቁጥር መሠርት እንደሚወሰን ያመለክታል። በተጨማሪም ይህ ሐረግ፣ በጣም አስከፊ ምዕራፍ ያለው ነው። ምክንያቱም፣ በሰሜን ግዛቶች ያሉት ዜጎች የደቡብ ግዛቶቹ ዜጎች ባሮቻቸውን በሕዝብ ቆጠራ ውስጥ እንዳያስገቡ ይቃወሙ ስለነበር፣ እንደ አስታራቂ ሀሳብ የተጻፈ ነው። ባሮችም እንደ 3/5 ሰው ተቆጠሩ። በዚህ ሐረግ መሠረትም ነው የአሜሪካ ሕዝብ ቆጠራ በየአሥር ዓመታት መከናወን ያለበት።

።።።።።።።

1.2.4. በማንኛውም ክፍለ ግዛት የውክልና ትርፍ ቦታ ሲኖር፣ የክፍለ ግዛቱ የአስተዳደር ባለ ስልጣን፣ የምርጫ ሰንድ በማቅረብ ቦታው እንዲሞላ ያደርጋል።

።።።።።።።

በዚህ ሐረግ መሠረት፣ የግዛቱ አገረ ገዢ ልዩ የምርጫ ጥሪ በማዘጋጀት፣ በመሞት ወይም ሥራ በማቆም የተፍጠሩ ክፍት ቦታዎችን ያሟላል።

።።።።።።።

1.2.5. የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የራሱን ሊቀ መንብርና ሌሎች ሀላፊዎችን የመምረጥና በጥፋት የተጠረንጠሩ ባለስልጣናትን ለፍርድ የማቅረብ የብቻ ስልጣን አለው።

ክፍል 3

Page �5

1.3.1. የሕግ መወሰኛው ምክር ቤት (Senate)፣ ከየክፍለ ግዛቱ (states) ባሉ ሕግ አውጭ አካላት በተመረጡ፣ ለስድስት ዓመት የሥራ ዘመን በሚመደቡ ሁለት ሁልት ተወካዮች ይካተታል። እያንዳንዱም አባል አንድ ድምጽ ይኖረዋል።።።።።።።

በአሥራ ሰባተኛው የማሻሻያ ሀሳብ መሰረት፣ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት አባል በግዛቱ ሕግ አውጭ አካል መመረጡ ቀርቶ፣ ቀጥታ በሕዝቡ እንዲመረጥ አድርጎታል። መሥራቾቹ የምክር ቤት አባል የሥራ ዘመን 6 ዓመት እንዲሆን ያደረጉበት ምክንያት፣ ምክር ቤቱ የሰከነና በአስቸኳይ የሕዝብ ፍላጎቶች እንዳይታወክ ስለፈለጉ ነው።

።።።።።።።

1.3.2. ከመጀመሪያው ምርጫ በሁዋላ ወዲያው እንደተሰበሰቡ፣ ወደ ሶስት ቦታ ይከፋፈላሉ። የመጀመሪያዎቹ ተመራጮች የሥራ ዘመን ከሁልት ዓመት በሁዋላ ሲፈጸም፣ የሁለተኛው ክፍል በአራተኛው ዓመት እና የሶስተኛው ክፍል ደግሞ በስድስተኛው ዓመት በመሆን፣ አንድ ሶስተኛው በየሁለት ዓምት እንዲመረጡ ይደረጋል። በማንኛውም ክፍለ ግዛት የሕግ አውጪ ክፍል ውስጥ፣ በሥራ ማቆም ወይም በሌላ ምክንያት ክፍት ቦታ ከተፈጠረ፣ እስከሚቀጥለው የሕግ አውጪው ስብሰባና ውሳኔ ድረስ፣ አስተዳደሩ ጊዜአዊ ሹመት ሊያደርግ ይችላል። ።።።።።።።

ይህ ሐረግ፣ ለሕግ አውጭው ክፍል አፈራራቂ ያገልግሎት ዘመንን መሠረተለት። በዚህም ምክንያት፣ በማንኛውመ ዓመት ለምርጫ የሚዘጋጁት አባላት 1/3ኛዎቹ ብቻ ናቸው። ይህም ሐረግ፣ ምክር ቤቱ የሰከነና የተረጋጋ ስሜት እንዲኖረው ያደርጋል። ስለዚህም በጊዜው

Page �6

መስራቾቹ፣ ተወካዮቹ ወዲያው እንደተመረጡ፣ ለሚቀጥለው ምርጫቸው ወደሚጠቅም የገንዘብ ስብሰባ ሥራ ይሰማራሉ ብለው አልገመቱም ነበር።

።።።።።።።

1.3.3. ማንኛውም ዜጋ፣ ዕድሜው ሰላሳ ዓመት ካልሞላው፣ ለዘጠኝ ዓመት የአሜሪካ ዜጋ ካልሆነና የክፍለ ግዛቱ ነዋሪ ካልሆነ በስተቀር፣ ለሕግ አውጭው አካል አባልነት መመረጥ አይችልም።

።።።።።።

በቀድሞዎቹ ዓመታት ይህ ያስፈለገበት ምክንያት ተወካዮቹ ለሁለት ክፍለ ግዛታ ታማኝነት እንዳይኖራቸው ነው።

።።።።።።።

1.3.4. የአሜሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት፣ የሕግ መወሰኛው ምክር ቤት (senate) ፕሬዝደንት ይሆናል። ነገር ግን፣ አባሎቹ ለእኩል ካልተከፈሉ በስተቀር ድምፅ መስጠት አይችልም።

።።።።።።።።

ይህ መብት፣ ምክትል ፕሬዝደንቱ እኩል የሆኑ ድምፆችን የመፍታት ስልጣን ይሰጠዋል። በተጨማሪ ግን፣ አባልነቱ ካስተዳደሩ ወይስ ከሕግ አውጭው ክፍል ስለመሆኑ ጉዳዩን አሻሚ አድርጎታል። ይህ ጥያቄ፣ እስከ ዛሬ ድረስ ሙሉ በሙሉ መልስ አላገኘም።

።።።።።።።።።

Page �7

1.3.5. ምክር ቤቱ የራሱን ሥራ አስኪያጅ መሪዎችና ፕሬዝዳንቱ በሌለብት ወይም የአሜሪካ ፕሬዚደንትነትን ቦት በያዘ ጊዜ የሚተካው ፕሬዝደንት (president pro temporarily) ይመርጣል።።።።።።።

ይህም፣ ምክር ቤቱ በፈለግው መንገድ እንዲደራጅ ስልጣን ሰጥቶታል። የምክር ቤቱ ተመራጭ ሊቀ መንበር፣ ባህላዊ የሆነ የበልይ ስፍራ ያለው ነው። እስከ መካከለኝው ሀያኛው ዘመናት ድረስ፣ የሀገሪቱ ምክትል ፕሬዝደንቶች ብዙውን ሥራቸውን የሚያከናውኑት በምክር ቤቱ ሊቀ መንበርነት ነበር። ከዚያ በሁዋላ ግን፣ ብዙም ጊዜ ስለማያሳልፉ፣ የምክር ቤቱን ተመራጭ ሊቀመንብር ሥራ ከፍተኛ ስፍራ ሰጥቶታል።

።።።።።።።

1.3.6. ምክር ቤቱ፣ ማንኛውንም የተከሰሰ የመንግሥትት ባለሥልጣን፣ የመበየን ሙሉ ስልጣን ይኖረዋል። ለዚህ ጉዳይ በሚሰየምበት ግዜ፣ ሥራውን በመሀላ ያከናውናል። የአሜሪካ ፕሬዝደንት በሚዳኝበት ግዜ፣ የአሜሪካ ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ የበላይ ሹም፣ በሊቀመንበርነት ይመራዋል። ማንም ሰው፣ ካሉት አባላት ያለ ሁለት-ሶስተኛ የድምፅ ስምምነት በስተቀር አይፈረድበትም።

።።።።።።።

የሕግ መወሰኛው አካል፣ በሕግ አውጭው ምክር ቤት በወንጀል የተከሰሰን ሰው የመዳኘት ስልጣን አለው። አግባብ ከሆነ፣ የሕግ አውጭው ክፍል የወንጀል ክስ ያቀርባል። የሕግ መወሰኛው ምክር ቤት ፍርድ ይሰጣል። ሁለቱ ይህ ክስ የቀረበባቸው፣ አንድሩ ጆንሰንና ዊሊያም ክሊንተን፣ በሕግ አውጭው ምክር ቤት ጥፋተኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል።

Page �8

።።።።።።።

1.3.7. በወንጀል የመከሰስ (impeachment) የፍርድ ወሳኔ፣ ከሥራ ከማባረርና ሌላ ክብር ካልው የአሜሪካ መንግሥት ሥራ ጥቅማ ጥቅሙና ዕምነት ከማገድ ሊያልፍ አይችልም። ነገር ግን፣ የተፈረደበት አካል፣ ከሌላ ሕጋዊ ክስ ሙክረት (trial) ፍርድና ቅጣት አይድንም።

።።።።።።።

ይህ አንቀፅ፣ የምክር ቤቱን የፍርድ ውሳኔ ስልጣን ይወስነዋል። ከሥራ ከማሰናበት አልፎ ሌላ ቅጣት መጣል አይችልም። ሌላ ቅጣት መጣል በፍርድ ቤቶች ክልል ስር ነው።

።።።።።።።

ክፍል 4

1.4.1. ሕግ መወሰኛ ምክር ቤትና የሕዝብ ሕግ አውጭ ምክር ቤት አባላት ምርጫ፣ ጊዜ፣ ቦታና ሥርዓት በየክፍለ ግዛቱ ባለው የሕግ አውጭ አካል ይወሰናል። ነገር ግን፣ ምክር ቤቱ ከሕግ መወሰኛ ምክር ቤት አባልነት ምርጫ ቦታዎች በስተቀር፣ እነዚህን መተዳደሪያ ደንቦች በሕግ መሻር ወይም መለወጥ ይችላል።

።።።።።።።።

ይህ አንቀፅ፣ ክፍለ ግዛቶች የምርጫ ጊዜንና የአሰራርን ዘዴ እንዲቆጣጠሩ መብት ይሰጣቸዋል። በተጨማሪ ግን፣ ምክር ቤቱ የክፍለ ግዛቶቹን መብት በመሰርዝ፣ የራሱን መመሪያ ሊያወጣ ይችላል።

Page �9

።።።።።።።።

1.4.2. ምክር ቤቱ ቢያንስ በዓመት አንዴ ይሰበስባል። ይህም ስብሰባ ወደ ሌላ ቀን በሕግ ካልለወጠው በስተቀር፣ በመጀመሪያው የታህሳስ ወር ባለው ሰኞ ዕለት ይውላል።

።።።።።።።።

ሕገ መንግሥቱ ምክር ቤቱ ቢያንስ በዓምት አንድ ግዜ የመሰብሰቡን አስፈላጊነት አስቀምጧል። በአህጉራዊዉ ምክክር ግዜ፣ በዓምት አንዴ የሚያሰባስብ በቂ ሥራ አይኖርም የሚል ስጋት፣ በአንዳንዶቹ አባላት ተነስቶ ነብር። አንዳንዶቹ ደግሞ ግዜው ካለው፣ ምክር ቤቱ አላስፈላጊ ውሳኔዎችን ያስተላልፋል የሚል ፍራቻ ነበራቸው። ውሎ አድሮ ግን፣ የስብስቡ አባላት ለጠንካራ ማእከላዊ መንግሥት ስላደሉ፣ የዓመታዊውን ስብሰባ አስፈላጊነት ተረዱት።

።።።።።።።።

ክፍል 5

1.5.1. እያንዳንዱ ምክር ቤት፣ የየራሱ የምርጫ፣ የምርጫ ውጤትና የአባልቹ ብቃት ለኪ ዳኛ ይሆናል። ሥራውንም በአብላጫ ምልአተ ጉባኤ ያከናውናል። ነገር ግን፣ አነስተኛ ቁጥር ያላቸው አባላት፣ ስብሰባዎችን ቀን በቀን ጥለው በመውጣት፣ ሕጉ በሚፈቅደው መሠረት፣ የቀሩ አባሎች እንዲገኙ ማስገደድ ወይም ማስቀጣት ይችላሉ።

።።።።።።።

Page �10

በሕገ መንግሥቱ መሠረት፣ አንድ ሰው በእርግጥ መመረጥ አለመመረጡን መወሰን የየምክር ቤቱ ፈንታ ነው። ማንኛውንም ሥራ ለማከናወን፣ ቢያንስ ግማሽ አባላቱ መገኘት ይኖርባቸዋል። ምክር ቤቱ፣ አባሎቹን በተቻለው መንገድ አስገድዶ ወደ ሥራ ቦታቸው እንዲቀመጡ የማድረግ መብት፣ በሕገ መንግሥቱ ተሰጥቶታል። በ1988 ዓ.ም. ፣ የምርጫ ውድድር ገንዘብ አሰባሰብ ጉዳይ በሚመከርበት ግዜ፣ ስርዓቱን ለማስተጉዋጎል ሪፖብሊካኖች ከወንበራቸው በቀሩበት ግዜ፣ ይህ አንቅፅ ሥራ ላይ ውሎ ነበር። በግዜው ምክር ቤቱን ይቆጣጠሩ የነበሩት ዴሞክራቶች፣ ይህንን አንቅፅ በመጠቀም፣ በሥራ አዳራሹ ወንበራቸው ላይ ያልተገኙት አባሎች እንዲታስሩ አደረጉ።

።።።።።።።

1.5.2. እያንዳንዱ ምክር ቤት፣ የየግሉን የስብሰባ ደንብ የማውጣት፣ ስነ ስረአት የሌላቸውን አባሎች የመቅጣትና በ3/4ኛ ድምፅ፣ አንድን አባል የማባራር መብት አለው።

።።።።።።።

ይህ ዓረፍተ ነግር፣ የሚፈልገውን ሕግ ማውጣት የምክር ቤቱ መብት እንደሆነ ያረጋግጣል። በተወካዮች ምክር ቤት የክርክር የግዜ ገደብ ስላለ፣ ሥራ ለማጉዋተት የሚደረግ ርዥም ንግግር አይፈቀድም። የሕግ መወሰኛው ምክር ቤት ግን፣ ረዣዥም ንግግሮችን የሚጋብዝ ደንብ አለው። የተወካይች ምክር ቤት በታሪኩ፣ ሶስቴ ብቻ ነው አባሎችን ያባረረው። አንድን የምክር ቤት አባል ለማባረር፣ ድምፅ መስጠት ብቻ እንጂ ለፍርድ መቅረብ አያስፈልግም።

።።።።።።።

Page �11

1.5.3. እያንዳንዱ ምክር ቤት፣ የየግሉን የቃለ ጉባኤ ማስታወሻ ይይዛል። አልፎ አልፎም፣ ምስጢር ያዘለ ከመሰለው ክፍል በስተቀር፣ ሌላውን በፅሁፍ ያወጣል። በማንኛውም ጥያቄ፣ የአዎንታና የአይታ ድምፆችም፣ በ1/5ኛ ተሳታፊ አባሎች ፍላጎት፣ በማስታወሻ መፅሔቱ ውስጥ ይመዘገባል።

።።።።።።።

በዚህ ሐረግ ምክንያት፣ የ"ምክር ቤት መዝገብ" የተባለ (ሁሉንም ድምፅና ውሳኔዎችን ያጠቃለለ) ፅሁፍ መታተም ጀመረ። ከፍተኛው ፍርድ ቤትም፣ የምክር ቤቱ መዝገብ መቶ በመቶ ትክክል ባይሆንም፣ የወጣውን ሕግ አያቃውሰውም ብሏል። የምክር ቤቱም የምስጢራዊ ስብስብ መብት፣ በዚሁ ሐርግ ስር ተካቷል። በቀደምቱ የአገሪቱ ዘመን፣ የምክር ቤቱ ስብስብ ለሕዝብ ዝግ ገበር። ወደ በሁዋላ ግን ክፍት ሆኑ። እስከ 1928 ዓ.ም. ድረስ፣ የሕግ መወሰኛው ምክር ቤት አስተዳደራዊ ስብስቦች፣ ለጋዜጥኞች ዝግ ነበሩ። ከዛ በሁዋላ ግን ክፍት ሆኗል። ከ1929 ዓ.ም. ወዲህ፣ የሕግ መወሰኛው ምክር ቤት 54 ሚስጥራዊ ስብስቦችን አድርግአል።

።።።።።።።።

1.5.4. በምክር ቤቱ የሥራ ዘመን ግዜ፣ ማንኛውም አካል ያለ ሌላኛው አካል ስምምነት፣ ከሶስት ቀን በላይ ከሥራ መበተን አይችልም። ሁለቱም አካላት ወደሌሉበት ሌላ የስብሰባ ስፍራም መዛወርም አይችልም።

።።።።።።።

ይህ ሀረግ ሕገ መንግሥቱ ውስጥ የተደረገው፣ ሁለቱ ምክር ቤቶች ሥራቸውን በትብብር እንዲያከናውኑ ለማረጋገጥ ነው።

Page �12

።።።።።።።

ክፍል 6

1.6.1. የምክር ቤቱ አባላት፣ በሕግ የተደነገገ ለሥራቸው የሚሆን ካሳ፣ ከአሜሪካ የገንዘብ ሚኒስቴር ይከፈላቸዋል። ከአገር መክዳት ከባድ ወንጀልና ሰላምን የሚያስተጏጉል ነገር ካለፈፀሙ በስተቀር፣ ለተመረጡበት ሥራ በተሰየሙበት ወቅት ወይም ወደ ሥራቸው ሲሄዱም ሆነ ሲመለሱ፣ ከመታሰር ነፃ ይሆናሉ። በሥራቸው ላይ ለሚያደርጉት ንግግረም ሆነ ክርክር ሌላ ቦታ አይጠየቁበትም። የትብብሩ አንቀፅ እንደሚጠቅሰው ሳይሆን፣ ደሞዛቸው ለራሳቸው እንጂ ለክፍለ ግዛታቸው አይከፈልም። የደሞዝ ክፍያው መብት የተሰጠው፣ ለሕግ አውጭው ምክር ቤት ነው። አንዱ የሕገ መንግሥቱ ማሻሻያ አንቀፅ፣ የተወሰነው የደሞዝ ጭማሪ፣ ከሚቀጥለው የአባላት ምረጫ በፊት፣ ሥራ ላይ እንዳይውል ይደነግጋል። ይህ አንቀፅ መጀመሪያ በምክር ቤቱ በተላለፈ ጊዜ፣ ክፍለ ግዛቶቹ አላፀደቁትም ነበር። ከሁለት መቶ ዓመታት በሁዋላ፣ በ1992 ዓም ፀደቀ። ይህ ሐረግ፣ ተወካዮቹ በምክር ቤቱ ለሚናገሩት ነገር ከመጠየቅ ነፃ ያደርጋቸዋል። ከምክር ቤቱ ውጪ ግን ለሚፈፅሙት ወንጀል፣ ከመጠየቅ አያድናቸውም።

።።።።።።።

1.6.2. ማንኛውም የምክር ቤቱ አባል፣ የአሜሪካ መንግሥት መስሪያ ቤት አባል ሊሆን አይችልም። ማንኛውም የመንግሥት ሥራ ያለውም ሰው፣ በሥራ ዘመኑ የምክር ቤት አባል መሆን አይችልም።

።።።።።።።

Page �13

ይህ ሐረግ፣ ሁለት አላማ አለው። አንደኛው፣ ምክር ቤቱ አዲስ ቢሮ ከፍቶ፣ ከአባሎቹ መሀል አንዱን ቀጥሮ ማሰራት እንደማይችልና ሁለተኛ፣ የአሜሪካን መንግሥት ዴሞክራሲያዊ አስተዳደር ከሌሎች የሚለየው፣ የመንግሥቱ ሚኒስትሮች የምክር ቤቱ አባሎች አለመሆናቸው ነው።

።።።።።።።

ክፍል 7

1.7.1. ማንኛውምን ከቀረጥ የሚገኝን ገቢ የሚጨምር የሕግ ረቂቅ የሚመነጨው፣ በሕግ አውጭው የተወካዮች ምክር ቤት ነው። ነገር ግን፣ የሕግ መወሰኛው ምክር ቤት፣ እንደ ማንኛውም ማሻሻያ ሀሳብ ወይም የሕግ ረቂቅ፣ ሀሳብ ማቅረብ ወይም መስማማት ይችላል።

።።።።።።።

ይህ ሐረግ፣ የቀረጥ ሕግ አወጣጥ ስርአት፣ በሕግ አውጭው ምክር ቤት እንዲጀምር ያደርጋል። የሕገ መንግሥቱ አርቃቂ አባላት፣ የቀረጥ የሕግ ረቂቅ ማውጣት ያለባቸው፣ ለሕዝቡ ቅርበት ያላቸውና በየሁለት ዓመቱ መመረጥ ያለባቸው ተወካይ አባሎች መሆን እንዳለባቸው አጥብቀው ያምኑ ነበር። ላለፉት ብዙ ዓምታት፣ ብዙ ገንዘብ የፈጁ፣ የሕግ መወሰኛው አካል ያወጣቸውን ሕጎች የሚቃወሙ ክሶች ቀርበው ነብር። ፍርድ ቤቱም፣ ይህ ሐረግ የሚያካትተው ንፁህ የቀረጥ ሕጎችን ብቻ መሆኑን በማመን፣ ክሶቹን ተመልክቷቸዋል።

።።።።።።።

Page �14

1.7.2. ማንኛውም በሁለቱ ምክር ቤቶች የተላለፈ የሕግ ረቂቅ ሕግ ከመሆኑ በፊት፣ ለፕሬዝደንቱ መቅረብ አለበት። ከተስማማበት፣ በፊርማው ያፀድቀዋል። ካልተስማማበት ግን፣ ተቃውሞውን ዘርዝሮ ረቂቁን ላመነጨው አካል ይመልሰዋል። ይህም አካል ተቃወሞውን በመፅሄቱ መዝግቦ፣ ጉዳዩን እንደገና በመጠንጠን ይወያይበታል። ከዚህ ውይይት በሁዋላ፣ ረቂቁን በ2/3ኛ ድምፅ ካፀደቀው፣ ከነተቃውሞው ወደ ሕግ መወሰኛው ምክር ቤት ይልከዋል። ይህም ምክር ቤት፣ ጉዳዩነ ከጠነጠነ በሁዋላ፣ በ2/3ኛ ድምፅ ካፀደቀው ሕግ ይሆናል። ነገር ግን፣ ለእንደዚህ ዓይነት ጉዳዮች በሙሉ፣ የእያንዳነዱ አባል ድምፅ በአዎንታና አይታ ተወስኖና የረቂቁ ደጋፊዎችና ተቃዋሚዎች ስም ተዘርዝሮ፣ በሁለቱም ምክር ቤቶች መፅሔት ውስጥ ይመዘገባል። ፕሬዝደንቱ፣ የተላከለትን ማናቸውንም የሕግ ረቂቆች፣ በአስር ቀን (ከእሁድ በስተቀር) ግዜ ውስጥ ካልመለሰው ወይም የሕግ አውጭው ምክር ቤት ከመመለሱ በፊት ካልተበተነ በስተቀር፣ እንደፈረመበት ተቆጥሮ፣ ሕግ ሆኖ ይፀድቃል።

።።።።።።።

ይህ ሐረግ፣ ረቂቁ ሕግ እንዲሆን በፕሬዝደንቱ መፈረም እንዳለበት ያመለክታል። ፕሬዝደንቱ ከተቃወመው፣ ወደ ምክር ቤቱ ይመልሰዋል። ይህም ማለት፣ የማገጃ ድምፁን (veto) ገለፀ ማልት ነው። 2/3ኛው የሁለቱም ምክር ቤት አባሎች እንደገና ከደገፉት፣ የፕሬዝደንቱን ማገጃ ድምፅ በማገድ፣ ረቂቁን የአገሪቱ ሕግ አድርገው ያፀድቁታል። የመጨረሻው የሐረጉ ክፍል፣ "የኪስ ማገጃ ድምፅ" (pocket veto) የተሰኘውን አባባል ያመለክታል። በምክር ቤቱ የመጨረሻው የሥራ ጊዜያት፣ ሕግ ከተላለፈና ምክር ቤቱ በእረፍት ላይ ከሆነ፣ ፕሬዝደንቱ ረቂቁን ይዞ፣ ሕግ እንዳይሆን ሊያስቆመው ይችላል።

።።።።።።።

Page �15

1.7.3. የሁለቱንም ምክር ቤቶች ስምምነት የሚጠይቅ (ከመበተን ጥያቄ በስተቀር) ማንኛውም ትዕዛዝ፣ ውሳኔ ወይም ድምፅ መስጠት፣ ለአሜሪካ ፕሬዝደንት ይቀርባል። ስምምነቱም ሥራ ላይ ከመዋሉ በፊት፣ ፕሬዝደንቱ ያፀድቀዋል። ካላፀደቀው ግን፣ አንደማንኛውም የሕግ ረቂቅ መተዳደሪያ ደንብና ውሱንነት መሠረት፣ የሁለቱም ምክር ቤት አባሎች በ2/3ኛ ድምፅ እንደገና ያሳልፉታል።

።።።።።።።

ይህ ሐረግ፣ ስለ ማገጃ ድምፅ ፅንሰ ሀሳብ ተጨማሪ ፍች ሰጥቷል። ለረቂቅ ሕግ ብቻ ሳይሆን፣ ለሌሎችም የምክር ቤቱ እርምጃዎች፣ የፕሬዝደንቱን ድጋፍ አስፈላጊነት በመጥቀስ፣ ሰፋ አድርጎታል። ፕሬዝደንቱ የማገጃ ድምፁን የመስጠት እድል ካልተሰጠው በስተቀር፣ ምክር ቤቱ ምንም አይነት እርምጃ መውሰድ እንደማይችል ግልፅ ያደርጋል።

።።።።።።።

ክፍል 8

ምክር ቤቱ የሚከተሉት ስልጣኖች ይኖሩታል።

1.8.1. የግብር የግዴታ፣ የኢምፖስትና የኤክሳይዝ ቀረጥ መጣልና መሰብሰብ፤ ዕዳ የመክፈል፤ ለጋራ መከላከያና ለአሜሪካ ሕዝብ ደህንነት

Page �16

አቅርቦት ማድረግ። ሁሉም የግብር፣ የግዴታ፣ የኢምፖስትና የኤክሳይዝ ታክሶች፣ በሁሉም አሜሪካ ግዛቶች አንድ አይነት ይሆናሉ።

።።።።።።።

ይህ ሐረግ፣ ለምክር ቤቱ ቀረጥ የመሰብሰብን መብት ሰጥቶታል። በክፍለ ግዛቶቹ ድጋፍ የሚተማመነው የቀድሞው አህጉራዊ ምክር ቤት፣ ይህ መብት አልነበረው። በቀረጥ የተገኘው ገንዘብ ለምን መዋል እንዳለበት፣ እሰከ ዛሬ ድረስ የሚያከራክር ጉዳይ ሆኗል። ይህ ሐረግ፣ "ዕዳ" ፣ "የጋራ መከላከያ " እና "የሕዝብ ደህንነት" የተሰኙ ፅንሰ ሀሳቦችን ይገልፃል። የመጀመሪያዎቹ ሁለቱ ፅንሰ ሀሳቦች፣ በቀላሉ መረዳት የሚቻሉና ያተረጉዋጎም ችግር የሚያስከትሉ አይደሉም። ሶስተኛው ቃል፣ "የሕዝብ ደህንነት" ግን፣ ግልፅ ያልሆነና የመስፋፋት መልክ ያለው ይመስላል። እነዚህን ሶስት ቃላቶች፣ ትልቅ መንግሥት የሚፈልጉ ወገኖች፣ ብዙውን የመንግሥት ድርጊቶች ተገቢ ለማስመሰል ይጠቀሙባቸዋል። የትልቅ መንግሥት ነቃፊዎች ደግሞ፣ መስራቾቹ በፍፁም እደዚህ የተስፋፋ መንግሥት አልታሰባቸውም ይላሉ። የታሰበው የመንግሥት ስፋት ምን ዓይነት የመሆኑ ክርክር የተጀመረው፣ በሕዝባዊው መንግሥት ምስረታ መጀመሪያዎቹ ጊዜአት፣ በሀሚልተንና በጄፈርሰን መካከል ነበር። የከፍተኛው ፍርድ ቤት፣ አንዳንዶቹን የ"አዲሱ ውል" ሕጎች፣ በምክር ቤቱ ያልተዘረዘሩ ሚናዎች ናቸው በማለት፣ ቀደም ብሎ ውድቅ አድርጏቸው ነበር። ከዛ ግን አቋሙን በመቀየር፣ "በሕዝብ ደህንነት" አስታኮ እንደ ማህበራዊ ዋስትና አበል (social security) የመሳሰሉትን ግዳጆች አፀደቀ። የ"ሕዝብ ደህንነት" የሚለው ቃል ትርጉም፣ በአሜሪካ ፖለቲካ አከራካሪ ጉዳይ ሆኖ መቀጠሉ አይቀሬ ነው። የመጨረሻው ሐረግ ቃላት ግልፅ ናቸው። ይህም ማለት፣ ቀረጥ ሁሉ በሁሉም ግዛቶች አንድ ዓይነት ይሆናል ማለት ነው።

።።።።።።።።

Page �17

1.8.2. በአሜሪካ ስም ተያዥነት፣ ገንዘብ መበደር።

።።።።።።።

ይህ ሐረግ፣ ለምክር ቤቱ የገንዘብ መበደርን ስልጣ ይሰጠዋል።

።።።።።።።።

1.8.3. ከሌሎች የውጭ አገሮች፣ በክፍለ ግዛቶቹ መካከልና ከህንድ ብሔሮች ጋር የሚደረግን ንግድ መቆጣጠር።

።።።።።።።

ይህ ሐረግ፣ የ"ንግድ ሐርግ" በመባል በሰፊው ይታወቃል። ለፌዴራሉ መንግሥት፣ ንግድን የመቆጣጠር ስልጣን ይሰጠዋል። በዚህም ምክንያት፣ የፌዴራል መንግሥቱ፣ ሰፋ ባሉ የንግድ ጉዳዮች ላይ ሕጎች እንዲያወጣ አስችሎታል። ከግዜ በሁዋላ፣ "ንግድ" የሚለው ቃል፣ መንግሥት ንግድ-ነክ ለሆኑ ጉዳዮችም ሕግ ለማውጣት የሚያስችለው ሐርግ ተብሎ ተተርጉሟል።

።።።።።።።

1.8.4. በአሜሪካ በሙሉ፣ እኩል የሆነ የዜግነት ማግኛ ደንቦችንና የንግድ ክስረት ሕጎችን ማውጣት።

።።።።።።።

Page �18

ይህ ሐረግ፣ ምክር ቤቱ ፍራንክ እንዲያወጣ፣ የገንዘብን ዋጋ እንዲተምንና አገራዊ ደረጃ ያለው የእቃዎች መመዘኛ ስርአት እንዲያወጣ ስልጣን ይሰጠዋል። አንዳንዱ ስልጣን፣ ለምሳሌ የውጭ አገር ገንዘብን ዋጋ ማውጣት አይነቱ፣ በአሁኑ ግዜ በአሜሪካ ተቀባይነት የለውም። አንዳንዶች፣ ሕገ መንግሥቱ "የፍራንክ ገንዘብ" ስለሚል፣ የወረቀት ገንዘብ ሕጋዊ መገበያያ ሆኖ መታየት የለበትም ብለው ይከራከራሉ። ከፍተኛው ፍርድ ቤት ግን ተቃራኒውን አፅድቆታል።

።።።።።።።

1.8.5. መሀለቅ ለማተም፣ ዋጋውንና ከውጭ ገንዘብ ጋር ተነፃፃሪነቱን መቆጣጠርና ደረጃውን የጠበቀ የክብደትንና የልክታን ዘርፍ መወሰን።

።።።።።።።

ይህ ሐረግ፣ መሀልቅ መስራት፣ የገንዘብን ዋጋ መተመንና ብሔራዊ የሆነ የሚዛን መለኪያ ደንቦችን የማውጣት ስልጣን ለምክርቤቱ ይሰጣል። አንዳንዶቹ ስልጣኖች፣ ለምሳሌ የውጭ አገር መሀለቆችን ዋጋ መተመን አይነቶቹ፣ በአሁኑ ግዜ በአሜሪካ ተቀባይነት የላቸውም። ሕገ መንግሥቱ "የመሀለቅ ገንዘብ" ስለሚል፣ አንዳንዶች የወረቀት ገንዘብ ሕጋዊ መገበያያ ገንዘብ መሆን የለበትም ብለው ይከራከራሉ። ከፍተኛው ፍርድ ቤት ግን በተቃራኒው ወስኗል።

።።።።።።

1.8.6. የአሜሪካንን ገንዘብ ወይም ጊዜአዊ መሀለቅን አስመስሎ የሰራን ሰው የመቅጣት ስርአት ማውጣት።

Page �19

።።።።።።።

ይህ ሐረግ የተፃፈው፣ የሀሰት ገንዘብ የሚያትምን ሰው የመቅጫ ስርአት ለመመስረት ነው።

።።።።።።።

1.8.7. የፓስታ ቤትና የፖስታ መንገዶችን መስራት።

።።።።።።።

ይህ ሐርግ፣ ፖስታ ማመላለስ የፌዴራሉ መንግሥት ሀላፊነት መሆኑን በግልፅ ያስቀምጣል። ተከታዩ ቃል "የፖስታ መንገዶች" ግን አከራካሪ ሆኗል። በዚህ ሐረግ መሰረት፣ መንገዶች የሚሰሩት ለፖስታ ማመላለሻ ብቻ ነው ወይስ የአጠቃላይ መጏጏዣ መሻሻሎችን፣ የቦይ መጏጏዣን ጨምሮ፣ ሁሉንም የሚያካትት ይሆናል?። ለብዙ ዓመታት፣ በመንግሥት የተደረጉ የአገሪቱ ታህታይ መዋቅር ወይም መሠረተ ልማት ማሻሻያ ወጭዎች፣ በዚህ ሐረግና በፌዴራል መንግሥቱ ንግድን የመቆጣጠር ስልጣን ስር ተሸፍነዋል። የውስጥ መሻሻዮችም የአገሪቱን የመከላከያ ሀይል ያጠናክሩታል ተብሎ ይታመንበታል። ይህም፣ በ1950ዎቹ ለተሰራው የውስጠ-ግዛት አውራ ጎዳና (inter-state)፣ እንደ አንድ የድጋፍ ምክንያት ሆኖ ይጠቀሳል።።።።።።።።

1.8.8. የሳይንስንና የጠቃሚ የስነ ጥበብ (arts) እድገትን ለማበረታታት፣ ለተወሰነ ግዜ ለፀሀፊዎችና ፈጣሪዎች፣ ለፅሁፎቻቸውና ግኝቶቻቸው ፍፁም መብት መስጠት።

።።።።።።።

Page �20

ይህ ሐረግ፣ ምክር ቤቱ የባለቤትነት መብትንና የፈጠራ ሥራ ባለቤትነት ማረጋገጫን እንዲፈጥር ስልጣን ሰጥቶታል። በአሁኑ ግዜ አከራካሪ የሆነው፣ "ለተወሰነ ግዜ" የሚለው ቃል ነው። በቀድሞው የሪፓብሊኩ ዘመን፣ "ለተወሰነ ግዜ" ማልት 14 ዓመት ነበር። ድርጅቶች (corporations) እንደ ሚኪ ማውስ ዓይነቱን የፈጠራ ሀብታቸውን በርዝመት ለመቆጣጠር ሲሉ፣ የባለቤትነት መብት ዘመን ከግዜ ወደ ግዜ እየተራዘመ መጥቷል። በአሁኑ ግዜ፣ የባለቤትነት ዘመን ከደራሲው የሕይወት ዕድሜ ላይ 75 ዓመት ይጨምራል።

።።።።።።።

1.8.9. ከከፍተኛው ፍርድ ቤት በታች ያሉ ልዩ ፍርድ ቤቶችን መመስረት።

።።።።።።።

ይህ ሐረግ፣ ከከፍተኛው ፍርድ ቤት በታች ያሉ ፍርድ ቤቶችን የመመስረት ስልጣን ይሰጣል። (ከከፍተኝው ፍርድ ቤት ዝቅ ያሉ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ማለት ነው።

።።።።።።።

1.8.10. በውቅያኖሶች ላይ የሚፈፀሙ ዘረፋዎችንና ወንጀሎችን፣ እንደዚሁም የአገሮችን ሕጎች የሚጥሱ ላይ፣ ድንጋጌን ማውጣትና ቅጣትን ማስተላለፍ።

።።።።።።።

Page �21

ሕገ መንግሥቱ በሚረቀቅበት ዘመን፣ በውቅያኖሶች ላይ የሚፈፀሙ ዘረፋዎችና ወንጀሎች፣ ከባድ ችግሮች ነበሩ። በ2009 ዓ.ም.፣ የአሜሪካ መንግሥት አንድን የሱማሌ ዜጋ በዚህ ወንጀል ከሶት ነበር። በ100 ዓምት ዘመን ውስጥ፣ አሜሪካ ማንንም ሰው በዚህ ዓይነት ወንጀል ስትከስ፣ ይህ የመጀመሪያ ግዜዋ ነው።

።።።።።።።

1.8.11. ጦርነትን ለማወጅ፣ የታዋቂነት ደብዳቤ ለመስጠትና ብቀላን ለመፈፀምና በመሬት ወይም በውሀ ላይ በተማረኩ ላይ ሕግጋትን ማውጥት።

።።።።።።

ጦርነትን የማወጅ ስልጣን ሲመረመር፣ ፕሬዝደንቱ ይሁን ወይም ምክር ቤቱ፣ የትኛው ስልጣን እንዳለው፣ ብዙ የሚያከራክር ጉዳይ ነበር። ይህ ሐረግ፣ ምክር ቤቱ ይህ ስልጣን እንዳለው በግልፅ ያስቀምጣል። ነገር ግን፣ ምክር ቤቱ መጨረሻ ጦርነት ያወጀው በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ግዜ ነበር። ከዛ በሁላ አሜሪካ፣ በኮርያ፣ በቪየትናም፣ በመጀመሪያው የባህር ሰላጤ (ገልፍ)፣ በአፍጋንስታንና በኢራክ ጦርነቶችን አኪያሂዳለች። ፕሬዝደንቶች የሀገሪቱ አዛዥ መሪዎች እንደምሆናቸው መጠን፣ አገሪቱን ወደ ጦርነት ማስገባት ወይም አለማስገባት መብታቸው መሆኑን ይጠቅሳሉ። ይህንን ጉዳይ ለማስተካከል፣ ከቪየትናም ጦርነት በሁዋላ (1973)፣ ምክር ቤቱ "የጦርነት ማመጅ ስልጣን" (War Powers Act)" የተሰኘ፣ የፕሬዝደንቱን ስልጣን የሚገድብ አንቀፅ አውጥቷል። በዚህም አንቀፅ መሰረት፣ ፕሬዝደንቱ የትም ቦታ ጦር ከላከ፣ በ48 ሰዓት ጊዜ ውስጥ፣ ለምክር ቤቱ ማስታወቅ አለበት። ይህንን ጦር ከ90 ቀናት በላይ እሚያቆየው ከሆነ፣ የምክር ቤቱን ስምምነት ማግኘት ይኖርበታል። "የታዋቂነት ደብዳቤ" የተባለው ደግሞ፣ ለግል ዜጎች፣ በውጭ አጥቂ

Page �22

ሀይል ወይም ግለ ሰብ ላይ፣ አፀፋ መልስ የመውሰድ ስልጣን የሚሰጥ ነው።

።።።።።።።

1.8.12. ወታደር መመልመልና ድጋፍ መስጠት። ነገር ግን፣ ለዚህ ጉዳይ የሚመደበው ገንዘብ፣ ከሁለት ዓምት ለማይበልጥ ጊዜ ብቻ መሆን አለበት።

።።።።።።

ይህ ሐረግ፣ ወታደር የመመልመልን (draft) ስልጣን፣ ለምክር ቤቱ ይሰጣል። በተጨማሪም፣ ለመከላከያ የሚውጣው ገንዘብ፣ ለሁለት ዓመት ብቻ እንዲሆን ይገድባል።

።።።።።።።

1.8.13. የባህር ሀይል ለማቆምና ለማስተዳደር።

።።።።።።ከጦር ሀይሎች መሀል፣ በሕገ መንግሥቱ ውስጥ ለብቻው የተጠቀሰው፣ የባህር ሀይል ነው።

።።።።።።

1.8.14. ለመንግሥት ሕግጋትን ማውጣትና መሬትንና የባህር ሀይልን የሚመለከት ስርአት መዘርጋት።

።።።።።።Page �23

ይህ ሐረግ፣ የወታደራዊውን የጦር ሀይል አደረጃጀት ስልጣን ለምክር ቤቱ ይሰጣል።

።።።።።።

1.8.15. የህብረቱን ሕጎች ለማስከበር፣ ብሔራዊ ጦር (ሚልሽያ) ለመጥራት፣ ሁከት ማስታገስና ወረራን ለመመከት አስፈላጊውን እርዳታ መስጠት።

።።።።።።።

ይህ ሐረግ፣ የግዛቶቹን ሁሉ ሚሊሽያ ወደ ብሔራዊ ጦር፣ አሁን "የብሔር ጠባቂ" (National Guard) ወደሚባለው፣ የመለወጡን ስልጣን ለፌዴራል መንግሥቱ ይሰጣል። እያንዳንዱ ክፍለ ግዛት የየራሱ የሆነ ብሔር ጠባቂ አለው። ነገር ግን፣ የፌዴራሉ መንግሥት እንዳስፈላጊነቱ፣ ሁሉንም በማንኛውም ግዜ መጥራት ይችላል።

።።።።።።።

1.8.16. ሚሊሻውን ለማዘጋጀት፣ ለማስታጠቅና ስነ ስርአት ለማስጠበቅ መርዳትና ለአሜሪካ በሚያገለግሉበት ግዜ፣ አስተዳደራዊ ድጋፍ በመስጠት፣ ለክፍለ ግዛቶቹ ባለስልጣን መኮንኖችን የመሾምና ምክር ቤቱ ባወጣው ስነ ስርአት መስረት፣ ሚሊሻውን የማሰልጠን ሀላፊነት ለፌዴራሉ መንግሥቱ ይሰጣል።

።።።።።።።

Page �24

በሰላም ግዜ፣ ሚሊሺያውን (ብሔር ጠባቅ) የማሰልጠኑ ሀላፊነት የክፍለ ግዛቶቹ መሆኑን፣ ሕገ መንግሥቱ በግልፅ ያስቀምጣል።

።።።።።።።

1.8.17. የአሜርካ ዋና ከተማ ለሚሆነው (ከአስር ኪሎ ማይል ካሬ (square) የማይበልጥ) ቦታ፣ ከአካባቢ ክፍለ ግዛቶች በመውሰድና የምክር ቤቱን አዎንታ በማግኘት፣ የመንግሥት መቀመጫ በማድረግና በሚመለከተው ክፍለ ግዛት ስምምነት በተገዛው ቦታ ላይ፣ ምሽግ፣ የመሳሪያ ማከማቻ፣ የመሳሪያ ፋብሪካ፣ የመርከብ ማቆሚያ ቦታዎችንና ሌሎች አስፈላጊ ህንፃዎችን፣ በማንኛውም ግዜ የመገንባት ብቸኛ የሆነ ሙሉ ስልጣን፣ ለፌዴራሉ መንግሥት ይሰጣል።

።።።።።።።

ይህ ሐረግ፣ አሁን 69 ማይል የሆነውን (በመቶ ማይል ፈንታ) የኮሎምቢያን ወረዳ (District of Columbia)፣ ለመመስረት ስልጣን ሰጥቶታል። እንደዚሁም፣ በአገሪቱ ሙሉ ላሉት የፌዴራል ህንፃዎችና ንብረቶች፣ ሀላፊነቱን ለፌዴራሉ መንግሥት ይሰጣል።

።።።።።።

1.8.18. ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትን ስልጣኖችና ሌሎች በሕገ መንግሥቱ የጠቀሱ፣ መንግሥትን ወይም የመንግሥት መስሪያ ቤቶችን የማስተዳደር ስልጣኖች በሥራ ለማዋል፣ የሚያስፈልጉትንና ተገቢ ሕግጋትን መደንገግ።

።።።።።።።

Page �25

ይህ ሐርግ፣ በሕገ መንግሥቱ "ሁሉንም አቀፍ ሐረግ" የሚባለው ነው። በዚህም ሐረግ መሰረት ምክር ቤቱ፣ ከላይ የተጠቀሱትን ስልጣናት በሥራ ለማዋልና አስፈላጊ የሆኑ ተጨማሪ ሕግጋትን ለማውጣት ይችላል። ይህንን ሐረግ ተመርኩዞ፣ ከፍተኛው ፍርድ ቤት፣ የመጀመሪያውን የአሜሪካ ባንክ ምስረታ ሕጋዊ አድርጎታል።

።።።።።።።

ክፍል 9

1.9.1. አሁን ያሉት ክፍለ ግዛቶች፣ አስፈላጊ ነው ብለው የሚያስገቡት ሰው ወይም ስደተኛ ከ1808 ዓ.ም. በፊት ከሆነ፣ ምክር ቤቱ ሊከለክላቸው አይችልም። ነገር ግን፣ በየአንዳንዱ ሰው ከአስር ብር የማይበልጥ የግዴታ አበል ወይም ታክስ መጣል ይችላሉ።

።።።።።።።

ይህ ሐረግ የሚያመለክተው፣ እስከ 1808 ዓ.ም. ድረስ ባሮችን ማስገባት መቀጠሉ፣ በሕገ መንግሥቱ ያልተከለከለ መሆኑን ነው። ከዚህ ግዜ በሁዋላ፣ ይህ ድርጊት ተከልክሏል። ይህ ሐረግ፣ ባርነትን የሚደግፉትንና የሚቃወሙትን ግዛቶች ለማስታረቅ የተደርገ የድርድር ውጤት ነበር።

።።።።።።።

1.9.2. በአመፅ ወይም በወረራ ግዜ፣ ለሕዝብ ደህንነት/ፀጥታ ሲባል ከሚደረገው በስተቀር፣ ማንኛውም ሰው ወይም ድርጅት፣ የተያዘን ሰው ለፍርድ ቤት ማስረከብ (Writ of Habeas Corpus) ይኖርበታል።

Page �26

።።።።።።። (Writ of Habeas Corpus) ይህ ቃል በቃል ሲተረጎም፣ "አካልን/ሰውነትን ማሳየት" ማለት ነው። ይህ አባባል፣ መንግሥት የያዘውን እስረኛ ለፍርድ ቤት ዳኛ በአካል ማሳየት እንዳለበት ያስገድዳል ማለት ነው። በሕገ መንግሥቱ ውስጥ፣ ለዚህ ቃል ያለ እርግጠኛ መግለጭ የለም። ነገር ግን፣ በእንግሊዝ ሕግ ውስጥ አይነተኛ ቦታ ያለው ስለነበር፣ በአሜሪካ ሕግም ተገቢ ቦታውን የያዘ ሀሳብ ነው ተብሎ ይታመናል። ይህ ሐረግ እንደሚጠቅሰው፣ በአመፅ (ለምሳሌ የርስ በርስ ጦርነት) ወይም አሜሪካ ስትወረር (ለምሳሌ የ1812 ዓ.ም. ጦርነት፣ ሁለተኛው የአሜሪካ ጦርነት የሚባለው፣ ከ1812 እስከ 1815 ከእንግሊዝ ጋር የተደረገው ጦርነት) በስተቀር ይፀናል። የሽብር ጦርንት በሚካሄዱበት ባለፉት ዓመታት፣ ይህ ሐረግ ብዙ ጥያቄ ውስጥ ገብቷል። ይህም፣ ሕጉ አሜሪካዊ ዜጋ ያልሆኑን ሰዎች ወይም አሜሪካ ግዛት ውስጥ የሌሉ ቦታዎችን (ለምሳሌ የጉዋንታናሞ ሰፈር እስር ቤት ዓይነትን) ይመለከታል ወይ የሚለውን ጥያቄ አስነስቷል።

።።።።።።።

1.9.3. ለከባድ ወንጀልና ክህደት መቅጫ የሚወጣ የሕግ ረቂቅ (bill of attainder) ወይም ላለፈ ጥፋት ቅጣት የሚያስከትል ሕግ (ex-post- facto law) አይተላለፍም።

።።።።።።።

"Bill of attainder" የሚባለው፣ በተወሰነ ሰው ወይም ሰዎች ላይ ያተኮረ ሕግ ነው። "Ex-post-facto" የሚባለው ሕግ ደግሞ፣ አንድ ድርጊት ካለፈ በሁዋላ ሕግ አውጥቶ፣ ድርጊቱን ሕገ ወጥ ማድረግ ማለት ነው።

Page �27

።።።።።።።

1.9.4. ከሕዝብ ቁጥር ጋር ተመጣጣኝ ያልሆነ፣ አንድ ወጥ ወይም ሌላ ቀጥተኛ ቀረጥ/ግብር ማስተላለፍ አይቻልም።

።።።።።።።

ይህ ሐረግ የተፃፈው፣ የአንድ ክፍለ ግዛት ነዋሪ የሚጣልበት ቀረጥ፣ ከማንኛውም ክፍለ ግዛት ነዋሪ ጋር ተመጣጣኝ እንዲሆን ለማድረግ ነው። ይህም ሐረግ፣ በሕዝቦች ላይ ለሚጣል ቀጥተኛ ቀረጥ እንጂ፣ በሸቀጣ ሸቀጥ ላይ የሚጣል ቀረጥን አይመለከትም። ሆኖም ይህ ሐረግ፣ የገቢን ልዩነት እሳቤ ውስጥ አላስገባም። በዚህም ምክንያት፣ ገቢ ላይ የተመሰረተ ቀረጥ መጣል አይቻልም። ስለዚህ፣ የሮድ አይላንድ ነዋሪዎች ከከኔቲከት የበለጠ ሀብት ቢኖራቸውና የበለጠ ቀረጥ እንዲከፍሉ ቢደረግ፣ ሕገ መንግስቱን የሚፃረር ድርጊት ይሆናል። ይህ ችግር፣ በአስራ ስድስተኛው የሕገ መንግሥቱ ማሻሻያ ሀሳብ (amendment)፣ የገቢ ቀረጥ ከሕዝብ ቁጥር ጋር ተመጣጣኝ መሆን እንዳይኖርበት በማድረግ ተፈቷል።።።።።።።።

1.9.5. ከማንኛውም ክፍለ ግዛት ወደ ውጭ የሚላክ ሸቀጥ ላይ ቀረጥ አይጣልም።

።።።።።።።

ይህ ሐረግ የተጨመረው፣ ሕገ መንግሥቱ ውስጥ የተቀመጠው፣ የደቡቡ ክፍለ ግዛቶች ወደ ውጭ የሚልኩት ሸቀጥ ላይ፣ የሰሜኑ ክፍለ ግዛቶች በወደባቸው በኩል ለሚያልፍ ሸቀጥ፣ ቀረጥ እንዲጣልበት ያደርጋሉ ብለው ሰለሰጉ ነው።

Page �28

።።።።።።።

1.9.6. ከአንዱ ክፍለ ግዛት ወደብ ለሌላው ክፍለ ግዛት ወደብ ምርጫ የሚሰጥ የንግድ መተዳደሪያ ደንብ ወይም የወደብ ገቢ አይደረግም። በተጨማሪም፣ ከአንድ ክፍለ ግዛት ወደ ሌላው የሚንቀሳቀሱ መርከቦች፣ ገብተው እንዲቆሙ፣ የማጣሪያ ሥራ እንዲካሄድባቸው ወይም አበል እንዲከፍሉ አይደረጉም።

።።።።።።።

ይህ ሐረግ፣ በጊዜው ከኖርፈክ የሚነሱ መርከቦች በቦስተን በኩል እንዲያልፉ የማይገደዱ መሆናቸውን አረጋገጠ።

።።።።።።።

1.9.7. በሕግ ካልተደነገገ ክፍፍል በስተቀር፣ ከግምጃ ቤቱ ገንዘብ ማውጣት አይቻልም። ከግዜ ወደ ግዜም፣ የሁሉም የገቢና ወጪ ደረስኝ መግለጫ ታትሞ ይወጣል።

።።።።።።።

ይህ ሐረግ፣ ፕሬዝደብቱ፣ ምክር ቤቱ ከመደበው ገንዘብ ውጭ ማውጣት እንደማይችል ይደነግጋል።

።።።።።።።

1.9.8. ምንም አይነት የባላባትነት ማዕረግ በአሜሪካ አይሰጥም። ማንኛውም በተከፋይነት ወይም በእምነት ሥራ ላይ ያለ ሰው፣ ያለ ምክር

Page �29

ቤቱ ፍቃድ፣ ከማንም ንጉሥ፣ ልዑል ወይም የውጭ አገር መንግሥት፣ ምንም ዓይነት ስጦታ፣ ደሞዝ፣ ሥራ ወይም ማዕረግ መቀበል አይችልም።

።።።።።።።

ይህ ሐረግ፣ በአሜሪካ ንጉሥ ወይም ልዑል እንዳይንኖር ይደነግጋል። በተጨማሪም፣ የመንግሥት ሥራ የያዘ ማንም ሰው፣ ልዩ ማዕረግ መቀበል እንደማይችል ይጠቅሳል። ብዙ አሜሪካኖች፣ "የክብር የጥንት ጀብደኛ ማዕረግ (honorary knight)" ተሰጥቷቸዋል። ይህ ግን፣ በመንግሥት ሥራቸው ላይ እያሉ አይደለም። የአሜሪካ ሕግ፣ በተለይ የወታደራዊዉ ክፍል አባሎች፣ የክብር ጌጦችን መቀበል እንዲችሉ በማሰብ፣ ከዚህ ሐረግ ነፃ ያደርጋቸዋል።

።።።።።።።

ክፍል 10

1.10.1. ማንም ክፍለ ግዛት፣ ምንም ዓይነት ውል፣ ኅብረተ ስምምነት ወይም ተባባሪነት ውስጥ መግባት፣ መርከብን ማስታጠቅና ብቀላን መፈፀም፣ ፍራንክ ማተም፣ የብድር ሂሳብ ማሰራጨት፣ ከወርቅና ነሀስ በስተቀር ሌላ ነገር ለእዳ መክፈያ መጠቀም፣ ያለፍርድ ሰውን የሚወነጅል ረቂቅ (bill of attainder) ማስተላለፍ፣ በተደረገ ጊዜ ሕጋዊ የሆነን ድርጊት በአዲስ ሕግ መወንጀል (ex post facto law) ወይም የውልን ግዴታ የሚያጏድል ሕግና የባላባትነት ማዕረግ መስጠት አይቻልም።

።።።።።።።

Page �30

ይህ ሐረግ፣ ማንኛውም ክፍለ ግዛት፣ የብሔራዊዉን መንግሥት ሥራ መውሰድ እንደሌለበት፣ በማያጠራጥር መንገድ ያስቀምጣል። በተጨማሪም፣ የጠቅላይ ግዛቶቹ አስተዳደር፣ በተደረገ ጊዜ ሕጋዊ የሆነን ድርጊት (ex post facto law)፣ በአዲስ ሕግ መወንጀል ወይም የውልን ግዴታ የሚያጏድል ወይም የሚያዳክም ሕግጋትን ማውጣት እንደማይችል ይገልፃል።

።።።።።።።

1.10.2. ማንኛውም ክፍለ ግዛት፣ የፍተሻ ሕጉን በሥራ ላይ ለማዋል የግድ አስፈላጊ ካልሆነ በስተቀር፣ ያለ ምክር ቤቱ መስማማት፣ የሚገቡና የሚወጡ ሸቀጣ ሸቀጦች ላይ ግብር ወይም አበል መጣል አይችልም። በዚህ መንገድ የተገኘውም የተጣራ ሰብል፣ ለአሜሪካ መንግሥት ግምጃ ቤት ጥቅም ገቢ ይደረጋል። ይህንን ነክ የሆኑ ሕግጋት በሙሉ፣ በምክር ቤቱ ምርምርና ቁጥጥር ስር ይሆናሉ።

።።።።።።።

ይህ ሐረግ በመሰረቱ የተፃፈው፣ በኮንፌዴሬሽኑ አንቀፅ መሰረት የተፈቀደውን፣ በግዛቶች መካከል ለሚደረግ ንግድ ቀረጥ መቀበል ያመጣውን ዋና ጉድለት ለመሸፈን ነው።

።።።።።።።

1.10.3. ማንኛውም ክፍለ ግዛት፣ ያለ ምክር ቤቱ ስምምነት፣ በመርከብ ላይ ቀረጥ መጣል፣ በሰላም ግዜ ወታደሮችን ወይም የጦር መርከቦችን ማስቀመጥ፣ ከክፍለ ግዛቶች ወይም የውጭ ሀይል ጋር ስምምነት ወይም ውል ውስጥ መግባት፣ ካልተወረሩ ወይም መወረራቸው የማይቀር መሆኑ ግልጽ ካልሆነ በስተቀር፣ ጦርነት ውስጥ መግባት እይችሉም።

Page �31

።።።።።።።

ይህ ሐረግ፣ ካለ ምክር ቤቱ ስምምነት፣ ማንኛውም ክፍለ ግዛት ከሌላው ጋር ምንም ዓይነት ስምምነት ውስጥ መግባት እንደማይችል ይጠቅሳል። ለምሳሌ ያክል፣ በኒው ዮርክ፣ኒው ጀርሲና ከኔቲከት መካከል የተፈጠረው የጋራ የትራንስፖርት ተቋም (Metropolitan Transport Authority)፣ ብሔራዊ ጠባቂ (National Guard) እንጂ በሰላም ግዜ ቋሚ ወታደር ሊኖረው ወይም የራሱን ጦርነት ሊያኪያሂድ (ለምሳሌ ካናዳን መውረር) እንደማይችል ይደነግጋል።

።።።።።።።

አንቀፅ ፪

ክፍል 1

2.1.1 የአስተዳደሩ ስልጣን፣ በተባበሩት አሜሪካ ፕሬዝደንት ስር ይሆናል። ስልጣኑን ከምክትል ፕሬዝደንቱ ጋር በመሆን፣ ለአራት ዓመት ይይዛል። የአመራረጡም ስርአት እንደሚከተለው ይሆናል።

።።።።።።።

Page �32

"የእስተዳደር ስልጣን" የሚለው ቃል፣ ሰፋ ያለ ፍች የያዘ፣ የፕሬዝደንቱን ስልጣን የሚገልፅ ቃል ነው። "የአስተዳደር ስልጣን" የሚያመለከተው፣ ፕሬዝደንቱ የተሰጠውን የቀን ተቀን መንግሥትን የማስተዳደር ስልጣን ነው። ሕገ መንግሥቱ፣ የፕሬዝደንቱን ስልጣን "በሰፊው" እንጂ በአሀዝ በተዘረዘሩ ጉዳዮች ብቻ አይገድበውም። በተጨማሪም ሕገ መንግሥቱ፣ ይህ ስልጣን፣ ከምክትል ፕሬዝደንቱ ጋር እንኳን ቢሆን መካፈል እንዳለበት አይጠቅስም። ሕገ መንግሥቱ ሙሉ ያስተዳደር ስልጣን የሚሰጠው፣ ለፕሬዝደንቱ ብቻ ነው። መስራቾቹ በአሜሪካ ንጉሥ እንዲኖር ባይፈልጉም፣ የፕሬዝደንቱ ጽህፈት ቤት፣ ሀያል ተቋም እንዲሆን ማረጋገጥ ፈልገው ነበር። ይህ ሐረግ፣ የፕሬዝደንቱ የአገልግሎት ዘመን አራት ዓመት እንዲሆን ይወስናል።

።።።።።።።

2.1.2. እያንዳንዱ ክፍለ ግዛት፣ ባስተዳደሩ መመሪያ መስረት፣ ለምክር ቤቱ በሚልካቸው የሕግ አስፈፃሚውና የተወካዮች ምክር ቤት አባሎች ቁጥር ልክ፣ መራጮች ይመርጣል። ነገር ግን፣ ማንም የምክር ቤት አባል ወይም በመንግሥት ሥራ የተቀጠረ ሰው፣ ለመራጭነት አይመረጥም።

ተመራጮቹ በየክፍለ ግዛታቸው በመሰብሰብ፣ በምርጫ ወረቀት ሁለት ሰው ይመርጣሉ። ከነዚህ ቢያንስ አንዱ፣ ከነሱ ክፍለ ግዛት ውጭ የሚኖር ሰው መሆን አለበት። የተመራጮቹን ስም ዝርዝርና ያገኙትን ድምፅ ቁጥር በመመዝገብና ሰነዱን በመፈረም፣ አሽገው ለአሜሪካ መንግሥት የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ፕሬዝደንት ይልኩታል። የምክር ቤቱ ፕሬዝደንት፣ የታሸገውን ሰነድ በሁለቱም ምክር ቤት አባሎች ፊት በመክፈት፣ የተሰጠውን ድምፅ ይቆጥራል። አብላጫ ድምፅ ያገኘው ሰው፣ ፕሬዝደንት ይሆናል። ሌላ ተመራጭ ተመሳሳይ የድምፅ ቁጥር ካለው፣ ያኔውኑ የተወካዮች ምክር ቤት አባሎች፣ በምርጫ ወረቀት፣ አንዱን ለፕሬዝደንትነት ይመርጡታል። ማንም አብላጫ ድምፅ ካላገኝ፣ አምስት

Page �33

አብላጫ ድምፅ ካገኙት መሀል፣ አንዱን በተመሳሳይ ድምፅ አሰጣጥ ለፕሬዝደንትነት ይመርጡታል። ነገር ግን፣ በዚህ መንገድ ፕሬዝደንቱን ለመምረጥ፣ የያንዳንዱ ክፍለ ግዛት አንድ አባል ተወክሎ፣ ለምልአተ ጉባኤው ደግሞ 3/4ኛው የክፍለ ግዛቶቹ ተወካዮችና የክፍለ ግዛቶቹ አብዛኛዎቹ ተወካዮች መኖር ይኖርባቸዋል። ፕሬዝደንቱ በዚህ መንገድ ከተመረጠ በሁዋላ፣ ምክትል ፕሬዝደንት የሚሆነው፣ ከክፍል ግዛት መራጮች የአብዛኛውን ድምፅ ያገኘው ነው። ግን፣ ከአንድ በላይ እኩል ድምፅ ያገኙ ካሉ፣ የሕግ መወሰኛው ምክር ቤት በምርጫ ወረቀት፣ ምክትል ፕሬዝደንቱን ይመርጣል።

።።።።።።።

ይህ ሐረግ (የሕገ መንግሥቱ ረጅም ሐረግ)፣ የአሜሪካንን ድንቅ የምርጫ ስርአት ያስቀምጣል። ይኸውም፣ "የምርጫ ኮሌጅ" የተሰኘው ነው። ለሀሚልተንና ለሌሎቹ መስራቾች፣ መራጮቹ ብርቅዬ የሆነ ሰው ብቻ ለፕሬዝደንትነት እንዲበቃ፣ ማረጋገጫ መንገዳቸው ነበር። የምርጫ ኮሌጁ መኖር፣ ማንም ሰው ዜጋውን እንዳያወናብድ ያደርጋል ብለው ያምኑ ነበር። የምርጫ ኮሌጁ፣ መራጮች በቀላሉ እንዳይታለሉ ማገጃም ነበር። ሀሚልተንና ሌሎቹ መስራቾች፣ በግዜው ያለው ሕዝብ እውቀት ያለው ትክክለኛ ምርጫ ያደርጋል ብለው አያምኑም ነበር። የምርጫ ኮሌጁ በዓመት አንዴ ብቻ ስለሚሰበሰብ፣ በሌላ ሰው ወይም የውጭ መንግሥት የመደለል እድል አይኖረውም ብለው ያምኑ ነበር። በተጨማሪም የምርጫ ኮሌጁ የተመሰረተው፣ በሕገ መንግሥቱ ምስረታ ስብሰባ ግዜ የተነሳውን፣ የትናንሽ ክፍለ ግዛቶች ቅሬታ ለማስታረቅ ነበር። በምርጫ ኮሌጁ ስርአት መሰረት፣ እያንዳንዱ ክፍለ ግዛት፣ ለምክር ቤቱ በሚልከው ተወካይ ቁጥር ልክ መራጭ ይኖረዋል። ማንም ክፍለ ግዛት ከሶስት ያላነሰ ተወካይ ይኖርዋል። በቅርብ ግዜ በተደረገ ምርጫ፣ የዋዮሚንግ ሕዝብ 210,000 ድምፅ ሰጥቶ ነበር። ለሶስት መራጮች 70,000 ድምፅ አለው ማለት ነው። በዚሁ ምርጫ፣ ካሊፎርኒያ 9,700,000 ድምፅ ሰጭዎች ነበራት።

Page �34

ለ54 መራጮች፣ በተመራጭ 179,000 ድምፅ ሰጪ ነበር ማልት ነው። ይህም ለትንሽ ክፍለ ግዛት ድምፅ ሰጭዎች፣ በቁጥራቸው መሰረት ብዙ ተመራጭ ስለሚሰጣቸው፣ በርግጥም ሚዛናዊ ያልሆነ ጥቅም ይሰጣቸዋል።

ይህ የመጀመሪያው ሐረግ፣ የ12ኛው ማሻሻያ ሀሳብ ተጨምሮበት ተስተካክሏል። በመጀመሪያው ድንጋጌ መሰረት፣ ፕሬዝደንቱን ወይም ምክትሉን ለመምረጥ፣ መራጮቹ የሚገቡት ቃል ኪዳን አልነበረም። በዚህ ምክንያት፣ ጆን አዳምስ ፕሬዝደንት ሲሆን፣ የሚቅጥለውን የድምፅ ብልጫ ያጎኘው ተቃዋሚው ቶማስ ጄፈርሰን፣ ምክትል ፕሬዝደንት ሆነ። ይህ አንቀፅ ባይሻሻል ኖሮ፣ የምክር ቤት አባሉ ማኬይን የፕሬዝደንት ኦባማ ምክትል ይሆን ነበር።።።።።።።።

2.1.3. ምክር ቤቱ፣ በክፍለ ግዛቶች በሙሉ፣ በአንድ ቀን የሚደረገውን የመራጮች ምርጫ ግዜና ድምፅ የሚሰጡበትን ቀን ይወስናል።

።።።።።።።

ይህ ሐረግ፣ ምክር ቤቱ፣ በሁሉም ክፍለ ግዛቶች አንድ ዓይነት የምርጭ ቀን እንዲመደብ ይፈቅዳል።

።።።።።።።

2.1.4. በትውልድ አሚሪካዊ ወይም ይህ ሕገ መንግሥት ሲፀድቅ የአሜሪካ ዜጋ ያልሆነ፣ የ35 ዓመት እድሜ ያልሞላውና ለ14 ዓመት የአሜሪካ ነዋሪ ያልሆነ ሰው፣ ለፕሬዝደንትነት ብቁ አይሆንም።

።።።።።።።

Page �35

"በትውልድ" የሚለው ቃል፣ በፖናማ ካናል ክልል የተወለደው ሴናተር ማኬይን ለውድድር በቀረበበት በ2008 ዓ.ም፣ ክርክር አስነስቶ ነበር። "በትውልድ" የሚለው ቃል ለብዙ ግዜ፣ በአሜሪካን ክልል ውስጥ መመለድን እንደሚያመለክት ነበር የሚታመንበት። ማኬይን በተወለደበት ግዜ፣ አባቱ የባህር ሀይል መኮንን ሆኖ፣ በካናሉ ክልል ያገለግል ነበር። ክልሉም በአሜሪካ ግዛት ስር ስለነበር፣ ጆን ማኬይን በትውልድ አሜሪካዊ ዜጋ መሆኑ ሰፊ ተቀባይነት ነበረው። ማንኛውም ውጭ የተወለደ የአሜሪካዊ ልጅ፣ ትውልደ-አሜሪካዊ የመሆን መብት ስላለው፣ በውጭ አገር ጉዞ ወይም ውጭ አገር በመኖር ግዜ የሚወለደው ህፃን ዜጋነት ጉዳይ፣ እስካሁን መልስ አላገኘም።

።።።።።።።

2.1.5. ፕሬዝደንቱ ከሥራው ከታገደ፣ ከሞተ፣ በፈቃዱ ስልጣኑን ከለቀቀ ወይንም ሥራውን በትክክል ለማከናወን ካልቻለ፣ ምክትል ፕሬዝደንቱ ሀላፊነቱን ይረከባል። ፕሬዝደንቱ ወይም ምክትሉ፣ ከሥራ በመወገድ፣ በሞት፣ በፈቃድ ስልጣንን በመልቀቅ ወይም ሥራን በትክክል ባለማከናወን መወገድ የተነሳ ለሚፈጠረው ክፍት ቦታ፣ ምክር ቤቱ በሕጋዊ መንገድ፣ ያለው ፕሬዝደንት እክል እስኪስተካከል ወይም ሌላ ፕሬዝደንት እስኪመረጥ ድረስ፣ በቦታው ሌላ ሀላፊ ማስቀመጥ ይችላል።

።።።።።።።

ይህ ሐረግ፣ ፕሬዝደንቱ ከሞተ፣ ሥራውን ከለቀቀ ወይም ሥራውን በትክክል መስራት ካልቻለ፣ ምክትል ፕሬዝደንቱ ስልጣኑን እንደሚረከብ ይገልፃል። ሁለት ማሻሻያ ሀሳቦች፣ ይህ ሐረግ ያስከተለውን አሻሚ ትርጉም ለማብራራት ሞክረዋል። "ፕሬዝደንቱ ሥራውን በትክክል ለማከናወን ካልቻለ" የሚለው አረፍተ ነገር ትርጉም፣ ብዙ ጥያቄ አስነስቶ ነበር። በዚህ

Page �36

ወቅት፣ ምክትል ፕሬዝደንቱ ስልጣኑን ይረከባል ወይስ ፕሬዝደንት ይሆናል? ይህንን ተመልክቶ የተጻፉት የማሻሻያ ሀሳቦች፣ ያፈፃፀሙን ቅደም ተከተል በትክክል አስቀምጠውታል። በ25ኛው የማሻሻያ ሀሳብ መሰረት፣ ፕሬዝደንቱ ስራውን በትክክል ማከናወን ካልቻለ፣ ምክትል ፕሬዝደንቱ ፕሬዝደንት ይሆናል።

።።።።።።።

2.1.6. ፕሬዝደንቱ፣ በተወሰኑ ግዜአት፣ በስልጣኑ ዘመን የሚከፈለው፣ የማይጨመር ወይም የማይቀነስ አበል ይኖረዋል። በዚህም ዘመን፣ ከአሜሪካ መንግሥት ወይም ክፍለ ግዛቶች፣ ሌላ ደሞዝ መቀበል አይችልም።

።።።።።።።

በዚህ ሐረግ መሰረት፣ ምክር ቤቱ፣ የፕሬዝደንቱን ደሞዝ መጨመር ወይም መቀነስ፣ በዚህም ድርጊት፣ የፕሬዝደንቱን ሥራ ማወክ አይችልም።

።።።።።።።

2.1.7. ፕሬዝደንቱ፣ ሥራ መደቡ ላይ ከመሰማራቱ በፊት፣ የሚከተለውን መሀላ ይፈፅማል። "የአሜሪካ ፕሬዝደንትነትን ስራ ለመፈፀም፣ በሙሉ ችሎታዬ፣ የአሜሪካን ሕገ መንግሥት ለማስከበር፣ ለመጠበቅና ለመከላከል፣ በሙሉ ልቤ ይህንን የቃል ኪዳን መሀላ እፈፅማለሁ።"

።።።።።።።

Page �37

በፕሬዝደንት ኦባማ የቃል ኪዳን መሀላ ስነስርአት ግዜ፣ የከፍተኛው ምክር ቤት ሹም ሮበርትስ፣ እነዚህን ቃላቶች አሳስቶ ተናግሮ ነበር። የፕሬዝደንትነቱን ሕጋዊነት ለማረጋገጥ ግን፣ ፕሬዝደንት ኦባማ በማግስቱ ሌላ መሀላ መፈፀም ነበረበት።

።።።።።።።

ክፍል 2

2.2.1.የአሜሪካ መንግሥት የጦር ሰራዊትና ባሕር ሀይል፣ ለመንግሥት ስራ በታዘዘ ግዜ፣ ፕሬዝደንቱ፣ የክፍለ ግዛቶቹ ሁሉ ብሔራዊ ጦር ወይም ሚሊሺያ፣ የበላይ መሪ ይሆናል። የየቢሯቸውን የስራ መስክ በሚመለከት፣ የአስተዳደሩን ዋና ዋና ሀላፊዎች ግላዊ አስተያየት በጽሁፍ የመቀበልና ከሕጋዊ ክስ (impeachment) ውጭ፣ አገሪቱ ላይ ለሚደረግ ሕግ የመጣስ ወንጀል፣ ቅጣትን የማስቀረት ወይም ምህረትን የመስጠት ስልጣን ይኖረዋል።

።።።።።።።

የዚህ ሐረግ የመጀመሪያው ክፍል፣ ከሕገ መንግሥቱ ሁሉ ብዙ ያከራከረ ሐረግ ነበር። ፕሬዝደንቱ "የጦር ሰራዊቱ የበላይ መሪ" የመሆኑ ስልጣን፣ ጦርነት ሳይታወጅ የሚደረገውን ጦር የማሰማራት እርምጃ አግባባዊነት ለመደገፍ መጠቀሚያ ተደርጏል። ምክር ቤቱ ለመጨረሻ ግዜ ጦርነት ካወጀበት ከሁለተኛው ዓለም ጦርነት ወዲህ፣ አሜሪካ በስድስት ዋና ዋና

Page �38

ጦርነቶችና ቁጥረ ብዙ አነስተኛ ውጊያዎች ተሳትፋለች። ፕሬዝደንቶች ድርጊታቸውን፣ "የበላይ መሪ" በሚለው ሐረግ መሰረት፣ ተገቢ አድርገው ያቀርቡታል። በሶቪየት ህብረትና በአሜሪካ መካከል በነበረው ቀዝቃዛው ጦርነት ዘመን ሰላምን ለማስጠበቅ፣ እርስ በርስ የመተላለቅ የጋራ ስምምነት (policy of mutual assured destruction) ስለነበር፣ ከሶቪየት ሕብረት ጋር ጦርነት የመጀመሩ ወሳኝ እርምጃ (ተወንጫፊ የጦር መሳሪያ ወደ አሜሪካ ካመራ) መወሰድ የነበረበት፣ በጦር ሀይሉ መሪ፣ በፕሬዝደንቱ ብቻ ነበር። በአሁኑ ግዜ፣ የፕሬዝደንቱ ጦር ማንሳት ስልጣን፣ በጦርነት ማንሳት ስልጣን ሕግ (War Powers Act) ስር ታስሯል። ይህ ሕግ፣ የፕሬዝደንቱን የጦር የበላይ መሪነት ስልጣንና የምክር ቤቱን ጦርነት የማወጅ ስልጣን አሻሚነት ለማስተካከል ይሞክራል። ይህ ሕግ ከተላለፈ በሁዋላ፣ ፕሬዝደንቶች ሕግጋቶቹን አንዳንዴም በመከተል፣ በጦር አዛዥነታቸውም የበላይነት በመመካት፣ ሕጉ አይመለከተኝም ባዮች ሆነዋል።

።።።።።።።

2.2.2. በሕግ መወሰኛው አካል ምክርና ስምምነት መሰረትና በ2/3ኛ የሕግ አባሎች የድጋፍ ድምፅ ብልጫ፣ ከመንግሥታት ጋር ውል መፈራረም ይችላል። በምክር ቤቱ ምክርና ስምምነት መሰረት፣ አምባሳደሮችን፣ ሌላ የመንግሥት ባልስልጣናትንና ቆንሲሎችን፣ የከፍተኛው ፍርድ ቤት ዳኞችንና ሌሎች ባዶ የመንግሥት የሹመት ቦታዎችን ለመሙላት፣ ሕጉን በተከተለ ስርአት፣ መምረጥና መሾም ይችላል። ነገር ግን፣ ምክር ቤቱ ተገቢ በመሰለው መንገድ፣ የበታች ባለስልጣናትን የመሾም ስልጣን በሕግ፣ ለፕሬዝደንቱ ብቻ፣ ለፍርድ ቤቶች ወይም ለተቋም ሹሞች ሊሰጥ ይችላል።

።።።።።።።

Page �39

ይህ ሐረግ፣ ለፕሬዝደንቱ፣ የዲፕሎማሲን ማኪያሄድና ውል የመፈራረምን ስልጣን ይሰጠዋል። ማንኛውም ውል ግን፣ በሕግ መመሰኛው አባላት 2/3ኛ ድምፅ ብልጫ መፅደቅ ይኖርበታል። በተጨማሪ፣ ፕሬዝደንቱ፣ ካቢኔውን የመሾምና አምባሳደሮችንና የከፍተኛው ፍርድ ቤት ዳኞችን የመምረጥ ስልጣን አለው። ነገር ግን፣ የሕግ መወሰኛው ምክር ቤት፣ ምርጫውን ማፅደቅ አለበት። በተጨማሪም፣ ይህ አንቀፅ፣ ምክር ቤቱ የትኞቹን ምርጫዎች ማፅደቅ እንደሚጠበቅበትና የትኞቹን ደግሞ ዝቅተኛ አድርጎ መተው የሚያስችለውን የአሰራር ዘዴ በግልፅ ያስቀምጣል።

።።።።።።።

2.2.3. ፕሬዝደንቱ፣ ምክር ቤቱ እረፍት ላይ ባለበት ግዜ ለሚፈጠሩ ክፍት ቦታውች፣ ምክር ቤቱ እስኪመለስ ድረስ የሚያገለግል ማዕረግ በመስጠት፣ ቦታውን ሊሞላ ይችላል።

።።።።።።።

ይህ ሐረግ፣ ለፕሬዝደንቱ፣ "የእረፍት ግዜ ሹመት" የመስጠትን ስልጣን ይሰጠዋል። እነዚህ፣ ምክር ቤቱ እረፍት ላይ ሲሆን የሚሰጡ ሹመቶች ናቸው።

።።።።።።።

ክፍል 3

2.3.1. ከግዜ ወደ ግዜ፣ ለምክር ቤቱ ስለ ትብብሩ ሁኔታ መግልጫ በመስጠት፣ አስፈላጊና አስቸኳይ የሆኑ ጉዳዮች ላይ ሀሳባቸውን እንዲሰጡበት ያቀርባል። በአጣዳፊ ጉዳዮች ላይ ለመነጋገር፣ አንዱን

Page �40

ወይም ሁለቱንም ምክር ቤት ለአስቸኳይ ስብሰባ ይጠራቸዋል። የስብሰባውም የግዜ ገደብ ስምምነት ላይ ካልተደረሰ፣ እንደ አስፈላጊነቱ፣ ግዜውን መወሰን ይችላል። አምባሳደሮችንና ሌሎች የሕዝብ ሚኒስትሮችን ይቀበላል። ሕግጋት በትክክለኛ መንገድ እንዲተገበሩ ያደርጋል። ለሁሉም የመንግሥቱ ሹማምንት ውክልና ይሰጣል።

።።።።።።።

ይህ ሐረግ፣ ዓመታዊዉን የፕሬዝደንቱን ገለፃ (State of the Union Address) ይጠቅሳል። በመጀመሪያዎቹ ዘመናት፣ እነዚህ ገለፃዎች በጽሁፍ ብቻ ነበር የሚቀርቡት። በ20ኛው ክፍለ ዘመን ግን፣ ፕሬዝደንት ውድሮ ዊልሰን በንግግር አቀረበው። ከ1933 ዓ.ም. ጀምሮ፣ ሁሉም የትብብሩ ሁኔታ መግለጫ፣ ፕሬዝደንቱ ምክር ቤቱ ውስጥ በአካል በመገኘት የሚሰጠው ንግግር ሆኗል። ይህ ሐረግ ለፕሬዝደንቱ፣ ልዩ የምክር ቤቱን ስብሰባ የመጥራትና ስብሰባውን የመበተን ስልጣን ሰጥቶታል። ፕሬዝደንቱ፣ አምባሳደሮችን የመቀበል፣ ብሎም ሹመታቸውን የማፅደቅ መብት አለው። በተጨማሪም፣ ሰፋ ያለ ትርጉም ባለው ("ሕግጋት በታማኝነት እንዲተገበሩ ይንከባከባል" በሚለው) ሐረግ መሰረት፣ ፕሬዝደንቱ የሀገሪቱ ዋና ሕግ አስከባሪ ይሆናል።

።።።።።።።

ክፍል 4

2.4.1.ፕሬዝደንቱ፣ ምክትል ፕሬዝደንቱና ማንኛውም የአሜሪካ መንግሥት ሲቪል ሹም፣ በመክዳት፣ በሙስና ወይንም በሌላ ከባድ ወንጀል የመፈፀምና ሕግ የመተላለፍ ጥፍት ከተከሰሰና ከተፈረደበት፣ ከስራ ይባረራል።

Page �41

።።።።።።።

ፕሬዝደንቱንም ሆነ ሌሎቹን የመንግሥት ባለስልጣኖች ከስራ የማባረሩ መንገድ፣ በክስና ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘት ነው። ክሱ የሚቀርበው በተወካዮች ምክር ቤት ሆኖ ሳለ፣ የክስ ማስረጃ አቀራረብ ሂደቱ፣ እንደ ሲቪል ክስ ነው። ምክር ቤቱ ፕሬዝደንቱን (ወይም ሌሎች ባለስልጣኖችን) በወንጀል ይከሳል። ከዛ ክሱ ወደ ሕግ መወሰኛው አካል ይተላለፋል። ይህ አካል ፍርዱን በ2/3ኛ ድምፅ ብልጫ ያስተላልፋል። በአሜሪካ ታሪክ ሁልት ፕሬዝደንቶች፣ አንድሩ ጆንሰንና ዊሊያም ክሊንተን፣ በወንጀል ተከሰው ነበር። የሕግ መወሰኛው ምክር ቤት ግን፣ ሁለቱንም በነፃ ስለለቀቃቸው ከስራ አልተባረሩም።

።።።።።።።

አንቀፅ ፫

ክፍል 1

3.1.1. የአሜሪካ የሕግ ስልጣን፣ በአንድ ከፍተኛ ፍርድ ቤትና ምክር ቤቱ ከግዜ ወደ ግዜ እንዳስፈላጊነቱ በሚሰይመው የበታች ፍርድ ቤት ስር ይውላል። የከፍተኛውም ሆነ የበታች ፍርድ ቤት ዳኞች የስራ ዘመን፣ በጥሩ ጠባይ የታነፀ፣ እድሜ ልክ ዘመን ይሆናል። ለዚህም አገልግሎታቸው፣ በተወሰነ ግዜ የሚከፈል፣ በስራ ዘመናቸው የማይቀነስ አበል ያገኛሉ።

Page �42

።።።።።።።

አንቀፅ ፫፣ ፍርድ ቤቱን፣ እንደ ሶስተኛው የመንግሥት አካል ያስቀምጠዋል። የሕግ ስልጣኑም በከፍተኛው ፍርድ ቤት እጅ መሆኑን ይገልፃል። ይህም ማለት፣ ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ፣ የአገሪቱ ሕግጋቶች፣ የመጨረሻው ሸምጋይ ነው ማለት ነው። ፍርድ ቤቱ ከመጀመሪያው፣ ያንድን ሕግ ሕገ መንግሥታዊነት መወሰን አይችልም። ሕጉን የሚቃወም ክስ ሲቀርብ ብቻ ነው የሚወስነው። ከከፍተኛው ፍርድ ቤት በስተቀር፣ ሕገ መንግሥቱ ሌላ ፍርድ ቤት አይፈጥርም። የበታች ፍርድ ቤቶችን፣ በተሰጠው ስልጣን (Judiciary Act) መሰረት፣ መፍጠር የሚችለው ምክር ቤቱ ነው። ሕገ መንግሥቱ፣ ለዳኞች፣ እድሜ ልክ የስልጣን ግዜ ይሰጣል። ዳኞች፣ በማንኛውም አካል ላይ በሰጡት ፍርድ ምክንያት፣ የአበል ቅነሳ ማስፈራሪያ አይደርስባቸውም።

።።።።።።።

ክፍል 2

3.2.1. የሕግ ስልጣኑ፣ ሁሉንም በዚህ ሕገ መንግሥት ስር የተካተቱትን ሕግጋትን ትክክለኛነት፣ የአሜሪካንን ሕግጋት፣ የተደረጉ ወይም የሚደረጉ ውሎችን ያጠቃልላል። አምባሳደሮችና ሌሎች የሕዝብ ሚኒስትሮችንና ቆንስሎችን የሚመለከቱ ጉዳዮች፤ የባህር ሀይል ጽፍት ቤት ጉዳዮችና የባህር መርከብ ነክ ሕግጋቶች፤ አሜሪካንን የሚመለከትና በክፍለ ግዛቶች መካከል የሚፈጠሩ አለመግባባቶች፤ በአንድ ክፍለ ግዛት ነዋሪና በሌላው መካከል የሚነሱ ጉዳዮች፤ በአንድ ክፍለ ግዛት ዜጋና በሌላ ክፍለ ግዛት በተሰጠ መሬት የተነሱ ጉዳዮች፤ በአንድ ክፍለ ግዛት ወይም ዜጋና

Page �43

በውጭ ግዛት ወይም ዜጋ መካከል የሚነሱ ነገሮች ሁሉ፣ በዚህ የሕግ ስልጣን ስር ይካተታሉ።

።።።።።።።

ይህ ሐረግ፣ በከፍተኛው ፍርድ ቤት ሕጋዊ ክንፍ ስር የሚሆኑትን ጉዳዮች ይዘረዝራል። እነዚህ ጉዳዮች፣ በሁለት አጠቃላይ ክፍል ይመደባሉ። የመጀመሪያዎቹ፣ በተለይ ሕገ መንግሥቱን የሚመለከቱት ጉዳዮች ናቸው። በሁለትኛ ደረጃ ያሉት ደግሞ፣ በክፍለ ግዛቶች መካከል የተፈጠሩ አለመግባባቶች፣ በልዩ ልዩ ግዛቶች ውስጥ በሚኖሩ ዜጎች መካከል የተፈጠሩ ጠቦችና የውጭ አገር ባለ ስልጣኖችን ወይም አገሮችን የሚመለከቱ ጉዳዮች ናቸው።

።።።።።።።።

3.2.2. ክፍለ ግዛትን የሚጨምር የአምባሳደሮች፣ የሌሎች የመንግሥት ሚኒስትሮችና የቆንስላዎች ጉዳይ፣ በቅድሚያ በከፍተኛው ፍርድ ቤት ሕግ አድማስ ስር ይሆናሉ። ለሌሎቹ ከላይ ለተጠቀሱት ጉዳዮች፣ ምክር ቤቱ ልዩ ድንጋጌ ካላወጣ በስተቀር፣ ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ በይግባኝ ሊያያቸው ይችላል።

።።።።።።።

ሕገ መንግሥቱ የሚገልፀው፣ የውጭ ተወካይንና አንድን ክፍለ ግዛት የሚመለከትን ጉዳይ፣ መጀመሪያ የሚሰማው ከፍተኛው ፍርድ ቤት መሆኑን ነው። ሌሎች ጉዳዮች በሙሉ፣ በሚመለከተው ክፍለ ግዛት ስር ተበይነው፣ ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ በይግባኝ ሊያያቸው ይችላል። ምክር ቤቱ ይህንን መንገድ ሊቀይረው ይችላል። ይህንንም ስልጣኑን በመጀመሪያው

Page �44

የሕግ ውሳኔ ((Original Judiciary Act of 1789)፣ በአንቀፅ ፫ ክፍል 1 መሰረት አሳይቷል።

።።።።።።።

3.2.3. በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከሚቀርብ ክስ (impeachment) በስተቀር፣ ማንኛውም የወንጀል ክስ፣ በሕዝብ ሸንጎ (jury) ይታያል። ይህም የፍርድ አስጣት ስርአት፣ በሚመለከተው ክፍለ ግዛት ፍርድ ቤት ይካሄዳል። ወንጀሉ ከክፍለ ግዛቶች ውጭ ከተፈፀመ ግን፣ ፍርድ አሰጣጡ፣ ምክር ቤቱ በሚወስነው ስፍራ ይካሄዳል።

።።።።።።።

ይህ ሐረግ፣ ማንኛውም የአሜሪካ የፍርድ አሰጣጥ ስርአት (trial)፣ ምክር ቤቱ ከሚያቀርበው ክስ በስተቀር፣ በሕዝብ ሸንጎ መሆን እንዳለበት ዋስትና ይሰጣል። በተጨማሪም ይህ ስርአት፣ ወንጀሉ በተፈፀመበት ክፍለ ግዛት መኪያሄድ እንዳለበት ያረጋግጣል።

።።።።።።።

ክፍል 3

3.3.1. የአገር መክዳት ወንጀል (treason)፣ በአገር ላይ ጦርነት ማወጅን፣ ከጠላት ጋር ማበርን ወይም እርዳታና ጥገኝነት መስጠትን ብቻ ይመለከታል። ማንም ሰው፣ ያለ ሁልት ምስክሮች ቃል ወይም የግል የጥፋት እምነት በስተቀር፣ በአገር መክዳት ወንጀል አይከሰስም።

Page �45

።።።።።።።

ይህ ክፍል፣ በሕገ መንግሥቱ የተጠቀሰው ወንጀል፣ አገርን መክዳት ብቻ መሆኑን ያመለክታል። ጠባብ ፍች በመስጠትም፣ ጦርነት ማወጅ ወይም አሜሪካ ላይ ጦርነት ያወጀን መርዳት ብሎ ይወስነዋል። ጥፋተኛ ሆኖ ለመገኘትም፣ ለወንጀሉ የሁለት ሰዎች ምስክርነት ወይም በፍርድ ቤት በጽሁፍ የሚሰጥ የግል እምነት መሆን እንዳለበት በፅኑ ያስቀምጣል።

።።።።።።።

3.3.2. ምክር ቤቱ፣ ለአገር መክዳት ወንጀል ቅጣት መስጠት ይችላል። ነገር ግን፣ ያለፍርድ መቅጣትና የተከሳሽን ዘመድ ወይም ዘሮቹን መቅጣት አይቻልም።

።።።።።።።

ሕገ መንግሥቱ፣ የተፈረደበትን ሰው ዘመዶች ወይም ልጆች መቅጣት እንደማይፈቀድ፣ በግልፅ ያስቀምጣል።

።።።።።።።

አንቅፅ ፬

Page �46

ክፍል 1

4.1. አንዱ ክፍለ ግዛት፣ የሌላውን ብሔራዊ ድርጊቶች፣ መዝገቦችና የፍርድ ቤት የችሎት ሂደቶች በሙሉ፣ እምነትና እውቅና ይሰጣል። ምክር ቤቱም፣ እነዚህ ድርጊቶች፣ መዝገቦችና የችሎት ሂደቶች፣ በምን መንገድ እንደሚረጋገጡና ምን ውጤት እንደሚያመጡ፣ በአጠቃላይ ሕግ ይደነግጋል።

።።።።።።።"ሙሉ እምነትና እውቅና (full faith and credit) ማለት፣ እያንዳንዱ ክፍለ ግዛት የሌላውን ክፍለ ግዛት ሕግጋት፣ መዝገቦችና ውሳኔዎችን ይቀበላል ማለት ነው። ለምሳሌ፣ በአንድ ክፍለ ግዛት የፀደቀ መፋታት/ፍች፣ በማንኛውም ክፍለ ግዛት ሕጋዊ ይሆናል ማለት ነው። እንደዚሁም፣ በፍታብሄር (civil) ወይም በወንጀል ፍርድ ያገኘ ጉዳይ፣ ሁሉም ጋ ተቀባይነት ይኖረዋል። የሐረጉ ሁለተኛ አረፍተ ነገር፣ ለምክር ቤቱ፣ ክፍለ ግዛቶቹ ይህንን ጉዳይ የሚቆጣጠሩበትን መንገድ የመደንገግ ስልጣን ይሰጠዋል። በዚህ ሐረግ መሰረት ነው ምክር ቤቱ፣ የጋብቻን ደጋፊ ሕግ (Defense of Marriage Act, DOMA) ያወጣው። ይህ በ1996 ዓ.ም. የወጣው ሕግ፣ ጋብቻን አንድ ሴት ካንድ ወንድ በማለት፣ አንዳንድ ክፍለ ግዛቶች የፈቀዱትን የአንድ አይነት ፆታ (same sex) ጋብቻ ሌሎቹ መቀበል እንደሌለባቸው አመለከተ። በ2013 ዓ.ም.፣ ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ፣ ይህ ሕግ፣ በአምስተኛው ማሻሻያ ሰነድ (5th amendment) መሰረት፣ሕገ መንግሥቱን የሚፃረር ነው በማለት ሰርዞታል።

።።።።።።።

Page �47

ክፍል 2

4.2.1. የአንድ ክፍለ ግዛት ዜጋ፣ ከማንኛውም ሌላ ክፍለ ግዛት ዜጋ እኩል፣ መብቱና ደህንነቱ በየትኛም ግዛት የተጠበቀ ይሆናል።

።።።።።።።

ይህ ሐረግ፣ አንድ ክፍለ ግዛት፣ ከየትኛውም ክፍለ ግዛት ለሚመጣ ዜጋ፣ ከዜጎቹ እኩል፣ ሙሉ መብት መስጠት እንዳለበት ይደነግጋል። የአንድ ክፍል ግዛት ዜጋ የሚያገኘውን የኮሌጅ ትምህርት ክፍያ ቅናሽ፣ የሌላ ክፍለ ግዛት ዜጋም ማግኘት እንደሚገባው የሚያደርግ ትርጉምም ይሰጠዋል። ።።።።።።።

4.2.2. በማንኛውም ክፍለ ግዛት ውስጥ፣ በመክዳት ወይም በሌላ ወንጀል የተከሰሰ ሰው፣ ከፍርድ በመሸሽ ሌላ ክፍለ ግዛት ከተገኘ፣ ከሸሸበት ክፍለ ግዛት በሚመንጭ ማዘዣ ተይዞ፣ ወንጀሉን ወደፈፀመበት ግዛት እንዲመለስ ይደረጋል።

።።።።።።።

4.2.3. በአንድ ክፍለ ግዛት ሕግ መሰረት፣ የስራ መቀጮ የተፈረደበት ሰው፣ አምልጦ ሌላ ክፍለ ግዛት ቢገኝ፣ ስራውን ለመስራት ከተፈረደለት አካል በሚመነጭ ጥያቄ መሰረት፣ ተይዞ እንዲመለስ ይደረጋል።

።።።።።።።

ይህ ሐረግ፣ ስለሚኮበልሉ ባሮች የወጣውን ሕግ (fugitive slave law)፣ መሰረት ያደረገ ነው። አንድ ባሪያ፣ የባርነት ስርአት ከሚካሄድበት ክፍለ

Page �48

ግዛት ወደ ነፃ ክፍለ ግዛት በመኮብለል፣ ከባርነት ነፃ እንደማይወጣ ያረጋግጣል።

።።።።።።።

4.3.1. ምክር ቤቱ አዳዲስ ክፍለ ግዛቶችን ወደ ትብብሩ ማስገባት ይችላል። ነገር ግን፣ ያለ ክፍለ ግዛቱ እስተዳደርና የምክር ቤቱ ስምምነት፣ ምንም ዓይነት አዲስ ክፍለ ግዛት፣ እሌላ ክፍለ ግዛት ክልል ውስጥ ወይም ከሌላ ክፍለ ግዛት ጋር በመደባለቅ ወይም ከሌላ ክፍለ ግዛት ተቆርሶ እንዲፈጠር ማድረግ አይችልም።

።።።።።።።

ይህ ሐረግ፣ አዲስ ክፍለ ግዛት ወደ ሕብረቱ የሚቀላቀልበትን መንገድ ያስቀምጣል። በተጨማሪም፣ አንድ ክፍለ ግዛት፣ ተገንጥሎ አዲስ ክፍለ ግዛት መመስረት እንደማይችል ይገልፃል። እንደዚሁም፣ ሌላ ክፍለ ግዛት እንዴት እንደሚቀላቀል በግልፅ በማስቀመጥ፣ ከሕብረቱም መገንጠል እንደማይቻል ይደነግጋል።

።።።።።።።

4.3.2. ምክር ቤቱ፣ የአሜሪካንን ግዛትና ንብረት በሚመመለከት ጉዳይ በሙሉ፣ አስፈላጊ ሕግጋትን የማውጣት ስልጣን ይኖረዋል። በዚህ ሕገ መንግሥት ውስጥ፣ የአሜሪካንን ወይም የክፍለ ግዛትን መብትም ሆነ ጥያቄ፣ የአድልዎ መልክ የሚያሳይ ትርጉም እንዳይሰጠው ይከለክላል።

።።።።።።።

Page �49

ይህ ሐረግ፣ ለምክር ቤቱ፣ የአገሪቱን አስፈላጊ ያስተዳደር ደንብ የማውጣት ስልጣን ሰጥቶታል።

።።።።።።።

4.4.1. ፌዴራል መንግሥቱ፣ ክፍለ ግዛቶቹ በሙሉ፣ በሕዝብ ምርጫ የሚያምን ያስተዳደር ስርአት እንደሚኖራቸው ዋስትና ይሰጣል፤ እያንዳንዳቸውንም፣ ከምንም ዓይነት ወረራና ሕግ በሚፈቅደው መሰረት፣ ከአገር ውስጥ ሁከት ማንሳት ድርጊት ይከላከልላቸዋል።

።።።።።።።ይህ ሐረግ፣ ሁለት ክፍል አለው። በአንድ በኩል፣ ክፍለ ግዛት ውስጥ ሁከት ካለ፣ መንግሥት ወታደር ልኮ ያስታግሳል። በሌላ በኩል፣ በማንኛውም ክልል አምባገነናዊ ስርአት ቢነሳ ለማስቆም፣ ፌዴራል መንግሥቱ ዋስትና ይሰጣል። እያንዳንዱ ክፍለ ግዛትም፣ በሕዝብ ምርጫ የሚሰራ ያስተዳደር ስርአት እንዲኖረው ያስገድዳል።

።።።።።።።

አንቀፅ ፭ምክር ቤቱ አስፈላጊ ከመሰለው፣ በ2/3ኛ የሁለቱም ምክር ቤት ድምፅ ብጫ፣ ለሕገ መንግሥቱ የማሻሻያ ሀሳብ ማቅረብ ይችላል። ወይንም በ2/3ኛ የክፍለ ግዛቶቹ ሁሉ ሕግ አውጭ ክፍል ድምፅ ብልጫ ማመልከቻ ሲገባ፣ የሕገ መንግሥት ማሻሻያ ሀሳብ ማቅረቢያ ጉባኤ በመጥራት፣ ወይም ምክር ቤቱ ከተስማማበት፣ የክፍለ ግዛቶቹ ሕግ አውጭ አካል በ3/4ኛ ድምፅ ካስተላለፈው፣ የማሻሻያው ሀሳብ ይፀድቃል። ይህ መሆን የሚችለው ግን፣ ከ1808ዓ.ም. በፊት የሚቀርብ የማሻሻያ ሀሳብ፣ የአንቀፅ

Page �50

፩፣ ክፍል 9፣ ሐረግ 1ና 4ትን (1.9.1 እና 1.9.4) በምንም መልኩ የማያስተጏጉል ከሆነና ማናቸውም ክፍለ ግዛት ካልፈቀዱ በስተቀር፣ የሕግ አውጭው ምክር ቤት አባልነት የምርጫ መብታቸው እስከተጠበቀ ግዜ ድረስ ብቻ ነው።

።።።።።።

ይህ ሐረግ፣ ሕገ መንግሥቱን ለመለወጥ ለሚወሰድ እርምጃ መሰረት ይጥላል። አንድ የማሻሻያ ሀሳብ ፀድቆ ሕገ መንግሥቱ ውስጥ ከገባ፣ እንደ ማንኛውም የመጀመሪያው ሕገ መንግሥት ፅሁፍ ሐረግ፣ እኩል ቦታ ይኖረዋል። ሕገ መንግሥቱን ለመቀየር ሁለት መንገዶች ተቀምጠዋል። የመጀመሪያው መንገድ፣ ከምክር ቤቱ የሚመነጭ፣ በ2/3ኛ ድምፅ ብልጫ መፅደቅ ያለበት የማሻሻያ ሰነድ ነው። ሁለተኛው፣ ክፍለ ግዛቶቹ የሕገ መንግሥት ማሻሻያ ልዩ ጉባኤ በመጥራት፣ የሚያስተላልፉት የማሻሻያ ሀሳብ ነው። እስከ ዛሬ ድረስ፣ የመጀመሪያው መንገድ ብቻ ነው ስራ ላይ የዋለው። በጠቅላላው፣ ከ10,000 በላይ የማሻሻያ ሀሳቦች ቀርበዋል። ከእነዚህ ውስጥ፣ 33 ብቻ ናቸው በምክር ቤቱ ተወስነው ወደ ክፍለ ግዛቶቹ የተላለፉት። ክፍለ ግዛቶቹ ሁልት የማፅደቂያ መንገድ አላቸው። አንድም፣ የክፍለ ግዛቱ የሕግ አውጭ ክፍል፣ በ3/4ኛ የድምፅ ብልጫ ያስተላልፈዋል። አልያም፣ እያንዳንዱ ክፍለ ግዛት፣ ልዩ ጉባኤ በመጥራት፣ ውሳኔውን ይሰጣል። በዚህ ዓይነት፣ 27 የማሻሻያ ሀሳቦች ፀድቀው፣ የሕገ መንግሥቱ አካል ሆነዋል። ከአንድ የማሻሻያ ሀሳብ በስተቀር፣ ሁሉም በክፍለ ግዛቶች የሕግ አውጭ ክፍል ፀድቀው ነው ሕገ መንግሥቱ ውስጥ የተካተቱት።

።።።።።።።

አንቀጽ ፮Page �51

6.1.1. ይህ ሕገ መንግሥት ከመፅደቁ በፊት የተገቡ እዳዎችና ውሎች በሙሉ፣ ልክ እንደ ኮንፌዴሬሽኑ ውሎች ሕጋዊ ይሆናሉ።

።።።።።።።

ይህ ክፍል፣ ታሪካዊ ሂደትን የተመለከተ ሆኖ፣ በሕገ መንግሥቱ መሰረት፣ የአሜሪካ መንግሥት ለፊተኞቹ እዳዎች በሙሉ፣ ሀላፊነቱን መውሰድ እንዳለበት ያመለክታል።

።።።።።።።

6.1.2. ይህ ሕገ መንግሥትና እሱን ተመርኩዘው የተፃፉ የአሜሪካ መንግሥት ሕግጋትና የተገቡ ወይም የሚገቡ ውሎች፣ የአገሪቱ ከፍተኛ ሕጎች ይሆናሉ። የክፍለ ግዛቶቹም ዳኞች፣ ሕገ መንግሥቱ ወይም ክፍለ ግዛቶቹ የደነገጉት ሕግ ከሌለ በስተቀር፣ በዚህ አንቀስ ስር ይውላሉ።

።።።።።።።

6.1.3. ይህ ሐረግ፣ በፌዴራል መንግሥቱ የተደረሱ ስምምነቶች በሙሉ፣ ከክፍለ ግዛቶች የተደረጉ ሕግጋት ላይ፣ የበላይነት ያለው መሆኑን ያረጋግጣል።

።።።።።።።

ይህ ሐረግ፣ ግልፅ ያለ ቢሆንም፣ ብዙ የተዛቡ ትርጉሞችን አስነስቷል።

Page �52

።።።።።።።

6.1.4. ከላይ የየጠቀሱት የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የሁሉም ክፍለ ግዛት የሕግ አውጭ ክፍል አባሎችና ሁሉም የአሜሪካ መንግሥትና የክፍለ ግዛቶች የአስተዳደርና የሕግ አባሎች፣ በመሀላ ለሕገ መንግሥቱ ድጋፍ ይሰጣሉ። ነገር ግን፣ ለማናቸውም የመንግሥት ሥራ ወይንም የሀልፊነት ሙያ፣ የሀይማኖት መመዘኛ ፈተና አይደረግባቸውም።

።።።።።።።

ይህ በጣም ግልፅ የሆነው የሕገ መንግሥቱ ቃል፣ የመንግሥት አባል ለመሆን፣ የምንም ወይም የማንኛውም ዓይነት ሐይማኖት አባል መሆን እንደማያስፈልግ፣ በግልፅ ያስቀምጣል።

።።።።።።።

አንቅፅ ፯

የስብስቡን ሰነድ ሕገ መንግሥታዊ አድርጎ ለማፅደቅ፣ የዘጠኙ ግፍለ ግዛቶች ስምምንነት በቂ ይሆናል።

።።።።።።

Page �53

በስብስቡ በነበሩት የክፍለ ግዛቶቹ ተወካዮች የአንድ ድምፅ ስምምነት፣ በመስከረም አስራ ሰባት ቀን፣ በጌታችን አቆጣጠር ሺህ ሰባት መቶ ሰማንያ ሰባት ዓምተ ምህረትና በተባበሩት አስራ ሁልቱ የአሜሪካ ክፍለ ግዛቶች የነፃነት ቀን ፀድቋል። ይህንንም ስምምነት ማፅደቃችንን በስማችን ፊርማ እናረጋግጣለን።

።።።።።።።።

የማሻሻያ አንቀፆች

ማሻሻያ ሀሳብ ፩

ምክር ቤቱ፣ የአንድን ሀይማኖት መመስረት የሚያከብር ወይም የሌላውን ነፃ እምነት የሚፃረር ወይም የነፃ ንግግርንና ጽሁፍን የሚገድብ ወይም የሕዝብን በሰላማዊ መንገድ ተሰብስቦ ቅሬታን የማቅረብ መብት የሚከለክል ሕግ አያወጣም።

።።።።።።።

የየጀመሪያዎቹ አስሩ የሕገ መንግሥቱ የማሻሻያ ሀሳቦች፣ "የመብት የሕግ ረቂቅ" (Bill of Rights) ይባላሉ። አነዚህ የማሻሻያ ሀሳቦች ያስፈለጉት፣ ሕገ መንግሥቱ የግለ ሰብን የግል መብት በሚገባ አልጠበቀም የሚል ስጋት ስለነበረ ነው። በተፃፉበት ግዜ፣ በመንግሥት ለሚወሰዱ እርምጃዎች፣ ግለ ሰቦች በቂ መከላከያ እንዲኖራቸው ታስቦ ነው። አስራ አራተኛው ማሻሻያ ሀሳብ የተላለፈው፣ የእርስ በርስ ጦርነቱ እንዳበቃ

Page �54

ነበር። ይህ የማሻሻያ ሀሳብ፣ መከላከያው ለክፍለ ግዛቶችና ለሀገር ውስጥ ሕግጋቶችም እንዲያገለግል መሰረት ሆነ። በሀያኛው ክፍለ ዘመን፣ የመብት የሕግ ረቂቁ፣ ሁሉንም የመንግሥት አካሎች እንዲሸፍን፣ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ቀስ በቀስ አስተላለፋቸው።

የመጀመሪያው የማሻሻያ ሀሳብ፣ ምክር ቤቱ የማንንም የሀይማኖት እምነት የሚገድብ ሕግ ማውጣት እንደማይችል ያረጋግጣል። ይህ የማሻሻያ ሀሳብ፣ በአሜሪካ ሙሉ የሀይማኖት ነፃነት እንደሚኖር ይጠቅሳል። መንግሥት የመናገርን መብት አያግድም። ይህም ማለት፣ ሰዎች የፈለጉትን ማለት ይችላሉ ማለት ነው። የሚከለከል ነገር ቢኖር፣ በታዋቂው የከፍተኛው ፍርድ ቤት አባል ኦሊቨር ዌንድል ሆልምስ በሰጠው ምሳሌ፣ ማንም ሰው ብዙ ሰው በተሰበሰበበት የሲኒማ አዳራሽ ውስጥ፣ በሀሰት "እሳት ተንሳ" ብሎ መጮህ እንደማይችል ነው። ይህም ማለት፣ በሰው ላይ ድንገተኛ አደጋን ሊያስከትል የሚችል ድርጊት ወይም አባባል መፈፀም እንደማይቻል ነው። ሕገ መንግሥቱ፣ ሙሉ በሙሉ ለመሆን ትንሽ የቀረው፣ የጽሁፍ ነፃነት ይሰጣል። የኒው ዮርክ ታይምስ የፔንታጎንን ጽሁፍች እንዳያትም መንግሥት ለመከልከል ሲሞክር፣ ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ አግዶት ነበር። ሕገ መንግሥቱ፣ ሕዝቦች መንግሥትን መቃወም እንደሚችሉ፣ በማያጠራጥር መንገድ ያስቀምጣል። ይህም ማለት፣ በሰላማዊ መንገድ ለመቃወም መሰብሰብ መቻል ማለት ነው። በመጨረሻም ይሄ ማሸሻሻያ፣ በዋሺንግተን በጣም የሚወቀሱትን የባለ ስልጣን አግባቢዎችን (lobbyists) ሥራ ይደግፋል።

ማሻሻያው፣ ሕዝቦች በመንግሥት ላይ ለሚያቀርቡት አቤቱታ፣ ምንም የሚያግዳቸው ሕግ እንዳይወጣ ይከለክላል። ይህ አባባል፣ የሚከፈላቸውን የባለ ስልጣን አግባቢ ቡድኖችንም (lobbyist) እንደሚያጠቃልል ተደርጎ ይተረጎማል።

Page �55

።።።።።።።።

ማሻሻያ ሀሳብ ፪

በደንብ የተስተካከለ ሚሊሺያ፣ ለነፃ ግዛት ጥበቃ አስፈላጊ እንደመሆኑ መጠን፣ የሕዝቦች መሳሪያ የመያዝና የመታጠቅ መብት አይደፈርም።

።።።።።።።

ይህ የማሻሻያ ሀሳብ፣ የአሜሪካኖችን ሽጉጥ የመያዝ መብት ያረጋግጣል። የዚህ ማሻሻያ ሀሳብ ትክክለኛ ትርጉም ብዙ ያከራከረ ጉዳይ ነው። የማሻሻያው ሀሳብ እንደ አንባቢው፣ መሳሪያ የመያዝ ወይም የመታጠቅ መብት፣ በቀጥታ ከሚሊሺያው ጋር የተገናኘና ሚሊሺያው የሚያስፈልገውን መሳሪያ ዓይነት የሚጠቅስ ወይም የግል መብት ሊሆን ይችላል። የዚህ ማሻሻያ ሀሳብ ትርጉም፣ በጣም አከራካሪ ለሆነው የመሳሪያ ግደባ ሙግት ስረ መሰረት ሆኗል።

።።።።።።።

ማሻሻያ ሀሳብ ፫

ማንም ወታደር በሰላም ዘመን፣ ያለባለቤቱ ፈቃድ በሰው ቤት ውስጥ አይቀመጥም። በጦርነትም ግዜ ቢሆን፣ በሕግ በተደነገገ መንገድ ብቻ ይሆናል።

።።።።።።።

Page �56

ይህ የማሻሻያ ሀሳብ የተፃፈው፣ የስር ነቀል ጦርነቱ (Revolutionary War) ሊከናወን አካባቢ ለነበረው የአሜሪካን ገጠመኝ ምላሽ ነበር። እንግሊዞች ወታደርን በግል ሰው ቤት ውስጥ ማኖር (Quartering Act) የተሰኘውን በአሜሪካኖች በኩል የተጠላውን ሕግ አስተላልፈው ነበር። በዚህ የማሻሻያ ሀሳብ መሰረት ግን፣ የአሜሪካ መንግሥት እንዲህ ዓይነት ተመሳሳይ ድርጊት መፈፀም እንደማይችል ያረጋግጣል። ይህ የማሻሻያ ሀሳብ ግን፣ ምንም ጊዜውን የጠበቀ ጥቅም አላመጣም።

።።።።።።።

ማሻሻያ ሀሳብ ፬

የሕዝቦችን የግል፣ የቤቶቻቸውን፣ የጽሁፎቻቸውንና የቁሳቁሶቻቸውን የተጠበቀ መብት መጣስ፣ ያለ በቂ ምክንያት መፈተሽ ወይም መያዝ፣ በፍፁም የተከለከለ ነው። በመሃላ ወይም በእምነት የተረጋገጠ ድርጊት ካልሆነና በተለይም የሚፈተሸውን ቦታና የሚያዘውን ሰው ወይም ነገር ያረጋገጠ ካልሆነ በስተቀር፣ የማዘዣ ትዕዛዝ አይሰጥም።

።።።።።።

ይህ የማሻሻያ ሀሳብ፣ የማንም ሰው ቤት ያለ በቂ ምክንያት መፈተሽ እንደማይቻል ያረጋግጣል። የማንንም ሰው ቤት ለመፈተሽ፣ መንግሥት ከዳኛ ልዩ ፈቃድ ማግኘት ይኖርበታል። መንግሥት በቅድሚያ ለመፈተሽ ያለውን ምክንያትና ማስረጃ፣ በግልፅ ለዳኛው ማቅረብ ይኖርበታል። የፍተሻ ፍቃድ ሰፋ ብሎ፣ የስልክ ግንኙነቶችንም ያጠቃልላል። ማሻሻያ ሀሳቡ የሚሸፍናቸው የኤሌክትሮኒክ መገናኛ መንገዶች ጉዳይ፣ አሁንም የሚያከራክር ጉዳይ ነው። በግል የቤት ኮምፒውተር ላይ ያሉ ኢሜሎች

Page �57

(በኮምፒውተር ዓለም አቀፋዊ የመረጃ ልውውጦች)፣ በማሻሻያ ሀሳቡ ጥበቃ ስር ይካተታሉ። ነገር ግን፣ ልውውጦቹ ከዌብ አገልግሎት ጋር የተያያዙ ከሆኑ፣ በአሁኑ ግዜ መንግሥት ያለ ማዘዣ የመፈተሽ ሀይሉ የተሻለ ነው።

።።።።።።።

ማሻሻያ ሀሳብ ፭

የባህር ሀይልንና ሚሊሻውን የማይመለከትና ጦርነት ወይም አስጊ ሁኔታ ካልተፈጠረ በስተቀር፣ ያለ የሕዝብ ታላቅ ሸንጎ (Grand Jury) ትዕዛዝ፣ ማንም ሰው በጥፋት ወይም ልዩ ወንጀል አይከሰስም። በተከሰሰበትም ወንጀል፣ ከአንድ ግዜ በላይ አይፈረድድበትም። ያለ ሕጋዊ ስርአትም፣ በወንጀል ክስ በራሱ ላይ መመስከር አልያም የህይወት፣ የንብረት ወይንም የነፃነት ገፈፋ አይኪያሄድበትም። የግል መሬትም፣ ያለ ተመጣጣኝ ክፍያ፣ ለጋራ አገልግሎት አይውልም።

።።።።።።።

የዚህ ማሻሻያ ሀሳብ የመጀመሪያው ክፍል፣ በ "ታዋቂ ከባድ ወንጀል"፣ በአሁኑ ግዜ "ፌሎኒ ክራይም" ለሚባለው ወንጀል የተከሰሰን ሰው ሙሉ ዋስትና ይሰጠዋል። ይህም ማለት፣ ከብያኔው በፊት፣ ክሱ በሕዝብ ታላቅ ሸንጎ (Grand Jury) መከሰስ አለበት። የሕዝብ ታላቅ ሸንጎ የሚባለው፣ ቢያንስ አስራ ሁልት አባሎች ያሉት፣ በአብዛኛ ድምፅ ብልጫ ተከሳሽ ላይ የፍርድ ውሳኔ መስጠት የሚችል አካል ነው። አብዛኛውን ግዜ፣ ይህ አካል የሚሰጠው ፍርድ፣ አቃቤ ሕጉ የጠየቀውን ነው። አንድ ታዋቂ አባባል እንዳመለከተው፣ "ማንም አቃቤ ሕግ ቢፈልግ፣ የአሳማ ወርች ሳንድዊች ላይ እንኳን ማስፈረድ ይችላል።"

Page �58

ሁለተኛው ክፍል፣ "እጥፍ አስጊ ሁኔታ" (double jeopardy) የተባለውን ሁኔታ፣ ሕጋዊ እንዳልሆነ ያስቀምጣል። አንድ ሰው በተከሰሰበት ወንጀል ነፃ ሆኖ ከተገኘና ሸንጎው ፍርድ መስጠት ካላቃተው (hung jury) በስተቀር፣ በዚህ ወንጀል በድጋሚ አይከሰስም። ተከሳሹ ሌላ ክልል በድጋሚ ካልተከሰሰ፣ በፍታብሔር ካልተከሰሰ ወይም ሌላ ወንጀል ካልተገኘበት በስተቀር፣ የእጥፍ አስጊ ሁኔታ ሕግ ተጠቅሶ ሥራ ላይ ይውላል። በዚህ መንገድ ፌዴራል መንግሥቱ፣ በደቡቡ የአሜሪካ ክፍል፣ ጥቁር አሜሪካዊ ሰው ገድሎ ነፃ የተለቀቀን ሰው፣ እንደገና በሰው ልጅ መብት ገፈፋ ወንጀል መክሰስ ችሏል። ሌላው ምሳሌ ደግሞ፣ በወንጀል ክስ ነፃ የወጣውን ኦ ጄ ሲምሰንን፣ በፍታብሔር ሕግ፣ አላግባብ ሞት በማለት እንደገና ሊከሰው እንደሚችል ነው።

ተከታዩ ክፍል ደግሞ፣ ማንም ስው ለተከሰሰበት ወንጀል፣ የራሱን የወንጀለኛነት ቃል ለመስጠት እንደማይገደድ ያመለክታል። ስለዚህ፣ አንድ የተከሰሰ ሰው፣ "አምስተኛውን ጠቅሻለሁ" (I plead the fifth) ካለ፣ አምስተኛውን ማሻሻያ ሀሳብ ተገን በማድረግ፣ እራስ ላይ ከመመስከር የመቆጠብን መብት ተጠቅሟል ማለት ነው። ከፍተኛው ፍርድ ቤት ይህንን መብት ሰፋ በማድረግ፣ "የሚራንዳ" ውሳኔ የተሰኘውን ዝነኛ ሰነድ አስተላልፏል። በዚህም ውሳኔ መሰረት፣ ማንም ተከሳሽ፣ መብቱ እንዲነበብለት ያስገድዳል። ከዚህ በሁዋላ፣ "ሚራንዳይዝ ማድረግ" የሚለው ቃል ተወለዷል።

የሚቀጥለው አረፍተ ነገር እንደሚያመለክተው፣ ሁሉን ያዥ ሀረግ ተብሎ፣ "ሕይወት፣ ነፃነትና ንብረት ያለ አግባባዊ ሂደት አይወሰዱም" ይላል። ይህም "የአግባባዊ ሂደት ሐረግ" (due process clause) ተብሎ፣ መንግሥት ከአንድ ግለሰብ ምንም ነገር ለመውሰድ፣ የሞት ቅጣት ለመወሰን ወይም ለማሰር፣ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ማግፕት እንዳለበት ያመለክታል።

Page �59

የዚህ አንቀጽ የመጨረሻው ክፍል ደግሞ፣ "የላቀ ግዛት" (eminent domain) የተሰኘ፣ መንግሥት የግልን ንብረት ወስዶ ወደ ሕዝብ ጥቅም የማዋል መብቱን ያረጋግጣል። በቅርብ ዘመን ያከራከረው ጉዳይ፣ "ብሔራዊ ጥቅም" የሚለው ቃል ነው። መንግሥት የግል ንብርትን በመውሰድና ለአካባቢው ይጠቅማል ብሎ የግል አራዳ ሱቅ ቢሰራበት፣ "ብሔራዊ ጥቅም" ይባላል?

።።።።።።።

ማሻሻያ ሀሳብ ፯

በሁሉም ዓይነት የወንጀል ክስ፣ ተከሳሽ ወንጀሉ በተፈፀመበት ሕጋዊ ቦታ፣ የወንጀሉ ዓይነትና ምክንያት በቅድሚያ ተነግሮት፣ ፈጣንና ግልፅ የሆነ፣ የተከሰሰበት ቦታ ላይ ባለ የማያዳላ ሕዝባዊ ችሎት፣ ፍርዱ እንዲሰጠው ያደረጋል። በዚህም ክስ፣ ተከሳሽ የከሳሽ ምስክሮችን በግልፅ ሰምቶ፣ የራሱንም ምስክሮች ቃል አሰምቶና የሚረዳውም ሕጋዊ ጠበቃ ተመድቦለት፣ የፍርዱ ስርአት ይከናወናል።

።።።።።።።

ይህ የማሻሻያ ሀሳብ፣ ተከሳሽ ፈጣን የፍርድ ብያኔ ማግኘት እንዳለበት ያረጋግጣል። ስለሆነም፣ መንግሥት ተከሳሽን ወደ ፍርድ ለማቅረብ መዘግየት እንደሌለበት ያመለክታል። በተጨማሪም፣ ይህ የማሻሻያ ሀሳብ፣ የድብቅ ፍርድ ቤት ወይም ችሎት መኖር እንደማይችልና ፍርዱ በአደባባይ ሕዝባዊ ችሎት መኪያሄድ እንዳለበት ያረጋግጣል።

Page �60

ተከሳሽ፣ ማንኛውንም ምስክር ማፋጠጥና መፈተን ይችላል። ለምስክርነት መቆም የማይችል የማንም ሰው አባባል፣ ተከሳሽን ለመወንጀል ብቃት አይኖረውም። ተጠቂው ወገን ህፃን በሚሆንበት ግዜ፣ የሚወሰደው የፍርድ ሂደት ፈታኝ ሆኗል። ማሻሻያ ሀሳቡ፣ ተከሳሽ ከአቃቤ ሕጉ እኩል፣ ምስክሮቹን አስገድዶ የማቅረብ መብት እንዳለው ያረጋግጣል። በመጨረሻም ይህ የማሻሻያ ሀሳብ፣ ተከሳሽ የሚሟገትለት ጠብቃ ሊኖረው እንደሚገባ ያረጋግጣል።

።።።።።።

ማሻሻያ ሀሳብ ፰

በጋራ ሕግ (common law) ክስ ግዜ፣ የክሱ መጠን ከሃያ ብር ከበለጠ፣ በሕዝብ የፍርድ ሸንጎ መዳኘቱ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ በዚህ መንገድ የተዳኘ ጉዳይ፣ የጋራ ክስ ሕጉ ከሚፈቅደው ውጭ፣ በመንግሥት ፍርድ ቤት እንደገና አይታይም።

።።።።።።።

ይህ የማሻሻያ ሀሳብ የሚያመለክተው፣ በፍታብሔር ክስ የተሳተፉ ግለ ሰቦችም በሕዝብ የፍርድ ሸንጎ መበየን እንደሚችሉ ነው። መስራቾቹ ሃያ ብር ያሉት፣ በሕዝብ ሸንጎ የመበየንን ገደብ በማሰብ ነው። በአሁኑ ግዜ፣ ያ መጠን ወደ $500 ይጠጋል።

።።።።።።።

ማሻሻያ ሀሳብ 9

Page �61

በሕገ መንግሥቱ ውስጥ የተዘረዘሩ አንዳንድ መብቶች መኖር፣ ሌሎች በሕዝብ ውስጥ የተያዙትን የመከልከል ወይም የማንኳሰስ ትርጏሜ ሊሰጣቸው አይገባም።

።።።።።።።

ይህ የማሻሻያ ሀሳብ፣ በሕገ መንግሥቱ ውስጥ በግልፅ ያልተቀመጡ፣ ሁሉንም የሕዝብ መብቶች እንደሚያረጋግጥ ተደርጎ ይተረጎማል። ከፍተኛው ፍርድ ቤት፣ 9ነኛውን የማሻሻያ ሀሳብ በመጥቀስ፣ የግለ ሰብን መብት ይሰጣል። 9ነኛው የማሻሻያ ሀሳብ፣ የእርግዝና መከላከያ መጠቀም መብትን የሚቃወሙ ሕግጋትን ጭምር፣ ሕገወጥ አድርጏቸዋል። በተጨማሪም፣ ፅንስ ማስወረድን የሚከለክሉ ሕግጋት እንዲሰረዙ ለማድረግ መሰረት ሆኗል።

።።።።።።።

ማሻሻያ ሀሳብ ፲

በሕገ መንግሥቱ ውስጥ፣ ለመንግሥት ያልተሰጡ ስልጣኖች ወይም ለክፍለ ግዛቶቹ ያልተከለከሉት ሁሉ፣ ለሚመለከታቸው ክፍለ ግዛቶች ወይም ለሕዝብ ተትተዋል።

።።።።።።።

ይህ የማሻሻያ ፅሀሳብ እንደሚያመለክተው፣ በሕገ መንግሥቱ ያልተጠቀሱ ስልጣኖች በሙሉ፣ ለክፍለ ግዛቶች ወይም ለሕዝብ ተሰጥተዋል።

Page �62

አከራካሪ የሆነው ጉዳይ፣ እነዚህ ስልጣኖች በግልፅ መጠቀስ እንዳለባቸው ወይም አመልካች (implied) መሆን እንዳለባቸው ነው።

።።።።።።።

ማሻሻያ ሀሳብ ፲፩

የአሜሪካ የሕግ ስልጣን፣ በአንድ ክፍለ ግዛት ወይም በአንድ የአሜሪካ ዜጋ ወይም በሌላ አገር ዜጋ መካከል የተመሰረተን የሕግ ወይም የንብረት ክስ አያጠቃልልም።

።።።።።።።

፲፩ኛው የማሻሻያ ሀሳብ፣ ክፍለ ግዛቶችን በፌዴራል ፍርድ ቤት መክሰስ እንደማይቻል ያረጋግጣል። የማሻሻያው ሀሳብ የተላለፈው፣ በቺስሎምና በጆርጂያ መካከል የተንሳውን ክስ ለመወሰን ሲባል ነበር። ጆርጂያ በቺስሎም ስትከሰስ፣ ብያኔው ለቺስሎም ተሰጠ። ይህ የማሻሻያ ሀሳብ የማያግዳቸው ጉዳዮችም አሉ። በዋናነት የሚጠቀሱት፣ የምርጫ መብትን የሚመለከቱት ጉዳዮች ናቸው።

።።።።።።።

ማሻሻያ ሀሳብ ፲፪

መራጮቹ በየክፍለ ግዛቶቻቸው በመሰብሰብ፣ በድምፅ መስጫ ወረቀት፣ ለፕሬዝደንትነትና ምክትል ፕሬዝደንትነት ድምፅ ይሰጣሉ። ቢያንስ አንዱ ተመራጭ፣ ከመራጩ ክፍለ ግዛት ውጭ ነዋሪ መሆን አለበት። መራጮቹ

Page �63

በድምፅ መስጫ ወረቀቱ ላይ፣ ለፕሬዝደንትነትና ምክትል ፕሬዝደንትነት የመረጡትን ሰው ስም በማስፈር፣ በተጨማሪም የተመረጡትን ሰዎች ሁሉ ስምና የደረሳቸውን ድምፅ ዝርዝር በመመዝገብና የማረጋገጫ ፊርማቸውን በማስፈር፣ በታሸገ ኤንቬሎፕ፣ በአሜሪካ መንግስት መቀመጫ ከተማ ለሚገኘው ለሕግ መወሰኛው ምክር ቤት ፕሬዝደንት ይልኩታል። የምክር ቤቱ ፕሬዝደንትም፣ የሁለቱም ምክር ቤት አባሎች በተሰበሰቡበት፣ የታሸገውን ኤንቬሎፕ በመክፈት፣ የድምፅ መስጭ ወረቀቶቹን ይቆጥራል። የመራጮቹ የድምፅ መስጫ ወረቀት ተቆጥሮ፣ አብዛኛውን የፕሬዝደንትነት ድምፅና ከመራጮቹ ሁሉ ያብዛኛዎቹን የድምፅ ብልጫ ያገኘው ሰው ፕሬዝደንት ይሆናል። ማንም ተመራጭ፣ የዚህ ዓይነት የድምፅ ብልጫ ካላገኘ፣ ከሶስት የማይበልጡ፣ ለፕሬዝደንትነት የበላይ ድምፅ ካገኙት መሀል፣ የሕግ አውጭ ምክር ቤቱ አባሎች ወዲያውኑ፣ አንዱን በድምፅ መስጫ ወረቀት ለፕሬዝደንትነት ይመርጣል። በዚህ ዓይነት ፕሬዝደንቱን ለመምረጥ ግን፣ ድምፅ አሰጣጡ በክፍለ ግዛቶቹ ሆኖ፣ እያንዳንዱ የክፍለ ግዛት ተወካይ አንድ ድምፅ ብቻ እንዲኖረው ይደረጋል። ለምልአተ ጉባኤው፣ የክፍለ ግዛቶቹ ተወካዮች ሁለት-ሶስተኛ የድምፅ ብልጫና የአብዛኛዎቹ ክፍለ ግዛቶች ተካፋይነት ያስፈልጋል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤቱ አባሎች የመምረጥ እጣ ደርሷቸው፣ ከተከታዩ መጋቢት አራት በፊት ፕሬዝደንቱን መምረጥ ካልቻሉ፣ ምክትል ፕሬዝደንቱ፣ እንደማንኛውም የፕሬዝደንቱ ሞትና ሕገ መንግሥታዊ እክል ግዜ ሁሉ፣ እንደ ፕሬዝደንትነት እንዲያገለግል ይደረጋል። አብላጫ የምክትል ፕሬዝደንትነት ድምፅ ያገኘው ሰው፣ ከአብላጫው የመራጮች ቁጥር ጋር ከተመጣጠነ፣ ምክትል ፕሬዝደንት ይሆናል። አብላጫ ድምፅ ያገኘ ሰው ከሌለ፣ የአብላጫ ድምፅ ካላቸው ሁለት ሰዎች መካከል፣ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤቱ፣ አንዱን ለምክትል ፕሬዝደንትነት ይመርጣል። ምልአተ ጉባኤው፣ የሕግ ምክር ቤቱ ሁለት-ሶስተኛው መላ አባሎች ቁጥርና የመላው አባሎች አብላጫ ቁጥር መሆን ይኖርበታል። ነገር ግን፣ በሕገ መንግሥቱ መሰረት ለፕሬዝደንትነት ብቁ ያልሆነ ተወዳዳሪ፣ ለምክትል ፕሬዝደንትነት ብቁ አይሆንም።

Page �64

።።።።።።።

ይህ የማሻሻያ ሀሳብ፣ የመጀመሪያውን የሕገ መንግሥቱን የምርጫ ቅድመ ተከተል ስርአት ይተካዋል። የፕሬዝደንቱንና የምክትል ፕሬዝደንቱንም የምርጫ ሕግጋት ጨምሯል። በዚህም መሰረት፣ የተሸነፈው ተወዳዳሪ፣ ያሸነፈው ፕሬዝደንት ምክትል አይሆንም።

ማንም ተወዳዳዳሪ ተግቢውን የመራጮች አብልጫ ድምፅ ካላገኘ፣ የፕሬዝደንት ምርጫው ስርአት ወደ ተወካዮች ምክር ቤት ተላልፎ፣ እንደ ክፍለ ግዛቶቹ ተወካይነት፣ የፕሬዝደንትነት ምርጫውን ያከናውናሉ። መራጮቹ ምክትል ፕሬዝደንቱን መምረጥ ካልቻሉ፣ የመምረጡ ሀላፊነት ወደ ሕግ መወሰኛው ምክር ቤት ይተላለፋል። በየካቲት 4 ፕሬዝደንቱ ካልተመረጠ፣ ፕሬዝደንት እስኪመረጥ ድረስ፣ ምክትል ፕሬዝደንቱ ተጠባባቂ ፕሬዝደንት ሆኖ ይመረጣል።

።።።።።።።

ማሻሻያ ሀሳብ ፲፫

ክፍል 1.

13.1. በሕግ የተወሰነ የወንጀል ቅጣት ካልሆነ በስሰተቀር፣ በማንኛው የአሜሪካ ክፍለ ግዛት ወይም በአሜሪካ ስልጣን ስር ባለ ስፍራ፣ የባርነት ወይም ያለውዴታ የማገልገል ስርአት አይፈቅቀድም።

ክፍል 2

Page �65

13.2. ምክር ቤቱ በተገቢ የሕግ ስርአት፣ ይህንን አንቀፅ የማስከበር ስልጣን አለው።

።።።።።።።

ይህ የማሻሻያ ሀሳብ፣ ባርነትን አስቀርቷል። በተጨማሪም፣ ባርነትን የሚያግዱ ሕግጋትን የማውጣትን ስልጣን፣ ለምክር ቤቱ ሰጥቷል።

።።።።።።።

ማሻሻያ ሀሳብ ፲፬ - 1868

[ሀሳቡ የቀረበው በ1866፣ የፀደቀው በ1868]

ክፍል 1

14.1. አሜሪካን ውስጥ የተወለዱ ወይም የአሜሪካ ዜግነት የተሰጣቸውና በዛ ስልጣን ስር ያሉ ሁሉ፣ የአሜሪካና የሚኖሩበት ክፍለ ግዛት ዜጋ ናቸው። ማንኛውም ክፍለ ግዛት፣ የአሜሪካዊን ዜጋ መብት ወይም መድን (immunity) የሚያሳጥር ወይም የማያስከብር ሕግ ማውጣት ወይም ያለ ሕጋዊ ስርአት፣ የማንንም ህይወት፣ ነፃነት ወይም ንብረት የሚገፍ ሕግ ማውጣት ወይም በክልሉ ውስጥ እኩል ሕጋዊ ስርአትን መከልከል አይችልም።

።።።።።።።።

Page �66

14ኛው የማሻሻያ ሀሳብ፣ በአሜሪካ የተወለደ ወይም የአሜሪካ ዜግነት የተሰጠው ማንም ሰው፣ ሙሉ የአሜሪካ ዜጋ መሆኑን ይጠቅሳል። የቀረው ክፍል፣ በከፍተኛ ፍርድ ቤቱ አተረጏጎም፣ የክፍለ ግዛቶች ድርጊት፣ በመብት የሕግ ረቂቅ (Bill of Rights) ጥበቃ ስር እንደሚውል እስቀምጧል። በሌላ አባባል፣ "ማንኛውም ክፍለ ግዛት፣ የአሜሪካዊን ዜጋ መብት ወይም መድን (immunity) የሚያሳጥር ወይም የማያስከብር ሕግ ማውጣት እንደማይችል"፣ በግልፅ አስቀምጧል። ስለሆነም፣ የክፍለ ግዛቶች ሕግጋት፣ የሕገ መንግሥቱንና የማሻሻያ ሀሳቦቹን ደርጃ የጠበቀ ሆኖ፣ በምንም መልኩ፣ ይህንን ደርጃ ማሳነስ ወይም መጨመር አይችልም። በተጨማሪም፣ ሁሉም ክፍለ ግዛት፣ የዜጎችን እኩል ሕጋዊ መብት መጠበቅ እንዳለበት ያመለክታል።

።።።።።።።

ክፍል 2

14.2. የተወካዮች ብዛት፣ በየክፍለ ግዛቶቹ፣ ታክስ የማይከፍሉ ህንዶችን ሳይጨምር፣ በሙሉ ሰው ቁጥር መሰረት ይወሰናል። ነገር ግን፣ ዕድሜው ሀያ አንድ ዓምት የሞላው፣ በአገር ማመፅ ወይም በሌላ ወንጀል ያልተከሰስ የክፍለ ግዛቱ ነዋሪና የአሜሪካ ዜጋ የሆነ ወንድ፣ ለፕሬዝደንትነት፣ ምክትል ፕሬዝደንትነት፣ ለተወካዮች ምክር ቤት አባልንት፣ ለአስተዳደሩና ለሕግ ተርጏሚ ባለስልጣን ወይም የሕግ አካል ምርጫ፣ መራጮች መምረጥ ከተከለከለ፣ የተወካዮቹ መጠን በዚሁ ቁጥር ልክ ይቀነሳል።

።።።።።።።

ክፍል 3

Page �67

14.3. በሕገ መንግሥቱ የተጠቀሰውን ሶስት-አምስተኛ የተሰኘውን፣ ባሮችን እንደ ሶስት-አምስተኛ ሰው የቆጠራቸውን ሐረግ ይሽረዋል። በተጨማሪም ለምክር ቤቱ፣ ለማንም ሰው የምርጫ መብቱን ለከለከለ ክፍለ ግዛት፣ የምርጫ ድምፃቸውን የመቀነስ ስልጣን ይሰጣል። ይህ ስልጣን እስከ ዛሬ ድረስ በሥራ ላይ አልዋለም።

።።።።።።።

ክፍል 4

14.4. ቀደም ብሎ፣ የአሜሪካንን ሕገ መንግሥት ለመጠበቅ ብሎ በመሀላ፣ የምክር ቤት አባል፣ የመንግሥት ባለስልጣን፣ የየትኛውም ክፍለ ግዛት የሕግ ወይም ያስተዳደር ክፍል አባል የሆነ ሰው፣ በመንግሥት ተቃውሞ አመፅ ወይም ሁክት ያስነሳ ወይም ለጠላት ጥገኝነትና ምቾት የሰጠ ከሆነ፣ የሕግ ምክር ቤት ወይም የተወካዮች ምክር ቤት አባል ለመሆን ወይም የፕሬዝደንት ወይም የምክትል ፕሬዝደንት መራጭ ለምሆን ወይም የአሜሪካ መንግሥት ወይም የየትኛውም ክፍለ ግዛት የሲቪል ወይም የወታደራዊ ሀላፊነት መውሰድ አይችልም። ምክር ቤቱ ግን በሁለት-ሶስተኛ የድምፅ ብልጭ፣ ይህንን እገዳ ሊያነሳው ይችላል።

።።።።።።።

ይህ ክፍል፣ ከዚያ ቀደም በነበረው ኮንፌዴሬሲ ውስጥ መሪዎች የነበሩት ሁሉ፣ የመንግሥት ሥራ እንዳይዙ ያግዳል።

Page �68

።።።።።።።

ክፍል 5

4.5. በሕግ የተፈቀደው የአሜሪካ እዳ፣ ለጡረታ፣ ለሁከትና ለአመፅ ማቆሚያ የተከፈለውን ጨምሮ፣ ተገቢነቱ አያጠያይቅም። ነገር ግን፣ አሜሪካም ሆነች ክፍለ ግዛቶች፣ አሜሪካ ላይ ለሚደርስ የሁከት ወይም የአመፅ እርዳታ ወጪ ወይም ባሪያ በማጣት ወይም ነፃ በማውጣት የሚደርስ ወጪ በሙሉ፣ ሕገ ወጥ ተብሎ ዋጋ ቢስ ይሆናሉ።

።።።።።።።

ይህ ክፍል፣ የባርያ ባለቤት የሆነ ሰው፣ ከአሜሪካ መንግሥት በፍፁም ካሳ እንደማይከፈለው ያረጋግጣል። በተጨማሪም፣ የአሜሪካ መንግሥት በምንም ዓይነት የኮንፌዴሬሽኑን እዳ እንደማይሸፍን ያስቀምጣል።

።።።።።።።

ክፍል 6

4.6. ምክር ቤቱ፣ በተገቢ ሕግጋት፣ የዚህን አንቀፅ ይዘት የማስምከበር ስልጣን ይኖረዋል።

።።።።።።።

ማሻሻያ ሀሳብ ፲፭

[ሀሳቡ የቀረበው በ1869፣ የፀደቀው በ1870]Page �69

ክፍል 1

15.1. የአሜሪካ መንግሥት ወይም ማንም ክፍለ ግዛት፣ በዘርና በመልክ ልዩነት ወይንም በቀዳሚ ባርነት ምክንያት፣ የማንንም ሰው የድምፅ መስጠት መብት ሊከለክል ወይም ሊያገድብ አይችልም።

።።።።።።።

ክፍል 2

15.2. ምክር ቤቱ፣ በተገቢ ሕግጋት፣ የዚህን አንቀፅ ይዘት የማስምከበር ስልጣን ይኖረዋል።

።።።።።።።

ይህ የማሻሻያ ሀሳብ የተላለፈው፣ የአሜሪካ ዜጎች በሙሉ ድምፅ የመስጠት መብት እንዳላቸው ለማረጋገጥ ነው። የደቡቡ ክፍለ ግዛቶች፣ በቅርብ ነፃ የወጡ ባሮችን ድምፅ መስጠት እንዳይከለክሏቸው በማሰብም ነው። በግንባታ (Reconstruction) ዘመን መጨረሻ አካባቢ ግን፣ እነዚህ የደቡቡ ክፍለ ግዛቶች ወደ ጎን በማፈግፈግ፣ የማሻሻያ ሀሳቡን መመሪያ ለመጣስ ችለዋል። በብዙዎቹ ደቡባዊ ክፍለ ግዛቶች፣ በ1960ቹ "የድምፅ መስጠት መብት ስርአት" (Voting Rights Act) ከተላለፈ በሁዋላ ነው አፍሪካዊ አሜሪካኖች የድምፅ መስጠት መብታቸውን ሙሉ በሙሉ የተቀናጁት።

።።።።።።።

Page �70

ማሻሻያ ሀሳብ ፲፮

[ሀሳቡ የቀረበው በ1909፣ የፀደቀው በ1913]

ምክር ቤቱ፣ እማንኛውም የገቢ ምንጭ ላይ፣ በማንኛውም ክፍለ ግዛት ላይ ሳይከፋፈልና የሕዝብን ቁጥር ከግምት ሳያስገባ፣ ታክስ የመጣል ስልጣን ይኖረዋል።

።።።።።።።

ከዚህ የማሻሻያ ሀሳብ በፊት፣ የገቢ ታክስ የሚሰበሰበው በክፍለ ግዛቶቹ የሕዝብ ቁጥር ልክ መሰረት ነበር። ይህ የማሻሻያ ሀሳብ፣ በክፍለ ግዛቶቹ ሕዝብ ቁጥር ልክ የሚሰበሰበውን ታክስ ሕገ ወጥ አደርጎታል። በበፊቱ ስርአት መቀጠል፣ ለሀገር አቀፍ ታክስ አሰባሰብ ፈፅሞ የማያስችል ነበር። ።።።።።።።

የማሻሻያ ሀሳብ ፲፯

[ሀሳቡ የቀረበው በ1912፣ የፀደቀው በ1913[

17.1. የአሜሪካ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት፣ በክፍለ ግዛቱ ሕዝብ ለስድስት ዓምት የሥራ ዘመን በሚመረጡ፣ ከየክፍለ ግዛቱ ሁለት አባሎች የተውጣጣ አካል ይሆናል። እያንዳንዱም አባል አንድ ድምፅ ይኖረዋል። የየክፍለ ግዛቱም መራጮች፣ ተገቢው ብቃት ያላቸው፣ የክፍለ ግዝቱ ሰፊ የሕግ አስተዳደር አካል አባል መሆን ይኖርባቸዋል።

Page �71

17.2. የክፍለ ግዛቱ የምክር ቤቱ አባልነት ቦታ ክፍት ሲሆን፣ የክፍለ ግዛቱ የሕግ አውጭ ክፍል የምርጫ ማዘዣ በማውጣት፣ ቦታውን ይሞላዋል። ይህም የሚሆነው፣ የሕግ አውጭው ክፍል፣ ተገቢውን ሕዝባዊ ምርጫ እስኪያኪያሂድ ድረስ፣ ለአስተዳደሩ ክፍል ጊዜአዊ ሰው መሾም እንዲያስችለው በማድረግ ነው።

17.3. ይህ የማሻሻያ ሀሳብ ሕገ መንግሥታዊ ከመሆኑ በፊት፣ የተመረጡ አባሎችንና የሥራ ዘመናቸውን የሚጨምር ተደርጎ መወሰድ የለበትም።

።።።።።።።

ይህ የሕገ መንግሥቱ የማሻሻያ ሀሳብ፣ የምክር ቤቱ ተወካዮችን አመራረጥ ስርአት ቀይሮታል። ከዚህ የማሻሻያ ሀሳብ በፊት፣ የክፍለ ግዛት ሕግ አውጭ አካል ነበር ተወካዮቹን የሚመርጠው። 17ኛው የማሻሻያ ሀሳብ ከተላለፈ በሁዋላ፣ የምክር ቤት አባሎቹ፣ በቀጥታ በሕዝቡ እንዲመረጡ ተደርጏል። በሞት ወይም ስልጣን በመልቀቅ ምክንያት ክፍት ቦታ ከተፈጠረ፣ በሕጋዊ መንገድ ሕዝባዊ ምርጫ እስከሚኪያሄድ ድረስ፣ የክፍለ ግዛቱ አስተዳዳሪ በቦታው ጊዜአዊ ሰው እንዲሾም ስልጣን ይሰጠዋል።

።።።።።።።።

የማሻሻያ ሀሳብ ፲፰

[ሀሳቡ የቀረበው በ1917፣ የፀደቀው በ1919]

Page �72

18.1. ይህ አንቀፅ ከፀደቀ ከአንድ ዓመት በሁዋላ፣ የሚያሰክር መጠጥ ማምረት፣ መሸጥ ወይም ማጏጏዝ፣ ወደ አገር ውስጥ ማስገባት ወይም ከአገር ውጭ መላክ፣ በፍፁም የተከለከለ ነው።

18.2. የአሜሪካ ምክር ቤትና ክፍለ ግዛቶች፣ በአንድነት አስፈላጊውን ሕግ በመደንገግ፣ ይህንን አንቀፅ ያስከብራሉ።

18.3. ይህ አንቀፅ፣ ምክር ቤቱ ለሁሉም ክፍለ ግዛቶች የሕግ አውጭ አካል፣ የማሻሻያ ሀሳቡን ባስተላለፈበት በሰባት ዓመት ግዜ ውስጥ ካልፀደቀ፣ በሥራ ላይ አይውልም።

።።።።።።።

ይህ የማሻሻያ ሀሳብ፣ የአልኮል ክልከላን ዘመን ጀምሯል። የአልኮል መጠጦችን ማምረትና መሸጥን ሕገ ወጥ አደረገው። ይህ የማሻሻያ ሀሳብ ብቻ ነው፣ የአሜሪካውያንን መብት የገደበው።

።።።።።።።

የማሻሻያ ሀሳብ 19

[ሀሳቡ የቀረበው በ1919፣ የፀደቀው በ1920]

የአሜሪካ ዜጋ የሆነ ሁሉ፣ በፆታው ምክንያት የድምፅ መስጠት መብቱ፣ በአሜሪካ መንግሥትም ሆነ በክፍለ ግዛቶች አይከለከልም፣ አይገደብም። የዚህን አንቀፅ ሕጋዊ ስርአት፣ ምክር ቤቱ የማስከበር መብት አለው።

።።።።።።።

Page �73

ይህ የማሻሻያ ሀሳብ፣ የሴቶችን የምርጫ ድምፅ የመስጠት መብት አስከበሯል።

።።።።።።።።

የማሻሻያ ሀሳብ ፳

[ሀሳቡ የቀረበው በ1932፣ የፀደቀው በ1933]

ክፍል 1

20.1. የፕሬዝደንቱና የምክትል ፕሬዝደንቱ የሥራ ዘመን ማብቂያ፣ ጥር 20 እኩለ ቀን ላይ ሲሆን፣ የሕግ አስፈፃሚ ምክር ቤትና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባሎች ደግሞ፣ የአገልግሎት ዘመናቸው ማብቂያ ይህ የማሻሻያ ሀሳብ ከመፅደቁ በፊት ከሆነ፣ ጥር 3 እኩለ ቀን ላይ ሆኖ፣ የተኪዎቻቸውም የሥራ ዘመን በዚሁ ግዜ ይጀምራል።

።።።።።።።

ይህ የማሻሻያ ሀሳብ የተላለፈው፣ ፕሬዝደንቱ ከተመረጠ በሁዋላ ስልጣን እስኪይዝ ድረስ ያለውን ግዜ ለማሳጠር ነው። ይህ ችግር ግልፅ የሆነው፣ ፕሬዝደንት ሮዝቬልት በሐምሌ 1932 ዓ.ም. ተመርጦ፣ እስከሚቀጥለው ዓመት መጋቢት ድረስ ሥራ ባልጀመረበት ግዜ ነበር። ይህ የአራት ወር ግዜ፣ በታላቁ ክፉ ዘመን (Great Depression) ውስጥ ለነበረው የአሜሪካ ሕዝብ፣ አስጨናቂ ግዜ ነበር።

Page �74

።።።።።።።።

ክፍል 2

20.2. በሕግ ካልተቀየረ በስተቀር፣ ምክር ቤቱ ቢያንስ በዓመት አንድ ግዜ፣ ጥር 3 እኩለ ቀን ላይ ይሰበሰባል።

።።።።።።

ይህ የማሻሻያ ሀሳብ፣ ደካማ (lame duck) ምክር ቤት የተሰኘውን ግዜ (ከምርጫ በሁዋላ ብዙዎቹ አባሎች፣ የሥራ ዘመናቸውን ጨርሰው፣ እንደገና ያልተመረጡበት የስብሰባ ግዜ) አሳጥሮታል። በተጨማሪም፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፕሬዝደንቱን መምረጥ ካለባቸው (የመራጭ ኮሌጁ መምረጥ ካልቻለ)፣ አዲሶቹ ተመራጮች ምርጫውን እንደሚይኪያሂዱ ያረጋግጣል።

።።።።።።።

ክፍል 3

20.3. የፕሬዝደንቱ ሥራ በሚጀምርበት ግዜ ተመራጩ በሕይወት ከሌለ፣ ምክትል ፕሬዝደንቱ ፕሬዝደንት ይሆናል። የፕሬዝደንቱ የሥራ ዘመን በሚጀምርበት ግዜ ፕሬዝደንት አልተመረጠ ከሆነ ወይም ተመራጩ ብቁ ሆኖ ካልተገኘ፣ የፕሬዝደንቱ ብቃት እስኪረጋገጥ ድረስ፣ ምክትል ፕሬዝደቱ

Page �75

ተጠባባቂ ፕሬዝደንት ሆኖ ያገለግላል። ፕሬዝደንቱ ወይም ምክትል ፕሬዝደንቱ ብቁ ሆነው እስኪቀርቡ ድረስ፣ ምክር ቤቱ ሌላ ብቁ ሰው የመምረጥና የምርጫውም ስርአት ሕጋዊ የሚሆንበትን መንገድ የመደንገግ መብት ይኖረዋል።

።።።።።።።

ይህ ክፍል፣ ፕሬዝደንቱ ብቁ ካልሆነ ወይም ከሞተ፣ ምክትል ፕሬዝደንቱ በተጠባባቂነት እንደሚተካው ግልፅ ያደርጋል። በተጨማሪም ይህ የማሻሻያ ሀሳብ፣ ከምክትል ፕሬዝደንቱ በሁዋላ የሚደረጉ የስልጣን ሽግግሮችን ስርአት ለምክር ቤቱ ይተወዋል።

።።።።።።። ክፍል 4

20.4. የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመረጠው ፕሬዝደንት በሞት ከተለየ ወይም የሕግ መወሰኛው ምክር ቤት የመረጠው ምክትል ፕሬዝደንት እንደዚሁ በሞት ከተለየ፣ ምክር ቤቱ ተተኪውን ሰው በሕጋዊ መንገድ የመምምረጥ መብት ይኖረዋል።

።።።።።።።።

ክፍል 5

20.5. የዚህ ማሻሻያ ሀሳብ ክፍል 1 እና 2፣ አንቀፁ ከፀደቀ በሁላ ባለው ጥቅምት 15 ቀን በሥራ ላይ ይውላል።

Page �76

።።።።።።።

ክፍል 6

20.6. ይህ አንቀፅ፣ በሕግ አውጭው አካል ሶስት-አራተኛ የድምፅ ብልጫ አልፎ፣ በቀረበ በሰባት ዓመት ግዜ ውስጥ ፀድቆ፣ የሕገ መንግሥቱ አካል ካልሆነ፣ ሥራ ላይ አይውልም።

።።።።።።።

የማሻሻያ ሀሳብ ፳፩

[ሀሳቡ የቀረበው በ1933፣ የፀደቀው በ1933]

ክፍል 1

21.1. ስምንተኛው የሕገ መንግሥቱ ማሻሻያ ሀሳብ እዚህ ላይ ይደገማል።

ክፍል 2

21.2. የሚያሰክሩ መጠጦችን ወደ አሜሪካ ክፍለ ግዛቶች ወይም በአሜሪካ ቁጥጥር ስር ወዳሉ አግሮች ማጏጏዝ ወይም ማስገባት ወይም መጠቀም፣ በሕግ የተከለከል ይሆናል።

ክፍል 3

Page �77

21.3. ይህ አንቀፅ፣ በክፍለ ግዛቶቹ ሁሉ ስብስብ አሳሳቢነት ቀርቦ፣ በሰባት ዓመት ግዜ ውስጥ ፣ ምክር ቤቱ አፅድቆ፣ የሕገ መንግሥቱ ማሻሻያ አካል ካላደረገው፣ በሥራ ላይ አይውልም።

።።።።።።።

ይህ የማሻሻያ ሀሳብ፣ የአልኮልን ሕገ ወጥነት (Prohibition) ሽሮ፣ አልኮልን የመሸጥና የማከፋፍልን መብት ሕጋዊ አድርጎታል።

።።።።።።።

የማሻሻያ ሀሳብ ፳፪

[ሀሳቡ የቀረበው በ1947፣ የፀደቀው በ1951]

ክፍል 1

22.1. ማንም ሰው፣ ለፕሬዝደንትነት፣ ከሁለት ግዜ በላይ መመረጥ አይችልም። የፕሬዝደንቱን ቦታ የያዘ ወይም በተጠባባቂ ፕሬዝደንትነት ከሁለት ዓመት በላይ ያገለገለ ሰው፣ ለፕሬዝደንትነት ከአንድ ግዜ በላይ ሊመረጥ አይችልም። ነገር ግን፣ ይህ አንቀፅ ለምክር ቤቱ ሲቀርብ ወይም በፀደቀበት ግዜ በስልጣን ላይ ያለ ፕሬዝደንት ወይም ተጠባባቂ ፕሬዝደንትን፣ የተረፈውን የሥራ ጊዜውን ከመጨረስ አያግደውም።

ክፍል 2

22.2. ይህ አንቀፅ፣ ምክር ቤቱ ለክፍለ ግዛቶቹ ያቀረበው ረቂቅ፣ በሰባት ዓመት ግዜ ውስጥ፣ በክፍለ ግዛቶቹ የሕግ መወሰኛ አካል፣ በሶስት-አራተኛ

Page �78

የድምፅ ብልጫ ፀድቆ ካልተላለፈ፣ የሕገ መንግሥቱ የማሻሻያ ሀሳብ ሆኖ ሊጠቃለል አይችልም።

።።።።።።።።።

ይህ የማሻሻያ ሀሳብ የተላለፈው ከፕሬዝደንት ሮዝቬልት ምርጫ በሁዋላ ነበር። በፕሬዝደንት ዋሺንግተን የተጀመረውን የሁለት ተርም ብቻ የአገልግሎት ዘመን ስርአት የቀየረው፣ ፍራንክሊን ሮዝቬልት ነበር። ሮዝቬልት አራት ግዜ ተወዳድሮ፣ አራቴም በተከታታይ ፕሬዝደንት ሆኗል።

በተጨማሪም፣ ፕሬዝደንት የሆነ ምክትል ፕሬዝደንት፣ ከሁለት ዓመት በላይ አገልግሎ ከሆነ፣ መመረጥ የሚችለው ለአንድ ተርም ብቻ እንደሆነ ይገልፃል። ስልሆነም፣ ከሁለት ዓመት በታች ፕሬዝደንት ኬነዲን ተክቶ ያገለግለውና በሚቀጥለው ምርጫ የተመረጠው ፕሬዝደንት ጆንሰን፣ ቢፈልግ እንደገና በ1968 ዓ.ም. ሊወዳደር ይችል ነበር።

።።።።።።።።።

የማሻሻያ ሀሳብ ፳፫

[ሀሳቡ የቀረበው በ1960፣ የፀደቀው በ1961]

ክፍል 1

23.1. በምክር ቤቱ መምሪያ መሰረት፣ የአሜሪካ መንግሥት መቀመጫ የሚሆነው ከተማ፣ ልክ እንደ ክፍል ግዛት በሚገባው በተወካዮች ምክር

Page �79

ቤትና የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት አባሎች ቁጥር ልክና ከትንሹ ክፍለ ግዛት ባልበለጠ ቁጥር፣ የፕሬዝደንትና የምክትል ፕሬዝደንት መራጮች ይሰይማል። እነዚህም፣ ክፍለ ግዛቶቹ ከመረጧቸው በተጨማሪ ሆኖ፣ ማንኛውም ክፍለ ግዛት እንደሚልካቸው ተመራጮች ሆነው፣ በዋሺንግተን ከተማ ተሰብስበው፣ የአስራ ሁለተኛው ማሻሻያ ሀሳብ በሚያመለክተው መሰረት ግዴታቸውን ይፈፅማሉ።

ክፍል 2.

23.2. በተገቢው ሕግ መሰረት፣ ምክር ቤቱ ይህን አንቀፅ የማስከበር ስልጣን ይኖረዋል።

።።።።።።።።። 23ኛው የማሻሻያ ሀሳብ ለዋሺንግተን አውራጃ ዜጋዎች፣ ለመጀመሪያ ግዜ፣ የፕሬዝደንቱንና ምክትል ፕሬዝደንቱን የመምረጥ መብት ሰጥቷቸዋል። የምክር ቤት ተወካያቸው ግን፣ የተመልካችነት እንጂ የድምፅ መስጠት መብት አይኖረውም።

።።።።።።።

የማሻሻያ ሀሳብ ፳፬

[ሀሳቡ የቀረበው በ1962፣ የፀደቀው በ1964]

ክፍል 1

Page �80

24.1. የምርጫ ታክስ ወይም ማንኛውንም ዓይነት ሌላ ታክስ ባለመክፈል ምክንያት፣ የአሜሪካ ዜጎች የመጀመሪያው ወይም ሌላ፣ የፕሬዝደንት ወይም ምክትል ፕሬዝደንት ምርጭ ላይ፣ መራጮችን ወይም የምክር ቤት ተወካዮቻቸውን የመምረጥ መብታቸው መከልከል ወይም መታገድ አይችልም።

ክፍል 2

24.2. በተገቢ ሕግ መሰረት፣ ምክር ቤቱ ይህንን አንቀፅ የማስከበር ስልጣን አለው።

።።።።።።።

የማሻሻያ ሀሳብ ፳፭

[ሀሳቡ የቀረበው በ1965፣ የፀደቀው በ1967]

ክፍል 1

25.1. ፕሬዝደንቱ ከሥራው ከተወገደ፣ ከሞተ ወይም ሥራውን ከለቀቀ፣ ምክትል ፕሬዝደንቱ ፕሬዝደንት ይሆናል።

።።።።።።።።።

Page �81

ይህ የማሻሻያ ሀሳብ የተላለፈው፣ ፕሬዝደንት ኬነዲ ከተገደለ በሁዋላ ነው። የመጀመሪያው ክፍል፣ ምክትል ፕሬዝደንቱ ተጠባባቂ ሳይሆን ፕሬዝደንት እንደሚሆን ያብራራል።

።።።።።።።።

ክፍል 2

25.2. የምክትል ፕሬዝደንቱ ቦታ ክፍት ሲሆን፣ ፕሬዝደንቱ ምክትሉን መርጦ፣ በምክር ቤቱ የድምፅ ብልጫ ማለፉ ከተረጋገጠ፣ ለቦታው ይመረጣል።

።።።።።።።

ይህ ክፍል፣ በሕገ መንግሥቱ ውስጥ የነበረውን ምክትል ፕሬዝደንቱን የመተካት ክስተት ይሸፍናል። የመጀመሪያው ፍራቻ፣ ፕሬዝደንቱ ቢገደል ወይም ሥራ ቢያቆምና ምክትሉ ፕሬዝደንት ቢሆን፣ ምክትል ፕሬዝደንቱ ማን ይሆናል የሚለው ነበር። ይህ ክፍል የሚያመለክተው፣ ፕሬዝደንቱ ምክትሉን መርጦ ለምክር ቤቱ ካስተላለፈ በሁዋላ፣ ምክር ቤቱ በቀላል የድምፅ ብልጫ፣ ተመራጩን ማፅደቅ እንደሚችል ነው። ይህ የማሻሻያ ሀሳብ በተለይ አግባብ የሆነው፣ በሁለተኛው የፕሬዝደንት ኒክሰን የስልጣን ዘመን፣ ምክትሉ ስፒሮ አግኒው፣ የሜሪላንድ አገረ ገዥ በነበረበትና በገጠመው የወንጀል ክስ ጉዳይ ግዜ ነበር። በዚህ ምክንያት፣ አግኒው ከምክትል ፕሬዝደንትነት ቦታው እንዲለቅ ተደረገ። በዚህን ግዜ፣ ፕሬዝደንት ኒክሰን፣ የምክር ቤት አባል የነበረውን ጀራልድ ፎርድን ምክትሉ አደረገው። በወተር ጌት ቅሌት ምክንያት፣ ፕሬዝደንት ኒክሰን ከስልጣኑ እንዲለቅ በተደረገበት ግዜ፣ ምክትል ፕሬዝደንት ፎርድ፣ በምርጫ ያላሸነፈ

Page �82

የመጀመሪያው ፕሬዝደንት ሆነ። ፕሬዝደንት ፎርድም፣ የኒው ዮርኩን አገረ ግዥ ኔልሰን ሮከፌለርን ምክትሉ አድርጎ ሲመርጠው፣ በዚህ አንቀፅ መሰረት የተመረጠ ሁለተኛው ምክትል ፕሬዝደንት ሆነ።

ክፍል 3

25.3. ፕሬዝደንቱ፣ የተሰጠውን የፕሬዝደንትነት ሥራ ማከናወን አለመቻሉን፣ በጽሁፍ ለሕግ መወሰኛው ምክር ቤት ተተኪ ፕሬዝደንት (pro tempore)ና ለተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ ባስታወቀ ግዜና ይኸንኑም በጽሁፍ በተቃራኒው ካላስታወቀ በስተቀር፣ ምክትል ፕሬዝደንቱ ተጠባባቂ ፕሬዝደንት ሆኖ ሥራውን ይረከባል።

።።።።።።።

ይህ ክፍል፣ ፕሬዝደንቱ በህመም ወይም ሌላ እክል ምክንያት፣ ጊዜአዊ ሥራ ማቆም የሚችልበትን መንገድ ይጠቅሳል። ፕሬዝደንት ሬጋን በጥይት በተመታ ግዜ፣ ይህንን አንቀፅ ተጠቅሞ ነበር። ፕሬዝደንትነቱን እንደገና ለመረከብም፣ ለሥራው ብቁ መሆኑን የሚገልፅ ደብዳቤ ለምክር ቤቱ ማቅረብ ብቻ ነበር የሚጠበቅበት። ።።።።።።።

ክፍል 4

25.4. ምክትል ፕሬዝደንቱና አብዛኛዎቹ የካቢኔው ባለስልጣኖች ወይም ምክር ቤቱ በሕጋዊ መንገድ የመረጠው ቡድን፣ ፕሬዝደንቱ ሥራውን ለማከናወን ብቁ እንዳልሆነ በጽሁፍ ለሕግ መወሰኛው ምክር ቤት ተተኪ ፕሬዝደንት (President pro tempore)ና ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት

Page �83

አፈጉባኤ ካስታወቁ፣ ምክትል ፕሬዝደንቱ ወዲያውኑ ተጠባባቂ ፕሬዝደንት ሆኖ ሥራውን ይረከባል።

ፕሬዝደንቱ፣ ሥራውን ለማከናወን ምንም እክል እንደሌለበት፣ በጽሁፍ ለሕግ መወሰኛው ምክር ቤት ተተኪ ፕሬዝደንት (President pro tempore)ና ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ ካስታወቀና ምክትል ፕሬዝደንቱና አብዛኛዎቹ የካቢኔው ባለስልጣኖች ወይም ምክር ቤቱ በሕጋዊ መንገድ የመረጠው ቡድን፣ ፕሬዝደንቱ ሥራውን ለማከናወን ብቁ እንዳልሆነ፣ በጽሁፍ በአራት ቀን ግዜ ውስጥ፣ ለሕግ መወሰኛው ምክር ቤት ተተኪ ፕሬዝደንት (President pro tempore)ና ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ ካላቀረቡ፣ ፕሬዝደንቱ ወደ ቦታው ይመለሳል። ከዚህ በሁውዋላ፣ ምክር ቤቱ ሥራ ላይ ካልሆነ፣ ለዚሁ ጉዳይ በ48 ሰዓት ውስጥ አስቸኳይ ስብሰባ ይጠራል። ምክር ቤቱም፣ የመጨረሻውን ደብዳቤ በተቀበለበት በ21 ቀን ግዜ ውስጥ ጉዳዩን መርምሮ፣ እውነትም ፕሬዝደንቱ ብቁ እንዳልሆነ በ2/3ኛ ድምፅ ብልጫ ካፀደቀው፣ ምክትል ፕሬዝደንቱ የተጠባባቂ ፕሬዝደንትነቱን ሥራ ይቀጥላል። አለበለዛ፣ ፕሬዝደንቱ በቢሮው ስልጣንና ሀላፊነት ሥራው ይቀጥላል።

።።።።።።።

ይህ የመጨረሻው የማሻሻያ ሀሳብ፣ ፕሬዝደንቱ ለቦታው ብቁ መሆን አለመሆኑን ባለመግለፅ ወይም ባለመፈልግ የሚፈጠረውን ሁኔታ ይመለከታል። የምክትል ፕሬዝደንቱ ተቃውሞ፣ በአብዛኛው የካቢኔው አባሎች ከተደገፈ፣ ምክትል ፕሬዝደንቱ ስልጣኑን ይረከባል። ከዛ በሁዋላ፣ ፕሬዝደንቱ ብቁ መሆኑን የሚገልፅ ደብዳቤ ሊልክ ይችላል። በካቢኔው ድጋፍ፣ ምክትል ፕሬዝደንቱ ተቃውሞውን እንደገና በጽሁፍ ሊገልፅ ይችላል። ይህ ሁኔታ ከተፈጠረ፣ ምክር ቤቱ ባስቸኳይ መሰብሰብ ይኖርበታል። ተቃውሞውን፣ የሁለቱም ምክር ቤት አባሎች በ2/3ኛ ድምፅ ካፀደቁት፣ ምክትል ፕሬዝደንቱ፣ ተጠባባቂ ፕሬዝደንት ሆኖ ይቀጥላል።

Page �84

።።።።።።።

የማሻሻያ ሀሳብ ፳፮

[ሀሳቡ የቀረበው በ1971፣ የፀደቀው በ1971]

ክፍል 1

26.1. ዕድሜያቸው ከአስራ ስምንት ዓመት በላይ የሆኑ የአሜሪካ ዜጎች፣ በዕድሜያቸው ምክንያት፣ የአሜሪካ መንግሥትም ሆነ ማንኛውም ክፍለ ግዛት፣ የመምረጥ መብታቸውን አያግድም፣ አይከለክልምም።

ክፍል 2

26.2. በተግቢ ሕግጋት፣ ምክር ቤቱ ይህንን አንቀፅ የማስከበር ስልጣን ይኖረዋል።

።።።።።።።

26ኛው የማሻሻያ ሀሳብ፣ የምርጫ መብትን ዕድሜ ወደ 18 ዝቅ አድርጎታል። በወቅቱ የጠቀመው መፈክር፣ "ለሀገርህ ለመሞት ዕድሜህ ከፈቀደ፣ ለመምረጥም ዕድሜህ ይፈቅዳል" የሚለው ነበር። ይህ ክርክር የተኪያሄደው፣ በቪዬትናም ጦርነት ግዜ ነበር።

።።።።።።።።

Page �85

የማሻሻያ ሀሳብ ፳፯

[ሀሳቡ የቀረበው በ1989፣ የፀደቀው በ1992; ከአስራ ሁለቱ የመብት የሕግ ረቂቆች (Bill of Rights) ሁለተኛው ነው]

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባሎች ጉዳዩን እስኪመለከቱት ድረስ፣ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤትና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባሎችን የአበል ልዩነት የሚያመለክት ሕግ አይተላለፍም።

።።።።።።።

ይህ የማሻሻያ ሀሳብ፣ ምክር ቤቱ፣ የአባሎቹን ደሞዝ መጨመር እንደማይችል ያስቀምጣል። ግሬጎሪ ዋትሰን የተባለ የኮሌጅ ተማሪ፣ በ1982ዓ.ም. በዚህ ጉዳይ ላይ ዘመቻ እስኪያኪያሂድ ግዜ ድረስ፣ ይህ የማሻሻያ ሀሳብ ሳይፀድቅ ለብዙ ዘመን ቆይቶ ነበር።

።።።።።።

Page �86